Tuesday, September 16, 2014

በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ፣ በአሚ ባራ፣ በገዋኔ፣ በአፍዴራ፣ በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች መሬታቸውን ተቀምተው በርሃብ እየተቆሉ ነው

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘሐበሻ እንደዘገበው

የደርግ ስርዓት ወድቆ የኢህአዴግ መንግስት ሲመጣ ብዙ የአፋር መሬት ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለስ ተደርጓል። በሰሜናዊው የአፋር ክልል በዳሉል ወረዳ ይተዳደሩ የነበሩ ብዙ የአፋር ህዝቦች በግዴታ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲተዳደሩ ተደርገዋል!
ለምሳሌ፦ ያህል፥ ታላክ፣ ጎደለ፣ ሰሄሎ እና ሰውነ ሲሆን ከዚህ በላይ ስማቸው በተጠቀሱት ቦታዎች ከኢህአዴግ ሰርዓት በፊት ከአጼዎች ዘመን ጀምሮ የአፋር መሬት እንደነበረ ይታወቃል። ታላክ እና ጎደለ እሰከ ሰሄሎ በደጅ አዝማች አህመድ ሲተዳደሩ ሰውነ ደግሞ በኦና ማሕሙድ ይተዳደር ነበር።


በዚህ አካባቢ የሚተዳደሩ የአፋር ህዝቦች እስካሁን ድረስ በቋንቋቸው የመማር ማስተማር እንዲሁም ባህላቸውን የማሳደግ የሰብዓዊ መብት ያላገኙ ሲሆን በሚኖሩበት የትግራይ ክልል እንኳን የአፋር ብሄረሰብ አይባሉም ኢህአዴግ ይኸው ቆምኩላችሁ መብታችሁን አስከበርኩላችሁ እያለ የአፋር ህዝብ ግን ገና ጭቆና ላይ መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ወገኖቻችንና ለዴሞክራሲም ሆነ ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ የመብት ታጋዬች ሊያውቁልን ይገባል! ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ደርግን ለመዋጋት ወደ ጫካ ሲገቡ ይሄ የአፋር ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የቅርብ ጎረቤት ስለነበር ምግባቸውን አብስለው ለተጋዬች ከማቅረብ ጀምሮ ከጎናቸው የቆመ ህዝብ ቢሆንም ዛሬም ከጭቆና ልወጡ አልቻሉም።

ወድ የተከበረችሁ ወገኖቼ ሆይ ይሄን ስናገር ግን የቀረው የአፋር ህዝብ መብት ተክሮለታል ማለት አይደለም! በክልላችን በወያኔ ያልተወረረ የአፋር መሬት የለም። በአይሳኢታ፣ በዱብቲ፣ በአዋሽ ፣በአሚ ባራ፣ በገዋኔ ፣በአፍዴራ ፣በዶቢና ሚሌ የሚገኙ አፋሮች በአሁኑ ጊዜ ከመሬታቸው ተፈናቅለው በረሀብ እየተሰቃዩም ይገኛሉ።

የተንዳሆ የስኳር ፋብሪካ የተጀመረው በ2001 ዓ.ም ቢሆንም እሰከ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከስኳር ችግር አልወጣም። ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠሩት የህወሃት ባለ ስልጣናት ሲሆኑ አብዛኛቸው ከመከላኪያ ሰራዊት በጡረታ የወጡ መኮነኖች ናቸው! የአፋር ክልል መንግስትም ቢሆን ለስራቸው የሚሰጠውን ባጀት ወደ ውጭ ሀገር እየላኩ ማስቀመጥ ብቻ ነው!! ሌላው ቀርቶ በአፋር ክልል በሰላም ሲኖሩ የነበሩ የአማራና የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን በግዳጅ ከአፋር ክልል እያስወጡ ይገኛሉ። በዚህ አመት ብቻ ከ400 ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች በሰፈራ ፕሮግራም ወደ አፋር ክልል ገብተዋል!!

በመጨረሻም:- የአፋር ህዝብ ከኢትዮጵያ ነፃነት ታጋዮች ጋር ለሚደረገው ትግል ከዳር እስከ ዳር ዝግጁ መሆኑን በአፋር ወጣቶች ስም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። የአፋር ህዝብ ይህ የአንባገነን ስርዓት አብቅቶ የነፃነት ፀሃይ የምትወጣበት ቀን በጉጉት የሚጠብቅ ጭቁን ህዝብ ነው!

ነፃነት ለኢትዮጵያ


No comments:

Post a Comment