ሁለት ሕጻናት አሉት። የመጀመሪያ ወንድ ልጁ ሩህ ይባላል። ከአራት አመታት በፊት፣ ልጁን ከትምህርት ቤት ሊያወጣ ወደዚያ ሲያመራ ታጣቂዎች ከበቡት። እየሰደቡ፣ እየደበደቡ ወደ ወህኒ ወሰዱት። አንድ ፖሊስ ይበቃ ነበር። ግን የለየለት ነፈሰ ገዳይ የሚይዙ ይመስል፣ ይሄን አንድ ሰላማዊ የልጅ አባት ለመያዝ ተረባረቡ። አይ ጭካኔ !
ይህ ሰው አንዱዋለም አራጌ ነው። የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳነት የነበረ፣ አንጋፋ ወጣት ፖለቲከኛ። ባላጠፋው ጥፋት፣ ለሰላም በቆመ፣ በዉሸት ክስ፣ ሽብርተኛ ተብሎ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት።
ይህ ሰው አንዱዋለም አራጌ ነው። የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳነት የነበረ፣ አንጋፋ ወጣት ፖለቲከኛ። ባላጠፋው ጥፋት፣ ለሰላም በቆመ፣ በዉሸት ክስ፣ ሽብርተኛ ተብሎ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት።
ልጅ ሩህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ከአባቱ ጋር አላደረም። አባቱ ለአገርና ለሕዝብ ሲል ወህኒ ወረደ። አገር ትጠቀም ተብሎ ልጅ ሩህ አባት ተነፈገ። አገር ልጥቀም ብሎ እንዱዋለም አራጌ፣ እንደ ሌሎች አባቶች ልጆቹን የማሳደግ እድል ተነፈገ። ለአገርና ለሕዝብ በመቆሙ፣ የአገርን የሕዝብ ጥቅምን በማስቀደሙ የጨካኞ በትር አረፈበት። ይህ የኢትዮጵያ ኔልሰን ማንዴላ የሆነው አንዱዋለም አራጌ !!!!!
አንዱዋለም አራጌ፣ አልጋ ዳር ሆኖ ከልጆቹ ጋር መጫወት፣ ለነርሱ ተረት ማውራት፣ የልጆች መጽሃፍ ማንበብ አልቻለም። ግን በመንፈስ ከነርሱ ጋር ነው የሚያድረው። ያለዉን ፍቅርና ናፍቆት ከቃሊቲ በጽሁፍ ይገልጻል። ለወንድ ልጁ ሩህ አንድዋለም ሲጽፍ “ከዘላለም በፊት የተቸርከኝ …እንኳን ወለድኩህ” ይላል። “የአምባብገነኖች ግፍ ሰለባ” ይለዋል፤ አገዛዙ በዉሸት ክስና በግፍ ዜጎችን በሚያስረበት ጊዜ የሚጎዱት ልጆች፣ ቤተሰብም እንደሆነ ለማሣየት።
አንዱዋለም አራጌ ከሚወዳቸው ልጆቹ መለየቱ ትልቅ ሕመም እንደሆነበት ደብዳቤው ያሳያል። ሆኖም አንዱዋለም እርሱ የኖረባት በግፍ የተሞላች፣ በዘረኝነት የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ለልጆቹ ማስረከብ አልፈለገም። እርሱ መስዋትነት ከፍሎ ልጆቹና የየልጅ ልጆቹ በነጻነት እንዲኖሩ ይህ ወያኔዎች “ሽብርተኛ” የሚሉት ምመላአው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እንደ ጀግና የሚያየው ወጣት የአንድነት መሪ በጨካኖች በትር ስቃይ እየደረሰበት ነው።
ከዋክብትና ብርሃናት ሰማያትና አለማት
በፈጣሪ ቃል ከመፌጥራቸው በፊት
በዚያ በፈጣሪ እቅፍ በዚያ በኔ ጉልበት ዉስጥ
ከስጋና ደሜ ተዋህደህ
ከነፍሴ ደም ስሮች ጋር ተገምደህ
በልቤ ጓዳ ዉስጥ ተኝተህ ሳለህ የማውቅህ
ከዘላለም ዘመናት በፊት የተቸርከኝ
ከዘላለም ዘመናት በፊት የወለድኩህ
በድቅድቅ ዉስጥ ያገኝሁህ
የነፍስያዬ ሃቅል ሩህ
የሕይወቴ የብርሃን ጎርፍ
የሕይወቴ ምገስ ካባ
የፌሽታዬ ምንም ቀዘባ
የአምባገነኖችን ግፍ ሰለባ
የአብይተነታቸው ማሳያ ጫማ
በውል የማታወቀው እስረኛ አባት ጠያቂ
ያለተመለሱ ጥያቄዎች ማህደር አማቂ
የነፍስዬ ሃቅል ሩህ በድቅድቅ ዉስጥ ያገኘሁህ
የሕይወቴ የብርሃን ጎርፍ
እንኳን ወደዚህ አለም መጣህ
እንኳን በድጋሚ ወለድኩህ
No comments:
Post a Comment