Tuesday, October 31, 2017

በቅርቡ በኢሉባቡር ዞን በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ግሎባል አልያንስ የላከው ከግማሽ ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብ ለተፈናቃዮቹ እንዳይደርስ ተከለከለ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 21/2010) በቅርቡ በኢሉባቡር ዞን በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ ዜጎች ግሎባል አልያንስ የላከው ከግማሽ ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገንዘብ ለተፈናቃዮቹ እንዳይደርስ ተከለከለ። በመላው አለም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለመታደግ የተቋቋመው አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ የኢሉባቡር ተፈናቃዮችን ለመታደግ የላከውን 700 ሺ ያህል ብር ለማድረስ የሄዱት ሰዎች ያለውጤት አካባቢውን እንዲለቁ ተገደዋል። በኢሉባቡር ዞን በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመታደግ አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አሊያንስ የላከውንና 25ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም 700ሺ የሚገመተውን የኢትዮጵያ ብር ለተፈናቃዮቹ ለማድረስ የተንቀሳቀሱት በሀገሪቱ በሕጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲ ተወካዮች መሆናቸው ታውቋል። በመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ በአቶ አዳነ ጥላሁን የተመራውና አራት አባላት የተካተቱበት የመኢአድና የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ገንዘቡን ለተፈናቃዮቹ ለማድረስ ኢሉባቡር ዞን መቱ ከተማ ከገቡ በኋላ ተፈናቃዮቹ ወዳሉበት እንዳይደርሱ መከልከላቸውን መረዳት ተችሏል። ገንዘቡን ለተፈናቃዮቹ ለማድረስ ያደረጉት ሙከራ ባለመሳካቱ ከቀናት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ኢሳት ያገኛቸው የቡድኑ መሪ አቶ አዳነ ጥላሁን እንደተናገሩት የኢሉባቦር ዞን ሃላፊዎች ለቀናት ካስጠበቋቸው በኋላ እንደከለከሏቸው አስታውቀዋል። ከክልሉ መንግስት ፈቃድ ሳትይዙ ተፈናቃዮችን ማግኘትም ሆነ እርዳታ ማድረግ አትችሉም መባላቸውንም ጨምረው ገልጸዋል። በዚህም ለተፈናቃዮቹ እርዳታ ለማድረስ የተደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ግሎባል አልያንስ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመታደግ በአባገዳዎች በኩል ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

Ethiopia: Nine killed in clashes in Benishangul Gumuz

ESAT News (October 31, 2017)
Reports reaching ESAT say nine people were killed in ethnic attacks allegedly instigated by operatives of the TPLF. Thousands of Amharas have also been displaced as a result of attacks by the locals.
ESAT sources say in Kamash Zone alone, nine people were killed in ethnically motivated attack which sparked the displacement of Amharas from the region.

የህወሃት አመራሮች በኦሮምያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ያደረጉት እቅድ አልተሳካም

ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የኦህዴድ የአመራር አባል እንደገለጹት በአቶ አባይ ጸሃዬ የተመራ 5 ነባር የህወሃት አመራሮችንና ሌሎችን ታማኝ ሰዎችን የያዘ ቡድን፣ በኦሮምያ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ ውሳኔ አሳልፎ የነበረ ቢሆንም፣ መረጃው አፈትልኮ በመውጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል። ቡድኑ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓም በተለያዩ ከተሞች ፈንጅዎች እንዲፈነዱና ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቶ በኦሮምያ ክልል “ ህዝብ እየተገደለ በመሆኑ፣ አስቸኳይ አዋጅ መታወጅ አለበት” የሚል ውሳኔ ለማሳለፍ አቅዶ እንደነበር ባለስልጣኑ ተናግረዋል።

በባህርዳር ከመደበኛ፣ ልዩ ሃይልና ከደህንነት ቢሮ የተውጣጡ የከፍተኛ መኮንኖች ህቡዕ ድርጅት ተመስርቷል የሚል ሪፖርት ቀረበ

ከክልሉ የደህንነት መስሪያ ቤት ባገኘነው መረጃ፣ ከአማራ ፖሊስ መደበኛ እና ልዩ ሀይል ከፍተኛ መኮነኖች እንዲሁም የክልል ደህንነት ቢሮ ሰራተኞች የተካተቱበት የህቡህ ድርጅት መመስረቱን የሚያመለክት ሪፓርት ቀርቧል ። የክልሉ የፖሊስ አባላት እና የደህንነት አባላት በክልሉ ውስጥ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ደስተኛ ባለመሆን የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስዱ ቆይተዋል። ትናንት የባህር ዳር የግንቦት 20 ክ/ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ የዞን ፖሊስ የመረጃ ቡድን ሃላፊው ኮማንደር አትንኩት አያሌው “በእኔ ላይ የግድያ እርምጃ ሊወሰድብኝ” ነው በማለት ለክልሉ ምክትል ኮሚሽነር ደስየ ደጀኔ አቤቱታ በማቅረብ የአመት እረፍት እንዲሰጠው ቢጠይቅም፣ ምክትል ኮሚሽነሩ ግን “ በክልል ደረጃ አጣሪ ቡድን ተቋቁሞ እየተባለ ያለውን እና በተቋሙ ላይ ያለውን የህቡዕ አደረጃጀት የሚመረምር አካል እንኪዋቀር በስራህ ላይ ቀጥል” ብሎ አሰናብቶታል። ኮማንደር አትንኩት በአማራ ክልል በይበልጥ ደግሞ በባህርዳር ከተማ ወጣት ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈፅሞአል በሚል በፖሊስ አባላቱ ቂም የተያዘበት ግለሰብ ሲሆን፣ የህቡዕ ቡድኑ የመጀመሪያ ኢላማ እኔ ነኝ የሚል ስጋት እንዳደረበትና ማስፈራሪያ እንደደረሰው ሪፖርት አቅርቧል። 

የሶማሊ ክልል የአገር ሽማግሌዎች በኦሮም ወገኖች ላይ የተወሰደውን እርምጃ ኮነኑ

በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሶማሊ ዞኖች የተውጣጡ የአገር ሽማግሌዎች፣ የክልላቸው አስተዳደር በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የወሰደውን እርምጃ በመተቸት፣ ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ ጠይቀዋል። ባለስልጣኑ የወሰዱትን እርምጃም ከፉኛ ነቅፈዋል። 
የአገር ሽማግሌዎቹ፣ ሶማሊያ ፈርሳ በጦርነት እየታመሰች እያየን፣ አሁን ደግሞ ጦርነቱን በእኛ ላይ ልታመጡብንና እኛን ከመሃል አድርጋችሁ ለትገድሉን ነው በማለት የአገር ሽማግሌዎች በቁጣ ሃሳባቸውን ገልጸዋል። 

የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ መሪ ስልጣን እንዲለቁ ተጠየቁ

የሃረሪ ክልልን በበላይነት የሚመራው የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ( ሃብሊ) አባላት ከሁለት መከፈላቸው ታውቋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሙራድ አብዱላሂን የሚቃወሙ የድርጅቱ አባላት፣ ድርጅታቸው ባለፉት 25 ዓመታት በተከተለው ፖሊሲ ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲጋጩ ያደረጋቸው በመሆኑና ዘላቂ ህልውናቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እርምጃዎችን እየወሰደ በመሆኑ፣ ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን እንዲወርዱ ድርጅቱም ፈርሶ ህዝቡ በሌሎች መንገዶች እንዲደራጅ እየጠየቁ ነው። እነዚህ አባላት፣ ችግሩ እየበዛ መሄዱንና የህልውና ስጋት እየደቀነባቸው መምጣቱን እየተናገሩ ነው። 
በህቡዕ የሚንቀሳቀሱት እነዚህ ተቃዋሚዎች፣ የተለያዩ የቅስቀሳ ጽሁፎችን እየበተኑ ነው። ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ያማከለ ስርዓትና አደረጃጃት በክልላቸው እንዲፈጠር የሚጠይቁት አባላቱ፣ ይህን ማድረግ ካልተቻለ የውስጥ ትግላቸውን እንደሚገፉበት ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተለው የኢሳት ወኪል ገልጿል።

ወ/ት ንግስት ይርጋ በስር ቤት ኃላፊዎች ማስጠንቀቂያ እየተሰጣት መሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረች

በንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ በዓቃቤ ሕግ የሽብር ክስ የቀረበባቸውን ክስ አስመልክቶ ተከሳሾቹ በክሱ ላይ ''ይከላከሉ ወይም በነጻ ይሰናበቱ'' በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤቱ ብያኔው አልደረሰም በማለት ለህዳር 1 ቀን 2010 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ወጣት ንግስት ይርጋ በስም ካስመዘገበቻቸው የቤተሰብ አባላት ውጭ እንዳትጠየቅ፣ እንዲሁም ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ባለው አንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እንድትጠየቅ ገደብ የተጣለባት መሆኑን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቤቱታ ማቅረቧ ይታወሳል። ሀምሌ 21 ቀን 2009 ዓ.ም በዋለው ችሎት በቤተሰብ፣ የሃይማኖት አባት፣ የትዳር ጓደኛ እና በጠበቃዋ የመጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብት እንዳላት፣ የሰዓት ገደብም እና ልዩ ክልከላ ሊደረግባት እንደማይገባ ፍርድ ቤቱ ወስኖ ለቃሊቲ እስር ቤት ትዕዛዝ ቢሰጥም የቃሊቲ እስር ቤት ግን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለማክበር እስካሁን ፈቃደኝነቱን አላሳየም።

Friday, October 27, 2017

ሁለት እስረኞች በተፈጸመባቸው ድብደባ መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ

ከአንድ ዓመት በፊት በርካታ እስረኞች በግፍ ባለቁበት የቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ወቅት በእስር ቤቱ አድማ አስነስታችኋል፣ ለማምለጥ ሙከራ ድርጋችኋል ተብለው ክስ ከቀረበባቸው እስረኞች ውስጥ ሁለት ታራሚዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በደረሰባቸው ድብደባ መገደላቸው ተዘግቧል። ግድያው ሲፈጸም በስፍራው የተመለከቱ እስረኞች ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም ለፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በቀረቡበት ወቅት የዓይን እማኝነታቸውን ለችሎቱ ተናግረዋል።

በአምቦና አካባቢው በቀጠለው የለውጥ እንቅስቃሴ የአጋዚ ወታደሮች ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ

ረቡዕ ፣ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓም የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ አምቦን አቋርጠው ወደ ክልሎች የሚሄዱም ሆነ በአምቦ መስመር ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ህዝቡ በወሰደው ሰላማዊ እርምጃ ተገተው ውለዋል።

ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓም) የአቶ በረከት ስምዖን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ፣ የአቶ አባዱላ ገመዳ ግን ገና በውይይት ላይ እንደሆነ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በርካታ አነጋጋሪ ጉዳዮችን ባወሱበት በፓርላማ ንግግራቸው፦” አቶ በረከት በተደጋጋሚ የመልቀቂያ ጥያቄ በማቅረቡ ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቷል። ከክቡር አባዱላ ጋር ግን ገና እየተወያዬን ነው። ውሳኔው ምን እንደሚሆን በቅርቡ እናያለን” ብለዋል።

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓም) እስር ቤት ውስጥ በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን የዋልድባ መነኮሳት ተናገሩ

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው በፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው የ"ሽብር" ክስ ቀርቦባቸው ቂሊንጦ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እስር ቤት ውስጥ በደል እየተፈፀመብን ነው ሲሉ ዛሬ ጥቅምት 16/2010 ዓም ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አመልክተዋል። መነኮሳቱ ማዕከላዊ እስር ቤት ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ከአሁን ቀደም መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን በሚገኙበት ቂሊንጦም በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

Tuesday, October 24, 2017

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 14 ቀን 2010 ዓም) በኢሉ አባቦር ዞን ጮራ ወረዳ ተፈናቅለው በአባጉሮ ከተማ የሚገኙ ዜጎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ነው።

ተፈናቃዮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ሰሞኑን በባለስልጣናት ቅንብር በተነሳው ብሄርን ማእከል ባደረገ ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ሌሊቱን በሰላም አሳልፈዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች የደረሰባቸውን ጥቃት ተከትሎ አካባቢያቸውን በመልቀቅ አንጻራዊ ሰላም ወደ ስፈነባት አባ ጋሮ ከተማ በመሰደድ በከተማዋ ተጠልለው ይገኛሉ።
የአገር ሽማግሌዎች ከተፈናቃዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ተፈናቃዮቹን ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ እየሰሩ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

Ethiopia: Displaced Amharas call for help

ESAT News (October 24, 2017)
Amharas displaced in last week’s ethnic violence in South Western Ethiopia have called for help as local elders are working to restore peace and normalcy.
Several people were killed last week in Chora, Illubabor, in what the Amharas say was killings perpetrated by the Oromos. Close observers of the developments meanwhile accused that the ethnic violence was instigated by the operators of the ruling TPLF regime.

Monday, October 23, 2017

ከኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በኢሉባቦር አካባቢ የተከሰተውን አሳሳቢና አሳዛኝ ሁኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

በአገራችን ውስጥ የተለያዩ ማህበረሰቦች ለዘመናት ተቻችለውና ተቀራርበው መኖራቸውንና እየኖሩም እንደሆነ ህዝቡ ራሱና ታሪክ ምስክር ናቸው። እነኚህ ማህበረሰቦች አብሮ ከመኖር ባሻገር የተጋቡና የተዋለዱ፤ ደስታና ሃዘናቸውን ሲጋሩ የኖሩም ናቸው። ይህ የአብሮነትና የመቻቻል መንፈስ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ እና   ወደፊትም የሚቀጥል ነው።

Wednesday, October 18, 2017

ኦሮምያ ከተሞች የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎ ሲውል የአንድነትና የትብብር ድምጾች ከፍ ብለው እየተሰሙ ነው

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓም) በኦሮምያ ከተሞች የሚካሄደው ተቃውሞ ቀጥሎ ሲውል የአንድነትና የትብብር ድምጾች ከፍ ብለው እየተሰሙ ነው
በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የሚካሄዱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለው ውለዋል። ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወሰዱት እርምጃ የተገደለውን ወጣት ፈይሳ አለሙን ለመቅበር የወጣው ህዝብ ተቃውሞውን ወያኔን በማውገዝ አሰምቷል። በአካባቢው ያለውን ውጥረት ተከትሎ ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃምና ጎንደር የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ መኪኖች በደብረ ብርሃን ደሴ ዞረው ለመጓዝ ተገደዋል።
በጫንጮ ሰሞኑን ከፍ ብሎ ሲሰማ የነበረው የአንድነን እና የእንተባበር ድምጽ ዛሬም ከፍ ብሎ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል። በመቱ እና በበደሌ ከተማ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴም እንዲሁ ህዝቡ ወያኔ የውደም የሚለውን መፈክር ሲያስተጋባ ውሎአል።
በሱሉልታም በነገው እለት የሚውለውን የገበያ ቀን ተከትሎ የመከላከያ ሲቪል ለባሽ የደህንነት አባላት ቅኝት ሲያደርጉ መዋላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመሰረተባቸው በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ በሚገኝ የብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመስርቶባቸዋል።

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓም) በብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመሰረተባቸው
በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ በሚገኝ የብአዴን ፅ/ ቤት ላይ ወታደራዊ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ግለሰቦች የ"ሽብር" ክስ ተመስርቶባቸዋል። ትናንት ጥቅምት 7/2010 በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች ክሱ ተነቦላቸዋል።
በእነ ፈለቀ አባብዬ የክስ መዝገብ ስር የተከሰሱት ፈለቀ አባብዬ፣ ዋሴ ታደሰ፣ ፈንታሁን አበበና ገደፋዬ ሲሆኑ ፈለቀ አባብዬ፣ ዋሴ ታደሰ እና ገደፋዬ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ አባላትን በመመልመል፣ መሳርያና ሌሎች ቁሳቁሶችን መግዧ የሚሆን ገንዘብ በመቀበል ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። በተጨማሪም ከዋና ሳጅን አገኘሁ አቻው ጋር ግንኙነት በመፍጠር ስማዳ፣ ስቴ እና ጋይንት አካባቢ ወታደራዊ ቤዝ

የኔዘርላንድስና የቤልጂየም መንግስታት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 08 ቀን 2010 ዓም) የኔዘርላንድስና የቤልጂየም መንግስታት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጣ
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው እና እስከዛሬ ባጸናው ውሳኔው ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎቹ በተለይ ወደ ሶማሊ እና ኦሮምያ ክልል እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
በመላ አገሪቱ ተቃውሞዎች በመካሄድ ላይ መሆናቸውንም የሆላንድ መንግስት ገልጿል።
የቤልጂየም መንግስትም እንዲሁ ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቋል። በአዳማ፣ አምቦ፣ አርሲ ነገሌ፣ ድሬዳዋ፣ ሃረር፣ ሻሸመኔ እና ወሊሶ እንዲሁም ሞጆ እና ሃዋሳ ፣ በጅማና አዲስ አበባ እና ሌሎችም አካባቢዎች ሲደረጉ ተቃውሞዎች ሲደረጉ እንደነበር በማስታወስ ዜጎቹ እንቅስቃሴያቸውን እንዲገቱ መክሯል።
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010)በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉት ዜጎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን መንግስት አስታወቀ። ከተፈናቀሉት ውስጥ ከ100 የሚበልጡ እናቶች ድንኳን ውስጥ ልጆቻቸውን መገላገላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ይፋ አድርገዋል። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም በችግሩ ሳቢያ የአንዱ ክልል ተማሪ ወደ ሌላው ክልል ዩኒቨርስቲ ሄዶ ለመማር እንደማይፈልግም ተመልክቷል። የመንግስት ቃልአቀባይ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ማክሰኞ ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራ የልኡካን ቡድን ተፈናቃዮቹን ለመጎብኘት በድሬደዋና በሀረር በተንቀሳቀሰበት ወቅት የችግሩን ስፋት መረዳቱን ገልጸዋል። በግጭቱና በተከተለው መፈናቀል ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር መለያየታቸውንና

በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ። አዋጁ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ፖልሲን ይቃርናል ተብሏል።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ። አዋጁ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ፖልሲን ይቃርናል ተብሏል። በወረቀት ላይ የሰፈረው ፖሊሲ በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ የሚኖር የምልመላና የእድገት ስራ በግለሰቡ ብቃት ላይና በዚሁ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያዛል። አሁን ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ደግሞ ከዚህ በተለየ መልኩ በፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የሚደረገው የስራ ቅጥር የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ እንዲሆን የሚያስገድድ ነው። ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ሊኢሳት አስተያየታቸውን የሰጡ የዘርፉ ሙያተኞች አሁን የቀረበው ህግ የፊዴራል የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲን የሚጥስ እንደሆነ ገልጸዋል። በወረቀት ላይ ከሰፈረውና በግለሰቡ ብቃት ላይ ተመስርቶ ይካሄድ ከሚለው ፖሊሲ ጋር በፍጹም የማይገናኝ ነው ይላሉ አስተያየት ሰጭዎቹ። በአሁኑ ሰዓት ይህንን መሰረታዊ መርሆ ለመጣስ የተፈለገው ሲቪል ሰርቪሱን በፖለቲካዊ አቋማቸው የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑትን ለመሙላትና የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆችን ለመጉዳት እንደሆነ አስታውቀዋል። የብሔረሰቦችን ተዋጽኦ መሰረት ያደረገ የስራ ቅጥር እንዲካሄድ የሚያስገድደው ረቂቅ አዋጅ በሃላፊነት ቦታዎች ስለሚኖረው የብሔረሰብ ስብጥር ግን ያነሳው ነገር የለም። ረቂቅ አዋጁ ከዚህም ሌላ በሙስናና በአስገድዶ መድፈር ተሳታፊ ሆነው የተገኙና የተፈረደባቸው ግለሰቦች በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች እንዳይቀጠሩ የሚያስገድድ ሀሳብንም አካቷል ። በሙስና፣በእምነት ማጉደል፣በስርቆት፣በአስገድዶ መድፈር፣በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ የተፈረደበት ግለሰብ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ እንዳይሰራ የሚከለክለው ይህው ረቂቅ አዋጅ በመንግስት መስሪያ ቤቶች የብሔረሰብ ተዋጽኦን ለማመጣጠን በሚደረገው ሒደት አነስተኛ ውክልና ያላቸውን በልዩ ድጋፍ ቁጥራቸውን ስለመጨመር ይዘረዝራል። ባለፈው ሳምንት ለፓርላማ የቀረበው ይህው የፌደራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ለሴት ሰራተኞች በወሊድ ጊዜ ይሰጥ የነበረውን የሶስት ወራት ግዜ ወደ አራት ከፍ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ መራዘሙ ተነገረ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በኢትዮጵያ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ለ2ተኛ ጊዜ ሕገመንግስቱን በመጣስ መራዘሙ ተነገረ። የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተወሰነው በሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ነው ተብሏል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የሕዝብ ቆጠራው እንዲራዘም የተፈለገው ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄዱ ሌላ ቀውስ ይፈጥራል በሚል ነው። ከሶስት ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተመድቦለት በህዳር 2010 ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ሀገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ማካሄድ እንደማይቻልና ህገ መንግስቱን መጣስ አማራጭ የሌለው መሆኑን የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ መወሰኑን የኢሳት የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። የአመቱን የመንግስትና የድርጅት እቅድ ለማውጣት በመቀሌ ተሰብስቦ የነበረው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን፣ኦህዴድና ደኢሕዴን ያቀረቡትን አስተያየት ከግምት በመውሰድ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የአመቱን የመንግስት ስራዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በሚያቀርቡበት ሰአት የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላይ ትኩረት እንዳይሰጡ ትእዛዝ በመተላለፉ ህገ

በኬንያ አንድ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን በደረሰባቸው የግድያ ዛቻ ምክንያት ወደ አሜሪካ መኮብለላቸው ተሰማ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 8/2010) በኬንያ አንድ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን በደረሰባቸው የግድያ ዛቻ ምክንያት ወደ አሜሪካ መኮብለላቸው ተሰማ። የከፍተኛ ባለስልጣኗ ከሀገር መኮብለል በድጋሚ በሀገሪቱ ሊካሄድ በዝግጅት ላይ ያለውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተአማኒነትን ጥርጣሬ ውስጥ መክተቱ ታውቋል። በሌላ ዜና በላይቤሪያ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ በቂ ድምጽ ማግኘት አልቻሉም በሚል ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ተወስኗል። በኬንያ የሚካሄደው የድጋሚ ምርጫ በሚቀጥለው ሳምንት ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት አንድ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ከፍተኛ አባል በደረሰባቸው የግድያ ዛቻ ምክንያት ወደ አሜሪካ ሸሽተዋል። ሮዝሊን አኮሞቤ ከኒዮርክ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የምርጫ ኮሚሽኑ የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱንና ምንም አይነት ውሳኔ መወሰን የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል። በሳቸው ላይ የግድያ ዛቻ እየተደረገ ባለበትና ባላፈው ነሀሴ የምርጫ ኮሚሽኑ የኢንፎርሜሽኝ ቴክኖሎጂ ሃላፊው በተገደሉበት ሁኔታ ውስጥ በሀገር ውስጥ መቆየታቸው በራሳቸው ሕይወት ላይ እንደመፍረድ የሚቆጠር ነው ብለዋል። በሀገሬ እየኖርኩ እንዲህ አይነት ፍርሃት ተሰምቶኝ አያውቅም ሲሉ አክለዋል። የምርጫ ኮሚሽኑ ወይዘሮዋ ከስራቸው በመልቀቃቸው ሀዘን ተሰምቶኛል ሲል የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ደግሞ

Ethiopia: Spread of HIV/AIDS reaches epidemic levels

ESAT News (October 18, 2017)
The spread of HIV in Ethiopia has reached epidemic levels as 27,000 people are infected with the virus every year, according to a conference organized to discuss the status of HIV/AIDS in the country.
19,000 people die of AIDS every year in Ethiopia with percentage of infections in some areas reaching 25%. Nationwide, 1.8 percent of people are infected with the virus, the conference disclosed.
Experts say the newly released figures show that the spread of HIV has reached epidemic levels in Ethiopia as per the guidelines set by WHO.
The country made great strides in containing the spread of the virus five years ago with new infections reduced by 90% and death from the disease by 70%. However, new infections has increased alarmingly in the last five years.

Two killed as protests continue in Ethiopia

ESAT News (October 18, 2017)
At least two people were killed as security forces fired shots into protesters in a village near Fiche town, 53 miles outside the capital Addis Ababa.
The anti-government protesters responded with setting government vehicles on fire. Four vehicles were set ablaze in Gebregurecha.
Protests continued in Melketuri, Gebreguracha, Ejerie, Chanco, Bedelle, Metu as well as in towns in West and East Wollega.
In Chancho, businesses and offices were closed as residents gathered for a funeral of a man who was killed by security forces yesterday.
Over a dozen people were killed since protests resumed last week in the country’s Oromo region.

በገብረጉራቻ ተቃውሞው ተባብሷል

በገብረጉራቻ ተቃውሞው ተባብሷል:: ማምሻውን ገብረጉራቻ አንዳንዳድ ክፍሎች እሳት ተነስቷል:: በርካታ ቤቶች እየተቃጠሉ ነው:: የመንግስት ተሽከርካሪዎች እየተለዩ በመቃጠል ላይ ናቸው:: ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል:: ዝርዝሩን እናቀርባለን:: ኢሳት

Image may contain: fire and outdoorImage may contain: sky, cloud, mountain, outdoor and nature

‪U.S. Embassy statement on the current protests in

 The United States sees peaceful demonstrations as a legitimate means of expression and political participation. We note with appreciation a number of recent events during which demonstrators expressed themselves peacefully, and during which security forces exercised restraint in allowing them to do so.   ‬

‹ኢህአዴግ ለሁለት የመሰንጠቁ ነገር አይቀርለትም› – አቶ በረከት ስምዖን

ዋዜማ ራዲዮ- አቶ በረከት ስምዖን የስልጣን መልቀቂያ ከማቅረባቸው ባሻገር ስለ ኢህአዴግ “መሰንጠቅና”  ስለ “ርዕዮት አለም መስመር አለመታመን” በአደባባይ እየተናገሩ ነው።
አቶ በረከት የፓርቲያቸውን ከፍተኛ ካድሬዎች ማጥመቂያ በሆነው ስልጠና ላይ እየሰጡ የነበረው አስተያየት መደናገርና ጥያቄ አጭሯል። በውስጣዊ ቀውስ የሚታመሰው ኢህአዴግ በአቶ በረከት የስልጣን መልቀቂያ ሳቢያ ወደ አዲስ ትርምስ መግባቱ እየተነገረ ነው።
ላለፉት ወራት በዙር ሲሰጥ የነበረውን  የፖለቲካ ትምህርት ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን የጠራ ርዕዮተ ዓለም ለማስታጠቅ የሚጠቀምበት ነው፡፡ ኾኖም ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ ባለፉት አራት ዓመታት ስልጠናው በሙሉ አቅም መሰጠቱን አቁሞ ነበር፡፡ ዘንድሮም ቢሆን አገሪቱ በወቅታዊው ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውስጥ ተዘፍቃ ባለችበት ወቅት ይህ ፖለቲካዊ ስልጠናው መሰጠቱ ስልጣኞቹ

Monday, October 16, 2017

I may be freed but my country is in prison: Temesgen Desalegn Released from prison, Temesgen Desalegn hugs his mom on Sunday.

ESAT News (October 16, 2017)

Temesgen Desalegn, a prominent journalist released on Sunday after three years in jail, said he may be out of prison but his country is not. He said he still feels that he is not free.
Speaking to ESAT from Addis Ababa, Temesgen said he was held in a dark cell for two years.
Temesgen was due to be released last Friday but authorities refused to release him despite completing his three year sentence without parole.

የነ ዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቆች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 6/2010)የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለተከሳሾች የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር ሊደርሳቸው ይገባል በሚል የነ ዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቆች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ። ከጥቅምት 23 ጀምሮም የአቃቤ ህግ ምስክሮች መደመጥ እንደሚጀምሩ ታውቋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 30 2009 በዋለው ችሎት ላይ የእነ ዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቆች የአቃቢ ህግ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለተከሳሾች ሊደርሳቸው እንደሚገባ ጥያቄ አቅርበው ነበር። ይህንን ጥያቄ ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾቹ የምስክሮች ስም ዝርዝር ሊደርሳቸው ይገባል አይገባም የሚለውን ለመወሰን የህገ መንግስት ትርጉም ለሚሰጥበት የፌዴሬሽን ምክር ቤት መላኩን ተከትሎ የምክር ቤቱ ውሳኔ በዛሬው ችሎት ተደምጧል። የፌዴሬሽን ምክርቤት ለፍርድ ቤቱ በላከው ውሳኔ መሰረት የምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ስም ዝርዝራቸው ለተከሳሾች እንዲደርስ አለመደረጉ ከህገመንግስቱ ጋር እንደማይጋጭ አስታውቋል። ይህን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ተከትሎ የከፍተኛው ፍርድቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የእነ ዶክተር መረራ ጉዲና የፍርድ ሂደት የምስክሮች ዝርዝር ሳይገለጽ እንዲቀጥል ወስኗል። ከጥቅምት 24/2010 ጀምሮ ምስክሮችን ለማዳመጥም ቀጠሮ ይዟል። በእለቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ የተጠየቁት ዶክተር መረራ ጉዲና የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈጸምኩም፣ጥፋተኛም አይደለሁም ብለዋል። የዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቆች በበኩላቸው በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔም ሆነ ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል። ህገ መንግስቱን እንዲተረጉም የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሁሉም ክልል ፕሬዝዳንቶችን፣የተመረጡ የክልል ምክር ቤት አባላቶችንና ሌሎች አስፈጻሚ አካላትን የያዘ የፖለቲካ ሃይል መሆኑ የሚታወቅ ነው።

እኔ ብፈታም ሀገሪቱ ግን እስር ቤት ውስጥ ናት ሲል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ገለጸ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 6/2010) እኔ ብፈታም ሀገሪቱ ግን እስር ቤት ውስጥ ናት ሲል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ገለጸ። በሶስት ዓመት የእስር ቤት ቆይታው ስለኢትዮጵያ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳላገኘ ጋዜጠኛ ተመስገን ከኢሳት ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል። ትላንት ከእስር የተለቀቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በእስር ቤት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሌላ የሚፈቀድ ሚዲያ ባለመኖሩ በሀገሪቱ ስለተከሰቱ ነገሮች መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ተናግሯል። ጋዜጠኛ ተመስገን በቀጣይም ህክምናው ላይ እንደሚያተኩር አስታውቋል። በሶስት ዓመታት 41 ክሶች ቀርበውበታል። ከዛ በኋላም ክሶቹ መቆሚያ አልነበራቸውም። ለመጀመሪያ ጊዜ በ3ክሶች ፋይል እንደተከፈተበት የሰማው በሬዲዮ ነው። በ2004 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ፍትህ የተሰኘው ጋዜጣ ሲዘጋና ከ30ሺህ ኮፒዎች በላይ በፖሊስ ሲወሰድ ጀምሮ ፍርድ ቤት በመመላለስ ለሁለት ዓመታት ያህል ቆይቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት በድርጅታቸውና በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይሁንታ መሆኑን ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 6/2010) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት በድርጅታቸውና በጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይሁንታ መሆኑን ገለጹ። የትልቅ ስልጣን ባለቤት ሆኜ የሕዝቤና የድርጅቴ ጥቅም ሲነካ ማየቱ ተገቢ ባለመሆኑ ርምጃውን ወስጃለሁ ሲሉ ለኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን ገልጸዋል። የስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ከአንድ ሳምንት በፊት ያረጋገጡትና አሁንም በሃላፊነታቸው ላይ የሚገኙት አቶ አባዱላ ገመዳ ስልጣን ለመልቀቅ የተገደዱበትን ምክንያት መልቀቂያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ እንደሚናገሩ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። አሁንም መልቀቂያቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ለኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን ምክንያታቸውን ተናግረዋል። የድርጅታችንንና የሕዝቡን መብትና ክብር የሚያጓድል ነገር እያዩ ያንን ተሸክሞ ከመቀጠል ከስልጣን በመልቀቅ ነገሩን ለማስተካከል መስራት ይገባል በሚል መልቀቂያ ማቅረባቸውን አቶ አባዱላ ገመዳ ተናግረዋል። ይህም በድርጅቱ ኢህአዴግና በድርጅቱ ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይሁንታ የቀረበ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ መሆኑን አብራርተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ለኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን በሳምንቱ መጨረሻ በኦሮምኛ ቋንቋ በሰጡት በዚህ ማብራሪያ በሀገር ውስጥና በውጭ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ አንድነት ወደ ኢኮኖሚ ልማት መለወጥ እንደሚገባም በቃለምልልሱ ወቅት አንስተዋል። ቀሪ ጊዜያቸውን ከኦህዴድና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር እንደሚሰሩም ጠቁመዋል። በኦሮሚያ ክልል ያለው የሰላም እጦት የክልሉን መንግስት አቅም ያዳክማል በማለት የተናገሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባም መክረዋል።

አቶ በረከት ስምኦን የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸው ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 6/2010)ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነት እንዲነሱ የተወሰነባቸው አቶ በረከት ስምኦን የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸው ተሰማ። ላለፉት ሰባት አመታት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሲሰሩ የነበሩት አቶ በረከት ስምኦን የፖሊሲ ምርምርና ጥናት ማዕከል በተባለው ተቋም የአቶ አባይ ጸሀዬ ምክትል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው አቶ በረከት ስምኦን የስራ መልቀቂያ ያቀረቡት ይሰሩበት ከነበረው የፖሊሲ ምርምርና ጥናት ማዕከል ነው። እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ሀሙስ በስራቸው ላይ እንደነበሩ የተገለጸው አቶ በረከት ስምኦን የስራ መልቀቂያቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ማቅረባቸው ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነቱንም ለሌላው የብአዴን አባል ዶክተር ይናገር ደሴ እንዲያስረክቡ የተወሰነባቸው አቶ በረከት ስምኦን የስንብት ደብዳቤው የደረሳቸው ከመንግስት የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ከዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል እንደሆነም ተመልክቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ መልቀቂያ ባቀረቡ ማግስት የአቶ በረከት መልቀቂያ መከተሉ በኢህአዴግ ውስጥ ቡድናዊ እንቅስቃሴ ለመኖሩ አመላካች እንደሆነ የሚገልጹት የፖለቲካ ተንታኞች በቀጣይ ተጨማሪ ርምጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ ሲሉም ያላቸውን ግምት አስቀምጠዋል።

Ethiopia: Bereket Simon submits resignation Bereket Simon

ESAT News (October 16, 2017)

Bereket Simon, a high ranking political figure with the ruling EPRDF, has submitted his resignation from his position as chair of the Ethiopian Economic Policy Research Institute, according a report by the BBC Amharic.
The report said Mr. Simon submitted his resignation to the Prime Minister, Hailemariam Desalegn.

ሰበር ዜና ኢሳት በአረብ ሳት ወደ አየር ተመልሷል።

ኢሳት በአረብ ሳት ወደ አየር ተመልሷል።
ዝርዝር መረጃዎች
Satellite : Arabsat Badr6
Position : 26°E
Transponder : 2
Downlink Polarisation : Vertical
Downlink Frequency : 11747 MHz
Modulation : DVB-S
Symbol rate 27500 and Dec 3/4

ESAT is now on air via Arabsat.

ESAT is now on air via Arabsat.
Satellite : Arabsat Badr6
Position : 26°E
Transponder : 2
Downlink Polarisation : Vertical
Downlink Frequency : 11747 MHz
Modulation : DVB-S

ተቃውሞው ቀጥሎአል።

ተቃውሞው ቀጥሎአል። በመቱ ኦሮሞው፣ አማራው፣ ጉራጌውና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች “ወያኔ በቃን፣ ለውጥ እንፈልጋለን፣ አንከፋፈልም” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ቅዳሜ የጀመሩትን ተቃውሞ ለ3ኛ ቀን ቀጥለዋል።
የመንግስት ሰራተኞች ፣ ፖሊሶችና የአካባቢው ባለስልጣናትም በተቃውሞው እየተሳተፉ ነው።

Thursday, October 12, 2017

Ethiopia: Unrest continues in Oromo region, six killed in Borena

ESAT News (October 12, 2017)
Security forces opened fire and killed six people in Borena, south Ethiopia, while 20 others were seriously injured as anti-government protests that began yesterday in the Oromo region continued today in various towns across the region.
Witnesses told ESAT that a convoy of soldiers heading to the Somali region was confronted by residents of Dire district in Borena who believed that the soldiers were carrying weapons that would be used to kill Oromos in the Somali region.
As residents blocked the progress of the convoy, the soldiers opened fire and killed six people while 20 others were injured. Several roads in Yabelo, Moyale and other towns were blocked following the attack.

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ሶዳ ከተማ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ ስድስት ሰዎች ተገደሉ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ሶዳ ከተማ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ ስድስት ሰዎች ተገደሉ። ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል። መሳሪያ ጭነው ወደሶማሌ ክልል እያጓጓዙ ነው ተብለው በነዋሪው መንገድ የተዘጋባቸው ስምንት የመከላከያ ተሽከርካሪዎች ላይ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝቡ ላይ ተኩስ መክፈታቸውንም ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ማምሻውን በሶዳ ሜጋ ያቤሎ፣ ዱብሉቅና ሞያሌ መንገዶች መዘጋታቸው የተገለጸ ሲሆን መሳሪያ ጭነዋል የተባሉት የመከላከያ ተሽከርካሪዎችም ከሶዳ ከተማ እስከምሽት ድረስ መውጣት እንዳልቻሉ ታውቋል። በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የተነሳው ግጭት ከተከሰተባቸው አከባቢዎች አንዱ በሆነው የቦረና ዞን ዳግም ውጥረት እንዲነግስ ያደረገው የዛሬው ግድያ መነሻው መሳሪያ ጭነዋል የተባሉት የመከላከያ

በሳምንቱ መጨረሻ ከፓርላማ አፈጉባኤነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ያሳወቁት አቶ አባዱላ ገመዳ አሁንም በአፈጉባኤነታቸው መቀጠላቸው ታወቀ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) በሳምንቱ መጨረሻ ከፓርላማ አፈጉባኤነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ያሳወቁት አቶ አባዱላ ገመዳ አሁንም በአፈጉባኤነታቸው መቀጠላቸው ታወቀ። ዛሬ ጥቅምት 2/2010 የተሰየመውን ፓርላማ በአፈጉባኤነት መምራታቸውም ታውቋል። አቶ አባዱላ ገመዳ በመሩት በዛሬው ስብሰባ ልዩ ልዩ አዋጆች ቀርበው ጸድቀዋል። ፓርላማው ሰኞ ዕለት ስራ ሲጀምር በስብሰባው ማጠቃለያ ከመድረክ ጀርባ የምስጋናና የስንብት አሸኛኘት ከፓርላማ አባላትና ከሃይማኖት አባቶች እንደጠበቃቸው የተገለጸው አቶ አባዱላ ገመዳ ተመልሰው በፓርላማ ወንበራቸው መቀጠላቸው ግልጽ አልሆነም። አቶ አባዱላ በመንበራቸው ላይ የቀጠሉት ለጊዜው ይሁን ለዘለቄታው ስለመሆኑ የታወቀ ነገር የለም። በስራቸው ላይ የቀጠሉት በማግባባት ይሁን በማስገደድ ይህም ግልጽ አልሆነም። አቶ አባዱላ ገመዳ መልቀቂያ ለማን እንዳቀረቡ አሁንም ግልጽ

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር ግፊት የሚያደርገው ኤች አር 128 በኮንግረስ ድምጽ እንዳይሰጥበት ያዘገየው በአሜሪካ ምክር ቤት የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መሆኑ ተጠቆመ።

(ኢሳት ዜና –ጥቅምት 2/2010) በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር ግፊት የሚያደርገው ኤች አር 128 በኮንግረስ ድምጽ እንዳይሰጥበት ያዘገየው በአሜሪካ ምክር ቤት የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መሆኑ ተጠቆመ። የቋሚ ኮሚቴው ስብሳቢ ማክ ቶርንቨሪ በምክር ቤቱ አብላጫ ድምጽ ላለው ሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ኬቨን ማካርቲ በረቂቅ ሕጉ ላይ የ30 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው የድምጽ አሰጣጥ ስነስርአቱ እንደዘገየ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትዎርክ ስብሳቢ ዶክተር አርአያ አምሳሉ ገልጸዋል። እንደ ዶክተር አርአያ ገለጻ የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኤች አር 128 እንዲዘገይ የፈለገው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ በጸረ ሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያቆምበመግለጹ ነው። ይህም ቢሆን ግን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ወደ ኮንግረስ አባላት ስልክ በመደወል ረቂቅ ሕጉ እንዲጸድቅ ግፊታቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ዶክተር አርአያ ጥሪ አቅርበዋል። ኤች አር 128

በወሊሶ ከተማ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) በወሊሶ ከተማ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። ትላንት በሻሸመኔ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ያስቆጣቸው የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የህወሀት መንግስት በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድ ጠይቀዋል። ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ ተጠቅሞ ሊበትን መሞከሩ ተገልጿል። በሌላ በኩል በቱሉቦሎና በሱሉልታም ተመሳሳይ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉት ዜጎች በችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው። ዘግይተው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዛሬም በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። ትላንት አምቦ፣ ሻሸመኔን፣ አዳባንና ኮፈሌን ጨምሮ በሀረርጌ የተለያዩ ከተሞችን ያዳረሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም በሌሎች ከተሞች በመካሄድ ቀጥሏል። ወሊሶ፣ ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፣ ቄሌም ወለጋ፣ አጋርፋ ፣ቱሉ ቦሎ፣ ሱሉልታ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጎባቸው ውለዋል። ትላንት ስምንት ሰዎች የተገደለባት ሻሸመኔ ዛሬም መረጋጋት እንደሌለ የተነገረ ሲሆን ተቃውሞ ቀጥሎ መዋሉን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመንግስት ሃይል ወደሻሸመኔ መግባቱንም ለማወቅ ተችሏል።

ከአዲስ አበባ ከተማ ተነስቶ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይበር የነበረ ቦይንግ 777 የበረራ ቁጥር 500 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) ከአዲስ አበባ ከተማ ተነስቶ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይበር የነበረ ቦይንግ 777 የበረራ ቁጥር 500 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ። የአየር መንገዱ ምንጮች እንደገለጹት ዋሽንግተን ዲሲ ጥቅምት 1/2010 ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ40 ደቂቃ መድረስ የነበረበት አውሮፕላን እስከ ከሰአት 7 ሰአት ከ22 ድረስ መዘግየቱም ታውቋል። ማክሰኞ ምሽት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው የበረራ ቁጥር 500 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ደብሊን አየርላንድ ነዳጅ ለመሙላት ያደረገው ጉዞ በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የተካሄደ ነበር። ነገር ግን ከደብሊን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሲጓዝ አንድ መንገደኛ አውሮፕላኑ ወስጥ ሕይወታቸው በማለፉ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ በካናዳ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰአት ከ55 ደቂቃ አርፏል። እስከ ቀትር 6 ሰአት ከ15 በዚያው አውሮፕላን ማረፊያ ቆይታ አድርጎ ከ1 ሰአት 5 ደቂቃ በረራ በኋላ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መድረሱ ታውቋል። የበረራ ቁጥር 500 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መስመሩን ለመቀየር ምክንያት የሆነውና ካናዳ ለማረፍ የተገደደው አንዲት ናይጄሪያዊት ተሳፋሪ በመታመማቸውና በኋላም ህይወታቸው በማለፉ እንደሆነ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ የሲቪክ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ለሽግግር የሚረዳ የውይይት ሰነድ በጋራ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ የሲቪክ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ለሽግግር የሚረዳ የውይይት ሰነድ በጋራ ማዘጋጀታቸውን ገለጹ። ለፖለቲካ ሃይሎችም ጥሪ አቅርበዋል። በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ መስከረም 27ና 28/2010 ለሁለት ቀናት በተካሄደው የውውይት መድረክ ላይ የተሳተፉት የሲቪክ ድርጅቶች በጉባኤው ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳሳቢና ትኩረት የሚሻ መሆኑን አስገንዝበዋል። በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያና በአማራ እንዲሁም በደቡብ ክልል ኮንሶ በአጠቃላይ ወደ አንድ ሺ ዜጎች የተጨፈጨፉበትን አሳዛኝ ድርጊት በማስታወስ አውግዟል። በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች የሚካሄደውንም ግጭት በሀገሪቱ የተዘረጋው ብሔረሰብን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝም ውጤት ነው በማለትም አጠቃላይ ለችግሩ መፍትሔ ፍለጋ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርቧል። በጉባኤው ላልተሳተፉ የሲቪክ ድርጅቶችም ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ ስርአት እንዲሻገር ለሚደረገው ጥረት የሽግግሩን ሒደት የሚያግዝ የውይይት ሰነድ ማዘጋጀቱንም የማህበረሰባዊ ድርጅቶቹ ጉባኤ አስታዉቋል። ለኢትዮጵያ ሕልውና ቀጣይነት እንዲሁም ለሉአላዊነቷ መከበር የዜጎቿ አንድነት፣የሕግ የበላይነት፣ዲሞክራሲና እኩልነት መከበርና መጠበቅ እንዳለባቸው ጉባኤው መስማማቱ ተመልክቷል።

Ethiopia: Oromo region rocked with renewed protests, four killed in Shashemene

ESAT News (October 11, 2017)
Protesters took to the streets in Ambo, Shashemene, Wollega, Hararghe, Adaba and other towns in the Oromo region denouncing the regime and demanding for the release of political prisoners. Four people were reportedly killed when security forces used lethal force to disperse protesters in Shashemene. At least twenty were injured.
What triggered the renewed protests in the Oromo region today was not clear, but protesters were chanting slogans demanding the removal of the TPLF regime.
Residents of several towns in Hararghe took part in the protest demonstrations. Several people were injured as security forces disperse crowds.
It was the first massive protest in the region after security forces killed hundreds of people in protests last summer in the Oromo and Amhara regions.

Ethiopia: Nine killed in clashes between Afaris and Tigray security forces

ESAT News (October 11, 2017)
Nine people were killed in clashes between the Afaris and security forces of the Tigray region in an area called Danti in Megalle district on the border between the two regions.
Six people were killed and nine others wounded on the Tigray side while three were killed and three others injured on the Afari side, according to the president of the Afar Human Rights Organization, Gaas Ahmed.
Ahmed told ESAT that the fighting was sparked when an Afari father retaliated the killing of his two children by the Tigray side.

በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ። ሶስት ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውም ታውቋል።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010)በበርካታ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ። ሶስት ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸውም ታውቋል። በአምቦ፣ ሻሸመኔ፣ ነቀምት፣ አዳባ፣ ኮፈሌና በሀረርጌ የተካሄዱት ሰልፎች የስርዓት ለውጥ በሚጠይቁ መፈክሮች የታጀቡ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቀው ህዝብ የህወሀት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድ በከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መጠየቁንም ለማወቅ ተችሏል። የሻሸመኔው ተቃውሞ ከበድ ያለ፡ እንደወትሮውም የመንግስት ታጣቂዎች ጭካኔ የታየበት ነበር። ሻሸመኔ በዛሬው ተቃውሞ በከፍተኛ የህዝብ ብዛት መንገዶቿ ተጥለቅልቀው መዋላቸው ታውቋል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማምሻው ድረስ በዘለቀው በዚሁ የሻሸመኔ ተቃውሞ ጸረ ህወሀት መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተኩስ መክፈታቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። እስካሁን ባለው መረጃ በሻሸመኔ የመንግስት ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ20 የማያንሱ ተማሪዎች መጎዳታቸው ታውቋል። ከተለያዩ አካባቢዎች ወደሻሸመኔ የሚያስገቡና የሚያስወጡ መንገዶች ተዘግተው የዋሉ ሲሆን ከሀዋሳ ወደ ሻሸመኔ ሲያቀኑ የነበሩ ተሽከርካሪዎች እንዲመለሱ መደርጋቸውም ተገልጿል። በአምቦ ዛሬ ቤቱ የቀረ ነዋሪ

በአፋር አርብቶ አደሮችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010) በአፋር አርብቶ አደሮችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል በተፈጠረ ግጭት በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ። የአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት ለኢሳት እንዳስታወቀው በመጋሌ ወረዳ ዳንቲ በተባለ አካባቢ ከትላንት ጠዋት ጀምሮ በሁለቱ ወገኖች በጦር መሳሪያ የታገዘ ውጊያ እየተደረገ ነው። የትግራይ ልዩ ሃይል የፈጸመው ድንገተኛ ወረራ ለግጭቱ መንስዔ መሆኑን የሚገልጸው የአፋር የሰብዓዊ መብት ድርጅት በግጭቱ ከልዩ ሃይሉ ስድስት፡ ከአፋር ደግሞ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል። ከተገደሉት ስድስቱ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት አንደኛው የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆኑን በኪሱ በተገኘ መታወቂያ መረጋገጡንም ገልጿል። ከሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ከሚገኘው ከኢሳ ጎሳ ጋር ግጭት መፈጠሩም ታውቋል። በአፋር ክልል በሶስት ግንባሮች ግጭት ተከስቷል። በገዋኔ ወረዳ ከኢሳ ጎሳ፣ በጭፍራ ወረዳ ከአማራ፣ በመጋሌ ወርዳ ደግሞ ከትግራይ ልዩ ሃይል ጋር። የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ፕሬዝዳንት አቶ ገአስ አህመድ ለኢሳት እንደገለጹት የአፋር ህዝብ በታሪኩ እንደዚህ ተደጋጋሚና የማያባራ ግጭት ውስጥ ገብቶ አያውቅም። የትግራይን መስፋፋት መነሻ ያደረገው የህወሀት መንግስት ወረራ ከአፋር ክልል መሬቶችን

በህወሀትና ብአዴን የተዘጋጀውንና ቅማንትን በአዲስ አስተዳደር ለመከለል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ የፌደሬሽን ምክር ቤት ማጽደቁ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 1/2010) በህወሀትና ብአዴን የተዘጋጀውንና ቅማንትን በአዲስ አስተዳደር ለመከለል የተካሄደውን ህዝበ ውሳኔ የፌደሬሽን ምክር ቤት ማጽደቁ ተሰማ። ያለህዝበ ውሳኔ በህወሀት ቀድመው የተካለሉት የ42 ቀበሌዎች ጉዳይ አሁንም የህዝብ ጥያቄ ማስነሳቱ ታውቋል። የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ያጸደቀበት ምክንያት ያለህዝብ ፍቃድ የተካለሉትን 42 ቀበሌዎች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የጎንደርን ህዝብ ለመከፋፈል የሚደረገውን የስርዓቱን ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ህዝቡ በንቃት እየተከታተለ እንዲታገለው የጎንደር ህብረት ጥሪ አድርጓል። መስከረም 7/2010 ህወሃት የፈለገውና የፈቀደው ሕዝበ ውሳኔ ሲካሄድ ውጤቱ ቀድሞም ይታወቅ ነበር። ለዘመናት ሳይለያዩ የኖሩትን የጎንደርና የቅማንት ማህበረሰብ በአስተዳደር ወሰን ለይቶ ለማካለል በሚል የልዩነት ምርጫ ይዞ የመጣው የህወሃት መንግስት

Tuesday, October 10, 2017

የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን በትግራይ ክልል ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስረከቡ ተሰማ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010) የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ደኢህዴን በትግራይ ክልል ትምህርት ቤት አስገንብቶ ማስረከቡ ተሰማ። ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 12 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉም ታውቋል። በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበርነት የሚመራው የደቡብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ንቅናቄ/ደኢህዴን የተመሰረተበት ጊዜና ቦታ በፓርቲው እራሱ ስምምነት ያለ አይመስልም። አንዴ ከደርግ ውድቀት በፊት የስምጥ ሸለቆ ንቅናቄ በሚል ደቡብ ውስጥ ተመሰረተ።ሌላ ጊዜ ደግሞ በትግራይ ክልል ተቋቋመ በሚል የተምታታ ታሪክ ነው የሚነገረው። ተመሰረተ የሚባልበት ጊዜ እራሱ በውል አይታወቅም። ሲያሻቸው በ1985 ሲፈልጉ ደግሞ ሕገመንግስቱ በጸደቀበት 1987 ተመሰረተ በሚል

በአማሮ ወረዳ የተጀመረው ግጭት የንጹሃንን ህይወት እያስከፈለ ቀጥሎአል

በአማሮ ወረዳ የተጀመረው ግጭት የንጹሃንን ህይወት እያስከፈለ ቀጥሎአል
የኦሮምያና ደቡብ ድንበርን እናካልላለን በሚል ባለስልጣናት ያስነሱት ግጭት ባለመብረዱ የአካባቢው ህዝብ በከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቋል። የኮሬ እና የጉጂ፣ የቡርጂና የጉጂ ማህበረሰብ አባላትን እርስ በርስ ለማጋጨትና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የተደረገው ሴራ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

በገዋኔ በሶማሊ ልዩ ሃይልና በአፋር ህዝብ መካከል በተነሳ ግጭት 7 ሰዎች ቆሰሉ

ትናንት በገዋኔ ወረዳ በሮማ ቀበሌ በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት እና በአፋር ህዝብ መካከል በተነሳ ግጭት ከአፋር በኩል 3 ሰዎች ሲቆስሉ ከሶማሌ ልዩ ሃይል በኩል ደግሞ 4 ሰዎች ቆስለዋል። የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት በአካባቢው የሚኖሩ ኢሳዎችን በማበረታታትና ድጋፍ በመስጠት ወረራ ማካሄዳቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የመከላከያ ሰራዊት በመሃል ገብቶ ግጭቱን ለማብረድ ቢችልም፣ በልዩ ሃይሉ ላይ የወሰደው እርምጃ ግን የለም።
በሌላ በኩል በመጋሌ ወረዳ አዲ ቀበሌ ትናንት አንድ የህወሃት ሹም መገደሉን ተከትሎ ፣ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት ከህዝቡ ጋር ተፋጠው እንደሚገኙ ታውቋል። (ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010)

የምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ለመጨመር ጥናት እየተደረገ ነው

በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ አገዛዙ የምንዛሬው ለውጥ ለማድረግ ውሳኔ ካሳለፈ በሁዋላ በነዳጅ የመሸጫ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እየተጠና ነው።
ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ26 ብር ከ93 ሳንቲም ይመነዘራል። እስከዛሬ 23 ብር በመያዝ አንድ ዶላር ይገዛ የነበረ ሰው፣ ከጥቅምት 1 ጀምሮ በ26 ብር ይገዛል። የብር የመግዛት አቅም መዳከም፣ አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ለውጡ የወጭ ንግዱን በማበረታታት የውጭ ምንዛሬ በበቂ ሁኔታ እንዲገኝ ያደርጋል የሚል መግለጫ ሰጥቷል።
የውጭ ምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ጥናቱን አጠናቆ ጨርሷል። (ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010)

የአማራ ልዩ ሃይል በፌደራል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው

በባህርዳር፣ ጎንደርና ሌሎችም በርካታ የሰሜንና ደቡብ፣ የምእራብና ምስራቅ ጎጃም ከተሞች የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ፣ በርካታ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ከህዝብ ጎን ቆመዋል በሚል ልዩ ሃይሉን በፌደራል ደረጃ አዋቅሮ የእዝ ሰንሰለቱም በህወሃት እንዲመራ የሚደረገው ጥረት በልዬ ሃይል አባላት ተቃውሞ አጋጥሞታል።

የምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ለመጨመር ጥናት እየተደረገ ነው

በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የዶላር እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ አገዛዙ የምንዛሬው ለውጥ ለማድረግ ውሳኔ ካሳለፈ በሁዋላ በነዳጅ የመሸጫ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት እየተጠና ነው።
ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ26 ብር ከ93 ሳንቲም ይመነዘራል። እስከዛሬ 23 ብር በመያዝ አንድ ዶላር ይገዛ የነበረ ሰው፣ ከጥቅምት 1 ጀምሮ በ26 ብር ይገዛል። የብር የመግዛት አቅም መዳከም፣ አሁን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ይበልጥ ያባብሰዋል ተብሎ ተሰግቷል። ብሄራዊ ባንክ የምንዛሬ ለውጡ የወጭ ንግዱን በማበረታታት የውጭ ምንዛሬ በበቂ ሁኔታ እንዲገኝ ያደርጋል የሚል መግለጫ ሰጥቷል።
የውጭ ምንዛሬ ለውጡን ተከትሎ በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ለማድረግ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ጥናቱን አጠናቆ ጨርሷል። (ኢሳት ዜና–መስከረም 30/2010)

የአማራ ልዩ ሃይል በፌደራል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ሃሳብ ተቃውሞ ገጠመው

በባህርዳር፣ ጎንደርና ሌሎችም በርካታ የሰሜንና ደቡብ፣ የምእራብና ምስራቅ ጎጃም ከተሞች የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ፣ በርካታ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ከህዝብ ጎን ቆመዋል በሚል ልዩ ሃይሉን በፌደራል ደረጃ አዋቅሮ የእዝ ሰንሰለቱም በህወሃት እንዲመራ የሚደረገው ጥረት በልዬ ሃይል አባላት ተቃውሞ አጋጥሞታል። ሰሞኑን ልዩ ሃይሉ ከክልል እዝ ወጥቶ በፌደራል ደረጃ መዋቀር ይገባዋል የሚል አጀንዳ በጥንቃቄ ለተመረጡ የልዩ ሃይል አዛዦች ለውይይት የቀረበ ቢሆንም፣ ተሰብሳቢዎቹ ግን “ እኛ ከአማራ ፖሊስ ውስጥ ተመልምለን ወደ ልዩ ሃይል ስንገባ የተነገረን በክልሉ ልዩ ሃይል ውስጥ እንድንሰራ ተነግሮን ነው። አሁን በፌደራል ደረጃ ይዋቀር የሚለው ነገር እኛን አይመለከተንም። የስራ ውል የያዝነው ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመሆኑ እቅዱን ለመቀበል ፈቃደኞች አይደለንም” የሚል መልስ በአንድ ድምጽ ሰጥተዋል።
በ2008 ዓም በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ የልዩ ሃይል አ

Monday, October 9, 2017

ባለፉት 3 ቀናት በኢትዮጵያ ሶማሊ እና በኦሮምያ ክልል ድንበር መካከል ያለው ግጭት እና ተቃውሞ ተባብሶ ሲቀጥል የመንግስት ባለስልጣናት ግራ ተጋብተዋል

(ኢሳት )ባለፉት 3 ቀናት በኢትዮጵያ ሶማሊ እና በኦሮምያ ክልል ድንበር መካከል ያለው ግጭት እና ተቃውሞ ተባብሶ ሲቀጥል የመንግስት ባለስልጣናት ግራ ተጋብተዋል
ባለፉት ሶስት ቀናት ምስራቅ ኦሮምያ በተለያዩ ተቃውሞዎች ሲናጥ ሰንብቷል። ተቃውሞዎች በአንድ በኩል የህወሃቶችን አጀንዳ እያስፈጸሙ ነው የሚባሉት የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ባለስልጣናትን በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸሙትን ግድያና ማፈናቀል እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተሻለ አስተዳደርና ፍትህ የሚያመጣ ስርዓት እንዲቋቋም የሚጠይቁ ናቸው።
በምስራቅ ሃረርጌ በጫት ምርታቸው የሚታወቁ ከተሞች እንቅስቃሴያቸው ተቋርጧል

በአማሮ ወረዳ በባለስልጣናት የተነሳው ግጭት ቀጥሎአል

ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘ ከሃምሌ ወር ጀምሮ በኦሮምያና ደቡብ ክልሎች የድንበር ከተሞች መካከል የተነሳው ግጭት እስካሁን አለመቆሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የአካባቢው ባለስልጣናት የሁለቱን አካባቢዎች ድንበር ለመለየት በሄዱበት ወቅት የተፈጠረው ግጭት 100 ሺ የሚሆኑ ዜጎችን ያፈናቀለ ሲሆን፣ ግጭቱን ለመቆጣጠር በሚል የፌደራል ፖሊስ በስፍራው ተሰማርቶ መጠነኛ ሰላም አውርዶ ነበር። ይሁን እንጅ ግጭቱ እንደገና በማገርሸቱ አሁንም ሰዎች እየተገደሉ ነው። ባለፉት ሶስት ቀናት በአማሮ ወረዳ 3 የኮሬ ብሄረሰብ አባላት ሲቆስሉ፣ አንድ የቡርጂ ብሄረሰብ ተወላጅም ተገድሏል። በጉጂ ብሄረሰብ በኩልም 3 ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም ወደ ቦታቸው ባለመመለሳቸው ለከፍተኛ ስቃይ ተዳርገዋል። ከአማሮ ዲላ የሚወስደው መንገድ እንደተከፈተ ተገልጾ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንዲሄዱ ከተገደዱ በሁዋላ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቶባቸዋል። ከቡርጂ ቡሌ ሆራ የሚወስደው መንገድ አሁንም ዝግ እንደሆነ ነው።
የሁለቱም ክልል ነዋሪዎች ወደ ድንበር ማካለል አንገባም የሚል አቋም በመያዙና ችግሩን ራሳችን እንፈታዋልን የሚል አቋም በመያዛቸው የአካባቢው ካድሬዎች ህዝቡን ስብሰባ በመጥራት የድንበር ማካለል እንዲኖር ለማሳመን እየተንቀሳቀሱ ነው።
(ኢሳት ዜና መስከረም 28 ቀን 2010 ዓም)

ለመከላከያ ሰራዊት የተመዘገቡ ወጣቶች በህዝብ ግፊት ሃሳባቸውን መቀየራቸውን አሰታወቁ

በሰሜን ወሎ ሰልጣኝ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ለመመልመል የሚደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ተከትሎ ፣ ካደሬዎችና ደላሎች ቤት ለቤት እየዞሩና በየገበያ ቦታዎች እየተገኙ የመከላከያ አባል ለሚሆኑት መንግስት 3 ሺ ብር እንደሚከፍል ሲቀሰቅሱ ሰንብተው የተወሰኑ ወጣቶችን ለማስመዝገብ ችለው ነበር። ይሁን እንጅ ህብረተሰቡ የተመዘገቡ ወጣቶችን ፈልጎ በማግኘት “ ማንም ልትወጉ ነው ፣ የጎንደር ወንድሞቻችሁን ነው ወይስ ግብር በዝቶብናል ብሎ የሚጨኸውን ነጋዴ ለማፈን” የሚሉ ጥያቄዎችንና ምክሮችን በማቅረብ፣ ወጣቶች ሃሳባቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ መቻሉን የገለጸው ወኪላችን፣ ወጣቶቹ ወደ ሚሊሺያ ጽ/ቤት በመሄድ “ ሃሳባቸውን መቀየራቸውንና ለመሄድ እንደማይፈልጉ” ተናግረዋል። የሚ

በምስራቅ አፍሪካ አድማሱን እያሰፋ የመጣውን የርሃብ አደጋን ለመዋጋት የግብረ ሰናይ ድርጅቶች የጋራ ትብብርብ ያስፈልጋል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ

በኢሊኖ የአየር መዛባት በተከሰተ የርሃብ አደጋ እና በእርስበርስ ጦርነቶች ምክንያት የአያሌ የምስራቅ አፍሪካ ዜጎች የመኖር አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ተመድ አስታውቋል። በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን የሚኖሩ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ አፋጣኝ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 24 ሚሊዮን ዜጎች ይገኛሉ።
በቀጠናው በተከሰተው ድርቅ እና የጸጥታ መደፍረስ ምክንያቶች 15 ሚሊዮን የሚ

የአፈጉባኤነት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመተው መልቀቂያ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸውን ምንጮች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የአፈጉባኤነት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለመተው መልቀቂያ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ መኖሪያቸውን እንዲለቁ መገደዳቸውን ምንጮች ገለጹ። ዛሬ በፓርላማ በመደበኛ ስራቸው ላይ የታዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውንም ትላንት አረጋግጠዋል። ላለፉት አስር አመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤነት የቆዩት አቶ አባዱላ ገመዳ ከኦሮሚያና ከሶማሌው አዋሳኝ ድንበር ግጭት ጋር በተያያዘ የጸጥታ ሃይሉ ሚና እንዳላስደሰታቸውና ስልጣን ለመልቀቅም ምክንያት እንደሆናቸው አዲስ ስታንዳርድ ቢገልጽም እርሳቸው ግን ለዚህ ጉዳይ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ ከመስጠት ተቆጥበዋል። አባዱላ ገመዳ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የፈለጉበትን ምክንያት ግን ወደፊት ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ እንደሚገልጹ ተናግረዋል። መልቀቂያ ማቅረባቸውን ተከትሎ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የያዙትን ቤት እንዲለቁ በማስገደዱ ማክሰኞ ቤቱን ያስረከቡ ቢሆንም ቤት ባለማግኘታቸው ጓደኞቻቸው ጋር ለመጠጋት መገደዳቸውን አዲስ ፎርቹን ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ቅዳሜ እለትም ቦሌ መንገድ አካባቢ ቤት ተከራይተው ወደዚያ መዛወራቸውም ታውቋል። ስልጣን ላይ ያለው ቡድን የስልጣን መልቀቂያቸውን ጥያቄ ሳይቀበልና ስልጣናቸውን ሳይለቁ ቤታቸውን እንዲለቁ ያደረገበት ምክንያት ግልጽ አልሆነም።

የፌደራል መንግስት የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው በሚል ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) የፌደራል መንግስት የኢትዮጵያ ሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በቅርቡ የሰጧቸው መግለጫዎች አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ናቸው በሚል ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠነቀቀ። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በኦሮሚያ ጥቃት ላይ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር የተደረገ የጋራ መግለጫ በሚል ያወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ የሚቃረን ነው። እናም የሚመለከተው አካል ይህንኑ ጉዳይ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ገልጿል። የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በሶማሌ ክልላዊ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና በቢሮ ሃላፊው ላይ ያወጣው መግለጫ መረር ያለ ነው። እንደ መግለጫው መስከረም 23/2010 በሶማሌ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ድረገጽና በቢሮው ሃላፊ የተሰራጨው መረጃ የፌደራል ስርአቱን ከሚያራምድ ማንኛውም አመራር የማይጠበቅ ነው። የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትና የቢሮ ሃላፊው በፌስቡክ ድረገጻቸው ያወጡት መግለጫ አፍራሽና ሕዝብን ጥርጣሬ ውስጥ የሚጥል መረጃን የያዘ ነው ብሏል መግለጫው። ይህ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ መገናኛ ብዙሃን ከእንዲህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ በቅርቡ የሰጡትን

በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው መታገዱ ተሰማ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ መምህራን ለአባይ ግድብ አናዋጣም በማለታቸው ደሞዛቸው መታገዱ ተሰማ። የአባይ ዋንጫ በዙር ጭኮ ወረዳ መግባቱን ተከትሎ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ከደመወዙ ከ300 ብር ጀምሮ እንዲያዋጣ መመሪያ ተወስኖበታል። የሴክተር መስሪያ ቤቶች ያለፈቃዳቸው እንደተስማሙ ተደርጎ የተቆረጠባቸው ሲሆን መምህራን ተቃውሞ በማንሳታቸው የመስከረም ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው አራት ቀናት መቆጠሩን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መምህራኑ ደሞዛችን ካልተከፈለን አንሰራም በማለት ዛሬ ስራ አቁመው መዋላቸው ታውቋል። የአባይ ዋንጫ ሲዳማ ሲደርስ የፈጠረው ስሜት የደስታ አልነበረም። አብሮት የመጣውና የነዋሪውን ኪስ የሚያራቁት መዋጮም ጭምር በመሆኑ አብዛኛው ሰው ቅሬታ እያሰማ ነው። በተደጋጋሚ የአባይ መዋጮ የተሰላቸው ህዝቡ ቀድሞ ያዋጣው ገንዘብ ሳይመለስለት ሌላ ዙር ሲጠየቅ ዝምታን አልመረጠም። በተለይ መምህራን። በሲዳማ ዞን የጭኮ ወረዳ መምህራን ዛሬ ስራ አልገቡም። ደሞዝ ሳይከፈላቸው አራተኛው ቀን አልፏል። ከኑሮ ሽክም መክበድ ጋር ተያይዞ እያንዳንዷን ዕለት ለመሻገር ከባድ የሆነባቸው መምህራን ደሞዝ ሳይከፈላቸው ቀናት ማለፋቸውን በመቃወም ከዛሬ ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን አስታውቀዋል። የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት የጭኮ ወረዳ

ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ እንደሚደረግ ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 29/2010) ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በቅርቡ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ እንደሚደረግ ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ የሚደረገው ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ነው ብለዋል። መንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደገጠመውም ፕሬዝዳንቱ በይፋ ተናግረዋል። እንደ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ገለጻ በኢትዮጵያ ላለፉት 3 አመታት በነበረው የውጭ ምርቶች መላክ መዳከምና ከዚህ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የወጭ ንግድ ሚዛኑ ትልቅ ክፍተት ፈጥሯል። በአሁኑ ጊዜም መንግስት ከፍተኛ የፋይናንስ እጥረት ስለገጠመው የባቡር ሀዲድ፣የዩኒቨርስቲ ግንባታና ሌሎችም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ መሰረተ ልማቶች በዚህ አመት አይካሄዱም ብለዋል። የታክስ አሰባሰብን በተመለከተም በ2009 ከታቀደው በእጅጉ አንሷል ሲሉ የመንግስት የፋይናንስ እጥረት የሚያሳስብ እንደሆነ ገልጸዋል። እናም በዚህ አመት በትላልቆቹ የታክስ ከፋዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ

Cholera hits Dire Dawa, 10 die in Benishangul Gumuz

ESAT News (October 9, 2017)
Cholera is spreading in an alarming rate from Dire Dawa in the east to Benishangul in the west and from the Capital Addis Ababa to the northern city of Mekelle claiming lives along its route.
Reports reaching ESAT from Benishangul Gumuz say 10 people have died due to cholera in Gobela town, Dangul district. The town’s hospital is admitting only people afflicted with cholera. Local authorities say the epidemic is just acute watery diarrhoea while health professionals say it is indeed cholera. No family visitation to the hospital is allowed in a bid to stop the spread of th

Friday, October 6, 2017

ኢትዮጵያ በጀመረችው የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የተደረገው ስምምነት ችግር እየገጠመው መሆኑን ግብጽ አስታወቀች።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) ኢትዮጵያ በጀመረችው የአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ የተደረገው ስምምነት ችግር እየገጠመው መሆኑን ግብጽ አስታወቀች። ግብጽ እንደምትለው የአባይ ግድብን በተመለከተ ከሱዳንና ከኢትዮጵያ ጋር የተካሄደው የሶስትዮሽ ስምምነት በአንዳንድ ምክንያቶች እየተስተጓጎለ ይገኛል። ጉዳዩን ይፋ ያደረጉት የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አጋጠሙ ስላሏቸው ችግሮች ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹኩሪ የሶስትዮሽ ስምምነቱን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅፋት ማጋጠሙን ይናገራሉ። ይህ የሶስትዮሽ ስምምነት የአባይ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ መካከል የተፈጸመ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015

በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አንድ ጄኔራል ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010) በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩ አንድ ጄኔራል ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ ጥገኝነት ጠየቁ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ስርአቱን ከድተው በአሜሪካ የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ የተባሉ ከፍተኛ መኮንን ናቸው። ከወር በፊት በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ አዘጋጅነት በዋሽንግተን በተካሄደ ጸረ አይ ሲስ አለም አቀፍ ዘመቻ ላይ ከተገኙ የኢትዮጵያ ልኡካን አንዱ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው ጥሩነህ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የተመራው ልኡካን ቡድን ወደ ሀገር ቤት ሲመለስ እርሳቸው ከቡድኑ ተለይተው ቀርተዋል። ግሎባል ኮአሊሽን ቱ ዲፊት አይሲስ በተባለውና 72 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው ጥምረት ጉባኤ ላይ ለመገኘት መጥተው ከልኡካኑ ተለይተው የቀሩት ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ ሽፈራው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በወታደራዊ ደህንነት መመሪያ ውስጥ ይሰሩ እንደነበር የተገለጸው ብርጋዴር ጄኔራል መላኩ

)በኢትዮጵያ ባለፉት 26 አመታት የተተገበረው የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ታዋቂው የአለም አቀፍ መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ዘገበ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 26/2010)በኢትዮጵያ ባለፉት 26 አመታት የተተገበረው የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ታዋቂው የአለም አቀፍ መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ዘገበ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን የብሔር ግጭት የዳሰሰው ዘኢኮኖሚስት የክልል መንግስታት በፌደራል መንግስት ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቢሆንም ከእጅ እያመለጡ ናቸው ብሏል። እናም የሕዝቡን አንድነት በማዳከም የጎሳ ፖለቲካን ሲያራምድ የቆየው የኢትዮጵያው አገዛዝ የማይወጣው ችግር ውስጥ እያስገባው መሆኑን ዘ ኢኮኖሚስት በሀተታው ዘርዝሯል። የዘ ኢኮኖሚስት ዘገባ በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል የተከሰተውን ደም አፋሳሽ ግጭት መነሻ አድርጎ በኢትዮጵያ ያለው የጎሳ ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ዘግቧል። የሀረር ከተማ የአንድነት መገለጫ እንደነበረች ያወሳው ዘ ኢኮኖሚስት የከፊል የራስገዝ አስተዳደር ቢኖራትም በአብዛኛው የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች እንደሚኖሩባትም ነው የገለጸው። በቁጥራቸው ትንሽ የሆኑት ሀረሪዎች ሌሎችም በብዛት የሚኖሩባትን የሀረሪ ክልል እንደሚያስተዳድሩና ይህም ችግር ሲፈጥር መቆየቱንም መጽሔቱ አስታውሷል። ዋናው ችግር ግን ይላል ዘኢኮኖሚስት ሰፊ ድንበር በሚጋሩት በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ መካከል የተፈጠረው ግጭት ከ70 ሺ በላይ እንዲፈናቀሉና በመቶዎች ደግሞ በግፍ እንዲገደሉ ማድረጉ ነው። እነዚህ ተፈናቃዮች ደግሞ ሐረር ከተማን ማጨናነቃቸውን ዘገባው ጠቅሶ የኢትዮጵያ በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝም ባመጣው ጣጣ አካባቢው እየተመሰቃቀለ መሆኑን ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል። ከተለያዩ ብሔሮች የተደበላለቁትን ጨምሮ ማንም ሰው በመታወቂያው ብሔሩን እንዲገልጽ መገደድም ለእርስ በርሱ መገዳደልና ለግጭቱ መባባስ ሰበብ ሆኗል ነው ያለው። ዘ ኢኮኖሚስት እንደገለጸው በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ብሔሮችን በመከፋፈል በእጅ አዙር ግን ክልሎችን ሲቆጣጠር ቆይቷል። አሁን ግን ክልላዊ መንግስታት እየጠነከሩና ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ እየሆኑ መሄዳቸውን መጽሔቱ በሀተታው አመልክቷል። እንደ ዘ ኢኮኖሚስት ዘገባ ክልላዊ መንግስታት ዋነኛ አጀንዳቸው የብሔራቸውን ጥቅም ብቻ ማስጠበቅ ነው። ለዚሁም የኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር በአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም መጠየቁንም ለአብነት አንስቷል። በሶማሌ ያለው አስተዳደርም ልዩ ፖሊስ በማቋቋም እየፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣና የመስፋፋት ሕልም በክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ጊሌ የሚዘወር መሆኑን መጽሔቱ ዘርዝሯል። እናም በሕወሃት የሚመራው የፌደራሉ አገዛዝ በእንዲህ አይነት ምስቅልቅሎች ውጥረት ውስጥ መግባቱንና ሁኔታውን መቆጣጠር አለመቻሉን ዘኢኮኖሚስት በዘገባው አስፍሯል። በቋንቋ ላይ የተመሰረተው ፌደራሊዝም ሕወሃት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ተግባራዊ ሲደረግ የኢትዮጵያ ችግር ብቸኛ መፍትሄ ሆኖ ይቆጠር ነበር። አሁን ግን ይላል ዘ ኢኮኖሚስት የግጭትና የአለመተማመን እንዲሁም የአመጽ መንስኤ እየሆነ መምጣቱን እየተመለከትን ነው ብሏል። ክሪስቶፎር ቫን ዳር ቤከን የተባሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ፕሮፌሰርን ጠቅሶ ዘኢኮኖሚስት እንዳለው የሕዝቡን አንድነት በመሸርሸር እውን የተደረገው ብሔር ተኮር ፖለቲካ በመጨረሻ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። እናም አሁን አንድነትን ለመመለስ የሚደረገውን ሙከራ ፈታኝ አድርጎታል ማለታቸውን ዘ ኢኮኖሚስት ዘግቧል።

One of the generals who served in military security in the Ethiopian Defense Force requested the asylum process in the United States.

ESAT News - September 26, 2010) An Ethiopian general who was serving in military security at the Ethiopian Defense Force requested that the asylum seeker escape in the United States. According to ESAT sources, Melaku Shiferaw, a senior officer in the United States, is a senior officer in the US. One month ago, Birhanu General Keffa Shiferaw, who was a member of the Ethiopian Orthodox Tewahedo International Campaign in Washington, USA, was left out of the group by Dr. Meinnah Gebeyehu.

The popular economist magazine, The World's Leading Journalist, has been in the country for over 26 years.

(ESAT News-September 26, 2010) The celebrated international magazine The Economist reported that the country's ethical political contest was underway in Ethiopia for 26 years. The recently concluded Economic Contracting Authority of Ethiopia, which is headed by the Federal Government, is under control of the Federal Government. And the economist insists that the Ethiopian regime, which has been grappling with tribal politics to undermine the unity of the people, is in trouble.

በኢትዮጵያ ባለፉት 26 አመታት የተተገበረው የብሔር ተኮር ፖለቲካ ፈተና እየገጠመው መሆኑን ታዋቂው የአለም አቀፍ መጽሔት ዘ ኢኮኖሚስት ዘገበ።


በቆላ ድባ አንድ ወጣት በመከላከያ አባላት ተደብድቦ ተገደለ

በደንቢያ ወረዳ ባርጫ ቀበሌ የተወለደው ወጣት ደመላሽ በመከላከያ አባላት ተይዞ ለሳምንታት ጃንጎ በሚባለው ወታደራዊ ካምጽ ውስጥ ሲደበደብ በመቆየቱ ህይወቱ ማለፉንና የቀብሩ ስነስርዓት ዛሬ መፈጸሙም የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡በርካታ ወጣቶችም እንዲሁ በዚሁ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ታስረው ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ። በሌላ ዜና ደግሞ በቆላ ድባ ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ የስልክ ኔትወርክ ማታ ማታ እየጠፋ ጠዋት ላይ እንደሚለቀቅ ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። አካባቢው የነጻነት ሃይሎች የሚንቀሳቀሱበት የሚንቀሳቀሱበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል።

Tuesday, October 3, 2017

የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው ሼባ ሌዘር ኢንደስትሪ አዲስ ፋብሪካ አስመረቀ።

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው ሼባ ሌዘር ኢንደስትሪ አዲስ ፋብሪካ አስመረቀ። አዲሱ ፋብሪካ ለውጭ ገበያ በሚያቀርበው ምርት በአመት ከ36 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምናዛሪ ያገኛል። በኤፈርት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍንና በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መብራሕቱ መለስ መስከረም 22 በትግራይ ውቅሮ ከተማ የተመረቀው ይህ ፋብሪካ ለውጭ ገበያ ከሚያቀርባቸው ቆዳ ጫማዎች በተጨማሪ ያለቀላቸው የሴቶች የእጅ ቦርሳዎችን ያመርታል። የህወሃት ፖሊት ቢሮ አባልና የኤፈርት ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወይዘሮ አዜብ መስፍን በማምረቻ ፋብሪካው ምርቃት ላይ ይሄ ፋብሪካ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በጥራት ደረጃው ተወዳዳሪ የሌለው ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በመርፌ አይን የማለፍ ያህል ከባድ የሆነውን የአለም ገበያ ሰብሮ መግባቱ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሮልኛልም ብለዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መብርሃቱ መለስ በሀገር ደረጃ ከዚህ ሴክተር የምናገኘው የውጭ ምንዛሪ ከ2 ሚሊየን ዶላር በታች መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አዲሱ የኤፈርት አካል የሆነው ፋብሪካ በወር እስከ 3 ሚሊየን ዶላር የሚያስገኝ በመሆኑ የውጭ ምንዛሪ ገቢያችንን ከ100 ፐርሰንት እጥፍ በላይ ያሳድገዋል ብለዋል። ፋብሪካው በአንድ የጂቲፒ ጊዜ እስከ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ ተናግረዋል። ፋብሪካው

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ አጥተው እየተሰቃዩ ነው

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010) የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መፍትሄ አጥተው እየተሰቃዩ ነው
ከአጠቃላይ ፈተና ጋር በተያያዘ የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የምህንድስና ተማሪዎች ያሰሙትን ተቃውሞ ተከትሎ ምግብ እና መጠለያ በመከልከላቸው ሌሊቱን በቤተክርስቲያንና በሰዎች ቤት ተጠግተው መሳለፋቸውን ተማሪዎች ተናግረዋል።
የዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ተማሪዎች ፈተና አንፈተንም እንዳሉ አድርጎ በአማራ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ መስጠታቸው ተማሪዎችን አሳዝኗል። ተማሪዎች እስከ ዛሬ ሲሰራበት የነበረው አሰራር መቀየሩን የሰሙት ለፈተና ሊቀመጡ የተወሰኑ ቀናት ሲቀራቸው በመሆኑ አሰራሩ በቂ ውይይት ሳይደረግበት ተግባራዊ መሆኑን ይቃወማሉ።
የዩኒቨርስቲው ፕ/ት ዶ/ር ባይሌ ዳምጤ አሰራሩ መቀየሩን ቢያምኑም ፣ ከተማሪዎች ጋር ዩኒቨርስቲው ተወያይቶ መፍትሄ ለምን እንዳላስገኘ ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ይህ እኮ ዩኒቨርስቲ ነው” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

አቶ አንዱዓለም አራጌ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቅ ተመድ ጠየቀ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)አቶ አንዱዓለም አራጌ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቅ ተመድ ጠየቀ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእስረኞች ጉዳይ ተከታታይ ቡድን የቀድሞው አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በነበረው አቶ አንዱዓለም አራጌ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ዓለምአቀፍ ሕጋዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ፈርዶበታል ሲል መግለጫ አውጥቷል። የተመድ አምስት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት አጣሪ ቡድን ኤክስፐርቶች ባወጡት የአቅዋም መግለጫ አንዱዓለም አራጌ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።
“የሌጋል ፍሪደም ናው” ዳሬክተር የሆኑት ኬት ባርዝ ፣ ''የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በ2009 እ.ኤ.አ. ይወጡትን ጸረሽብር ሕጉን ሕጋዊ የሆኑትን የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን እና የተለየ ሃሳቦችን ለማፈኛነት ይጠቀሙበታል። አንዱዓለም አራጌን ለእስር ያበቃው ይህን ኢፍትሃዊ ሕግ በመቃወሙ ነው። የሰብዓዊ ቡድኑ አባላት በጋራ ለኢትዮጵያ መንግስት የምናቀርበው ጥያቄ የቡድኑን አስተያየት አክብረው በአፋጣኝ ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች አንዱዓለም አራጌን እና አብረውት የታሰሩት ባልደረቦቹን በሙሉ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።'' ሲሉ በአጽንኦት ጠይቀዋል።
አንዱዓለም አራጌ እና ታዋቂው አንጋፋ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የመሳሰሉ አያሌ የፖለቲካ እስረኞች በተደጋጋሚ ግዜያት ከሕግ አግባብ ውጪ እንደተፈረደባቸው ፍሪደም ናው ዘግቧል።

ለውትድርና የሚመዘገብ ሰው በመጥፋቱ በደላላ ማፈላለግ ተጀመረ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)ለውትድርና የሚመዘገብ ሰው በመጥፋቱ በደላላ ማፈላለግ ተጀመረ
በደቡብ ወሎ የተለያዩ ከተማዎች ለውትድርና የሚመዘገብ ወጣት በመጥፋቱ፣ ደላሎች ለውትድርና በሚያስመዘግቡት የሰው መጠን ገንዘብ እንደሚሰጣቸው ታውቋል። በተለያዩ መንገዶች ለሳምንታት የተደረገው ቅስቀሳ ውጤት አልባ መሆኑን ተከትሎ፣ደላሎቹ ባስመዘገቡዋቸው ወጣቶች ልጅ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
እነዚሁ ደላሎች በየሰፈሩ እየዞሩ የተለያዩ የቅስቀሳ ስራዎችን እየሰሩ ቢገኙም፣ እስካሁን አልተሳካላቸውም።
በተለያዩ ክልሎች ወጣቶችን ለውትድርና ለመመልመል የተደረገው ጥረት እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም አለመሳካቱን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች የግብር ጥያቄያቸው ለዓመታት ባለመፈታቱ በርካታ ላኪ ነጋዴዎች ስራ ማቆማቸው ተነገረ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 23/2010)የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች የግብር ጥያቄያቸው ለዓመታት ባለመፈታቱ በርካታ ላኪ ነጋዴዎች ስራ ማቆማቸው ተነገረ
ሰሞኑን በጎንደር ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት የከተማው ንግድ ዘርፍ ማህበራት ተጠሪ እንዳስታወቁት በርካታ ላኪ (ኤክስፖርተር) ባለሃብቶች ላለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ስራ ማቆማቸውን ገልጸዋል፡፡ይህ የሆነው በተደጋጋሚ የጠየቁት የግብር አወሳሰን ችግር እንዲስተካከል ጠይቀው ምላሽ በማጣታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የጥራጥሬና እህል ላኪዎች፣ የቡና ንግድ ጅምላ ነገዴዎችና ላኪዎች ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥያቄያቸው እየተገፋ በመሄዱ ስራ ለማቆም መገደዳቸውንና በየዓመቱ ንግድ ፈቃዳቸውን ብቻ በማሳደስ ፍትህ እየጠየቁ መሆኑን የዘርፍ ማህበሩ አመራራር ተናግረዋል፡፡
የንግድ ዘርፍ ማህበሩ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን በየደረጃው ለሚገኙ የመንግስት አካላት ቢያስታውቁም ችግሩ ሳይፈታ መዘግየቱን የሚገልጹት የነጋዴዎች ተወካይ፣ የገዥው መንግስት አመራሮች ጥናታዊ ጽሁፍ አጥንተው እንዲያቀርቡ ጠይቀው ይህንኑን ቢፈጽሙም፣ ችግሩ ሳይፈታ ለሰባት ዓመታት መዘግየቱ ከተማዋ ብሎም ክልሉና ሃገሪቱ ልታገኝ የሚገባትን የውጭ ምንዛሬ አንዳስቀረ ጠቁመዋል፡፡

Monday, October 2, 2017

የኢሬቻ በአል የህዝብ የተቃውሞ ማእከል ሆኖ ተጠናቀቀ

(መስከረም 22 ቀን 2010 ዓም) የኢሬቻ በአል የህዝብ የተቃውሞ ማእከል ሆኖ ተጠናቀቀ
በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የኢሬቻ በአል ህዝቡ በአገዛዙ ላይ ያለውን ተቃውሞ ያሰማበት፣ አገዛዙ ላለፈው አንድ አመት ከላይ እስከታች ባካሄድኩት ጥልቅ ተሃድሶ ከህዝብ ጋር ስምምነት ላይ ደርሻለሁ በማለት ሲያሰራጨው የቆየው ፕሮፓጋንዳ ትክክል አለመሆኑን ያሳዬበት ሆኖ ተጠናቋል። በአሉን የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ሳይሆን የሌሎች ብሄር ተወላጆችም በበአሉ ላይ በመገኘት ለኦሮሞ ወገናቸው ድጋፍ ከማሳየት አልፈው በተቃውሞው ተሳትፈዋል።

በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኘው የቴሌ ቢሮ ላይ ፈንጂ ተጠምዶ ተገኘ

(መስከረም 22 ቀን 2010 ዓም) በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 04 የሚገኘው የቴሌ ቢሮ ላይ ፈንጂ ተጠምዶ ተገኘ
በባህርዳር ቀበሌ 04 በሚገኘው የቴሌ ቢሮ ውስጥ ፈንጂ ተጠምዶ በመገኘቱ ከመከላከያ ባለሙያ ተጠርቶ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲነሳ ተደርጓል። መረጃው ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን የተደረገው ፣ ዜናውን ይፋ ማድረጉ የፀረ ሰላም ሀይሎችን በራሳችን አንደበት ሃይል እንዳላቸው አድርገን ለህዝብ ማስተዋወቅ ነው በሚል ምክንያት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። 
የተገኘው ፈንጅ ተቀጣጣይና ከባድ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። 
በተመሳሳይ ቀበሌ 15 በሚገኝ ግሮሰሪ ውስጥ ዳሽን ቢራ ባዘጋጀው የደስታ ምሽት ( happy hour) ላይ “ዳሽን አይጠጠም” ብላችሁ ሁከት ፈጥራችሁዋል የተባሉ 3 ልጆች በ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ልጆቹ የተያዙት ቀበሌ 3 ውስጥ ሲሆን፣ በዚሁ ግሮሰሪ ውስጥ ቦንብ ተወርውሮ ሳይፈነዳ በመገኘቱ ልጆች እንዳደረጉት ተቆጥሮ ከያሉበት ተይዘው በ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።
ቴሌ ላይ የተጠመደው ፈንጅ እና ባለፈው ባህር ዳር አየር መንገድ የተገኘው ፈንጅ አንድ አይነት በመሆኑ የፖሊስ ኮሚሽን እና የደህንነት ባለስልጣናት ጠንካራ ጥቃት በቅርቡ ሊፈፀም ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል።
አዲሱ የደህንነት ሹም እዘዝ ዋሴ አጠቃላይ የደህንነት አባላትን ለስብሰባ ጠርቷል።

Ethiopia: Scores of people arrested following protests at annual Irreecha festival

ESAT News (October 2, 2017)
Scores of people were arrested on Sunday following anti-TPLF protests at the annual Irreecha festival in Bishoftu a.k.a. Debrezeit, 25 miles outside the capital Addis Ababa, according to information received by ESAT.
The religious festival on Sunday turned into protest rally with thousands of festival goers chanting anti-TPLF slogans and demanding freedom for the Oromo people. “Down, down, Woyane!” protesters chanted in Oromifa and Amharic. People from other ethnic group have also joined the Oromos at Sunday’s festival which also marks the one year anniversary of the death of hundreds of people as security forces fire at the protesting crowd and stampede ensued.

በተቃውሞ ታጅቦ በተከበረው በዘንድሮው የእሬቻ በዓል ላይ ተሳትፈው ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ የነበሩ አንድ ባስ ሙሉ ታዳሚዎች ትላንት ቃሊቲ ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) በተቃውሞ ታጅቦ በተከበረው በዘንድሮው የእሬቻ በዓል ላይ ተሳትፈው ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ የነበሩ አንድ ባስ ሙሉ ታዳሚዎች ትላንት ቃሊቲ ላይ በፖሊስ ተይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በፖሊስ የተያዙትን ሰዎች ለማግኘት የተደረገው ሙከራም አለመሳካቱን ምንጮቹ ገልጸዋል። የሕወሃት አገዛዝ ይብቃን ከስልጣንም ይውረድ በሚል ድምጻቸውን ያሰሙት የበአሉ ተካፋዮች የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ፎቶግራፍ በመያዝና ስማቸውን በመጥራት ተቃውሞ ማሰማታቸው ታውቋል። ለበዓሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደቢሾፍቱ ደብረዘይት ያመሩት ታዳሚዎች ባለፈው ዓመት የተገደሉትንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የእሬቻ በዓል ታዳሚዎችን በህሊና ጸሎት አስበዋቸዋል። ዕሁድ ዕለት ከንጋት ጀምሮ ወደ ቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሀይቅ የእሬቻ በዓል ታዳሚ ሶስት መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ነበር የተመመው። የአባገዳዎች ምክር ቤትና የኦሮሚያ ክልል መንግስት ውሳኔዎች ተጥሰው የመንግስት ታጣቂዎች በበዓሉ ስፍራ ይገኛሉ የሚለው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ በበዓሉ ላይ ስጋት እንዲያንዣብብ ማድረጉን የሚጠቅሱ ወገኖች የባለፈው ዓመት ዕልቂት እንዳይደገም
(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) የባህርዳር የምህንድስና ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ። በዩኒቨርስቲው ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ምግብ የተከለከሉት ከ1500 በላይ ተማሪዎች ከዛሬ መስከረም 22 ጀምሮ ማንኛውንም የግቢውን ንብረት አስረክበው እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል። ተማሪዎቱ በየአብያተ ክርስቲያናት የተጠለሉ ሲሆን የመንግስት ታጣቂዎች ከአንዳንድ ቤተክርስትያን ውስጥ ተማሪዎቹን እየደበደቡ ሲያስወጡ እንደነበረ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ተማሪዎቹ አራተኛ ዓመት ላይ በሚወስዱት ፈተና ውጤት አሰጣጥ ላይ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ያወጣውን አሰራር በመቃወማቸውና ፈተናውን እንደማይወሰዱ አቋም በመያዛቸው ነው ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ያደረገው። ለተማሪዎቹ ድጋፍ እንዲደረግም ተጠይቋል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ዘርፎች በምህንድስና ትምህርት ክፍል ለአራተኛ ዓመት የደረሱ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ በመጨረሻም ከግቢው ለቀው እንዲወጡ በማድረግ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። ቀደም ሲል የነበረው የውጤት አሰጣጥ በመቅረቱና በምትኩም መውደቅና ማለፍ ብቻ በሆነው አዲሱ አሰራር ፈተና አንወስደም ያሉት ከ1500 በላይ ተማሪዎች ላለፉት 10ቀናት ያደረጉትን አድማ ተከትሎ ዛሬ ከዩነቨርስቲው እንዲወጡ መደረጋቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች ገልጸዋል። የባህርዳር ዩኒቨርስቲ አዲሱን የውጤት አሰራር ለምን ተግባራዊ እንዳደረገ በግልጽ ለተማሪዎቹ አልተነገራቸውም። ኢሳት የዩንቨርስቲውን አስተዳደር ለማግኘት ያደረገው ሙከራም አልተሳካም። ተማሪዎቹ እንደሚሉት አዲሱ አሰራር ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘ በርካታ ተማሪዎችን ለማባረር ሆን ተብሎ የተቀመጠ

የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ህወሃት/ማዕከላዊ ኮሚቴ በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር በመቀሌ ነገ መወያየት እንደሚጀምር ተገለጸ

(ኢሳት ዜና–መስከረም 22/2010) የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ህወሃት/ማዕከላዊ ኮሚቴ በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ በማተኮር በመቀሌ ነገ መወያየት እንደሚጀምር ተገለጸ። ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብአዴን፣ደኢህዴንና ኦህዴድ በሕወሃት የተቀመጠላቸውን ድክመት እንዲያርሙ በተሰጣቸው አጀንዳዎች ላይ ግምገማ ሲያደርጉ ሕወሃት ግን በብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። በሕወሃት ስብሰባ ላይ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ያልሆኑ የቀድሞ ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ይሳተፋሉ ተብሏል። በእድሜና በተለያዩ ምክንያቶች ከህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱትን አንጋፋ የህወሃት አመራሮችን ያካተተው ስብሰባ ከመስከረም 22 ጀምሮ እንደሚካሄድ ታውቋል። በስብሰባው ሕወሃት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች እንዴት እንደመራው ግምገማ እንደሚካሄድ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ በድረ ገጹ እንዳመለከተው የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የሚመለከታቸው እጀንዳዎች የድርጅትና መንግስት የ2009 አፈጻጸም፣ በጥልቅ ተሀድሶ የነበረውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመገምገም ተጠናክሮ የሚቀጥልበት አቅጣጫ ማስቀመጥና የቀጣይ የ2010 ትኩረት አቅጣጭዎችን እንደሚያስቀምጥ አመላክቷል። በሌላ በኩል ከሳምንት በፊት በባህርዳር ግምገማ ያካሄደው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አምስት ገዳይና ተላላፊ ፖለቲካዊ በሽታዎች የተባሉት የርዕዮተ አለም መስመር ክህደት፣የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ተግባር፣የትምክህት ተግባርና አመለካከት፣የአቅም ውስንነትና ስር የሰደደ አድርባይነትና ጸረ ዲሞክራሲ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አሳውቆ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራው የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 2 እስከ 5/2010 ባደረገው ግምገማ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሳይሆን የውስጠ ድርጅት አጀንዳዎች ላይ ማተኮሩን ለማወቅ ተችሏል። የደኢህዴን ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ቤልጂጌ በሰጡት መግለጫ ደኢህዴን በጎሰኝነት፣በጎጠኝነትና በመንደርተኝነት ሃሳብ የሚያራምዱ ጎታችና ኋላቀር የሆኑ ከፋፋይ አመለካከቶችን በመገምገም የተግባር ርምጃ መውሰድ መጀመሩን ገልጸዋል። ህወሃት ሀገራዊ እቅድና አቅጣጫ በሚነድፍበት ይህ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰናበቱትን አቶ ስብሀት ነጋ፣አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋ ካድሬዎችን ሊያሳትፍ እንደሚችል የደረሰን መረጃ አመላክቷል።