(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)አቶ አንዱዓለም አራጌ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቅ ተመድ ጠየቀ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስረኞች ጉዳይ ተከታታይ ቡድን የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በነበረው አቶ አንዱዓለም አራጌ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ዓለምአቀፍ ሕጋዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ፈርዶበታል ሲል መግለጫ አውጥቷል። የተመድ አምስት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ቡድን ኤክስፐርቶች ባወጡት የአቅዋም መግለጫ አንዱዓለም አራጌ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።
“የሌጋል ፍሪደም ናው” ዳሬክተር የሆኑት ኬት ባርዝ ፣ ''የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በ2009 እ.ኤ.አ. ይወጡትን ጸረሽብር ሕጉን ሕጋዊ የሆኑትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን እና የተለየ ሃሳቦችን ለማፈኛነት ይጠቀሙበታል። አንዱዓለም አራጌን ለእስር ያበቃው ይህን ኢፍትሃዊ ሕግ በመቃወሙ ነው። የሰብዓዊ ቡድኑ አባላት በጋራ ለኢትዮጵያ መንግስት የምናቀርበው ጥያቄ የቡድኑን አስተያየት አክብረው በአፋጣኝ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች አንዱዓለም አራጌን እና አብረውት የታሰሩት ባልደረቦቹን በሙሉ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።'' ሲሉ በአጽንኦት ጠይቀዋል።
አንዱዓለም አራጌ እና ታዋቂው አንጋፋ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የመሳሰሉ አያሌ የፖለቲካ እስረኞች በተደጋጋሚ ግዜያት ከሕግ አግባብ ውጪ እንደተፈረደባቸው ፍሪደም ናው ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment