ከቀናት በፊት በአርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት እና በሕወሓት ቅጥረኛ ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰው ውጊያ አድማሱን አስፍቶ በመቀጠል ዛሬ ወልቃት ጠገሌ ላይ መድረሱ ተሰምቷል። በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ትንቅንቅ አርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ ድል መቀናጀቱን ምንጮች አመልክተዋል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ እየተቸረው እንደሚገኙ እየተነገረ ሲሆን ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ነዋሪዎች አጋጣሚውን በመጠቀም ሰራዊቱን እየተቀላቀሉ መሆኑም ታውቋል። ዝርዝር መረጃዎችን ከንቅናቄው በቅርብ ሰአታት ውስጥ እንደምንሰማ እጠብቃለሁ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት ሹማምንት ጦርነት አልተከፈትብንም በማለት የተለመደ ቅጥፈታቸውን ወደ ህዝብ ቢያደርሱም ሁኔታዎች እየተካረሩ መሄዳቸውን ተከትሎ ከትላንት እሁድ ጀምሮ በካድሬዎቻቸው እና አይጋፎረም በሚባለው የአገዛዙ ልሳን አማካኝነት በድንበር አካባቢዎች ”ከሻዕብያ” ጋር ግጭት መፈጠሩን እየተናገሩ እንደሚገኙ ይታወቃል።

No comments:
Post a Comment