Tuesday, September 16, 2014

“ከአሁን በኋላ ትግላችን ወደ ኋላ ሊመለስ አይገባም”የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ

ክቡራት እና ክቡራን የሙያ ባልደረቦቻችን መምህራን ሰላሙ ይብዛላችሁ:: የእናንተው የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ የእኛን የመምህራንን ድምጽ ለማሰማት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ይታወቃል:: እስካሁን ባደረገው ትግል በርካታ ማስፈራሪያ እና ዛቻ በሰልጣን ላይ ካለው መንግስት ቢደርስብንም ትግሉን ስንጀምር ጉዟችን ረጅም እንደሆነ በማወቃችን በየጊዜው የሚደርሱብንን በድሎች ተሸክመን እዚህ ደርሰናል ሆኖም የህወሀት የደህንነት ሀይሎች በኮሚቴው ላይ እያደረሱት ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት አካሄዳችንን እንድንቃኝ አስገድዶናል::
ከአሁን በኋላ ትግላችን ወደ ኋላ ሊመለስ አይገባም ትግላችን ከመከላከል ወደ ማጥቃት ሊሻገር ይገባዋል::
በዚህም መሰረት ከነገ ማለትም ከመስከረም 5,2007 አ.ም ጀምሮ በአዲስ መንገድ ለመንቀሳቀስ ጊዜያዊው ኮሚቴ የተለያዩ የትግል ስልቶችን ቀይሶ የሙያ ባልደረቦቻችንን ለማንቀሳቀስ እቅድ ነድፎ ወደ ስራ መግባቱን ይገልጻል::
በዚህም መሰረት ከነገው ከመስከረም 5 ጀምሮ የሚካሄዱ የተቃውሞ አካሄዶች:-
1. ከማንኛውም የኢህአዴግ አባል መምህር ጋር ያለንን ግኑኝነት ማቋረጥ::
የኢህአዴግ አባላት እንደሆኑ የምናውቃቸውን ግለሰቦች እየመረጥን ከማንኛውም ማህበራዊ ግኑኝነቶች ማግለል ማለትም ሰላምታ አለመለዋወጥ: በተሰበሰብንበት አካባቢ አባላቶቹ መጥተው ሲቀላቀሉ መበተን ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን የማግለያ መነገዶች በመጠቀም ከህዝቡ እንዲገለሉ እና ብቻቸውን እንዲቀሩ ማስቻል::
2. ነገ በሚጀመረው የመምህራን ስልጠና ላይ ተቃውሟችንን ለማሰማት ስበሰባው ላይ በተደጋጋሚ ሰበብ እየፈጠሩ መውጣት: ስብሰባውን መከታተል አቁመን መጽሀፍት እና ጋዜጣ ማንበብ እንዲሁም በስብሰባው ላይ ምንም አስተያየትም ሆነ ድጋፍ ከመስጠት መቆጥብ ይኖርብናል::
ማሳሳቢያ ይህንን ስናደርግ የኢህአዴግ ቅጥረኞች እየነጠሉ እንዳያጠቁን ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅብን ሲሆን ይህንን መረጃ ለቀሪው ባልደረቦቻችን ሼር በማድረግ ሁሉም የትግሉ አካል እንዲሆን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናድርግ ::
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ


No comments:

Post a Comment