የፋሽስቱ ወያኔን አገዛዝ ለመገርሰስ በተለያዩ መንገዶች ሲታገሉ የቆዩት 3 ቱ ድርጅቶች ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን የጋራ ስምምነት ፊርማ መፈራረማቸውን ለሬዲዮ ክፍላችን የተላከው መረጃ ያመለክታል። የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ካሉበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ በጋራ የመስራቱን አስፈላጊነት ድርጅቶቹ ገልፀዋል።ይሀ በእንዲህ እንዳለ ውህደት የፈጸሙት 3 ቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የተጀመረውን የነፃነት ትግል ከግብ ለማድረስ ህዝባዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ዘንድ ጥሪ አቀረቡ የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፋሽስታዊ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ከገቡበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት ለማድረግ የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ የውህደቱን አስፈላጊነት የገለፁት ድርጅቶቹ አያይዘውም አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የጉጅሌው ወያኔን እድሜ ለማሳጠር በምናደርገው እልህ አስጨረሽ የነፃነት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው በመሰለፍ ድጋፍ ያደርግላቸው ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የነፃነት ቀኑ እየተቃረበ መሆኑን ያመላከቱት የድርጅቶቹ ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ህዝብ ባለበት ቦታ ሆኖ ትግሉን ማፋፋምና መቀላቀል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአገር ቤት፤ በውጭና በጎረቤት አገር የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከድርጅቶቹ ጎን በመሰለፍ የሞራል፤ የገንዘብና የሃሳብ ድጋፍ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ እንዳቀረቡም ለማወቅ ተችሏል። እየተደረገ ያለው ትግል ሁለገብ ትግል መሆኑን ያመለከቱት ድርጅቶቹ በተለይ በውጭ አገራት እንደተጀመረው ሁሉ በአገር ቤት ውስጥም ህዝቡ በተቀናጀ ሁኔታ ለወያኔ አልገዛም ብሎ እምቢተኝነቱን ማሳየት መጀመር እንዳለበት፤ የወያኔን ንግድ ድርጅቶች የሚያዳክሙ ማንኛውም እምጃዎችን መውሰድ መጀመር እና የፋሽስቱ ወያኔ ካድሬዎችንና ተከታዮችን በማግለል ቅጥረኞቹ እንዲሸማቀቁ ብሎም አገዛዙን ሸሽተው የነፃነት ትግሉን እንዲደግፉ አልያም እንዲቀላቀሉ ማድረግ የሚቻልባቸውን ርምጃዎች በተጠናከረ ሁኔታ መውሰድ መጀመር እንዳለባቸው አ ሳስበዋል።የድርጅቶቹ ውህደት በኢትዮጵያውያን ዘንድ እየተወደሰ መሆኑንም ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በተለይ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በጋራ ሆነው መታገል ባለመቻላቸው በተናጠል ያደርጉት የነበረው ትግል ውጤት ባለማምጣቱ አገዛዙ ለ 23 አመታት በስልጣን መቆየት መቻሉን በመግለጽ ይሄ አሁን የተጀመረው ሂደት ይህንን ለወያኔ አገዛዝ የተመቻቸ ትግል ይቀለብሳል በማለት ለነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ውህደቱ በሰው ሃይል፤ በእውቀትና በገንዘብ ረገድም ድርጅቶቹን መፈርጠም እንደሚያስችላቸውና የተጀመረውን የነፃነት ትግል ዕድሜ እንደሚያሳጥር በብዙዎች ዘንድ እየተገለጸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን አንድነት ያስቀደሙት፤ የህዝቦቿን ነፃነት የሚናፍቁና በሁለገብ የትግል እንቅስቃሴ አገዛዙን ለማስወገድ ውህደት ፈፅመው ኢትዮጵያን ለማዳን የተዘጋጁትን እነዚህን ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በተለይ የመከላከያ ሰራዊቱና አገር ተረካቢ የሆነው ወጣት ትውልድ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል።
No comments:
Post a Comment