Sunday, September 30, 2018

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮነን በክብር እንዲሰናብቱ ያቀረበውን ሀሳብ ጉባኤው ሳይቀበለው ቀረ።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በ12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ለማዕከላዊ ኮሚቴ እንዳይወዳድሩ ያላቸውን 13 አባላት ይፋ አድርጓል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከአመራርነት መልቀቅ የማይቀለበስ አቋሜ ነው ቢሉም ጉባኤው ወቅቱ አይደለም በሚል ወሳኔያቸውን ወድቅ አድርጎታል።

Friday, September 28, 2018

በብአዴን ጉባኤ ላይ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች አልተገኙም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 18/2011) በባህርዳር እየተካሄደ ባለው የብአዴን ጉባኤ የለውጥ አደናቃፊ የሚባሉት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች አልተገኙም ተባለ።
በጉባኤው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ጨምሮ ብአዴንን ሲያሽከረክሩት የነበሩት አንጋፍዎቹ የአመራር አባላት አለመገኘታቸው ታውቋል።በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ አልተገኙም ከተባሉት አባላት መካከልም አቶ ከበደ ጫኔና አቶ አዲሱ ለገሰ ይገኙበታል።
የብአዴንን ጉባኤ በፕሬዝዲየም አባልነት ኣንዲመሩ የተመረጡት አቶ ደመቀ መኮንን፣አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ዶክተር አምባቸው መኮንን፣አቶ ብናልፍ አንዱአለምና አቶ ምግባሩ ከበደ ናቸው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት ስማችንና ክብራችን ይመለስልን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 18/2011) የቀድሞ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት አባላት አሁን ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው መንግስት የተቀማነውን ስማችንንና ክብራችንን ያስመልስልን ሲሉ ጥያቄ አቀረቡ።
የሰራዊት አባላቱ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት በአርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ አማካኝነት መሆኑም ታውቋል።አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ 800 ያህል ለሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት የምስጋናና የአክብሮት የምሳ ግብዣ ማድረጉም ተመልክቷል።
ከ22 አመታት በኋላ ወደ ሃገሩ የተመለሰው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከተለያዩ የህብረትሰብ ክፍሎች ጋር በመገናነት ምስጋናና ክብር በመስጠት ግብዣ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ ዛሬ ላይ ደግሞ የምስጋናና የአክብሮት የምሳ ግብዣ ስነስርአቱን ለቀድሞ የጦር ሰራዊት አባላት አድርጓል።
800 የሚሆኑ የሰራዊቱ አባላት ተገኝተዋል በተባለበት በዚህ ስነስርአት ላይ የቀድሞ የምድር ጦር፣የባህር ሃይል፣የአየር ሃይል፣የአየር ወለድና ሌሎች የሰራዊቱ አባላት ተገኝተዋል።

የምህረት አዋጅ የመጠቀሚያ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ ቀረው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 189/2011) መንግስት በቅርቡ ባጸደቀው የምህረት አዋጅ የመጠቀሚያ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ እንደቀረው ተገለጸ።
እስካሁን በዚህ እድል የተጠቀሙና የምህረት ሰርተፍኬት የወሰዱ ሰዎች ቁጥርም 495 ብቻ መሆኑ ታውቋል።
በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውጪ ከሆኑ በኦንላይን በመመዝገብ በወጣው የምህረት አዋጅ መጠቀም እንደሚችሉም ተመልክቷል።
በምሕረት አዋጁ መሰረት በማረሚያ ቤት የሚገኙና ከማረሚያ ቤት ውጭ የሆኑ፣ከግንቦት 30 ጀምሮ የምህረት ሰርተፍኬት እየተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።
እስከ ህዳር 30/2011 ይህው እንደሚቀጥልም ተገልጿል፣በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ድረ ገጽ www.Fag.gov.et እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

Thursday, September 27, 2018

ከምንም ጊዜ በላይ ዛሬ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ላይ ነን ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 17/2011) ከምንም ጊዜ በላይ ዛሬ ለእውነት የምንቆምበት ጊዜ ላይ ነን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ገለጹ።
“የሐሰት ወሬዎች፣ አሳሳች አሉባልታዎች በስሜት የሚነዱ ማስመሰሎች በገፍ አሉ”በማለት የመስቀልን በአል በማስመልከት መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር አብይ አሕመድ እንደደመራ ችቦ ተደምረን መቆም አለብን ሲሉም ጥሪ አስተላልፈዋል።
“ችቦዎች ብቻቸውን ደመራ አይመሰርቱም፣አንድ ላይ ሆነው በአንድ ዋልታ ዙሪያ መቆም አለባቸው ይህ ዋልታም ኢትዮጵያዊነታችን ነው “ብለዋል ዶክተር አብይ አህመድ የመስቀል በአልን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ።

በሃረር ከተማ ያለው የቆሻሻ ክምችት አስጊ ደረጃ ላይ ደረሰ።

( ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሃረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት የደረቅ እና እርጥብ ቆሻሻን የማስወገድ ሥራውን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በማቋረጡ ከተማዋ በከፍተኛ የቆሻሻ ክምር እየተዋጠች ነው። ይህን ተከትሎ በከተማዋ ያጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በሽታ ይነሳል የሚል ስጋት በነዋሪዎቹ ዘንድ አሳድርዋል። በ4ኛ፣ ሸንኮር፣ ፖሊስ ሜዳ፣ ደከር መውጫ፣ ኦጋዴን አንበሳ አካባቢዎች ከፍተኛ የቆሻሻ ክምር የተከማቸባቸው አካባቢዎች ናቸው። በተለይም ከቀላድ አንባ እና ከቀበሌ 10 ኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚወጣው የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ ክምችት በአፋጣኝ እልባት ካልተሰጠው የከፋ የጤና ቀውስ ይፈጠራል ተብሎለታል። የክልሉ መስተዳድር የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ የዜጎችን ጤንነት እና ደኅንነት ለመጠበቅ አፋጣኝ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አለመውሰዱ እንዳሳዘናቸው የከተማ ነዋሪዎችን አሳዝኗል። በሃረር ያለው አስተዳደራዊ ችግሮች በፈጠሩት ችግር የከተማዋ ቆሻሻ እየተከማቸ መምጣቱንና የጤን እክሎች መፈጠራቸው ከዚህ በፊት ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

አሜሪካ ፖሊሲዋን በመቀየር የአብይን መንግስት ማገዝ እንደሚገባት አንድ የአሜሪካ የስትራቴጂክ ጥናት ባለሙያ ተገናጉ

( ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአሜሪካ ኢንተርፕራይዝ ኢንስቲቲዩት ዋና አጥኝ የሆኑት ኤሚሊ ኤስቴሊ “የኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ፋይዳ” በሚል ርዕስ ለአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኪሜቴ ባወቀረቡት ጥናት ላይ እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ መሻሻል በማሳየቷ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት በማሻሻሏ የተስፋ ስሜቶችን ቢፈነጥቁም፣ በየጊዜው በሚታዩት የአካባቢ ግጭቶችና የውጭ ሃይሎች አካባቢውን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት እሩጫ የተነሳ በአገሪቱ ከፍተኛ የሆነ አደጋ መደቀኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የሚታየው ፈጣን የፖለቲካ ለውጥ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱት የብሄር ግጭቶች የአገሪቱን ሰላም አደጋ ውስጥ ጥለውታል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በወሰዱዋቸው የሰብአዊ መብት ማሻሻያ እርምጃዎች የህዝቡ ተስፋ ከፍ ብሎአል። ነገር ግን በዚያው ልክ የብሄር ግጭቶች ጨምረዋል። በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት 130 ሺ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ተደጋጋሚ ግጭቶች መከሰታቸው አልሸባብ የኢትዮጵያ የሶማሊ ተወላጆችን በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ሊፈጽም ይችላል። የአብይ መንግስት የሰብአዊ መብት አያያዙን እያሻሻለ በሚመጣም ዜጎችን በብዛት እያፈሰ ማሰሩና ኢንተርኔት ማፈኑ ይህን የተወሳሰብ ችግር የሚያባብሰው እንጅ የሚቀንሰው አይሆንም። የቀድሞ የጸጥታ አባላት በሶማሊ ክልል በሚፈጥሩት ችግር ተጨማሪ አለመረጋጋት ሊፈጠር እንደሚችል አጥኝዋ አመልክተዋል። ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ ባለስልጣናትም በአገሪቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ቀውስ በመፍጠር የዲሞክራሲ ሽግግር እንዳይካሄድ ሊያደርጉ ይችላሉ። አቢይ እየጨመረ የመጣውን የብሄር ፍጥጫ እያረገበ መምጣት ካልቻለ እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያ የተጣለበትን ከፍተኛ ተስፋ እውን ማድረግ ካልቻለ ከራሱ ወገን የሚያገኘውን ህዝባዊ ድጋፍ ሊያጣ ይችላል በማለት ጥናቱ አመልክቷል። የኢትዮጵያ አለመረጋጋት አሜሪካ አልሸባብንና በሶማሊያ የሚገኘውን አልቃይዳን ለመቆጣጠር እንቅፋት ይፈጥርባታል። ኢትዮጵያም የውስጥ ጉዳዩዋን ለመፍታት በምትወስደው እርምጃ በአፍሪካ ህብረትና በአካባቢው ፖለቲካ ላይ የምትጫወተውን ሚና ይቀንሰዋል። በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተጀመረው መልካም ግንኙነት ጥቅምና ጉዳቶችን ይዞ መምጣቱም በጥናቱ ተመልክቷል። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያደረገችውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር መወሰኗ የዲፕሎማሲ

Four local officials from Benishangul killed in Wollega

by Engidu Woldie
ESAT News (September 27, 2018)
Four local officials from Benishangul Gumuz region in Western Ethiopia were killed in an ambush in Wellega, Oromo region.
The officials were on their way back to Kemash Zone from a security meeting in Wellega when they were attacked by unidentified gunmen in Gimbi, West Wellega, the report by the Ethiopian Television said.
The report quoted the regional police commissioner, Seyfedin Harun, as saying that the four officials of Kemash Zone were in Wellega for a joint regional security meeting with their counterparts from the Oromo region on Tuesday and were ambushed and killed on Wednesday as they were returning to Kemash.
The commissioner said a search is underway to catch the gunmen.
Tensions remain high in Kemash town following news of the killings and businesses and local government offices are closed.
The commissioner said there are elements in the region that were bent on inciting violence between the people in Oromo and Benishangul regions.

“አዲሱ አስተሳሰብ አሮጌውን ያሸንፋል” ሲሉ የብአዴን ሊቀመንበር ተናገሩ

( ኢሳት ዜና መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ/ም ) ሊቀመንበሩ አቶ ደመቀ መኮንን የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር አሁን የሚታየው ግጭት በአሮጌው አስተሳሰብ እና በአዲስ አስተሳሰብ መካከል በሚፈጠር ቅራኔ የመጣ ነው። አዲሱ አስተሳሰብ አሮጌውን ያሸንፋል ሲሉም በእርግጠኝነት ተናግረዋል። አቶ ደመቀ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ከመወጋገዝ ይለቅ መተጋገዝ፣ ከመጠላለፍ ይለቅ መተቃቀፍ እንዲሁም ከመሰባበር ይልቅ መተባበር እንደሚገባ ገልጸዋል። ለውጡ በብርቱ ትግል የመጣ እንደመሆኑ፣ ለውጡን ለማስቀጠልም ብርቱ ትግል ይጠይቃል ብለዋል። አገሪቱ በሁለት የፖለቲካ አስተሳሰቦች መካከል እየተናጠች እንደምትገኝ የገለጹት አቶ ደመቀ፣ በአንድ በኩል አህዳዊ አስተሳሰብን ለማስፈን የሚፈልጉ በሌላ በኩል ደግሞ ብሄረሰባዊ ማንነትን ከሌሎች ለመነጠል የሚሹ ሃይሎች በሁለት ጫፍ ቆመው እየታገሉ ነው ። የድርጅቱ ምክትል ሊ/መንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ዘመኑ እርስ በርስ የምንወነጃጀልበት ሳይሆን በይቅርታና በፍቅር የምንጓዝበት ነው ብለዋል። በክልሉ አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት መስፈኑን የገለጹት አቶ ገዱ፣ በክልሉ ስራ መፍጠር ዋናው ፈተና ሆኗል ብለዋል። የጨለማው ዘመን ምዕራፍ እስከወዲያኛው መዘጋቱንና አዲስ የተስፋ ጸዳል እየመጣ ቢሆንም፣ ለውጡ ቀጣይነት የሚኖረው ተቋማት ሲገነቡ ነው በማለት ድርጅታቸው ለተቋማት ግንባታ ተገቢውን ትኩረት እንደሚሰጥ ገልጸዋል። በዚህ ጉባኤ ወጣቶች ወደ አመራር ቦታ እንዲመጡ መደረግ እንዳለበት ሁለቱም የብአዴን መሪዎች አሳስበዋል።

Wednesday, September 26, 2018

ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ተፈቱ


(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ ከተከሰተው አልመረጋጋት ጋር በተያያዘ የታሰሩት ብርሃኑ ተክለያሬድና መኮንን ለገሰ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ።

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት ወደ ኢትዮጵያ በገቡበት ወቅት አስተባባሪ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሁለቱ ወጣቶች የታሰሩት በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች በታፈሱበት ወቅት እንደነበርም ይታወሳል።

ሁለቱ ወጣቶች ዛሬ ከወህኒ ወጥተው ቤተሰባቸውን መቀላቀላቸው ተረጋግጧል።

የአየር ትራፊክ ሰራተኞች ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ።

ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲወጡ ትላንት ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን አቃቢ ሕግ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ እጠይቃለሁ ማለቱ ተመልክቷል።

በሃገሪቱ ላይ የ70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ኪሳራ አድርሰዋል በሚል ተጠርጥረው የአየር ትራፊክ ተቆጣጠሪ ሰራተኞች በ20ሺ ብር ዋስ እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ትላንት ነው።

Tuesday, September 25, 2018

የድሬዳዋ ፖሊስ የምርመራ ውጤት ይፋ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 16/2011) የድሬዳዋ ፖሊስ ለ13 ሰዎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን ግጭትና መንስኤ በመመርመር ውጤቱን ይፋ አደረገ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ ሐምሌ 29 /2010 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት በ3 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ የ13 ንፁሀን ዜጎች ህይወት ማለፋንና በ42 ቤቶች ላይ ቃጠሎና ዝርፊያ መካሔዱን ገልጿል።ኮሚሽኑ ባደረገው ምርመራ 4 ግለሰቦች በቤት ቃጠሎ፣ 21 ግለሰቦች ደግሞ በቀጥታ በግድያው መሳተፋቸው በማስረጃ ተረጋግጧል።
በ5 ተጠርጣሪዎች ላይ ደግሞ ማስረጃ እያሰባሰበ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
ከ13 ሟቾች 8ቱ የ1 ዓመት ህፃንን ጨምሮ ከ15 ዓመት በታች እድሜ ያላቸው ናቸው።
በንብረት ረገድም ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት ሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 15/2011)የኢትዮጵያ መንግስት በገባው ቃል መሰረት ሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ።
የሃገሪቱን ወህኒ ቤቶች ከሕግ አግባብ ውጭ ከታሰሩ ሰዎች ነጻ በማድረግ የጀመረውን ርምጃ መቀልበስ አይኖርበትም ሲልም አሳስቧል።
ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ ሰልፍ በመውጣታቸው የታሰሩ በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቅርቧል።
“የጅምላ አፈሳና እና እስራት በሰብዓዊ መብት አከባበር የታየውን ርምጃ ስጋት ውስጥ ጥሎታል” በሚል ርዕስ ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል  መግለጫ አውጥቷል።
ፖሊስ ከሶስት ሺህ ሰዎች በላይ መታሰራቸውን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ በአስረጅነት በመጥቀስ መንግስት ከህግ ውጭ ሰዎች ማሰሩን ያቁም ሲል ጥሪ አቅርቧል።
ባለፉት ወራት የሃገሪቱን ወህኒ ቤቶች ያለፍርድ ለታሰሩ ሰዎች ነጻ ለማድረግ የጀመረውን የሚደነቅ ሙከራ ሌሎችን ከህግ ውጭ በማሰር ሊደግመው አይገባም ሲልም አሳስቧል።
በሃገሪቱ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ሰልፍ በመውጣታቸው የታሰሩት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጥሪ ያቀረበው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሺሻ በማጨስና ከጫት ጋር በተያያዘ የታሰሩትን በተመለከተም ተቃውሞውን አቅርቧል።

የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተወሰዱ

ባለፈውሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ። ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠይቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩትየማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል ::
ይሁን እና ምን አይነት ስልጠና ላይ እንዳሉ የገለፁላቸው ነገር የለም::
ለልጆቻቸው የቋጠሩትን ስንቅም በአካባቢው ላገኟቸው የኔ ቢጤዎች መፅውተው ተመልሰዋል::
በአዲስ አበባ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ ወጣቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታፈሱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ ::

የዛሬ ሳምንት ሰኞ ከአዲስ አበባ ታፍሰው ሰንዳፋ የነበሩ 36 የጨርቆስ ወጣቶች ወደ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ መወሰዳቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታውቁ::

( ኢሳት ዜና መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) ትላንት ልጆቻቸውን ለመጠየቅ ጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ የተገኙት በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን መጠየቅ ሳይችሉ እዚያው አድረው ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ለኢሳት እንደተናገሩት የማሰልጠኛው ጠባቂዎች ልጆቻቸው ስልጠና ላይ ስለሆኑ ሊያገኟቸው እንደማይችሉ ነግረዋቸዋል :: ይሁን እና ምን አይነት ስልጠና ላይ እንዳሉ የገለፁላቸው ነገር የለም:: ለልጆቻቸው የቋጠሩትን ስንቅም በአካባቢው ላገኟቸው የኔ ቢጤዎች መፅውተው ተመልሰዋል:: በአዲስ አበባ ቁጥራቸው በውል ያልተገለፀ ወጣቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ እየታፈሱ መሆኑን መረጃዎችን ጠቅሶ ባልደረባችን ስለሺ ሽብሩ ከአዲስ አበባ ዘግቧል።

Monday, September 24, 2018

Ethiopia: New figures emerge in death toll as mass arrest in Addis Ababa also targets opposition supporters

ESAT News (September 24, 2018)
Police announced new figures in death toll in deadly violence in Addis Ababa as they carried out mass arrests over the weekend. Police said the arrests were made to fight growing crimes and lawlessness in the capital but the presence of supporters and members of opposition parties among the detainees and the alleged criminals have led some to believe a return to old tactics by the government.
Twenty eight people have been killed last week in deadly violence in several districts in Addis Ababa, according to the capital’s police commissioner. The new figures are in addition to the 23 people police said were killed last week in Burayu, in the outskirts of the capital.

በጋምቤላ 5 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በጋምቤላ ከተማ 5 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ተገደሉ።
ባለፉት ሁለት ቀናት በከተማው ህዝብ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ በወሰደው የሃይል እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በሀገሪቱ ለውጥ ቢኖርም በጋምቤላ ግን ለውጡን ለማየት አልቻልንም በሚል የተጀመረው ተቃውሞ ተጨማሪ የሰው ህይወት ሊያጠፋ እንደሚችል ነዋሪዎች ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በክልሉ አስተዳደራዊ ለውጥ እንዲመጣ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው።
በተለይም የክልሉ ፕሬዝዳንት ጋት ሉዋክ ቱት የሕዝብ ችግሮችን አልፈቱም በሚል ከስልጣን እንዲነሱ በመጠየቅ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ በክልሉ የጸጥታ ሃይሎች ተገድለዋል።

በብአዴን ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በቅርቡ በባህርዳር ይካሄዳል ከተባለው የብአዴን ጉባኤ በፊት በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት መንገሱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።
በድርጅቱ ስራአስፈጻሚ አባላት መካከል ከፍተኛ አለመተማመንና አለመግባባት መፈጠሩን ከአካባቢው ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በብአዴን ውስጥ ያለው ሃይል ሂደቱን ላለማስቀልበስ ጠንክሮ እየሰራ ቢሆንም የተወሰኑ የድርጅቱ አመራሮች ጉባኤውን ለማደናቀፍ እየሰሩ ናቸው ተብሏል።
የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ስራ አስፈጻሚ አካላት በውጥረት ውስጥ ሆነው በባህርዳር ስብሰባ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።
በክልሉ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ጽሕፈት ቤት አዳራሽ ምሽቱን ስብሰባ የሚያደርጉት 12ቱ የብአዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከመስከረም 17/2011 ጀምሮ የሚካሄደውን የድርጅቱን ጉባኤ በተመለከተ በአጀንዳዎችና በሪፖርቱ ላይ ሲከራከሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
በጭቅጭቅና በንትርክ በተካሄደው ስብሰባ ለውጡን የሚያደናቅፉት የብአዴን አመራር አባላት በማህበራዊ ድረ ገጾች ዘመቻ ተከፍቶብናል ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
በተለይም በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ያነጣጠረ ትችት ሲያቀርቡ እንደነበር ነው የተነገረው።

Ethiopia: Security forces kill five in Gambella

ESAT News (September 24, 2018)
Security forces killed five people in Gambella, western Ethiopia in a protest demonstration by residents demanding the removal of the regional president, Gatluak Tut.
Residents say the political reform reform measures at the federal level has not trickled down to their region, and hence demand changes in the local government.
Federal police and defense forces have opened fire at demonstrators demanding changes in the local government, according to residents Gambella who spoke to ESAT.
The residents also said Gambella remains tense after the killing of the protesters.

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የ28 ሰዎች ተገድለዋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 14/2011) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተፈጠረው ሁከት ጋር ተያይዞ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ።
መስከረም 7/2011 በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን 5 ሰዎች ጨምሮ ከመስከረም 2 እስከ መስከረም 7/2011 28 ሰዎች መገደላቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ናቸው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከግድያውና ሁከቱ ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ የተያዙ ቢሆንም እየተጣራ በከፊል መለቀቃቸውን ገልጸዋል።
ከነዚህ ውስጥ 1 ሺ 200 የሚሆኑት ተለይተው ወደ ጦላይ መወሰዳቸውንም ገልጸዋል።
እነዚህም ተሃድሶ ከተሰጣቸው በኋላ ይለቀቃሉ ብለዋል።

Friday, September 21, 2018

ኢትዮጵያ የተደቀኑባት ፈተናዎች የገዘፉ መሆናቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) ኢትዮጵያ የተደቀኑባት ፈተናዎች የገዘፉ መሆናቸውን አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ ሃይሎችም ከችግሩ ስፋት አንጻር በሃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል።
አዲሶቹ የኢሕአዴግ መሪዎች ከ27ቱ አመት ኢሕአዴግ በተለየ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/በቅርቡ በቀጣይ ጉዞው ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም አስታውቀዋል። ለዊሊያም ዴቪሰን በኢትዮ-ኢንሳይት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት አቶ ሌንጮ ለታ ለፖለቲካ ሃይሎችም ምክር ለግሰዋል።
ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ማምጣት ይቻላልን በማለት ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ሌንጮ ለታ “የትኛው ኢሕአዴግ” በማለት ምላሽእቸውን የጀመሩት አቶ ሌንጮ ለታ በሃገሪቱ የማሻሻያ ርምጃዎችን እየወሰደ ያለው ኢሕአዴግ፣አምና ከነበረው ኢሕአዴግ በመሰረቱ ፍጹም የተለየ ነው ብለዋል። 
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011) ኢትዮጵያ የተደቀኑባት ፈተናዎች የገዘፉ መሆናቸውን አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ የፖለቲካ ሃይሎችም ከችግሩ ስፋት አንጻር በሃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱም ጥሪ አቅርበዋል።
አዲሶቹ የኢሕአዴግ መሪዎች ከ27ቱ አመት ኢሕአዴግ በተለየ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ቁርጠኛ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር/ኦዴግ/በቅርቡ በቀጣይ ጉዞው ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም አስታውቀዋል። ለዊሊያም ዴቪሰን በኢትዮ-ኢንሳይት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት አቶ ሌንጮ ለታ ለፖለቲካ ሃይሎችም ምክር ለግሰዋል።
ኢሕአዴግ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ በኢትዮጵያ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ማምጣት ይቻላልን በማለት ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ሌንጮ ለታ “የትኛው ኢሕአዴግ” በማለት ምላሽእቸውን የጀመሩት አቶ ሌንጮ ለታ በሃገሪቱ የማሻሻያ ርምጃዎችን እየወሰደ ያለው ኢሕአዴግ፣አምና ከነበረው ኢሕአዴግ በመሰረቱ ፍጹም የተለየ ነው ብለዋል። 

በሕጻናት ሞት ኢትዮጵያ ከግንባር ቀደም አምስት ሃገራት አንዷ መሆኗ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 11/2011)በሕጻናት ሞት ኢትዮጵያ በአለም ላይ ከግንባር ቀደም አምስት ሃገራት አንዷ መሆኗን ተገለጸ።
የተባበሩት መንግስታት ተቋም እንዳስታወቀው ባለፈው የምዕራባውያኑ አመት 2017 133ሺ ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ሞተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ኢንተር ኤጀንሲ ቡድን ከአለም ጤና ድርጅት፣ከተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የሕጻናት ድንገተኛ ፈንድና ከአለም ባንክ የሰበሰባቸውን መረጃዎች መሰረት በማድረግ ባጠናቀረው ዘገባ በ2017 አመተ ምህረት የሞቱት 133ሺ ሕጻናት እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ነው።
ከነዚህ ውስጥ 95ሺ የሚሆኑት አንድ ወር ሳይሞላቸው መሞታቸውም ተመልክቷል። ለሕጻናቱ ሞት የተመጣጠነ ምግብና ውሃ እጦት፣መሰረታዊ ሕክምና አለማግኘት ምክንያት መሆናቸው ተመልክቷል።
ህንድ፣ናይጄሪያ፣ፓኪስታንና ኮንጎ በተመሳሳይ ከፍተኛ የሕጻናት ሞት የተመዘገበባቸው ሃገራት ሆነዋል።

Ethiopia: Suspects in Burayu ethnic attack arraigned before court

ESAT News (September 21, 2018)
Over 200 suspects of ethnic attack perpetrated last weekend outside Ethiopia’s capital Addis Ababa have been arraigned today before the 19th bench of the federal high court.
The defendants were accused of planning and coordinating the attacks in Burayu and other districts in the outskirts of the capital where at least 58 people were killed.
The federal police also presented names of individuals who allegedly used vehicles in transporting the perpetrators and making payments to the alleged participants in the ethnic attack.

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና አቶ ለማ መገርሳን በድጋሜ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

( ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ/ም ) የቀድሞው ኦህዴድ የአሁኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ለሶስት ቀናት በጅማ ከተማ ባካሄደው 9ኛ ድርጅታዊ ጉባዔው የቀድሞው የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን እና አቶ ለማ መገርሳን በነበሩበት እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል። አመራሮቹ እስከ ቀጣይ የድርጃታዊ ጉባኤ ድረስ በሹመታቸው ላይ ይቆያሉ። ድርጅቱ የፓርቲው መሪዎችን ከመምረጥ በተጨማሪ የሥያሜ ለውጥ፣ ድርጅታዊ መዝሙሩን በመቀየር የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱን መሪዎቹንም በማሰናበት ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። አዲሱን የኦዴፓ አመራርን አስመልክቶ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አዳዲስ አመራሮች ወደ ፊት የመጡበት በመሆኑ ይህ ጉባኤ ከሌላው ጊዜ የተለየ ታሪካዊ ነው። በአዲስ መንፈስና ሀሳብ ለማገልገል የተነሳው ፓርቲው በፍቅርና በአንድነት

ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ወገኖቻቸው ድጋፍ ለማግኘት የተንቀሳቀሱ 35 ወጣቶች ታሰሩ

( ኢሳት ዜና መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ/ም ) 35 የጨርቆስና እና አካባቢው ወጣቶች ከቡራዩ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆናቸውንና ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በሰንዳፋ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ተናግራል። ወጣቶቹ ከአካባቢያቸው በሰበሰቡት ገንዘብ የገዟቸውን ምግብ እና ቁሳቁሶች አስረክበው ሲመለሱ ፣ የኮልፌ ቀራንዮ ፖሊስ ምግብ እና ቁሳቁስ ጭነውበት ከነበሩት 3 መኪኖች ጋር በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስን አስተያየት ለማግኘት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ቢደረግም አልተሳካም።

Thursday, September 20, 2018

ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች እርዳታ የማሰባሰብ ዘመቻ ተጀመረ

( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት በቡራዮ ከተማ ለደረስው አስከፊ ጭፍጨፋ ስለባ ለሆኑ ወገኖቻችን የገንዘብ ማስባስብ ዘመቻ ጀምሯል። የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የሰብ ዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ ጉዳተኞቹን ስፍራው ድረስ በመሄድ ከጎበኙ በኋላ ጎፈንድ አካውንት በመክፈት በአፋጣኝ ዜጎችን ለመታደግ የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻውን አስጀምረዋል። ግሎባል አሊያንስ የጠየቀውን የእርዳታ ጥሪ ተከትሎ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ፈጣን ምላሻቸውን እየሰጡ ነው። እሳክሁንም ከሁለት መቶ ሽህ ዶላር በላይ ተሰብስቧል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ”Global Alliance for the Rights of Ethiopians” በተለያዩ የዓለማችን ክፍል በሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጉዳት ሲደርስባቸው እገዛ ያደርጋል። በተጨማሪም በአገራቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለተፈጸሙባቸው፤ በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ከአማካኝነት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ጉዳት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያዊያንም ሲረዳ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሰራተኞች፤ የጋሞ ጎፋ ዞን አስተዳደርን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የገንዘብና የቁሳቁስ አስተዋጾ በማድረግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ታዋቂው የኪነጥበብ ባለሙያው ቴዎድሮስ ከሳሁን ከቡራዩና አካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ልገሳ አድርጓል ።

ኦህዴድ ነባር አመራሮችን አሰናበተ

( ኢሳት ዜና መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ/ም ) የኦህዴድ መስራቾችና የህወሃት ደጋፊዎች ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጌታቸው በዳኔ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ ግርማ ብሩ፣ እሸቱ ደሴ፣ ተፈሪ ጥያሩ፣ ደግፌ ቡላ፣ አበራ ሃይሉ፣ ሱሌይማን ደደፎ፣ ኢተፋ ቶላ፣ ዳኛቸው ሽፈራውና ጊፍቲ አባሲያ ከድርጅቱ ተሰናብተዋል። ፓርቲው ራሱን ከኦህዴድ ወደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወይም ኦዴፓ ቀይሯል። በጅማ እየተካሄደ ባለው የድርጅቱ ጉባኤ ላይ ሊቀመንበሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ቀን ቀን ከድርጅቱ ማታ ማታ ደግሞ ከጠላቶች ጋር አብረው የሚውሉ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቀው ነበር።

Wednesday, September 19, 2018

የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ኦሮሞ ሃላፊነት አለበት ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ

( ኢሳት ዜና መስከረም 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) ጠ/ሚኒስትር አብይ ይህን የተናገሩት በሊቀመንበርነት የሚመሩትን የኦህዴድን 9ኛ ድርጅታዊ ጉበኤ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር ነው። ኦሮሞ “ የዚህን አገር አንድነት የማስጠበቅ ሃላፊነት አለበት” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስና ለውጡን ለመቀልበስ የሚሞክሩ ሃይሎችንም አስጠንቅቀዋል። ከጠላቶቻችን ጋር ሆናችሁ የኦሮሞን ትግል ወደ ሁዋላ ለመመለስ የማታስቡን ከጠላቶቻችን ለይተን አናያችሁም ያሉት ዶ/ር አብይ፣ በኦሮሞ ስም መነገድ ማብቃት አለበት ብለዋል። አብሮ መቆም ማለት ጠዋት እዚህ ከሰዓት እዛ እየሄዱ መስራት አለመሆኑን ፣ በኦሮሞ ስም እየነገዱ ለውጡን ለመቀልበስ ለሚሞክሩ ሃይሎች ማስጠንቀቂያ ልከዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የአብዴንን ምልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጽ/.ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ለዘመናት በታሪክ የተሳሰረ፣ ደስታና ችግሮችን አብሮ ያሳለፈ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት 27 አመታት አማራና አሮሞን ለመለያየት ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር የገለጹት አቶ ንጉሱ፣ አሁንም ይህንን አንድነት ሊሸረሽሩ የሚችሉ ሃይሎች የፍቅር ማርከሻ ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል። በጉባኤው ላይ የደኢህዴንና የህወሃት ተወካዮችም ንግግሮችን አድርገዋል።

58: Death toll in weekend ethnic violence in Addis Ababa

by Engidu Woldie
ESAT News (September 19, 2018)
The number of people killed in ethnic violence in the outskirts of Ethiopia’s capital Addis Ababa is at least 58, AFP reported quoting an Amnesty International researcher.
The number could be higher, according to the report, which also quoted a source involved in counting the bodies. The source put the toll at 65.
The numbers revealed today are much higher than what the police commissioner said on Monday, although the commissioner Zeinu Jamal was careful not put any figures. Jamal was asked by a reporter to confirm if the toll was 25. He responded saying “it was much higher than that,” and that they were still working to determine the exact toll.

Tension in Addis Ababa as police bans demonstrations

by Engidu Woldie
ESAT News (September 19, 2018)
The capital’s police department warns against any demonstrations in Addis Ababa saying “some individuals” have called for a rally for tomorrow without any permit from the city government.
The statement from the Addis Ababa Police Commission says legal actions would be taken against those who would hold a demonstration tomorrow.
Tension have been escalating in the capital since Saturday after a group carried out deadly ethnic attack in Burayu, west of the capital and other areas where latest figures show as many as 65 people have been killed.
Many residents of the capital today attended the funeral of two people killed in the violence.

ኢትዮጵያን ከመገንባቱ ሂደት ማንም ሃይል ሊያስቆመን አይችልም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) ኢትዮጵያን ከመገንባቱ ሂደት ማንም ሃይል ሊያስቆመን አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
ኢትዮጵያንም አፍሪካንም እንገነባለን ያሉት ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ህልውና እንዲቀጥል ኦሮሞዎች ሃላፊነት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በጅማ ዛሬ በተጀመረው የኦህዴድ 9ኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጠላት ጋር ሆናችሁ የኦሮሞን ትግል ወደኋላ ለመመለስ ያሰባችሁ ካላችሁ ከጠላት ለይተን አናያችሁም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ኢትዮጵያ ከጠላቶቿ ጋር ባደረገችው ጦርነት ሁሉ ኦሮሞዎች ትልቅ ሚና እንደነበራቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የዚህች ሐገር አንድነት ለማስጠበቅም ኦሮሞዎች ሃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በጅማ ዛሬ በተጀመረው የኦሕዴድ ጉባኤ ላይ ጅማን መሰረት አድርገው የጅማውን አባጅፋር የጠቀሱት ዶ/ር አብይ አህመድ አባጅፋር ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ጭምር አርቀው የሚያስቡ ነበሩ ሲሉ ምስክርነት ሰጥተዋል።

የመንጋ ፍትህና ስርአት አልበኝነት እየተስፋፋ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) የመንጋ ፍትህና ስርአት አልበኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አሳሰበ።
የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በቡራዪ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ ጨምሮ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ርምጃዎች አሳሳቢ መሆናቸውንም አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸው ሐገሪቱ ተጋርጦባት የነበረውን አደጋ ያስታገሰና የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ነው ሲልም ሰመጉ አስታውቋል።
ነሐሴ 9/2010 በደቡብ ክልል ሰካ ዞን ብሔርን መሰረት ባደረገ ግጭት ሶስት ሰዎች መገደላቸውንና ንብረት መውደሙን ገልጿል።
በመንግስት ሃይሎች ጣልቃ ገብነት ግጭቱ የበረደ ቢሆንም እንደገና አገርሽቶ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን አሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ባሌ ዞን ጎባ ከተማ የተደራጁ ወጣቶች ከነሐሴ 13 እስከ 16/2010 በፈጸሙት ጥቃት 10 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውም ተመልክቷል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የተፈራረሙት ባለ ሰባት አንቀጽ ስምምነት ይፋ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 9/2011) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ የተፈራረሙት ባለ ሰባት አንቀጽ ስምምነት ይፋ ሆነ።
ባለፈው ሳምንት በሳውዳረቢያ ጅዳ ሁለቱ መሪዎች በፈረሙት ስምምነት መሰረት በጸጥታና መከላከያ እንዲሁም በንግድና በኢንቨስትመንት መስክ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
በባህልና በማህበራዊ ጉዳዮች ጭምር በትብብር ለመስራት ፊርማቸውን ያኖሩት ሁለቱ መሪዎች በጋራ ኢንቨስትመንት ለመሰማራትና የጋራ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመፍጠር መስማማታቸው ተመልክቷል።
የጦርነቱ ዘመን አክትሞ የሰላም ዘመን መግባቱን፣ወዳጅነትና አጠቃላይ ትብብር መጀመሩን በአንቀጽ አንድ ላይ ያስቀመጠው የሁለቱ መንግስታት የስምምነት ሰነድ፣በጸጥታና መከላከያ፣በንግድና ኢንቨስትመንትና በሌሎችም መስኮች በትብብርና በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን ይዘረዝራል።
የኢትዮጵያና ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ዘሔግ ኔዘርላንድ ከ15 አመታት በፊት ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በዚሁ ስምምነት ላይ ጭምር ያረጋገጡት ሁለቱ መሪዎች ለአካባቢውና ለአለም ሰላምና ጸጥታ ለመስራት እንዲሁም ሽብርን ለመዋጋት እንዲሁም ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የመሳሪያና የአንደንዛዥ እጾችን ዝውውር ለመግታትም ተስማምተዋል።

Tuesday, September 18, 2018

በእስር ላይ የሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጠሪዎች እንዲፈቱ ባልደረቦቻቸው ጥያቄ አቀረቡ

( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከነሃሴ 21 የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያ የታሰሩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንዲፈቱ የድርጅቱ ሰራተኞች ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጻፉት ደብዳቤ አመልክተዋል። ሰራተኞቹ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ቢሆንም፣ ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ተገደው ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን ተቃውመው፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል በሚል የታሰሩት 9 ባልደረቦቻቸው ከእስር ተፈተው ስራቸውን እንዲጀምሩ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ሰራተኞች በደብዳቤያቸው “ ያቀረብነው የመብት ጥያቄዎች መ/ቤቱ በቸልታ በማለፍ ጉዳዩ መጨረሻ ላይ ሲደርስ ሰራተኞው ሃላፊነቱን መወጣት እንዳልቻለ በማድረግ የማይገባ ግዴታ ውስጥ በማስገባት ወደ ስራ እንድንመለስ ከማድረግ ባለፈ የስራ ባልደረቦቻችን ሁሉም በጋራ በመሆን የመብት ጥያቄ ባቀረቡበት ሁኔታ 9ኙ ሰራተኞች ብቻ የጥያቄው አቅራቢዎችና የጉዳዩ አስተባባሪዎች እንዲሆኑ በማድረግ በእስር ሆነው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጉላሉ ማድረጉ ተገቢነት የሌለው “ ነው በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋል። መስከረም 7 ቀን 2011 ዓም ለተጻፈው ደብዳቤ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት መልስ ይስጥ አይስጥ አልታወቀም። በጉዳዩ ዙሪያ ሰራተኞችን አነጋግረን ይዘን ለመቅረብ ሙከራ እንደምናደርግ ለመግለጽ እንወዳለን።

የመስቃን ቤተ ጉራጌዎችንና የማረቆ ብሄረሰብ አባላትን ለማጋጨት በተደረገ ጥረት የበርካታ ዜጎች ህይወት አለፈ

( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) መስከረም 3 ቀን 2011 ዓም የወረዳ የካቢኔ አባላት ምርጫን ተከትሎ በምርጫው የተከፉ ወገኖች የማረቆን ብሄረሰብና የመስቃን ጉራጌ ብሄረሰቦችን አነሳስተው በፈጠሩት ግጭት ከሁለቱም ወገን ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ግጭቱን ለማብረድ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ የገባ ሲሆን፣ የጦር መሳሪያ በታጠቁት እና ለግጭቱ መንስዔ ሆነዋል በተባሉት ግለሰቦች ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። በአካባቢው አንጻራዊ መረጋጋት የታየ ቢሆንም፣ ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሚከሰቱት ግጭቶች በአንድ ማዕከል እንደሚቀነባበሩ የድህንነት መስሪያ ቤት አስታወቀ

( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) የብሄራዊ ድህንነት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያም ሆነ በሶማሊ ክልል የተፈጠሩት ግጭቶች አላማቸው አንድ ነው ብሎአል። በአዲስ አበባ ዙሪያ የተከሰተው ግጭት በሶማሊ ክልልና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጠሩት ግጭቶች ተቀጽላ ነው። የግጭቶች ዋና አላማ የለውጡን እንቅስቃሴ መግታትና በመስከረም ወር የሚካሄደውን የኢህአዴግ ጉባኤ ማደናቀፍ ነው ያለው የደህንነት መስሪያ ቤቱ፣ሁከቱ በትናንሽ ችግሮችና ልዩነቶች የሚነሳ ሳይሆን በታቀደ መልኩ የሚከናወን፣ ድብቅ ፖለቲካዊ አላማ ያለው እና አገሪቱን በማያባራ ግጭት ውስጥ በመክተት ለውጡን ለማሽመድመድና ለመቀልበስ የሚደረግ ሴራ ነው ብሎአል። የደህንነት ምክር ቤቱ ለዜጎች ህይወት ዋስትና ለመስጠት መንግስት ማንኛውንም ህጋዊና የማያዳግም እርምጃ መውሰድ መጀመሩንና ድርጊቱም እንደሚቀጥል ገልጿል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ልዩነትን በሚያሰፉና

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያን መበተን አይቻልም አሉ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/201) የወንድምን ደም ማፍሰስ፣ ህጻናትን ማሰቃየት ትችላላችሁ ኢትዮጵያን መበተን ግን መቼም አይሳካችሁም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቡራዩ ሰሞኑን የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን ከጎበኙ በኋላ እንደተናገሩት የወንድሞቻችሁን ደም በመጠጣት የምትረኩ ሃይሎች ኢትዮጵያን ማፍረስ ግን ህልም ነው ሲሉ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተፎካካሪና አክቲቪስት ነን ባዮች በማስተዋል እንድትንቀሳቀሱ እጠይቃለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
መንግስት ለተጎጂዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ ከጎናችሁ ነን በማለት የተፈናቀሉ ዜጎችን አጽናንተዋል።
በፖሊስ ሪፖርት መሰረት በቡራዩ ጥቃት ከ25 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። ህጻናት፣ ነፍሰ ጡር፣ አቅመ ደካማ የሆኑ አዛውንቶች የጥቃቱ ሰለባ ሆነዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩት ከቀዬአቸው ተፈናቅለው አዲስ አበባ በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለዋል። በዛሬው ዕለት እነዚህ ተፈናቃይ ዜጎችን የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድርጊቱን አሳፋሪና የኢትዮጵያውያን የውርደት ታሪክ ሲሉ ገልጸውታል።

በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት ከግለሰብ ጸብ ጋር የተገናኘ አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) በቡራዩ አካባቢ የተፈጠረው ግጭት በአንዲት የ6 ዓመት ሕጻን ላይ ከተፈጸመ አሰቃቂ ግድያ ጋር ተያይዞ ችግሩ ቢባባስም ጉዳዩ ከግለሰብ ጸብ ጋር ብቻ የተያያዘ እንዳልነበር አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ።
የብሔር ግጭት ለመፍጠር ታርጋ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች አሰላ ድረስ የነበሩ የትንኮሳ ሙከራዎችም በሕዝብ ጥረት መክሸፋቸውን አስረድተዋል።
በቡራዩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማስመልከት ትናንት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡት አቶ ለማ መገርሳ በዚህ አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት የተሳተፉ 200 ያህል ሰዎች መታሰራቸውንና የጦር መሳሪያዎችም መያዛቸውን ገልጸዋል።
ከፌደራል ፖሊስ ጋር በተቀናጀ መንገድ ምርመራ መቀጠሉን የገለጹት አቶ ለማ መገርሳ ተፈናቃዮችን ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።
እስከ ትናንት ድረስ 300 ያህል አባወራዎች መመለሳቸውንም አስታውቀዋል።
ግጭቱ በአንዲት የ6 ዓመት ሕጻን ላይ በተፈጸመ አሰቃቂ ግድያ ቢባባስም የብሔረሰብና የሃይማኖት ጸብ ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ይህንን ርምጃቸውን እስከ አሰላ ድረስ ለመውሰድ ሰሌዳ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች ያደረጉት ጉዞና ጥረት በህዝብ ጥረት መክሸፉን ገልጸዋል።
በተለይ በኦሮሞና በአማራ መካከል ግጭት ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት መደረጉን የገለጹት አቶ ለማ መገርሳ የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር መመከሩንም አስታውቀዋል።

የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) መንግስት ያለበትን የህግ የበላይነትና የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት ለመወጣት ማንኛውንም ህጋዊ፣ የማያዳግምና ተገቢ ርምጃ ለመውሰድ በሙሉ ዝግጅትና አቋም ላይ ነው ሲል የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ የጥፋት ሃይሎች የመንግስትን ሆደ ሰፊነት ከአቅመ ቢስነት በመቁጠር የወጣቱን ስሜት በማነሳሳት የሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱና እየተበራከቱ በመምጣታቸው መንግስት ሰላምና መረጋጋትን የማስከበር ሃላፊነቱን ለመወጣት በመስራት ላይ ነው ብሏል።
ልዩነትን የሚያራግቡና ብጥብጥን የሚቀሰቅሱ አክቲቪስቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እጃሁን ሰብስቡ ይላል የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት መግለጫ።
የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህግ የበላይነት የዲሞክርሲ ስርዓት ግንባታ አንዱ መገለጫ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቶበታል።
የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከህግ የበላይነት ውጭ ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም ብሏል የምክር ቤቱ መግለጫ።
አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደቀደሙት መንግስታት ነገሮችን በሃይል ለመፍታት አይቸኩልም ይህ አዲስ አካሄድ ፍርሃትና አቅመ ቢስነት የመሰላቸው ሃይሎች ተሳስተዋል ብሏል።

አቶ ኦባንግ ሜቶ አቀባበል ተደረገላቸው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011)የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በጋምቤላ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
አቶ ኦባንግ ሜቶ ከ16 ዓመታት በኋላ ወደ ጋምቤላ ሲያመሩ የከተማዋ ነዋሪዎችና የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት አደባባይ በመውጣት እንደተቀበሏቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
አቶ ኦባንግ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የልዑካን ቡድን አባላትን በመምራት ወደ ኢትዮጵያ ያመሩት ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውም ታውቋል።
በኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል ስማቸው ከሚጠቀሱ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች ግንባር ቀደም ናቸው።
በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ስቃይና መከራ ሲደርስባቸው ድምጻቸውን ከማሰማት አንስቶ ቦታው ድረስ በመሄድ ከወገናቸው ጎን በመቆም ከመንግስታት ጋር ሆነው የሚሟገቱ፡ ለኢትዮጵያውያን ጠበቃ ሆነው የሚቆሙ ሰው ናቸው- አቶ ኦባንግ ሜቶ።

አቶ ለማ መገርሳ የኢሳት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተሸላሚ ሆኑ

Bildergebnis für ለማ መገርሳ(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 8/2011) ኢሳት በየዓመቱ በሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት አቶ ለማ መገርሳ የ2010 አሸናፊ ሆኑ።
በህዝብ ድምጽ የሚካሄደውንና በአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስም የተሰየመውን የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ማሸነፋቸው የተገለጸው ዕሁድ ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደ ስነ-ስርዓት ነው።
መስከረም 6/2011 በተካሄደው በዚህ በኢሳት የአዲስ ዓመት ዝግጅት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የኢሳትን የ8 ዓመታት ጉዞ የሚያሳይ ስዕል ለጨረታ ቀርቦ በ30ሺህ የአሜሪካን ዶላር ተሽጧል።

Monday, September 17, 2018

በአዲስ አበባ እና በአርባምንጭ ከተሞች በቡራዩና ዙሪያ ከተሞች የተፈጸሙትን ግድያዎች የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ

( ኢሳት ዜና መስከረም 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሰልፈኛው ላይ በወሰዱት እርምጃ እስካሁን 5 ሰዎች መገደላቸውን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በቡራዩና በተለያዩ የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች የተደራጁ ወጣቶች በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ተፈናቅለዋል። መንግስት ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ተናግሯል። ህዝቡ ግን መንግስት እየወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም፣ ወንጀለኞችን ማባበል ይዟል የሚል ትችት እያቀረበ ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው የኢሳት ሪፖርተር ጋዜጠኛ ስለሺ

በቡራዩና አካባቢው የተፈጸመው ጥቃት የተቀነባበረ ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 7/2011) በቡራዩና አካባቢው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተቀነባበረና በአንድ እዝ ስር ያረፈ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገለጹ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሁለ የፖለቲካ ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት ገልጸዋል።

በቡራዩና አካባቢው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ25 ይበልጣል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 7/2011)በቡራዩ፣በአሸዋ ሜዳና በከታ በሳምንቱ መጨረሻ በንጹሃን ላይ በደረሰው ጥቃት
ከ25 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ይህንን ጥቃት ለመቃወም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከወጡ ዜጎች መካከልም 5 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች መቁሰላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ግድያውም መሳሪያ በነጠቁ ግለሰቦች ላይ የተፈጸመ ነው ብሏል።

Friday, September 14, 2018

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ እና ግብረአበሮቻቸው ላይ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ ተሰጠባቸው።

 ( ኢሳት ዜና መስከረም 04 ቀን 2011 ዓ/ም ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ አብረዋቸው የተከሰሱትን ሌሎች ተጠርጣሪዎችን አቤቱታ እና መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ አድምጧል። ተከሳሾቹ ለችሎቱ እንዳሉት ”ቤተሰብ እይጠየቀን አይደለም። ምግብና ህክምናም በአግባቡ እያገኘን አይደለም። መዝገቡ ሁሉንም ተጠርጣሪዎች በአንድ የያዘ ነው እንደ ኃላፊነታችን መጠን ሊለያይ ይገባል። የዋስትና መብታችን እንዲከበር።” ሲሉ ቅሬታቸውን በጠበቆቻቸው አማካኝነት እቅርበዋል። በብጥብጡ ወቅት ሞተዋል የተባሉ የ36 ሰዎችን አስክሬን ምርመራ ውጤትን የሚገልጽ ሰነድ ከካራማራ ሆስፒታል መሰብሰቡን፤ የ130 ሰዎችን የምስክር ቃልም መቀበላቸውን፤ ተከሳሾች በሞባይል ስልክ ሲለዋወጡ የነበሩትን መልዕክቶች እንዲመረመሩ ለኢትዮጵያ የደህንነት ኤጄንሲ/ ኢንሳ/ መላካቸውን፤ የበርካታ ሰዎችም የት እንዳሉ አድራሻቸው ስለማይታወቅ እነሱን የማፈላለግ ስራም እየተከናወነ ነው። በዝርፊያ እና በቃጠሎ የወደሙ ንብረቶች ግምትም እንዲሰላ ትዕዛዝ መተላላለፉም ፖሊስ ለችሎቱ አሰምቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ፖሊስ ተገቢውን ማስተካከያ እንዲያደረግ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል። የተጠረጠሩበት ወንጀል የዋስትና መብት አያሰጥም በማለት የዋስትና ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል። ችሎቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለመስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በአዲስ አበባ ዛሬም ግጭት ተቀስቅሶ ዋለ

 ( ኢሳት ዜና መስከረም 04 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን ኦነግ ለመቀበል የሚደረገውን ዝግጅት ተከትሎ የተነሳው ውጥረት እያየለ በመሄዱ ዛሬ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ተፈጥሯል። በርካታ ቄሮዎች ወደ መሃል አዲስ አበባ በመግባት የተለያዩ መፈክሮችን ሲያሰሙ የዋሉ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ በቄሮዎችና በአዲስ አበባ ወጣቶች መካከል በነበረው ድንጋይ ውርወራና ፖሊስ ግጭቱን ለማስቆም በመወሰደው እርምጃ የተወሰኑ ሰዎች ተጎድተዋል። የሰብአዊ መብት ታጋዩ ዮናታን ረገሳ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ሰላም መሆኑን፣ ወደ አስኮና ፒያሳ አካባቢ ግጭት መቀስቀሱን ገልጾ፣ በአሁኑ ሰዓት ወጣቱ በተለያዩ ወሬዎች ስሜታዊ እየሆነ ነው ብሎአል። በሌላ በኩል “ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፊት አውራሪነት ተግባራዊ በመሆን ላይ ያለው አገራዊ ለውጥ ከባንዲራ ቀለማት በላይ ትላልቅ ዓላማዎችን አንግቦ የተነሳ ነው። የለውጡ ዓላማ እውነተኛ ፍትህን፣ እኩልነትን፣ ነጻነትንና ልማትን ማረጋገጥ ነው። ጉዳዩ ይህ ሆኖ ሳለ ገና ከወዲሁ በጥቃቅን ልዩነቶች ላይ ተመስርቶ የሚካሄድ አፍራሽ እንቅስቃሴ በምንም መልኩ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም።” ሲል የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። “በባንዲራ ቀለምም ይሁን ከፖለቲካ ድርጅቶች አርማዎች በላይ ባሉ በርካታ ጉዳዮች ላይ ያሉ የአመለካከት እና የሃሳብ ልዩነቶች ሁሉ እንደ ፀጋ እና እንደበረከት ሊቆጠሩ እንደሚገባ” የገለጸው መንግስት “ ይህንን ዕውነታ ተቀብሎ ልዩነቶችን በሰለጠነ አካሄድ፣ በውይይት እና በሃሳብ ትግል ብቻ መፍታትን ከዚህ በኋላ ባህላችን ልናደርግ ይገባል።” ብሎአል።

ሁሉም ወገኖች ለሰላም እንዲሰሩ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በአዲስ አበባ የተፈጠረው ግጭት እንዲቆምና ሁሉም ወገኖች ለሰላም እንዲሰሩ ተጠየቀ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫ በመስጠት ወጣቶች ከእርስ በእርስ ግጭት ራሳቸውን እንዲያርቁ ጥሪ አድርገዋል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በባህርዳር የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አቀባበል ዝግጅት ተጠናቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በባህርዳር ነገ ለሚካሄደው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አቀባበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኮሚቴው አስታወቀ።

የንቅናቄው አመራሮች ዛሬ ባህርዳር መግባታቸውም ታውቋል።

ከባህርዳር በተጨማሪ በተለያዩ የአማራ አካባቢዎችም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችና አባላትን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በጎንደር የፊታችን እሁድ ተመሳሳይ የአቀባበል መርሃ ግብር እንደሚኖር አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በ32 ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።

ቅዳሜና ዕሁድ በባህርዳርና ጎንደር ለሚደረገው የአቀባበል ዝግጅት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራርና አባላቱ ከዛሬ ጀምሮ ባህርዳር እየገቡ ነው።

የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡ ዋና ጸሀፊው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎች አመራሮች ባህርዳር መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በነገው ዕለት በባህር ዳር ስታዲየም ለሚዘጋጀው አቀባበል ፕሮግራም ከተለያዩ የዕለም ክፍሎች ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የንቅናቄው አባላትም እስከ ማምሻውን ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባህርዳር ሳምንቱን ለአቀባበል ፕሮግራሙ ስትዘጋጅ ቆይታለች። ከተማዋ በኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማና በአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ፎቶግራፎች የደመቀች ስትሆን እንኳን ለአገራችሁ አበቃችሁ የሚሉና ሌሎች መልዕክቶች በተለያዩ የከተማዋ ክፎሎች ተሰቅለው ይታያሉ።

የባህርዳር የአርበኞች ግንቦት ሰባት አቀባበል ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ ለሀገራቸው መስዋዕትነትን የከፈሉ የንቅናቄውን አመራሮች ለመቀበል የባህር ዳር ህዝብ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቋል።

እንግዶቻችንን ተቀብለን በሰላም እስክንሸኝ ሁሉም ወገን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ እንጠይቃለን ብሏል ኮሚቴው።

በነገው ዕለት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የንቅናቄውን አመራሮች እንዲቀበልም ኮሚቴው ጥሪ አድርጓል። በሚቀጥለው ቀን ዕሁድ በጎንደር ከተማ ተመሳሳይ የአቀባበል መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

እነእመዋይሽ አለሙና በእስር ቤት ስቃይ የደረሰባቸው ታጋዮች በጎንደሩ የአቀባበል ኮሚቴ ውስጥ በመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ ወታደራዊ ሰፈሩን ዘግቶ ወደ ሀገር ቤት ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የገባ ሲሆን በአዲስ አበባና በሌሎች 31 ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ተራዘመ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በአዲስ አበባ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለነገ የታቀደው የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት መራዘሙ ታወቀ።

መስከረም አምስት ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ የተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ከ20ሺ በላይ ትኬቶች ተሽጠው ያለቁ መሆናቸውን የገለጹት የኢሳት ምንጮች በአንድ ሳምንት እንዲራዘም መደረጉን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ አስተዳደር በኩል ኮንሰርቱ እንዲራዘም መጠየቁም ታውቋል።

ከአንድ ዓመት በፊት ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበም ከወጣ በኋላ የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት በሀገር ውስጥ እንዲያቀርብ ታቅዶ እንደነበረ ቢገለጽም በተለያዩ ምክንያቶች ሲስተጓጎል ቆይቷል።

በባህር ማዶ በአሜሪካና አውሮፓ ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ የተሰኘውን የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ የቆየው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በሀገር ቤት ባህርዳር ላይ ተመሳሳይ ዝግጅቱን ማሳየቱ የሚታወስ ነው።

በአዲስ አበባ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ለአዲስ አበባ አስተዳደር ጥያቄ ያቀረበው ቴዲ አፍሮ ለእንቁጣጣሽ ዋዜማ አቅዶ የሚሌኒየም አዳራሹ በሌላ ፕሮግራም በመያዙ ለአንድ ሳምንት እንዲያራዘምና እንዲያካሂድ ተፈቅዶለት ነበር።

ይህም ሲደረግ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት በተላከ ደብዳቤ መሆኑንና ያም ደብዳቤ ብዙ እንግዶችን በአንድ ላይ የምንጋብዝበት መድረክ ስላስፈለገን ነውና ተባበሩን የሚል ይዘት ያለው ነው ብሎናል በውጭ ሃገር የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት አስተባባሪው ጴጥሮስ አሸናፊ።

ነገ በሚሌኒየም አዳራሽ ለታቀደው የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ከ20 ሺህ በላይ ቲኬቴች ተሽጠው ማለቃቸውን አስተባባሪው ተናግሯል።

በዓይነቱ የተለየ እንደሚሆን የተነገረለትን ይህን ኮንሰርት ለመታደም፣ በሙዚቃ አፍቃሪው ዘንድ ከፍተኛ ጉጉት እንደነበረ የሚገልጹት አዘጋጁ አዳራሹ መያዝ ከሚችለው በላይ ቲኬቶች መሸጣቸውንም ጠቅሰዋል።

ሆኖም አዲስ አበባ ላይ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ለነገ የታቀደው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት መራዘሙንና ይህንንም የአዲስ አበባ መስተዳድር ከቴዲ አፍሮ ጋር በመነጋገርና ፍቃዱን በመጠየቅ የተደረገ መሆኑም አስተባባሪው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ነገ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ለጥንቃቄ በሚል የመራዘም ጥያቄው ከከተማው አስተዳደር መቅረቡን የገለጹት አስተባባሪው ቴዎድሮስ ካሳሁንም ጥያቄውን ተቀብሎ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ እንዲካሄድ ተስማምቷል።

የሕወሃት ደጋፊዎች በግልጽ ቅስቀሳ ጀመሩ

(ኢሳት ዲሲ--መስከረም 4/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኦነግ ልኡካንን ለመቀበል የሚደረገው ዝግጅት ወደ ግጭት እንዲያመራ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ደጋፊዎች በግልጽ ቅስቀሳ መጀመራቸው ታወቀ።

ጸረ ለውጥ ሃይሎች የሚያደርጉትን ይህንን እንቅስቃሴ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በቅንጅት እንዲያከሽፉትም ጥሪ ቀርቧል።

Thursday, September 13, 2018

ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መታመማቸው ታወቀ

 ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) በኢትዮጵያ የቀድሞው ሰራዊት ውስጥ በአየር ሃይል ምድብ ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብዱ በመፈጸም የተለያዩ የጀግና ሜዳሊያዎችን የተሸለሙት የቀድሞው የአርበኞች ግንባር መሪ ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ታመው ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ኮ/ል ታደሰ አስመራ ውስጥ ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝተው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት ሄደው ለመታከም ዝግጅት መጀመራቸውም ታውቋል። የኤርትራ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ኮሎኔል ታደሰ በፍጥነት

የረጲ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተመረቀ በሁለት ሳምንቱ ስራ አቆመ

 ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ ከተማ 2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበት የተገነባው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢመረቅም በሁለት ሳምንቱ ስራውን አቋርጧል። ለፕሮጀክቱ አገልግሎት መቋረጥ ያልተጠናቀቁ ሥራዎች መኖራቸውን በምክንያትነት ቢጠቀስም፣ የካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዓለማየሁ ግን ”የእኛ ኃላፊነት ፕሮጀክቱን አጠናቆ የአራት ቀናት ሙከራ ማድረግ እንጂ፣ ሥራውን ማስቀጠል ኃላፊነታችን አይደለም” ማለታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡

ከአርማና ሰንደቃላማ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ተቀሰቀሰ

 ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) የፊታችን ቅዳሜ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትን በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን የኦነግ አመራሮችን ለመቀበል በሚካሄደው ዝግጅት ላይ የኦነግን አርማ ለመስቀል እና መንገዶችንና አጥሮችን በኦነግ አርማ ለመቀባት አደባባይ የወጡ ወጣቶች፣ ድርጊቱን ከሚቃወሙ የአዲስ አበባ ወጣቶች ጋር ተጋጭተዋል። የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች ግጭቱ እንዳይባባስ የማረጋጋት ስራ ሲሰሩ የዋሉ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድና የፌደራል ፖሊስ

Wednesday, September 12, 2018

የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 2/2011) የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ ሲሉ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጥሪ አደረጉ።

ሃላፊው አቶ ታዬ ደንደአ በግል የማህበራዊ መድረካ ላይ ባስተላልፉት ጥሪ ኢትዮጵያውያን ከትንንሽ አጀንዳዎች ወጥተው ስለሀገር ከልብ እንዲያስቡ ጠይቀዋል።

አቶ ታዬ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት ዛሬ በአዲስ አበባ ከሰንደቅ ዓላማና አርማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን መለስተኛ ግጭት ተከትሎ ነው።

Internal displacement surpasses Syria, DRC

ESAT News (September 12, 2018)
1.4 million new internal displacements have already been recorded in Ethiopia, surpassing both Syria and the Democratic Republic of the Congo, says the Internal Displacement Monitoring Centre (IDMC).
“IDMC’s mid-year report shines light on Ethiopia, where new conflict broke out in Gedeo and West Guji zones in the south of the country earlier this year, triggering more than a million new displacements,” the report said.

Thursday, September 6, 2018

በሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት ተጠርጣሪ በሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

 ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል ዓደባባይ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተጠራው የምስጋና እና የመደመር የድጋፍ ሰልፍ ወቅት በተፈጸመው የቦንብ ጥቃት እጃቸው አለበት ተብለው ከተጠረጠሩት አንዱ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ተቀበለ። ፖሊስ ለፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት ባቀረበው አቤቱታ በተጠርጣሪው አቶ

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉና ያባከኑ ሰዎች ሜቴክን እየለቀቁና ማእረጋቸውን እየለወጡ በሲቪል አስተዳደርነት እየተቀጠሩ ነው

 ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም )የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ላወደመውና ላዘረፈው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ዋና ተጠያቂ የሆኑ የቀድሞ ወታደራዊ መሪዎች ማእረጋቸውን እየተዉ በሲቪል ተቋማት ውስጥ እየተቀጠሩ ነው። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ዶ/ር ሶሎሞነ ኪዳኔ ወደ ከንቲባነት ከመምጣታቸው በፊት የሜቴክ ዋና ተቋራጭ ነበሩ። ዶ/ር ሶሎሞን ኪዳኔ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩ፣ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ገብተው ከተመረቁ በሁዋላ፣ ስኮላር ሽፕ ተሰጥቷቸው ወደ አውሮፓ ከተጉዋዙ በሁዋላ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጭ በራሳቸው ጊዜ የፒ ኤች ዲ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል። ዶ/ር ሶሎሞን አልትራ ቴክ የሚባል ኩባንያ

የሜቴክ ዘረፋ የተደራጀ ሌብነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) በመሰረታዊ ብረታብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ ውስጥ የሚካሄደው ዘረፋ ብሔርን መሰረት ያደረገና እጅግ የተደራጀ ሌብነት መሆኑ ተገለጸ።

ሜቴክን ከምስረታው ጀምሮ የሚያውቁት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ለኢሳት እንደገለጹት በዘረፋው ሒደት በደላላነት በሚሊየን ዶላሮች የሃገሪቱን ሃብት የሚቀራመቱ ግለሰቦችን በዝርዝር አስቀምጠዋል።

የዲያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010) በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የዲያስፖራ ኤጀንሲ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ።

 በዳይሬክተር የሚመራውና ምክትል ዳይሬክተር የሚኖረው የዲያስፖራ ኤጀንሲ በራሱ በጀት ኖሮት፣ለፓርላማው በራሱ ሪፖርት የሚያቀርብ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዛሬ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

አቶ ኦባንግ ሜቶ አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 1/2010)የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ።

ለረዥም ዓመታት በስደት የቆዩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ዛሬ ሐሙስ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርሱ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ የመብት ጥሰቶችን ግድያና አፈና በአሜሪካ ኮንግረስና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር ሲያጋልጡ የቆዩት አቶ ኦባንግ ሜቶ በኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የሚፈጸሙ የመሬት ወረራዎችን በማጋለጥና የሰለባዎቹን ድምጽ ሲያስተጋቡ ቆይተዋል።

Ethiopia reopens Embassy in Eritrea

ESAT News (September 6, 2018)
Ethiopia has reopened its Embassy in Eritrea, after twenty years hiatus sparked by a border war.
The thawing of diplomatic relations between the two countries began in July when Ethiopia’s Prime Minister made a historic visit to Eritrea after he announced that his country had accepted a boundary commission decision to resolve a border dispute.
Eritrea’s President Isaias Afwerki paid a visit to Ethiopia, a week after Ahmed’s trip to Asmara. Eritrea also reopened its Embassy in July.

Wednesday, September 5, 2018

METEC received hundreds of millions of dollars but has not completed any project at Ethiopia’s mega dam

ESAT News (September 5, 2018)
Seven years after the launch of what would be Africa’s largest hydroelectric dam, the contractor, Metal and Engineering Corporation (METEC), has received millions of dollars in payments without completing any of its electro mechanical projects.
An investigative report by Walta Information Center revealed that METEC has completed only 30% of the electro mechanical projects at the site of the dam dubbed Ethiopia’s Renaissance Dam but has received over 65% of the total payments.
METEC, that has been run by TPLF army generals until recently, signed a 963 million dollar contract with the government when the project began in 2011. It has so far received 630 million dollars. METEC received payments for the 35% of electro mechanical work that it has not performed.

የራያ ተወላጆች ሰልፍ አካሄዱ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010) ከወሎ ክፍለ ሃገር ተወስዶ ወደ ትግራይ ክልል ያለፍላጎቱ የተጠቃለለው የራያ ተወላጆች የማንነት ጥያቄ በማንሳት የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

የራያ ተወላጆች በአዲስ አበባ ከተማ ባካሄዱት ሰልፍ በራያ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆምና በሕገ መንግስቱ መሰረት ማንነታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል።

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በእስር ላይ እንዲቆዩ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010) አድማ በማስተባበር ተጠርጥረው የታሰሩት ዘጠኝ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በእስር ላይ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳለፈ።

በሌላም በኩል በአድማ ላይ የቆዩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ ስራ መጀመራቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስፍረዋል።

አንዲት የ13 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት አሲድ ሕይወቷ አለፈ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010)አንዲት የ13 አመት ታዳጊ ከተደፍረች በኋላ በተደፋባት አሲድ መሰል ንጥረ ነገር ሕይወቷ አለፈ።

ጫልቱ አብዲ የተባለችውና ከምስራቅ ሐረርጌ በደኖ ወደ ሐረር መጥታ የቤት ሰራተኛ የነበረችው ይህች ታዳጊ የተደፈረችውና ሕይወቷ ያለፈው በአሰሪዋ እንደሆነም ተመልክቷል።

የሕዳሴው ግድብ ገንዘብ የገባበት አይታወቅም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 30/2010)ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ተሰብስቦ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የገባበት አይታወቅም ተባለ።

ገንዘቡ የደረሰበትን ለማወቅም በመጣራት ላይ መሆኑን የሜቴክ የኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።

Tuesday, September 4, 2018

በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋዲሳ ተስፋዬ፣ የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ ጄ/ል ዱባለ አብዲ፣ የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ በመሩት ስብሰባ የክልሉ የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከአጎራባች ክልሎች ተደራጅተው የሚመጡ እና በተለያዩ ሰዎች በግልጽም በስወርም ድጋፍ የሚደረግላቸው ሃይሎች ናቸው ብለዋል። የእነዚህ ሰዎች ዋና አላማ የሃይማኖት እና የብሄር ግጭት በመፍጠር የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ማደናቀፍ ነው ያሉት የፍትህ ቢሮ ሃላፊው አቶ አበበ፣ ክልሉ በሳለም የቆየው ህዝቡ በሰላምና በፍቅር ተቻችሎ የመኖር ባህሉ ስላለው እንጅ ክልሉን በድሬዳዋና በጅግጅጋ እንተፈጠረው የችግር ቀጠና ለማድረግ አስበው ነበር ብለዋል። የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ዱባለ አብዲ በበኩላቸው ወጣቶች “ አባገዳዎችና ቄሮዎች የመንግስትን ስራ መተካት የለባቸውም፣ የሰላም አጋዥ መሆን አለባቸው፣ መንግስት ግንዛቤ ይሰጥ በሚ እስካሁን ታግሶ ቆይቷል” ብለዋል። ከተሰብሳቢዎች መካከል 3 ዓይነት ቄሮዎች መኖራቸውን የተናገሩ አሉ። አንደኛው አሁንም ለውጡን ለማስቀጠል የሚፈልጉ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ በገንዘብ እየተገዙ የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ የሚሞክሩ በብሄርና ሃይማኖት ለማጋጨት የሚመክሩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ችግር ሲፈጠር ጠብቀው የሚዘርፉ ናቸው ብለዋል። መንግስት ተቃዋሚዎችንና የመብት ተሟጋቾችን እያሳተፈ የዜጎችን ደህንነትና ሰላም ያስጠብቅ ብለዋል። አንዳንዶች በህዝቡ መካከል ችግር የለም፣ ችግር የሚፈጥሩት ላለፉት 27 አመታት ስልጣናቸውን ተገን አድርገው በሃይማኖትና በብሄር ሲያገጩ የነበሩ ናቸው ፣ እነዚህ ሰዎች አሁንም ስልጣን ላይ ናቸው፣ እነሱ እስካሉ ድረስ ሰላም አይኖርም ብለዋል። ብክልሉ የሁሉንም ህዝብ ጥቅም እኩል የሚያስከብሩ አስተዳደሪዎች እንዲሾሙላቸው ጠይቀዋል።

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ

( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከመልካም አስተዳደር፣ ከደሞዝ፣ ከማበረታቻና ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት ጥያቄ የደህንነት ሰራተኞች እና ፖሊስ ድጋፋቸውን ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ በሌሎች ባለስልጣናት ታዘው የአድማ መሪዎች የተባሉ ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ አስገርሟቸዋል። 120 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የአለማቀፍ ሲቪል አቬሽን እና አለማቀፍ የሰራተኞች ድርጅት መመሪያዎች በሚፈቅዱት መሰረት ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን የሚገልጹት ሰራተኞቹ፣ ከህዳር 2010 ዓም ጀምሮ ጥያቄያዎችን

የሀገር መከላከያ 13 ጄኔራል መኮንኖች ከሰራዊቱ በጡረታ ተሰናበቱ።

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 29/2010)  ጄኔራል መኮንኖቹ በጡረታ የተሰናበቱት የሐገር መከላከያ ሰራዊትን በተሻለ አደረጃጀት ለማዋቀር የተጀመረውን መርሃ ግብር ተከትሎ መሆኑ ታውቋል። ከሃገር መከላከያ ሰራዊት በጡረታ ከተገለሉት መካከል ሜጄር ጄኔራል በርሃነ ነጋሽ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሃላፊ የነበሩ፣ሌተናል ጂኔራል ሃለፎም እጅጉ የመከላከያ ኮሌጅ አዛዥ፣ሜጄር ጄኔራል ሙሉ ግርማይ ከመከላከያ ሎጅስቲክ ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ሰአረ መኮንን ፊርማ በጡረታ ከተሰናበቱት 13 ጄኔራል መኮንኖች ውስጥ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሜጀር ጄኔራል ዮሐንስ ወልደ ጊዮርጊስ፣ሜጀር ጄኔራል አትክልቲ በርሄ፣ሜጀር ጄኔራል ኢብራሒም አብዱል ጂላል፣ሜጀር ጄኔራል ገብሬ ዲላ በተመሳሳይ በጡረታ ተሰናብተዋል። ቀደም ሲል ጄኔራል አብርሃ ወልደማርያም እንዲሁም ሜጄር ጄኔራል መሐሪ ማአሾ በጡረታ መሰናበታቸው ታውቋል። በሐምሌ ወር መጨረሻ በመከላከያ ስታፍ ኮሌጅ የሰለጠኑ ከፍተኛ መኮንኖች በተመረቁበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመከላከያ ውስጥ ጠንከር ያለ ሪፎርም መጀመሩን መግለጻቸው ይታወሳል። የመከላከያው አዲስ አደረጃጀትን በማስጠናት ጄኔራል ሰአረ መኮንን ለመንግስት ማቅረባቸውን ገልጸው በጥናቱ መሰረት ተግባራዊ ርምጃ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር።

Monday, September 3, 2018

“በትግል ወቅት የተሰዉ የነጻነት ታጋዮችን አጽም ሰብስቦ ወደ ኢትዮጵያ ማምጣትና በክብር ማሳረፍ የሚቀጥለው ስራችን ይሆናል

“በትግል ወቅት የተሰዉ የነጻነት ታጋዮችን አጽም ሰብስቦ ወደ ኢትዮጵያ  ማምጣትና በክብር ማሳረፍ የሚቀጥለው ስራችን ይሆናል” ሲሉ  አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለኢሳት ተናግረዋል።

የአማራ ሕዝብ ክፉዎች በፈጸሙበት በደልና ግፍ ሳቢያ ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዝቅ አይልም ሢል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተናገረ።

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) አክቲቪስት ታማኝ ይህን ያለው፣ ዛሬ በባህር ዳር ስታዲዬም አቀባበል ላደረገለት እጅግ በርካታ የባህር ዳርና አካባቢው ሕዝብ ባደረገው ንግግር ነው። የባህ ዳር ስታዲየም አርቲስት ታማኝን ለመቀበል ከየ አቅጣጫው እየተግተለተለ በመጣው የሰው ጎርፍና በፈጣን ፈረሰኞች ከአፍ እስከ ገደፉ መሙላት የጀመረው፣ ገና ከማለዳው አንስቶ ነው። ለረዥም ሰዓታት በትዕግስት ሢጠባበቅ የቆዬው በስታዲየሙ የታደመው ሕዝብ ፣አክቲቪስት ታማኝ በስፍራው ሢደርስ

የአርበኞች ግንቦት ታጋዮች አባላት ወደ አገራቸው ተመለሱ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኤርትራ ውስጥ በትጥቅ ትግል ላይ የቆዩ የሰራዊቱ አባላት ትናንት ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት አቀባበል አድርጎላቸዋል። በሁመራ፣ በጎንደርና በወረታ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ አቀባባል አድርገዋል። ለታጋዮች አቀባበል ያደረጉት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ በተለያዩ ጎራ የተሰለፉ ወንድማማቾች በተሰለፉበት ጎራ አንደኛው ሌላኛውን ሊያሸንፍ ይችላል፣ ኢትዮጵያ ግን አታሸንፍም ብለዋል።

በቴፒ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቃውወሞ ሰልፍ አደረጉ

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከመልካም አስተዳደር፣ ከሙስናና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የመንግስት ባለስልጣናት ተገቢውን መልስ አልሰጡንም በሚል ዛሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ውለዋል። ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ሚስጢሩ ሲሳይ እንደገለጸው ሰልፉ የተደረገው እስካሁን ሲንከባለሉ የነበሩ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ለመጠየቅ ነው ብለዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።