ስለ አምባገነን አገዛዝና ግብር ሲነሳ መጥቀስ የምወደው የእውቁ ኢኮኖክስ ማንኩር ኦልሰን Dictatorship, Democracy, and Development ነው። ከዚህ ጽሁፍ በዛ አድርጌ ልጥቀስ።
===
ዘላን ወንበዴዎች /roving bandits/ ነጥቀው ይሮጣሉ፤ መቼ እንደሚመለሱ አይታወቅም። እነዚህ ወንበዴዎች ነጥቀው በሮጡ ቁጥር የማኅበረሰቡ ሀብት የማፍራት ፍላጎት ስለሚዳከም በሚቀጥለው ዙር የሚዘርፉት ነገር እያነሰባቸው ይመጣል። ቀን ባለፈ መጠን ነጥቆ መሮጥ ራሳቸውን እንደሚጎዳቸው ይገነዘቡና ከተዘዋዋሪ ወንበዴነት ወደ ቋሚ ወንበዴነት /stationary bandit/ ይቀየራሉ። ለንጥቂያቸውም ሥርዓትና ልክ ያበጁለታል፤ ስሙን “ግብር” ይሉታል። ማኅበረሰቡንም፣ ራሳቸውንም ከሌሎች ተዘዋዋሪ ወንበዴዎች ይከላከላሉ። ይህ ሥርዓት ከሥርዓተ አልበኝነት የተሻለ፣ የቅሚያውም መጠንም አስቀድሞ የሚታወቅ ከመሆኑ ጋር ማኅበረሰቡ ለሚከፍለው ተመጣጣኝ ባይሆንም የሚያገኘው ጥቅም (ሰላምና ሌሎችም ማኅበራዊ ምርቶች) ስላሉ ምርት ይጨምራል፣ ዕድገትም ይኖራል።

ይሁን እንጂ አምባገነን ሰፋሪዎች በተደላደሉ መጠን ፍጆታቸው እየናረ መሄዱ ፈጽሞ የማይቀር ነው። ለጦር ሠራዊቱ፣ ለቤተመንግሥቱ፣ ለማሰልጠኛው፣ ለመታሰቢያ ሀውልቶች ግንባታ፣ ለአዳራሾች ግንባታ፣ ለአምባገነኖች፣ ለተከታዮቻቸውና ቤተሰቦቻቸው የክብር ልብሶችና ጌጣጌጦች፣ “ለመጠባበቂያ“፣ ..... የሚያስፈልገው ወጪ በጨመረ ቁጥር ሕዝቡ በግብር አሊያም በሌላ መንገድ እንዲከፍል ስለሚገደድ ሥርዓት በመስፈኑ ምክንያት አንሰራርቶ የነበረው የሥራ ፍላጎት እንደገና ያሽቆለቁላል። የሰፋሪ ወንበዴዎችን የሀብት ማጋበስ፣ ምቾትና እዩልኝ ፍላጎቶችን ማርካት አይቻልም።
==