"አልሸባብ ማለት ተፈጥሮ ጋር ተዋህዶና ተመሳስሎ ጥቃት የሚሰነዝር ሲሆን፣ የመገርመው ነገር የእነሱን ተዋጊዎች መሬት ሁሉ ትደብቃቸዋለች። በጭራሽ አይታዩም። ……… ከእለታት ባነዱ ቀን ወደሶማሊያ ስንዘምት ከአዛዦች የተነገረን ድስኩር አልሸባብ ማለት በቅጡ እንኳ ባልተጠገነ መሳሪያ የሚዋጋ፣ የጥቂት ፈሪዎች ጥርቅም በመሆኑ እኛ ካለን ዘመናዊ መሳሪያ እና የሰራዊት ብዛት አንፃር ጠንካራ የስነ ልቦና ብርታት እንድንገነባ ነበር። ……… በጉዟችን ላይ መንገድ የማፅዳት ስራው በዶዘርና በግሬደር ታጅቦ ፈንጂ አምካኞች ቦታው መፅዳቱን መስክረው ጉዞ ጀመርን ነገር ግን ደቂቃዎችን እንደተጓዝን የፊተኛው ኦራል በፈንጂ እንዳልነበረ ሆነ። ብዙም ሳይቆይ ከየት እንደሚተኮስ 'ማናየው ጥይት ሰራዊቱን አመድ አደረገው። የዚያን እለት አቧራው ሲጨስ በወኔ እየፎከሩ ከምሽግ የሚወጡ በርካታ የቤኒሻንጉል ልጆች እንዳልነበሩ ሆኑ። በድናቸውን አይናችን እያየ በመኪና ይጎትቱት ነበር። … …… አንዳንዴ አልሸባብን ማግኘት ሲያቅተን በንዴት ደባቂ ሊሆኑ ይችላሉ ያልናቸውን ሁሉ ገድለን የአልሸባብ ወታደር እንደገደልን ሪፓርት እናደርግ ነበር። አለቆቻችን በተጠገነ መሳሪያ የሚዋጋ ነው ያሉት አልሸባብ ድባቅ ከመታን በኃላ እንኳ ድስኩራቸው አሁንም ስለአልሸባብ የተጠገነ ማሳሪያ መያዝና ድክመት ነው። በዚህም ከፍተኛ አለመግባባትና ቅራኔ ተፈጥሯል።
ነገር ግን አልሸባብንም ሻዕቢያንም አይቻለሁ፣ በትግል ስልታቸውም ሆነ በማጥቃት ስትራቴጂያቸው ለየት ያሉና እጅግ ፈታኝ የሆኑብን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊቶች ናቸው። የሚገርመው ሀምሌ 12 ለእግር ጉዞ በወጣንበት ሰአት ነበር 24ኛ ክፍለ ጦርን እንዳልነበር ያደረጉት። አፀፋ ለመስጠት እንኳ ፋታ አልሰጡንም። የሚተኮሰው መሳሪያ የሚያርፈው ከድንጋይ ላይ ሲሆን ዲንጋዩ ደግሞ በርካታ ጠይት ሆኖ እኛ ላይ ያርፋል። የሚገርመው ነገር እነዚያ በእርዳታና አሮጌ መሳሪያ የሚዋጉ ናቸው የተባሉት ሰዎች ጨርሰናቸዋል ብለው ሲሄዱ አንድም መሳሪያ ከእኛ አለመውሰዳቸው ነው። በዚያች ፋታ በማትሰጥ የጭንቅ ሰአት እኛን ከመሞት የታደገን ስሙንና ሀገሩን መጥቀስ የማልፈልገው የአማራ አዛዥ ነበር፣ እንዲህም አለን "ጓዶች የሌላውን አዛዥ ትታችሁ ከዚህ ዲንጋይ እራሳችሁን አትርፉ አለበለዚያ እዚሁ ትቀራላችሁ" ይህን በሰማን ጊዜ ነፍሳችንን ለማትረፍ በየገደሉ ተንከባለልን እንጂ አፀፋ ለመስጠት እንኳ ሀይላችን ተዳክሞ ነበር። እኔን የገረመኝ የአዛዣቸው ብልጠትና ስልታዊነት ነው። የኛ አዛዦች እኮ "እነዚህ በእርዳታ መሳሪያ የሚንቀሳቀሱና አቅም የሌላቸው ናቸው፣ እንዴት ስነ ልቦናዊ ድል አስቀድመው ይቀዳጁብናል" እያሉ ከመዘብዘብ በስተቀር በውጊያው ከመሳተፍ ጀምሮ የጦር ቴክኒካዊ ጥበቦችን ከአካባቢው ሁኔታ ጋር አቀናጅተን በማድረጉ ረገድ የሉበትም። እነሱ በቀላል መሳሪያ አንድን ግለሰብ ኢላማ ለማስገባት ከመሞከር በቅልጥፍና የመሸግንበትን ድንጋይ ሲመቱት በርካታ ሙትና ቁስለኛ ያደርጉ ነበር። ከጥቃቱ በኃላ አለመግባባቱ ተካረረ፣ የአዛዦችን ድስኩር የሚሰማ ጠፋ፣ ሁሉም ሰባት አመት ግዳጁን የጨረሰ በመሆኑ እራሱን ለማግለል ወሰነ፣ የሻእቢያ ጦርነት ሲገርመን አሁን ደግሞ ሌላ ስህተት አንሰራም የሚለው ተበራከተ። ተቃውሞ ካሰሙት አባላት በርካቶቹ ታሰሩ፣ ገሚሶቹ አዲስ ምልምል ሲመጣ እንደሚሰናበቱ ቃል ተገባላቸው፣ ለጥቂቶች ደግሞ እረፍት ተሰጠን። ……… አዛዥና ሰራዊቱ፣ አዛዥና አዛዥ የብሄር ጥያቄን የተንተራሱና ሌሎች ጥጎች ይዘው አለነግባባቱን ከጫፍ አድርሰውታል። ሰራዊቱ ዳግም ወደወንድሙ የመተኮስ መራሉ የለውም እንቢ ካሉም ከዚያኛው ወገን ለመቀላቀል ወስኗል።……" ይቀጥላል… …… (ይህ ፅሁፍ የቅ/ተከተልና የተወሰነ የቃላት መሻሻያ ከማድረጌ በስተቀር ሙሉ በሙሉ የአይን እማኙ የምስክርነት ቃል ነው።)

No comments:
Post a Comment