ሰኔ 28/2009
በወላይታ ሲዳማ ዞን የተነሳው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ወደ ግጭት እንዳያመራ መንግስት እጁን ከጉዳዩ እንዲሰብስብና በሃገር ሽማግሌዎች እንዲፈታ ጥሪ ቀረበ ።
በሰሜን አሜሪካ የወላይታ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር በውዝግቡ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የወላይታ ህዝብ የሲዳማን ህዝብ ጨምሮ ከሁለቱ ጎረቤቶቹ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖርን በማስታወስ አሁን የገጠመንም ችግር ከሲዳማ ህዝብ ጋር በመነጋገር እንዲፈታው ያለውን እምነት ገልጿል ። የውዝግቡ መነሻ የሆነውንና አሁን በወላይታ ዞን የሚገኘውን ቦታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት የውዝግቡን አነሳስ የሚዳስሰው መግለጫ ሁለቱም ወገኖች የግዛት ይገባኛል ጥያቄ አንስተው እንደማያውቁም አስታውሰው አሁን የተፈጠረውም ችግር የተከተለው በመንግስት አካላት ጣልቃ ገብነት እንደሆነም አመልክተዋል ።
በአባያ ሀይቅና በብላቴ ወንዝ አዋሳኝ የሆነው “ጨከሬ ‘ የተባለው ቦታ ዛሬ የውዝግብ መነሻ ሆኖ መገኘቱን የሚዘረዝረው የወላይታ ተወላጅና ወዳጆች ማህበር በመንግስት አካላት ጣልቃ ገብነት በሁለቱ ብሄረሰቢች መካከል ግጭት ሊከተል እንደሚችል ስጋቱን በመግለጽ መንግስት እጁን እንዲሰበስብ ጥሪ አድርጓል ። “ይህ ጉዳይ በጥንቃቄ ካልተያዘ በአካባቢው የማያባራ ግጭት ሊፈጠር እንደሚችልና አላስፈላጊ መናቆር ብሎም ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል አያጠራጥርም “ በማለት ስጋቱን የሚገልጸው የወላይታ ተወላጅና ወዳጆች ማህበር ችግሮችን በጋራ የመፍታት የዳበረ ልምድ ያላቸው ሁለቱ ብሄረሰቦች በራሰቸው እንዲጨርሱት እድል እንዲሰጣቸው ጠይቋል ።
ከወላይታና ሲዳማ ብሄረሰቦች የተውጣጡ የሃረር ሽማግሌዎች ምሁራናን ታዋቂ ግለሰቦች ያካተተ አካል እንደሚመሰረትና ለችግሩ እልባት እንዲሰጥ ምእሕበሩ ጥሪውን አቅርቧል ።
No comments:
Post a Comment