(ኢሳት ዜና – ሀምሌ 3/20009) የተባበሩት መንግስታት የሰብኣዊ መብት ድርጅት በምስራቅ ኣፍሪካ ከተከሰተው ከባድ ድርቅ ጋር ተያይዞ 27 ሚሊየን የሚጠጋ ህዝብ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ኣስታውቀ። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በኣፍሪካ ቀንድ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስደተኛ ዚጎች ቁጥር ከ4 ሚሊየን በላይ ኣሻቅቧል። ከምስራቅ ኣፍሪካ ብቻ ባለፉት ስምንት ወራት 3 ሚሊየን የሚሆኑ ዜጝች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲል ሪፖርቱ ኣመልክቷል። በኣካባቢው ያለው ድርቅ ፥ሰብል በወቅቱ ያለመሰብሰብ፥ የእርስ በርስ ግጭት ፥የአካባቢው ሰላም የተርጋገጠ ኣለመሆንና ተያያዥ ምክንያቶች በቀጣይም የስደተኞቹ ቁጥር እንዲያሻቅብ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል ሪፖርቱ አክሏል። በኣካባቢው የሚጥለው ዝናብ ወቅቱን ኣልምጠበቅ ደግሞ ለችግሩ መባባስ ምክንያት ሆኗል። በኣሁኑ ሰኣት በምስራቅ ኣፍሪካ እየተከሰተ ያለው ሰብአዊ ቀውስ በታሪክ ከባድ በመባል ተመዝግባል ይላል ሪፖርቱ እንደ ኣለም ኣቀፉ የኣየር ንብረት ተቃም ሪፖርት ከሆነ ደግሞ በመጪው የመጸው ወቕት ይከሰታል ተብሎ በሚጠበቀው አውሎ ንፋስ ኢትዮጽያን ሰሜን ኬንያን ሶማሊያን ምእራብ ዩጋንዳን ሩዋንዳን ቡርንዲንና ሰሜን ምእራብ ደቡብ ሱዳንን ሊያጠቃ ይችላል
No comments:
Post a Comment