Tuesday, July 21, 2015

የደቡብ ምስራቅ እዝ በርካታ ወታደሮችን አሰረ:

Minilik Salsawi 


– በጄኔራል አብርሃ የሚመራው የደቡብ ምስራቅ እዝ ካለፈው እሮብ ጀምሮ ቀጥራቸው 180 የሚጠጉ ወታደሮቹን ከስሩ ካሉት ክፍሎች ሰብስቦ ማሰሩን የወታደራዊ ደህንነት ምንጮች ገልጸዋል::ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ እንዳሉት በከፍተና የስለላ መረብ ስር የወደቁት የእዙ ወታደሮች የሃገሪቱን ጉዳይ እና በግል የሚደርስባቸውን ጉዳይ እርስ በእርስ ይወያያሉ የራዲዮ ፕሮግራሞችን ይከታተላሉ የከትማ ወሬ ይዘው ይመጣሉ ወዘተ የተባሉ ወታደሮች ተጣርቶ ተለቅመው በጅጅጋ ወታደራዊ ማጎሪያ ወህኒ ቤት መታሰራቸው ታውቋል::

ከዚህ ቀደም ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ያነሱ የተቃዋሚዎችን ሁኔታ ሲነጋገሩ ነበር የተባሉ መታሰራቸው ሲታወቅ እንዲሁም ሶስት ከፍተኛ መኮንኖች ከሰራዊት ከድተው ኬንያ ከገቡ በኋላ ተመልሰው በባሌ ከሚገኘው የኦነግ ሰራዊት ጋር መቀላቀላቸው ይታወሳል::የደቡብ ምስራቅ እዝ ከሌሎቹ የወያኔ ሰራዊት እዞች ይልቅ በከፍተኛ ደረጃ የወታደራዊ ደህንነት በስለላ ስራ ውስጥ ውስጡን የተበራከቱበት መሆኑ ይታወቃል::በደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው ትእዛዝ በርካታ የደህነት አባላት በከፍተኛ አበል የፌዴራል ፖሊሱን እና ሰራዊቱን የተቀላቀሉ መሆኑ ይታወሳል::
ወያኔ በውስጡ በተፈጠረው ከፍተኛ ድንጋጤ ሕወሓቶች ማንንም ያለማመን ደረጃ ላይ በመድረሳቸው በዘረኝነት ላይ በተመሰረተ ጥላቻ በጦላይ ያሰለጠኗቸውን አባሎቻቸውን ሁሉ ወደ ተለያዩ ተቋማት ከበፊቱ በእጥፍ አድርገው በማስገባት በከፍተኛ ደረጃ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ የስለላ ስራ በቀሪ ዜጎች ላይ በመስራት መንግስታዊ ሽብር በስፋት እያራመዱ ይገኛሉ::

No comments:

Post a Comment