(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010)የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።
ለረዥም ዓመታት በስደት የቆዩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ግድያና አፈና በአሜሪካ ኮንግረስና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ሲያጋልጡ የቆዩት አቶ ኦባንግ ሜቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የሚፈጸሙ የመሬት ወረራዎችን በማጋለጥና የሰለባዎቹን ድምጽ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል።

No comments:
Post a Comment