« አንድ የውጭ መርማሪ አቋቁመን ሥር ሰዷል የተባለውን ሙስና ከማረት ስንመረምር የት እንደገባ የማይታወቅ 5ሚሊዮን 60ሺህ ብር ተገኘ። ተጠያቂ ሆኖ የተገኘው ግርማይ ካህሳይ የሚባል የድርጅቱ ሒሳብ ሰራተኛ ሲሆን ሌላው ተጠያቂ ደግሞ ተክለ ወይኒ ነበር። ግርማይ ፍ/ቤት ሳይቀርብ 1ሚሊዮን 5መቶ ሺህ ብር መቀሌ ላይ አስረከበን። አዲስ አበባ ላይ በክንፈ ገ/መድህንና ጌታቸው አሰፋ በኩል 1ሚሊዮን 5መቶ ሺህ ብር በካሽ አስረከበ። ..ይህ ሁሉ ሲሆን ከግርማይ ይልቅ ከፍተኛ ስጋት ያደረበት ተክለወይኒ « ይህ ኮራፕሽን እያላችሁ የምታደርጉት ምርመራ ትክክል አይደለም፤ ማረት ላይ የተከሰተው ችግር የአሰራር ግድፈት እንጂ ሙስና አይደለም፤ እያንዳንዱ የህወሀት አመራር አባል ቢፈተሽ ተመሳሳይ ግድፈት ሊገኝበት ይችላል። ዓባይ ፀሐዬ ደግሞ ከሁሉም የባሰ ሙሰኛ እንጂ ሙስናን ሊታገል የሚችል፤ ሰው አይደለም» እያለ ያማርር ነበር። (ገፅ 322 -323)….
ወደ ሌላው ልሻገር፤ ዮሴፍ ረታ (በቅፅል ስማቸው ገይድ) የአማራ ክልል ፕ/ትና የብአዴን ማ/ኮሚቴ አባል ነበሩ። አቶ ዮሴፍ አቶ መለስና ተከታዮቻቸውን ከስልጣን እንዲወርዱ የጠየቁ ተቀዳሚ ሰው ናቸው፤ « ጠ/ሚ/ርና የአገሪቱ የጦር ኅይሎች ጠ/አዛዥ መለስ ዜናዊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ስዩም መስፍን፣ ዶ/ር ካሱ ኢላላ የሻዕቢያን ወረራ ለመቀልበስ የሚደረገውን ጦርነት እየተቃወሙ እንዴት ባሉበት የሥልጣን ደረጃ ሊቆዩ ይችላሉ? ለምናደርገው የሻዕቢያን ወረራ የመቀልበስ ጦርነትስ ዕንቅፋት አይሆንሁም ወይ? በማያምኑበት ጦርነት እንዴት ንቁ ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ? ስለዚህ ከዚሁ ውሳኒያችን ጋር የሥልጣን ሹም ሽር ማድረግ የለብንም ወይ?» ሲሉ መጠየቃቸውን የአቶ ገብሩ አሥራት መፅሐፍ በገፅ 306 አስፍሮዋል።
አቶ አውአሎም ወልዱ ተመሳሳይ ጥያቄ ሰንዝረዋል። አቶ ዮሴፍ ከዚህ ጥያቄ በኋላ በመለስ ዜናዊ ምን እንደደረሰባቸው ወይም ያሉበትን ሁኔታ መፅሐፉ ባይገልፅም ነገር ግን በመለስ ተባረው በእርሻ ስራ እንደተሰማሩ ማወቅ ተችሏል። አቶ ዮሴፍ የህሊና ነፃነታቸውን ይዘው የሚኖሩ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ብያቸዋለሁ!! .
.የአቶ ገብሩ “ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” መፅሐፍ በተለይ ሕወሐት ውስጥ ተዳፍኖ የቆየውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደሚያቀጣጥለው ምንም አያጠራጥርም። በገዢው ሰፈር ከባድ ቀውስ የሚያስነሳ እንደሆነ አያጠራጥርም!! ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የቀድሞ የገዢው ባለስልጣናት፣ የህግ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ዜጎች ስለመፅሐፉ የላቀ ትኩረትና ግምት ሰጥተው እየተነጋገሩበት ነው። ብዙ ጉድና ምስጢር የያዘ መፅሐፍ
No comments:
Post a Comment