Monday, September 15, 2014

ሽመልስ ከማል የሚመራው የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስልጠና በጩኸት ተበተነ።

ምንሊክሳልሳዊ‬
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ (ቂሊንጦ-አቃቂ) ውስጥ ይሰጣል የተባለው ስልጠና በተማሪው ጉርምርምታ እና ተቃውሞ የተበተነ ሲሆን ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው ሽመልስ ከማል ብከፍተና ድንጋጤ እና መረበሽ ውስጥ እንደነበር ታውቋል። ትማሪው ከተቃውሞ በተጨማሪ ሽመልስ ሲለፈልፍ የሚሰማው ባለመኖሩ እና ፌስቡክ በመጠቀም ፡የጆሮ ማዳመጫ በማድረግ ሙዚቃ እየስማ ሊለው ደሞ መስማት ደብሮት እያንቀላፋ የስልጠናውን ወንበር ገጥሞ ሲተኛ ተስተውሏል።‪ተማሪው እረፍት እንፈልጋለን ወሬ ሰለችን በማለት ቢጮህም ሽምመስ ከማል ዲስኩሩን ቢቀጥልም ተማሪው ተቃውሞውን ስብሰባውን በመርገጥ ወጥቶ ገልጿል። ይህን ተከትሎ ከሰአት በኋላ በየግሩፓችሁ እንድትገኙ ሲል ዩንቨርስቲው ማሳሰቢያ ሰቷል። ተማሪዎቹ ከየክፍለከተማቸው ጥሪ ተደርጎላቸው ትላንትና ወደ ዩንቨርስቲው ግቢ ይተስባሰቡ ሲሆን ከገቡ በኋላ መውጣት አይቻልም ተብሎ ግቢውን በመዘጋጋት ተማሪው በግድ ዩንቨርስቲው ውስት እንዲያድር እና ለዛሬው ስልጠና እንዲገባ ቢደረግን ስልጠናው ሳይሳካ ተበትኗል።ትላንትና ማታ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን ከግቢው መውትታ የሚቻለው በመጭው ቅዳሜ ከሰአት በኋላ መሆኑ ተነግሯል።የካፌው ምግብን በተመለከተ ደረጃውን ያልተበቀ እና ለጤንነት አስጊ ነው ያሉት ተማሪዎቹ በጥዋት ስልጠና ግቡ ቢባሉም እየተነጫነጩ 2 ሰአት ግቡ የተባሉ 3 ፡10 ገብተዋል፡ ወደ ስልጠናው እንደገቡም ለአንድ ሰአት ያህል ሳይቀጥል ሽመልስ ከማል ምናገር ሲጅምር ጩሀት ስለተጀመረ እና ስልጠናውን አንፈልግም የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች በመስማታቸው ረግጠው ለመውጣት ተማሪዎቹ ሲሞክሩ በአስተባባሪዎች በሩ በመዘጋቱ ሁኔታው ስላላማራቸው በሩን በመክፈት ከሰአት ብህውላ በቡድን ስልጠናው እንዲሰጥ በማለት አደራሹ ተዘግቷል።

No comments:

Post a Comment