(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) የምክር ቤቱን አባላት ያነጋገረና ከፍተኛ ጥያቄ ያስነሣ የ2010 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት የስድስት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ይፋ ተደርጓል፡፡ ዋና ኦዲተሩ ረዳት ፕሮፌሠር ገረመው ወርቁ ለምክር ቤቱ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት የጐንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ፣ የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ፣ የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ፣ የሁሉን አቀፍ የገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራም /ዩራፕ/፣ የጤና ጥበቃ ቢሮ እና የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በዓመቱ ውስጥ ኦዲት አድርጐ ያጠናቀቃቸውና ከፍተኛ ጉድለት የተገኘባቸው መስሪያ ቤቶች መሆናቸውን አጋልጧል፡፡ ዋና ኦዲተሩ በሪፖርታቸው ተቋማቱ ሥራዎችን ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ አልፈጸሙም፡፡ ከአራት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ የሚያወጡ የህክምና መሣሪያዎችን ከአስር ዓመት በላይ
Monday, April 30, 2018
ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢንሳን ለረጅም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ከለቀቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን በሚለቁ የህወሃት ባለስልጣናት ቦታ ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እየተተኩ ነው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎችን እየሾሙ መሆኑን የደረሱን የሹመት ደብዳቤዎች ያመለክታሉ። ህወሃቶች በርካታ የስለላ መሳሪያዎችን ወደ መቀሌ የወሰዱ ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ የድርጅቱ የህወሃት አባላት ወደ ውጭ የተላኩ ሲሆን፣ 30 የሚሆኑ የህወሃት አባላት ደግሞ በእስራኤል ስልጠና እየወሰዱ ነው። አንዳንድ መሳሪያዎች እንዲወድሙ ወይም እንዲጠፉ መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የስለላ ክፍል ሃላፊው ሻለቃ ቢኒያም ተወልደ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በምስራቅና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቀርብበት የነበረው የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ተጨማሪ የ10 አመት የኮንትራት ስምምነት ማግኘቱን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ስምምነቱን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በአዶላ ወዮ ተማሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ስምምነቱን ተቃውመዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች የሚድሮክ ወርቅ ላለፉት 20 አመታት ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅ ማእድን ሲያወጣ ቢቆይም፣ ለአካባቢው ነዋሪዎች ያመጣው የህይወት ለውጥ የለም። ማእድኑ በሚረጨው ኬሚካል በርካታ ዜጎች አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን የሚጠቅሱት ነዋሪዎች፣ መንግስት ኮንትራቱ እንዲራዘም ማድረጉ ህዝቡ ለአመታት ሲያቀርብ ለነበረው ጥያቄ ትኩረት
Locals protest extension of gold mining project in Southern Ethiopia
ESAT News (April 30, 2018)
The renewal of a gold mining project for another ten years has triggered street protests in five towns in Southern Ethiopia. Locals say the project, which has exploited their natural resources for over twenty years has not benefited the poor.
ESAT News (April 30, 2018)
The renewal of a gold mining project for another ten years has triggered street protests in five towns in Southern Ethiopia. Locals say the project, which has exploited their natural resources for over twenty years has not benefited the poor.
Friday, April 27, 2018
Town of Jijiga, Dire Dawa join protests in Eastern Ethiopia
ESAT News (April 27, 2018)
Businesses were closed and transportations disrupted in the Eastern commercial town of Jijiga as residents joined protest against the administration of the regional president Abdi Illey.
Protest demonstrations against the regional president drew momentum on Tuesday when Abdi Illey fired his deputy, Abdihakim Igal, sparking street protests in Shilnille, his constituent and the base of his clan.
ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ሰላም አወረዱ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 19/2010)ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በመካከላቸው ያለው ጦርነት ማክተሙን አወጁ።
ከ63 አመታት በኋላም የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የደቡብ ኮሪያን ድንበር ተሻግረው ከአቻቸው ሙን ጄ ኢን ጋር መገናኘታቸው ተሰምቷል።
ሁለቱ መሪዎች በሰላጤው የነበረው ጦርነት ማክተሙን እውን ለማድረግም ለሰላም፣ለብልጽግናና ለአንድነት በጋራ ሊሰሩ የፓንሙንጆም ስምምነትን ተፈራርመዋል።
ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ በሰጣ ገባና በጠላትነት ሲፈላለጉ 63 አመታትን አስቆጥረዋል። በየጊዜው በድንበሮቻቸው አካባቢ በሚቀሰቀሱ ግጭቶች የሰላጤው አካባቢ ሰላም ርቆት ቆይቷል።
ዛሬ ላይ ግን ለዘመናት በግጭትና በትንኮሳ ይናጥ የነበረው አካባቢ የሰላም አየር እንዲነፍስበት ሆኗል።
ሁለቱ ኮሪያዎች ለዘመናት ላይነኩት አጥረውት የነበረውን ድንበር ዛሬ ላይ የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ተሻግረውት ገብተዋል።
የደቡብ ኮሪያው አቻቸው ሙን ጄ ኢንም እጃቸውን ዘርግተው ተቀብለዋቸዋል። ኪም ጆንግ ኡን በ63 አመታት ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ ኮሪያን የጎበኙ የሃገራቸው መሪም ሆነው ስማቸውን አስመዝግበዋል።
የሁለቱ መሪዎች የመጀመሪያ የድንበር ላይ ሰላምታንም በካሜራ መስኮታቸው ላይ አስቀርተውታል።
በሽንሌ እና አጎራባች አካባቢዎች ሕዝብ እና ታጣቂዎች ተፋጠዋል።
በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ በተቃውሞ ሰልፍ ስትናጥ፣ጅግጅጋ ደግሞ በሥራ ማቆም አድማ ጸጥ ረጭ ብላ ውላለች።ሕዝባዊ ቁጣውና ተቃውሞው በሚቀጥሉት ቀናት አድማሱን በማስፋት በርካታ አጎራባች ወረዳዎችን እና ከተሞችን እንደሚያዳርስ ከአካባቢው የሚወጡ ዜናዎች ይጠቁማሉ።
-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሟቶ፣ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመወያዬት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።ዘግይቶ በደረሰን ዜና ያማሟቶ ከአኦቦ በቀለ ገርባ፣ ከዶክተር መረራ ጉዲና፣ከአቶ አንዷለም አራጌ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ተወያይተዋል።
-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ -ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሽልማት መስጠታቸው ከፍ ያለ ሕዝባዊ ቅሬታ አስከትሏል።
Wednesday, April 25, 2018
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝርፊያ እየተፈጸመባቸው ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢትዮጵያኑ እንዳሉት የአገሪቱ ዜጎች የፖለቲካ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ ከወጡ በሁዋላ የስደተኞችን ንብረቶች በመዝረፍ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል። ኢሳት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደገለጹት፣ በዝርፊያው በርካታ ኢትዮጵያውያን ሃብትና ንብረታቸውን አጥተዋል። በሌላ በኩል ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው 26 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሞዛንቢክ ውስጥ ተያዙ በሕገወጥ መንገድ ሞዛምቢክን አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ የነበሩ ያላቸውን ቁጥራቸው 26 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማኒካ አውራጃ ውስጥ መያዛቸውን የአገሪቱ የፖሊስ ባለስልጣናት አስታወቁ። የአገሪቱ መንግስታዊ ሬዲዮ ጣቢያ ባለስልጣናቱን ጠቅሶ ማክሰኞ እለት እንደዘገበው ስደተኞቹ ይጓጓዙበት የነበረው ተሽከርካሪም ከስደተኞቹ ጋር በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል። በእስር ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በሙሉ ወንዶች ሲሆኑ እድሜአቸው ከ19 እስከ 40 ዓመት እንደሚሆናቸው የማኒካ ፖሊስ ጣቢያ ቃል አቀባይ ኮማንደር ኤልሲዲያ ፊሊፔ አስታውቀዋል። ስደተኞቹ ማላዊን አቆራርጠው ባለፈው ዓርብ ወደ ሞዛቢክ የገቡ ሲሆን ምሽት ላይ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው አስቀድሞ በጫካ ውስጥ ለ24 ሰዓታት ተደብቀው ቆይተዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ባደረጉት ጥቆማ መያዛቸውን ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በተደጋጋሚ ጊዜያት በሕገወጥ መንገድ ወደ ሞዛምቢክ እንደሚገቡና ሕጋዊ ሂደቶችን ተከትሎ ወደ ትውልድ አገራቸው እንደሚመለሱ ኤ.ኤፍ.ፒን ጠቅሶ ጆርናል ዲ ካሜሩን ዘግቧል።
“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይህን የተናገሩት በቤተመንግስት የመሸኛ ዝግጅት በተደረገላቸው ወቅት ነው። አቶ ሃይለማርያም ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ከገለጹ በሁዋላ በአገሪቱ እየነፈሰ ያለው የለውጥ ንፋስ ህዝቡ በሚፈልገው መሰረት እንዲከናወን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው፡፡ ለውጡ የሁላችንንም ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ልንረባረብ ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህን ጥሩ የለውጥ ንፋስ አቅጣጫ የሚያስቀይር ከሆነ ወደ አስከፊና የማንወጣበት ነገር ሊያስገባን ይችላል” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አስጠንቅቀዋል። ለውጡ የተወሰኑ ቡድኖችን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ፍላጎት ማእከል ያደረገ መሆን
“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይህን የተናገሩት በቤተመንግስት የመሸኛ ዝግጅት በተደረገላቸው ወቅት ነው። አቶ ሃይለማርያም ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ከገለጹ በሁዋላ በአገሪቱ እየነፈሰ ያለው የለውጥ ንፋስ ህዝቡ በሚፈልገው መሰረት እንዲከናወን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው፡፡ ለውጡ የሁላችንንም ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ልንረባረብ ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህን ጥሩ የለውጥ ንፋስ አቅጣጫ የሚያስቀይር ከሆነ ወደ አስከፊና የማንወጣበት ነገር ሊያስገባን ይችላል” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም አስጠንቅቀዋል። ለውጡ የተወሰኑ ቡድኖችን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ፍላጎት ማእከል ያደረገ መሆን
በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በረባራት እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች በአቶ አብዲ ኢሌ አገዛዝ በመማረር የጀመሩትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በርካታ ወጣቶች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች፣ የእስር ዘመቻው ተጠናክሮ በመቀጠሉ አካባቢው በውጥረት እንደሚሞላ አድርጎታል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በአካባባቢው በማሰማራት ተቃውሞውን ለማፈን ጥረት መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮ-ሶማሊው ክልል መሪ አቶ አብዲ ኤሌ የሚፈጽሙትን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚያወግዙ የውስጥና የውጭ ተቃውሞዎች እየበረከቱ ነው። የአሜሪካ መንግስት ባወጣው አመታዊ የስብአዊ መብት ሪፖርት በሶማሊ ክልል በ2009 ዓም ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጾ ነበር። ግድያውን የሚፈጽሙት ደግሞ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ናቸው።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችና ጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል። ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ዙሪያ እና አገሪቱ መውሰድ ስለሚገባት እርምጃ አስተያቶችን ሰብስበዋል። በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከተከለከሉ ከሁለት ዓመት በኋላ ድጋሚ ተፈቅዶላቸው እንዲመጡ መደረጉን የሚገልጹት ባለስልጣኑ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቢሮ አዲስ አበባ ላይ ለመክፈት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በተወያዮቹ በአገሪቱ መጠነ ሰፊ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙ ለኮሚ ነሩ ገልጸውላቸዋል። አሁን ያለው አመራር ጥገናዊ ለውጥ ለማምጣት የሚሰራ ከሆነ አገሪቱ ወደነበረችበት ችግር ዳግም
የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) የአብዲ ዒሌና የሽንሌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ድርድር ያለውጤት ተበተነ::
አንድ ሳምንት የሞላውን ተቃውሞ ለማስቆም በአብዲ ዒሌ በኩል ግፊት የተደረገበት ድርድር የከሸፈው በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች እንደማይፈቱ በመገለፁ ነው::
የክልሉን ምክትል ፕሬዝዳንት የላከው አብዲ ዒሌ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩ በመሆናቸው ልንፈታቸው አንችልም የሚል መልስ ለሽማግሌዎቹ ተነግሯቸል ::
ይህ በእንዲህ እንዳለም በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ ታውቋል:: ድርድሩ የተካሄደው በድሬዳዋ ከተማ ነው።
የሶማሌ ክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ አዲስ በሾሟቸው የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት አማካኝነት ከሽንሌ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ዛሬ ድርድር የተቀመጡት ባልፈው ሳምንት የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማስቆም መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በድርድሩ ላይ በሀገር ሽማግሌዎቹ በኩል የቀረበው ቅድመ ሁኔታ በህዝባዊ ንቅናቄው ወቅት የታሰሩ የሶማሌ ወጣቶች ይፈቱ የሚል እንደነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ተጠርጣሪዎችን በነጻ ያሰናበቱት ዳኛ ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በኮማንድ ፖስት የተያዙ ተጠርጣሪዎችን በነጻ አሰናብተዋል የተባሉ ዳኛ መታሰራቸው ተሰማ።
ዳኛው በሰጡት ውሳኔ ላይ የለመታሰር መብታቸው ተጥሶ ወደ ወህኒ መውረዳቸውም ታውቋል።
ዳኛው ለሚመሩት ችሎት ተጠርጣሪዎቹን አቅርበዋል የተባሉት አቃቤ ሕግም ለአንድ ቀን ታስረው መለቀቃቸው ተሰምቷል።
ግዳዩ የተፈጸመው በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ደኖ ወረዳ ነው።ቀኑ ደግሞ ሚያዚያ 12/2010። የወረዳው ኮማንድ ፖስትም ሶስት ተጠርጣሪዎችን ያስራል።ተጠርጣሪዎቹም ችሎት ይቀርባሉ።
ነገር ግን ተጠርጣሪዎቹ ስለተያዙበት ወንጀልም ፈጸሙት ስለተባለው ድርጊት የሚያስረዳ አካል አልተገኘም።
ስለዚህ ዳኛው አብነት ታደሰ የተጠርጣሪዎቹን ቃል ከሰሙ የሚያሳስራቸው ወንጀል ባለማግኘታቸው በነጻ ያሰናብቷቸዋል።
ተጠርጣሪዎቹን ያሰናበቱት ዳኛም ከወረዳው ከኮማንድ ፖስቱ ጽሕፈት ቤት በተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ዳኛው ከተጠሩ በኋላ በዚያው ወደ ወህኒ እንዲገቡ መደረጉም ታውቋል።
የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጫ አቅጣጫ ለማሳት ያለመ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 17/2010) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአክቲቪስት ገዛህኝ ገብረመስቀል ግድያ ላይ ያወጣው መግለጫ ጉዳዮን አቅጣጫ ለማሳት የታለመ በመሆኑ እንደሚያወግዘው በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ገለፀ::
የኮሚኒቲው ሰብሳቢ አቶ ታምሩ አበበ ለኢሳት እንደገለፁት የኤምባሲው መግለጫ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ እንደመጮህ የሚቆጠር ነው::
Monday, April 23, 2018
Wednesday, April 18, 2018
PM to announce cabinet, House to replace speaker
by Engidu Woldie
ESAT News (April 18, 2018)
ESAT News (April 18, 2018)
Ethiopia’s new Prime Minister is expected to announce his new cabinet as he addresses the Parliament tomorrow.
It is the second time since his appointment that Abiy Ahmed will speak before the House of People’s Representatives that also replaces its speaker, Abadula Gemeda.
Critics say the formation of a new cabinet will be a political litmus test for the Prime Minister and challenged him to nominate people from the opposition or outside the ruling party; or technocrats who are known critics of the government. But tradition shows that, based on their quotas, the four ethnic parties making the ruling coalition would send a list of names to the Prime Minister, who would then present the nominees to the Parliament, which in turn automatically rubber stamp it.
ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለሕክምና ወደ ስላሴ ክሊኒክ በመኪና እየተጓዘ እያለ በድንገተኛ አደጋ ራሱን ስቶ ሕይወቱ አልፏል። ድምጻዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር። በሻሸመኔና ሃዋሳ ከተማ አማካኝ ላይ በምትገኘው በጥቁር ውሃ ከተማ በ1971 ዓ.ም የተወለደውና በሻሸመኔ ከተማ ያደገው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለቤተሰቦቹ 2ኛ ልጅ ሲሆን ሁሉም ወንዶች ናቸው። በተወለደ በ39 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ የዝግጅት ክፍላችን መጽናናትን ይመኛል።
በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የተጣለውን ቅጣት በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ የቡድኑ ደጋፊዎችና አጋሮቻቸው ተቃውሟቸውን አሰሙ፤ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ታመው ሆስፒታል ገቡ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵይያ በእግር ኳስ ሜዳዎች ከከስፖርት መርህ ውጪ ስርዓት አልበኝነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተሳፋ መጥቷል። በዚህም የብዙ ሰላማዊ ዜጎች ህይወትና ንብረት ለመውደም ምክንያት ሆኗል። ችግሩን ከመሰርቱ እንዲፈታ ወቅታዊ የሕግ እርምጃዎች መውሰድ የነበረበት የእግርኳስ ማኅበሩ ስርዓት አልበኝነትን ወደጎን በማለት ለችግሩ መባባስ ቀዳሚው ተጠያቂ ነው። ሰሞኑን ወልዲያ ላይ በሼክ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን መጫወቻ ሜዳ በወልዲያና በፋሲል ከነማ መሃከል ተደርጎ በነበረው ጫወታ ላይ አወዛጋቢ የሆነውን የዳኛውን ውሳኔ በመቃወም በደጋፊዎች መሃከል ረብሻ ተፈጥሮ በደጋፊዎችና በንብረት ላይ ጉዳት ደርስዋል። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ስምንት ነጥብ ያለው የቅጣት ብያኔ አሳልፍዋል። ለፋሲል ከተማ ፎርፌ እንዲሰጥ። ይህም 3 ነጥብ እና 3 ጎል እንዲሰጠው፣ የሚጫወትበት የመሀመድ ሁሴን አላሙዲን ስታድየም ለአንድ ዓመት ጨዋታ እንዳይካሄድ። ቀሪ የሜዳው ጨዋታዎችን ከወልዲያ በ500 ኪ.ሜ ርቀት እንዲያደርግ። 250 ሺህ ብር ቅጣት። የዳኞች ህክምና ወጪ እንዲሸፍን። አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ የአንድ ዓመት እገዳ እና 10 ሽህ ብር፣ ብሩክ ቃልቦሬ የአንድ ዓመት እገዳ እና 10 ሽህብር ቅጣት እንዲቀጡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ወስኗል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማኅበር ቀድም ብሎ ሃዋሳ ላይ በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ላይ እስከ ግድያ የደረሰ
በምስራቅ ጎጃም ዞን የመርጦ ለማርያም ከተማ ወጣቶች በአገዛዙ ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ዋሉ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ለተቃውሞው መነሻ የሆነው ለድልድይ ስራ የዋለ ትርፍ ብረት በ4 መኪኖች ተጭነው ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዛቸውን የአካባቢው ህዝብ በመቃወሙ ነው። ወጣቶቹ እቃውን የጫኑትን መኪኖች አስቁመው እቃው እንዲራገፍ ሲጠይቁ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ባለስልጣኑ ግለሰቦቹ ህጋዊ ፍቃድ እንዳላቸው ገልጸው ለማሳመን ቢሞክሩም ህዝቡ አሻፈረኝ በማለት ውዝግቡ እስከምሽት ቀጥሎአል። ህዝቡ በተቃውሞው በመቀጠሉ እቃው እንዲራገፍ የተደረገ ሲሆን፣ በዚህ የተደሰቱ ወጣቶች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ፣ አገዛዙን የሚቃወሙ መፈክሮችንም ሲያሰሙ አምሽተዋል። ነዋሪዎች ፣ ንብረቱ ዘመድኩን የሚባል የህወሃት ሰው እንደሆነ ሲገልጹ፣ አባይ ድልድልይን ከሚጠብቁት ግለሰቦችና ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር እንዲሁም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ንብረት ለማሸሽ በመሞከሩ ህዝቡን ለቁጣ እንዳስነሳው ገልጸዋል። ሌሎች የቀሩ ብረቶችም እንዳይቀንቀሳቀሱና ብረቶችን ለመውሰድ በሚመጣ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ የከተማዋ ወጣቶች አስጠንቅቀዋል።
ወ/ሮ ጠይባ ሃሰን የአቶ ለማ መገርሳ ምክትል ሆነው ተሾሙ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ወ/ሮ ጣይባ ሃሰን የኦሮምያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል። በሻሸመኔ ህዝባዊ የለውጥ ትግል በሚካሄድበት ወቅት፣ የአጋዚ ወታደሮች ሲወስዱት የነበረውን እርምጃ አጥብቀው በመቃወም እንዲሁም በተለያዩ ዝርፊያዎች የተሰማሩ የህወሃት አባላትን በቁጥጥር ስር በማድረግና በድፍረት ለመገናኛ ብዙሃን አሳባቸውን በመስጠት የሚታወቁት ወ/ሮ ጣይባ ሃሰን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ኦህዴድ ጠንካራ አባሎቹን ወደ ማዕከል እየሰበሰበ የሚል አስተያየት እንዲሰጥ አድርጓል። የኦፌኮ ም/ል ሊመንበር አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ሲፈቱ እርሳቸውን ለመቀበል በተዘጋጀ ስነስርዓት ላይ በመገኘታቸው አድናቆት ሲቸራቸው የቆዩት የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ሃቤቤ ደግሞ የኦህዴድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው
በጉጂ እና በጌዲዮ ብሄረሰቦች መካከል የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚገልጹት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ለስደት የዳረገው የሁለቱ ብሄረሰቦቸ ግጭት ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በተለይ ባንቆ ጎትቲ 2 የቡና ሳይቶች እንዲሁም በጨልጨል አንድ የቡና ሳይት ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን፣ በቃርጫ ደግሞ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከተሰደዱ ህጻናት መካከል ደግሞ የተወሰኑ ህጻናት መሞታቸው ታውቋል። ቆስለው ከነበሩ የጌዲዮ ተወላጆች መካከልም በህክምና እጦር 4 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ግጭቱ በተነሳባቸው አካባቢዎች የተገኙ ቢሆንም፣ ግጭቱን ለማስቆም እርምጃ ሲወስዱ አለመታየቱን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ከ1987 ዓም ጀምሮ ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ በሁለቱ ብሄረሰቦች መካከል የተነሳው ግጭት፣ለበርካታ ዜጎች ሞትና ስደት ምክንያት ሆኗል። አርበኞች ግንቦት7 ሆን ተብሎ የተቀሰቀሰውን ግጭት አውግዟል። ንቅናቄው ባወጣው መግለጫ “ በዚህ ወንጀል እጃቸው ያለበት ሁሉ በህግ ፊት እንዲቀርቡ” ጠይቋል። ንቅናቄው ሚያዝያ 9 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተወረወረ ቦንብ እና በጭፍን በተተኮሱ ጥይቶች ሳቢያ የዜጎች ሕይወት መጥፋቱንም ኮንኗል።
Tuesday, April 17, 2018
ጠ/ሚኒስትሩና የመቀሌ ቆይታቸው
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን
ሰኞ ሶስተኛ ሳምንታቸውን ይጀምራሉ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጉዞ፡ በስብሰባ፡ በጉብኝት፡ ተጠምደው ቆይተዋል። ጂጂጋ ሄደው፡ አምቦ ደርሰው ከመቀሌ ቆይተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል። በመሃል በቤተመንግስት ''ተፎካካሪ'' በሚል ከሚጠሯቸው የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፡ ሲቪክ ማህበራት፡ ታዋቂ ሰዎች ጋር እራት በልተዋል። ነገ 25ሺህ የሀገሪቱን ወጣቶች ይሰበስባሉ።
በዚሁ ከቀጠለ ወደ ባህርዳር ጎራ ብለው የአማራውን ህዝብ መጎብኘታቸው ይጠበቃል። አንዱ ጋር መጥተው ሌላው ጋር መቅረት ችግር አለውና ወደ ሀዋሳ አቅንተው፡ አሶሳ ደርሰው፡ ከሰመራ ጎራ ብለው፡ ከጋምቤላ አርፈው፡ ከሀረር ጆጎል ሄደው፡ ድሬ ከዚራን ብለው ከሸገር አዱ ገነትም ህዝቡን ሰብስበው ኢትዮጵያዊነትን ሰብከው፡ በጣፋጭ ንግግሮች አረስርሰው የጫጉላ ጌዜያቸው እስኪያበቃ እረፍት ባጣ ጉዞ መሰንበታቸው የሚጠበቅ ነው።
Friday, April 13, 2018
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ከበዓለ-ሲመታቸው ጀምሮ ያሰሙት ንግግር ለአገራችን ፖለቲካዊ መረጋጋት ተስፋ ሰጪዎች ቢሆንም ሁሉን አቀፍ ለውጥ ለማምጣት አፋኝ ሕጎችን በማንሳት ተግባራዊ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ተናገሩ።
የጠቅላይ ሚንስትሩ ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ የሕዝብ ግንኙነታቸውን በስፋት መቀጠላቸው ባለድርሻ አካላትን ተቃዋሚዎቹን ማነጋገራቸው መልካም ቢሆንም ከተለመደው የተለየ አይደለም። ከዚህ በፊት ተደርገው የነበሩትን ድርድሮች ትርጉም ሰጥተው ድርድሩ እንዲቀጥል መናገራቸው፣ የአገር አቀፍ ፓርቲዎችን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል። ታዋቂ ግለሰቦችና፣ፖለቲከኞች በግብዣው ላይ ሲታደሙ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለመገኘታቸው ተገቢ አለመሆኑን የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ አስታውቀዋል።
ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ ጉዳት እስካሁን ከ7 ያልበለጠ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና- ሚያዚያ 5 ፣ 2010 ዓም)
የአካባቢው ነዋሪዎእ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ አለመገኘቱን፣ በጎርፍ ከተወሰዱት መካከል የንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ የሆነ ግለሰብም እንደሚገኝበት የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጿል።
በጎርፉ አንድ የመብራት ሃይል መኪና እና 4 አይሱዙ መኪኖች በጎርፍ ተወስደዋል። አንድ ኮካ ኮላ የጫነ መኪና እስከሙሉ ጭነቱ የተገለበጠ ሲሆን፣ የጫነው ኮካ ኮላም በጎርፍ ተወስዷል። በመኪኖች ላይ የነበሩ ሰዎችም በጎርፍ ተወስደዋል።
ጎርፉ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ጭናክሰን ከተማ በዘነበው ዝናብ ምክንያት የተፈጠረ ነው::
የአካባቢው ነዋሪዎእ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ አለመገኘቱን፣ በጎርፍ ከተወሰዱት መካከል የንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ የሆነ ግለሰብም እንደሚገኝበት የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጿል።
በጎርፉ አንድ የመብራት ሃይል መኪና እና 4 አይሱዙ መኪኖች በጎርፍ ተወስደዋል። አንድ ኮካ ኮላ የጫነ መኪና እስከሙሉ ጭነቱ የተገለበጠ ሲሆን፣ የጫነው ኮካ ኮላም በጎርፍ ተወስዷል። በመኪኖች ላይ የነበሩ ሰዎችም በጎርፍ ተወስደዋል።
ጎርፉ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ጭናክሰን ከተማ በዘነበው ዝናብ ምክንያት የተፈጠረ ነው::
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉት ውይይት በጎ ጅምር ቢሆንም አፋኝ ሕጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ከበዓለ-ሲመታቸው ጀምሮ ያሰሙት ንግግር ለአገራችን ፖለቲካዊ መረጋጋት ተስፋ ሰጪዎች ቢሆንም ሁሉንአቀፍ ለውጥ ለማምጣት አፋኝ ሕጎችን በማንሳት ተግባራዊ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ተናገሩ። የጠቅላይ ሚንስትሩ ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ የሕዝብ ግንኙነታቸውን በስፋት መቀጠላቸው ባለድርሻ አካላትን ተቃዋሚዎቹን ማነጋገራቸው መልካም ቢሆንም ከተለመደው የተለየ አይደለም። ከዚህ በፊት ተደርገው የነበሩትን ድርድሮች ትርጉም ሰጥተው ድርድሩ እንዲቀጥል መናገራቸው፣ የአገር አቀፍ ፓርቲዎችን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል። ታዋቂ ግለሰቦችና፣ ፖለቲከኞች በግብዣው ላይ ሲታደሙ አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አለመገኘታቸው ተገቢ አለመሆኑን የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ግርማ በቀለ አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የእራት ግብዣ በማድረግ መወያየታቸውና ተቃዋሚዎችን የሚለውን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተብሎ መነሳቱ መልካም ጅምር ነው። ሆኖም ግን ሰፊ ድርድርና ውይይት ያስፈልጋል። ለዚህ ሁሉ ቁልፍ የሚሆነው አፋኝ ቀፍዳጅ የሚባሉ ህጎችን በማንሳት የፖለቲካ ምኅዳሩን ማስፋት ያስፈልጋል። ይህ ጅምር መነሻ ነው። የግል ፕረሱ ቢያንስ ከ1997 ዓ.ም በፊት እንደነበረው መመለስ አለበት። በአሁኑ ሰዓት ይህ ነው የሚባል የፕሬስ ውጤት የለም። ጋዜጠኞች ሳንሱር ቀርቶ ሳይሳቀቁ በሚዛናዊነት የሚሰሩበት ሁኔታ ሊመቻችላቸው ይገባል። ከዚህ አንጻር ጠቅላይ ሚንስትሩ ብዙ ሥራ ይጠበቅባቸዋል ሲል ጋዜጠኛ ነብዩ ገልጿል።
በምዕራብ ጉጂ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ ዜጎች እየተገደሉና እየተሰደዱ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 05 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በጉጂና በጌዲዮ ማህበረሰብ መካከል የተነዛውን ወሬ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ከሁለቱም ወገን በርካታ ዜጎች ሳይገደሉ አልቀረም። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ጌዲዮ ዞን፣ ቡሌ ሆራና ሌሎችም አካባባቢዎች እየተሰደዱ ነው። የግጭቱ መንስኤ በውል ባይታወቅም ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች እንደሚሉት በጉጂ ዞን ቀርጫ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ የጌዲዮ ተወላጆች አካባቢው ወደ ደቡብ ክልል እንዲካለል ሊጠይቁ ነው የሚል ወሬ በመነዛቱ በኦሮምያ ክልል ስር የሚገኙ ጉጂዎችን በማሰቆጣቱ የተጀመረ ግጭት ነው። በጌዲዮ በኩል ደግሞ ጉጂዎችን ሊጨርሱዋችሁ ነው የሚል ወሬ እንዲሰራጭ በመደረጉ ግጭት እንዲፈጠር ተደርጓል ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ በጉጂ ዞን የሚኖሩ የጌዲዮ ተወላጆች በቋንቋችን እንማር የሚል ጥያቄ
Thursday, April 12, 2018
የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 4፣ 2010ዓም)
ነባሮቹ የኢህአዴግ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት አለው ብለው እንደማያምኑ እየተናገሩ ነው።
የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት ነባር ከሆኑት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ስዩም መስፍንና ሌሎችም በድርጅቱ ውስጥ የቆዬ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ኢህአዴግ ከሚመራበት የልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ይልቅ ወደ ሊበራል አስተሳሰብ የሚያዘነብል ፖለቲካ የሚከተል፣ የህዝብን ጥያቄ ያለሳይንሳዊ ትንታኔ እፈታለሁ ብሎ ቃል የሚገባና ለመተግበር የሚቸገር እንዲሁም ከኢህአዴግ ድምጽ ይልቅ የተቃዋሚዎችን ድምጽ ለመስማት የፈጠነ ነው በማለት ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የኢህአዴግ መስመር በጸረ-ህዝቦች መስመር ሲደለዝ አናይም በማለት አዲስ ቅስቀሳ የጀመሩት እነዚህ ነባር አመራሮች፣ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት ከሌለው መስዋትነት የተከፈለበትን ድርጅት ለማዳን እንደሚተጉ እየገለጸ ነው።
የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት ነባር ከሆኑት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ስዩም መስፍንና ሌሎችም በድርጅቱ ውስጥ የቆዬ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ኢህአዴግ ከሚመራበት የልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ይልቅ ወደ ሊበራል አስተሳሰብ የሚያዘነብል ፖለቲካ የሚከተል፣ የህዝብን ጥያቄ ያለሳይንሳዊ ትንታኔ እፈታለሁ ብሎ ቃል የሚገባና ለመተግበር የሚቸገር እንዲሁም ከኢህአዴግ ድምጽ ይልቅ የተቃዋሚዎችን ድምጽ ለመስማት የፈጠነ ነው በማለት ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የኢህአዴግ መስመር በጸረ-ህዝቦች መስመር ሲደለዝ አናይም በማለት አዲስ ቅስቀሳ የጀመሩት እነዚህ ነባር አመራሮች፣ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት ከሌለው መስዋትነት የተከፈለበትን ድርጅት ለማዳን እንደሚተጉ እየገለጸ ነው።
የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 4፣ 2010ዓም)
የአዲ ረመጥ ወረዳ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት "የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ትግራይ ቅርንጫፍ" የካቲት 2 ቀን 2010 ዓም አዲስ ክስ እንደቀረበባቸው አመልክተዋል።
“ከወንጀል ሕግ አልፎ በሽብርተኝነት ተከሰው የነበሩ ሰዎች ክሳቸው በተቋረጠበት ሁኔታ በእኛ ላይ አዲስ ክስ መመስረቱ የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄውን እንዳያነሳ በእኛ ለማስፈራራት እና እኛንም ለመበቀል፣ በተለይም የወልቃይት ህዝብ በሰበብ አስባቡ ተበትኖ ከተወለደበት ሀገር ወጥተን ስደተኛ እንድንሆን፣ እኛን እያሰሩ እና እያባረሩ የትግራይን ሕዝብ በእኛ እርሻና ቤት እየተኩ የወልቃይትን ሕዝብ ከስር መሰረቱ ለመንቀል እንደሆነ ከግምት አልፎ እውነትነት እየታየበት ያለ ሁኔታ ላይ ደርሰናል” የሚሉት አስተባባሪዎች፣ ይህንንም በማስረጃ የሚያረጋገጡት እውነታ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የአዲ ረመጥ ወረዳ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት "የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ትግራይ ቅርንጫፍ" የካቲት 2 ቀን 2010 ዓም አዲስ ክስ እንደቀረበባቸው አመልክተዋል።
“ከወንጀል ሕግ አልፎ በሽብርተኝነት ተከሰው የነበሩ ሰዎች ክሳቸው በተቋረጠበት ሁኔታ በእኛ ላይ አዲስ ክስ መመስረቱ የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄውን እንዳያነሳ በእኛ ለማስፈራራት እና እኛንም ለመበቀል፣ በተለይም የወልቃይት ህዝብ በሰበብ አስባቡ ተበትኖ ከተወለደበት ሀገር ወጥተን ስደተኛ እንድንሆን፣ እኛን እያሰሩ እና እያባረሩ የትግራይን ሕዝብ በእኛ እርሻና ቤት እየተኩ የወልቃይትን ሕዝብ ከስር መሰረቱ ለመንቀል እንደሆነ ከግምት አልፎ እውነትነት እየታየበት ያለ ሁኔታ ላይ ደርሰናል” የሚሉት አስተባባሪዎች፣ ይህንንም በማስረጃ የሚያረጋገጡት እውነታ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ጥለው ወጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010) የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቋሙ ውስጥ ምግብ በመከልከላቸው ግቢያቸውን ጥለው መውጣታቸው ተነገረ።
ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው የሚቀርብላቸው ምግብ በመቆሙ ሕይወታቸውን ለማቆየት ግቢያቸውን ለቀው ወደ ሐሮማያ ከተማ ለመሔድ ተገደዋል።
ዩኒቨርስቲው ለተማሪዎቹ ምግብ እንዳይሰጥ የከለከለው በግቢው ውስጥ የትምህርት ማቆም አድማ በመጀመሩ ነው ተብሏል።
የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢያቸው ውስጥ ተማሪዎች በወታደራዊ እዝ/ኮማንድ ፖስት/በመታሰራቸው ይህንኑ በመቃወም ትምህርት አቁመዋል።
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሁለት ተማሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ዘጋቢ እንደገለጹት በሐሮማያ ዩኒቨርስቲ በቀጠለው የእስር ርምጃ እስካሁን 20 ተማሪዎች በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የአዲስአበባና የድሬደዋ ምርጫ በአንድ አመት እንዲራዘም ተወሰነ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010)በዚህ አመት መካሄድ የነበረበት የአዲስአበባና የድሬደዋ ምርጫ እንዲሁም በመላ ሃገሪቱ የሚካሄዱ የአካባቢና ማሟያ ምርጫ በአንድ አመት እንዲራዘሙ ፓርላማው ዛሬ ወሰነ።
ከአመት በኋላም ምርጫው መቼ ይካሄዳል ለሚለው ወርና ቀን ተቆርጦ አልተቀመጠለትም። 8 የፓርላማ አባላትም ድምጸ ተአቅቦ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ከ230 በላይ የፓርላማ አባላትም አልተገኙም። የሕወሃቱ ኤፈርት ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና እንደዘገበው በፓርላማው የዛሬ ውሎ የማሟያ ምርጫም ለአንድ አመት ተራዝሟል።
ፓርላማው ዛሬ ሚያዚያ 4/2010 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ምክር ቤቶች በየአምስት አመት የሚያካሂዱት ምርጫም ወደሚቀጥለው አመት ተሻግሯል።
የአዲስ አበባ ምርጫ በዚህ በሚያዚያ ወር መካሄድ የሚጠበቅበት ሲሆን በምርጫው ከተማዋን የሚያስተዳድሩ ሃላፊዎች ከንቲባው ጭምር የሚመረጡበት እንደሆነም ታውቋል።
በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላት ተፈቱ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010)በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላቱ አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔርና አቶ ገብረስላሴ ገብሬ በዋስትና መፈታታቸው ተነገረ።
በሕጉ መሰረት ቢሆን ኖሮ በሙስና የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት አይፈቀድለትም።
በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ተከሰው የነበሩት የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔር በ750ሺ ብር የኮሜት ኩባንያ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብሬ ደግሞ በ5 መቶ ሺ ብር ዋስ ተለቀዋል።
ሁለቱ ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ከታሰሩ ከ5 አመት በላይ ሆኗቸዋል።
በእነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔርና የኮሜት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብሬ በሙስናና ግብር በመሰወር ተወንጅለው ነበር።
Ethiopia: University denies food to protesting students
The Haramaya University in Eastern Ethiopia has denied food to students who were protesting the detention of their fellow students by security forces.
The report by the Addis Standard portal says the students have left campus and went to the nearby town of Haramaya where residents were providing them with food assistance.
Tuesday, April 3, 2018
በተወሰኑ ክሶች አቶ መላኩ ፋንታን ነጻ ያሉት ዳኞች ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ደረሳቸው
(ኢሳት ዜና መጋቢት 25 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ አቶ መላኩ ፋንታ በተወሰኑ ክሶች ነጻ እንደተባሉ፣ ደህንነቶች ዳኞችንና የዳኞቹን ፕሬዝዳንት ጭምር በመሰብሰብ እንዳነጋገሯቸው፣ “ ለምንድነው ነፃ የላችሁት?” የሚል ጥያቄ እንደጠየቁዋቸው ምንጮች ገልጸዋል። ዳኞቹ “ ሰውየው ከታሰረ ረጅም አመት ነው፣ ክሱን በደንብ አይተን የሚያስፈርድበት ሆኖ አላገኘነውም” ብለው ሲመልሱ፣ ደህንነቶቹም “ከአሁን በሁዋላ ባሉበት ክሶች ላይ እንድትፈርዱበት፣ ነፃ እንዳትሉት” ብለው ሲያስፈራሩ፣ ምክትል የዳኞች ሰብሳቢ ስብሰባውን ጥለው ወጥተዋል። ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ውሎውን እንዳይዘግቡ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ታውቋል ። የፋና ጋዜጠኛ በቀኑ ስድስት ሰአት የዜና ፕሮግራም ላይ ዜናውን ከሰራችው በሁዋላ፣ የስድስት ሰአቱ ዜና አስራ አንድ ሰአት ላይ የሚደገም ቢሆንም ፣ በደህንነቶች ትእዛዝ ዜናው እንዳይደገም ተደርጓል። የፋናዋ ጋዜጠኛም ተጠርታ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷታል ። ኢቢሲ የእነመላኩን የፍ/ቤት ዘገባ በተከታታይ ይሰራ የነበረ ቢሆንም፣ አቶ መላኩ ነጻ በተባሉበት ቀን ዘገባውን አልሰራም። አቶ መላኩ የቀራቸው አራት ክሶች ሲሆኑ፣ በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው እንዲፈረድባቸው ደህንነቶች ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። ባለፈው በተሰጠው ውሳኔ ላይም ዓቃቢ ህግ ይግባኝ እንዲጠይቅ ታዟል ። “ ኢቢሲም ሆኑ ሌሎች የመገናኛ ብዙሃን አቶ መላኩ ነፃ ሲባሉ ያልዘገቡት ህዝቡ እንዲያውቅ ስላልተፈለገ ፣ ህዝብ እንዲያውቅ የተፈለገው ወንጀለኛነቱን እንጂ ነፃ ሰው መሆኑን አይደለም “ ሲሉ ምንጮች ተናግረዋል።
በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት ተገኘ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2010)ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ ካሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በ10 ዩኒቨርስቲዎች ብቻ የ3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ጉድለት መኖሩን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ ገለጸ።
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ብቻ 64 ሚሊየን ብር ጉድለት በመኖሩ በፓርላማ የመንግስት ወጭ አስተዳደርና ቁጥጥር ኮሚቴ ተቋሙን መገሰጹ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ካሉ 158 የመንግስት ተቋማት ብቻ ባለፈው አመት የ20 ቢሊየን ብር ጉድለት መገኘቱን የጠቅላላ ኦዲት ቢሮ መግለጹ ይታወሳል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በበጀት እጥረት ምክንያት የአመቱን የትምህርት ክፍለ ጊዜ በአስቸኳይ እንዲያጠናቅቁ ተማሪዎች በተፋጠነ ሂደት ተከታታይ ፈተናዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።
እነአቶ መላኩ ፈንታ በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 25/2018) በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው ከአራት ዓመታት በላይ ሲከራከሩ የከረሙት እነአቶ መላኩ ፈንታ በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ሲባሉ በሌሎች ክሶች ደግሞ በነፃ ተሰናበቱ፡፡
አቶ መላኩና አቶ ገብረ ዋህድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ሙስና ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር ።
በዚሁ ክስ የተካተቱት አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ በላቸው በየነ፣ አቶ ማሞ አብዱ፣ አቶ አሞኘ ታገለና አቶ ጥሩነህ በርታ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ባቀረቡት የመከላከያ ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች ሊያስተባብሉ አልቻሉም በሚል ጥፋተኛ ናቸው ሲል በተወሰኑ መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤቱ ወሳኔ ሰጥቷል፡፡
ሁለቱም ተከሳሾች ያማቶ ኢትዮጵያ የተባለ ድርጅት መክፈል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ ከተወሰነበት ግብር 50 በመቶ አስይዞ መከራከር ቢኖርበትም፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀምና ዝቅ አድርገው በመገመት የመንግሥት ሥራን በማያመች ሁኔታ መምራታቸውን ማስተባበል ባለመቻል ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
አቶ ገብረ ዋህድ ጥፋተኛ የተባሉት በተመሳሳይ የክስ መዝገብ በአምስተኛ ክስ ነው።
እነአቶ መላኩ ፈንታ በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 25/2018) በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው ከአራት ዓመታት በላይ ሲከራከሩ የከረሙት እነአቶ መላኩ ፈንታ በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ሲባሉ በሌሎች ክሶች ደግሞ በነፃ ተሰናበቱ፡፡
አቶ መላኩና አቶ ገብረ ዋህድ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተርና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ሙስና ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው ነበር ።
በዚሁ ክስ የተካተቱት አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ፣ አቶ በላቸው በየነ፣ አቶ ማሞ አብዱ፣ አቶ አሞኘ ታገለና አቶ ጥሩነህ በርታ ናቸው፡፡
ተከሳሾቹ ባቀረቡት የመከላከያ ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች ሊያስተባብሉ አልቻሉም በሚል ጥፋተኛ ናቸው ሲል በተወሰኑ መዝገቦች ላይ ፍርድ ቤቱ ወሳኔ ሰጥቷል፡፡
ሁለቱም ተከሳሾች ያማቶ ኢትዮጵያ የተባለ ድርጅት መክፈል የሚገባውን ግብር ባለመክፈሉ ከተወሰነበት ግብር 50 በመቶ አስይዞ መከራከር ቢኖርበትም፣ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀምና ዝቅ አድርገው በመገመት የመንግሥት ሥራን በማያመች ሁኔታ መምራታቸውን ማስተባበል ባለመቻል ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡
አቶ ገብረ ዋህድ ጥፋተኛ የተባሉት በተመሳሳይ የክስ መዝገብ በአምስተኛ ክስ ነው።
የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት በካርቱም ሊመክሩ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2010) በሕዳሴው ግድብ ላይ ለመነጋገር የኢትዮጵያ፣የግብጽና የሱዳን ባለስልጣናት ነገ በካርቱም እንደሚገናኙ ታወቀ።
በግድቡ ዙሪያ በሃገራቱ በተለይም በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት በሚል የተጠራው ስብሰባ ላይ ለመገኘት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ረቡዕ ካርቱም እንደሚገቡ ኦህራም ኦንላይን ዘግቧል።
ባለስልጣኑም የስብሰባው አላማ ውዝግቡን ለመቋጨት እንደሆነም አስገንዝበዋል።
በካርቱም ነገ በሚካሄደው ስብሰባ የየሃገራቱ የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የደህንነት ባለስልጣናት የሚገኙበት መሆኑም ተመልክቷል።
Monday, April 2, 2018
በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አሁንም በችግር ላይ ናቸው
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንት በፊት ያልተፈቀደ ስብሰባ እና አርማ የሌለውን የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ ተጠቅማችሁዋል በሚል በእስር ላይ የሚገኙት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አሁንም ያሉበት ሁኔታ አለመሻሻሉ ታውቋል። አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝና ሌሎችም ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የታሰሩበት ሁኔታ እጅግ መጥፎ የሚባል መሆኑ መዘገቡ ይታወቃል። በአገራቸው ጉዳይ ምንም አይነት መረጃ እንዳያገኙ ተደርገው መታሰራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።
“ከልባችን ይቅር ተባብለን በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ እንሻገር” ሲሉ አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ማጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም) አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መንግስታዊ ስልጣኑን ሲረከቡ ባደረጉት ንግግር፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውን ከልባቸው ይቅር ተባብለው፣ የትናንትናውን ምዕራፍ ዘግተው በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዩ አገራዊ ጉዞ እንዲሸጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ይህን እውን ለማድረግ አንዳንድ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ቢናገሩም፣ በተጨባጭ ስለሚወስዱት እርምጃ ግን አልገለጹም። ዶ./ር አብይ ከኢህአዴግ ውጭ ያሉ ፓርቲዎች የሚታዩበት መነጸር እንደሚቀየር ተናግረው፣ ፓርቲዎቹ “ እንደተቃዋሚ ሳይሆን እንደ ተፎካካሪ፣ እንደ ጠላት ሳይሆን እንደ ወንድም፣ አማራጭ ሃሳብ አለኝ ብለው እንደሚጡ የዜጎች ስብስብ” ይታያሉ ብለዋል። ዶ/ር አብይ በተለያዩ ጊዜዎች መስዋትነት ለከፈሉ የመብት ተከራካሪዎች፣ ፖለቲከኞችና በደንብ ሳይቦርቁ ህይወታቸው ለተቀጠፈው ለውጥ ፋላጊ ወጣቶች፣ ለስነ ልቦናና አካላዊ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል። የኢትዮጵያን ህዝብም እንደሚክሱ ቃል ገብተዋል። ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ ታሪክ
በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)በኢትዮጵያ ዘረኝነትና መከፋፈልን ማጥፋት እንደሚገባ በፓርላማ የሃገር መሪነትን ስልጣን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስገነዘቡ።
ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ወደ እድልና መልካም አጋጣሚ መቀየር እንደሚገባ ዶክተር አብይ ለፓርላማው በስልጣን ርክክብ ስነስርአቱ ላይ ተናግረዋል።
ካለፉት 27 አመታት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ ያወደሱት ዶክተር አብይ ሰብአዊነት ያለው ንግግር በማድረግ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን አትርፈዋል።
ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣኑን በመረከብ በፓርላማ ተሰይመዋል።
በዚሁ ስነስርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ታዲያ ካለፉት 27 አመታት ወዲህ ባልታየ ሁኔታ ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ የሕዝቡን አንድነት የሚያስተሳስር ንግግር አድርገዋል።
አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፌን እሰጣለሁ አለች
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት፣እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች የደስታ መግለጫ አስተላለፉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች።
አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩልም ባወጣቸው መግለጫ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት አፋጣኝ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን እንዲያመጣ ድጋፍ እንደምትሰጥ የገለጸችው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣የአፍሪካ ሕብረት ኮሚስን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ፣የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ ሹመቱን ተከትሎ የደስታ መግለጫቸውን ካስተላለፉት ውስጥ ይጠቀሳሉ።
የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)