Sunday, September 30, 2018

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮነን በክብር እንዲሰናብቱ ያቀረበውን ሀሳብ ጉባኤው ሳይቀበለው ቀረ።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በ12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳድሩ ያላቸውን 13 አባላት ይፋ አድርጓል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከአመራርነት መልቀቅ የማይቀለበስ አቋሜ ነው ቢሉም ጉባኤው ወቅቱ አይደለም በሚል ወሳኔያቸውን ወድቅ አድርጎታል።


ብአዴን በማዕከላዊ ኮሚቴነት የማይወዳደሩ ብሎ ያቀረባቸው 13 ቱ አባላት በትምህርት፣ በአምባሳደርነት እና በክብር የተሰናበቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሚል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለትምህርት የሚላኩ እና አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙ ተብለው ከውድድር ወጭ የሚሆኑት አቶ ዓለምነው መኮንን፥ አቶ ለገሰ ቱሉ ፥አቶ ጌታቸው ጀምበር፤ አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ፣አቶ ደሳለኝ አምባው እና ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ ናቸው።

በክብር ቢሰናቱ ያላቸው ደግሞ አቶ ደመቀ መኮንን፥ አቶ ከበደ ጫኔ፥አቶ መኮንን የለውምወሰን፤ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና አቶ ጌታቸው አምባየን ናቸው፡፡

በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉትን አቶ ካሳ ተክለብርሀንና ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ ማዕከላዊ ኮሚቴው መነሻ ሀሳብ አቅርቧል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት 13 አመራሮች ለቀጣይ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ ያቀረበ ሲሆን ይህ መነሻ ጉባኤው ካጸደቀው በኋላ ብቻ ተግበራዊ የሚሆን ነው፡፡
ጉባኤው ነገ ጠዋት ከ1፡30 ጀምሮ ይቀጥላል የተባለ ሲሆን 65 አባላትን ያካተተ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ይመረጣል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ከተመረጡት   ውስጥም 13 ለብአዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይመረጣሉ ተብሏል።የአቶ በረከት ስምኦን እና የአቶ ታደሰ ካሳ ከማእከላዊ ኮሚቴው መታገዳቸው በጉባኤው ጸድቋል።

No comments:

Post a Comment