(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢንሳን ለረጅም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ከለቀቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን በሚለቁ የህወሃት ባለስልጣናት ቦታ ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እየተተኩ ነው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎችን እየሾሙ መሆኑን የደረሱን የሹመት ደብዳቤዎች ያመለክታሉ። ህወሃቶች በርካታ የስለላ መሳሪያዎችን ወደ መቀሌ የወሰዱ ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ የድርጅቱ የህወሃት አባላት ወደ ውጭ የተላኩ ሲሆን፣ 30 የሚሆኑ የህወሃት አባላት ደግሞ በእስራኤል ስልጠና እየወሰዱ ነው። አንዳንድ መሳሪያዎች እንዲወድሙ ወይም እንዲጠፉ መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የስለላ ክፍል ሃላፊው ሻለቃ ቢኒያም ተወልደ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
No comments:
Post a Comment