Friday, July 10, 2015

ጋዜጠኛ ኤዶም፣ርዮትና ማህሌት-ከተፈቱ በሁዋላ ሀብታሙ ምናለ ታፍኖ ተወሰደ

የጋዜጣው ስራ አስኪያጅ በአዲስ አበባ በደህነቶች ታፍኖ ተወሰደ

፣ከእነ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ በተጨማሪ ሌሎችም የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲፒጄ ጠየቀ

የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ሶስቱ ጋዜጠኞችና ሁለቱ ጦማሪያን መፈታት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ሰፊ መነጋገሪአ በሆነበት በአሁኑ ወቅት እንደ ሌሎች ሁሉ እንካን ከጠባቡ እስር ቤት ተፈታችሁ ያለውን የቀዳሚ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምናለን የአገዛዙ ደህንነቶች ዛሬ ማምሻውን ከቤቱ አፍነው መውሰዳቸውን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

የሀብታሙ ምናለን ከቤቱ ዛሬ ዕኩለ ሌሊት ላይ ታፍኖ መወሰድ ይፋ ያደረገው ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ማንነታቸው ባልታወቀ የደህነት አባላት ታፍኖ ት እንደወሰዱት እንደማያውቁና ከዚህ በፊት ለአንድ ሙሉ ቀን ጥብቅ ምርመራ ሲደረግበት ውሎ አሻራ ሰጥቶ መውጣቱን አስታውሷል።

የቀዳሚ ገጽ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው ሀብታሙ ምናለ ዛሬ ማለዳ ከአራት ዓመት እስር በሁዋላ የአመክሮዋ ጊዜ አልፎ በአመክሮ ከእስር ወጣች የተባለችውን ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙን አስመልክቶ በፌስ ቡክ ገጹ የርዮትን መፈታት የፈጠረበትን ስሜት በመግለጹ አይዘነጋም።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ መፈታትን አስመልክቶ ዓለም አቀፉ ጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ አስቀድሞም መታሰር የሌለባት ርዮት በመፈታቱዋ ደስተኛ መሆኗንና የጤናዋን ጉዳይ ተጠይቃም የህመም ማስታገሻ እየወሰደች መሆኑን መግለጿን ጠቅሷል። መጀመሪያውኑ መታሰር እንደሌለባትና ከአራት ዓመት በላይ በእስር በልዩ ልዩ ክልከላዎች ጭምር መቆቷን፣ከእስር በሁዋላ የጡቷ ህመምን ጠቅሷል። ሁሉም ጋዜጠኞች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል።

በአሁኑ ወቅት የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ውብሸት ታዬ፣ተመስገን ደሳለኝ፣ የሱፍ ጌታቸው እና የሌሎቹም ፖለቲካና የህሊና እስረኞች የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵአ ጉዞ ዕቅድ ተከትሎ ከእስር ይፈቱ ወይም አይፈቱ ታወቀ ነገር የለም በሚባልበት በዚህ ወቅት የቀዳሚ ገጽ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ የነበረው ሀብታሙ ምናለ በደህነቶች ታፍኖ መወሰድ አንዱን ፈቶ ሌላ ማሰር እንቅስቃሴ አስመስሎታል።

ትላንት ተፈቱትን ከዞን ዘጠኝ አባላት አምስቱ በስተቀር በቀሪዎቹ ላይ ክሱ ይቀጥላል ከመባል አልፎ የፖለቲካው ውሳኔ ምን እንደሆነ አልታወቀም። በትላንቱ ዘገባችን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ፣ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጦማሪ ዘላለም ክብረት፣ማህሌት ፋንታሁንና ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ ዛሬ ማምሳውን በፍትሕ ሚኒስቴር ውሳኔ መፈታታቸው የታወቀ ሲሆን ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።የቀሩት በእስርና በስደት ያሉ አምስት ጦማሪያን ጉዳኢ በተጀመረው የክስ ሂደት ይቀጥላል ቢባልም ቁርጥ አለ ውሳኔ አለመሰጠቱ ታውቋል። በክሱ ላይ ብኢን ለመስጠት ከመጪው ቀጠሮ ሐምሌ 13 ቀን 2007 በፊት ይፈቱ ወይ እንደተባለው ክሱ ቀጥሎ ብይን ይሰጥ አልታወቀም።

ከአስሩ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች መካከል የክስ ሂደታቸው ይቀጥላል የተባለው የክሱ መዝገብ በስሟ የተከፈተውን ሶሊያና ሽመልስ ፣ አቤል ዋበላ ሱጌቦ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሃይሉ እና አጥናፉ ብርሃኔ ጉዳይ መታየቱ እንደሚቀጥል ከፍርድ ቤቱ የተገኘ መረጃ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

No comments:

Post a Comment