መንግስት አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ማሪያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍንና ተዋቸው ዳምጤ ዛሬ ሰኔ 29/2007 ዓ.ም መናገሻ ፍርድ ቤት ቀርበው ለሐምሌ 28/2007 ዓ.ም ተቀጥረዋል፡፡ የዛሬው ቀጠሮ ባለፈው ፍርድ ቤት ማረሚያ ቤት ተዋቸው ዳምጤ በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብለት የጠየቀውን ብርሃኑ ተክለያሬድ ‹‹ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አይገኝም፡፡ ታስሮ የሚገኘው ቃሊቲ ነው፡፡ በሚቀጥለው እናቀርባለን›› በማለቱ ሲሆን በዛሬው ቀንም ሳያቀርበው ቀርቷል፡፡
ይሁንና ተዋቸው ዳምጤ ማረሚያ ቤቱ ብርሃኑ ተ/ያሬድን በመከላከያ ምስክርነት ለማቅረብ ፍላጎት እንደሌለው ገልጾ ቀሪዎቹ ሶስት ምስክሮች እንዲሰሙለት ቢገልጽም ፍርድ ቤቱ ‹‹ስራ በዝቶብናል፡፡ በመሆኑም ዛሬ ምስክር እናሰማ ብንል የዛሬ መዝገቦችን መጨረስ አንችልም›› በሚል ለሐምሌ 28/2007 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ሰኔ 26/2007 ዓ.ም ሊታዩ የነበሩ መዝገቦችን በስብሰባ ምክንያት ለዛሬ እንዳዞረ የገለጸ ሲሆን በርካታ መዝገቦችንም ‹‹በስብሰባ ምክንያት ዛሬ መስራት አልቻልንም›› እያለ ቀጠሮ ሰጥቷል

No comments:
Post a Comment