በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሶማሊ ዞኖች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ የክልላቸው አስተዳደር በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የወሰደውን እርምጃ በመተቸት፣ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጠይቀዋል። ባለስልጣኑ የወሰዱትን እርምጃም ከፉኛ ነቅፈዋል።
የአገር ሽማግሌዎቹ፣ ሶማሊያ ፈርሳ በጦርነት እየታመሰች እያየን፣ አሁን ደግሞ ጦርነቱን በእኛ ላይ ልታመጡብንና እኛን ከመሃል አድርጋችሁ ለትገድሉን ነው በማለት የአገር ሽማግሌዎች በቁጣ ሃሳባቸውን ገልጸዋል።
እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ፣ “ እኔ ኦሮሞዎች እንዲፈናቀሉም ሆነ እንዲገደሉ ትእዛዝ አልሰጠሁም” በማለት ለመሸንገል ቢሞክርም፣ የአገር ሽማግሌዎቹ ግን የሚቀበሉት አልሆነም። “ ወገኖቻችንን አፈናቅላችሁ ምን አገኛችሁ? ይኸው በኑሮ ውድነት አሰቃያችሁን፣ እኛ ተዋልደን፣ ተጋብተን አንዳንችን ሌላችንን መለዬት በማንችልበት ደረጃ ደርሰን ባለበት ሰአት ለምን ትለያዩናላችሁ” ያሉት የአገር ሽማግሌዎች፣ “ ብዙ ዘመን አብረን ኑረን አሁን እነሱን ስናጣ ባዶ ሆነናል። ከፍተኛ ጉዳትም ደርሶብናል” ሲሉ በስሜት ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት አብዲ መሃመድ የአገር ሽማግሌዎችን ቁጣ በመፍራትና ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን ፣ “የተፈናቀሉት ዜጎች እንዲመለሱ ለማድረግ ስራ እየሰራን ነው፣ የማፈናቀል እርምጃ የወሰዱትን ይዘን ለፍርድ ለማቅርብ እንቅስቃሴ ጀምረናል” በማለት ተናግሯል። የአገር ሽማግሌዎች ግን ፣ ጉዳዩ በግለሰብ ደረጃ መታዬት እንደሌለበትና የችግሩ ምንጭና ዋናው ተጠያቂ ሌላ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

No comments:
Post a Comment