ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)
ከወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቅርቡ ለእስር የተዳረጉት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማክሰኞ ፍርድ ቤት መቅረባቸውንና ለከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት የዋስትና መብት ጥያቄ በፖሊስ ተቃውሞ እንደቀረበበት እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
በኮሚቴ አባሉ ላይ ምርመራን እያካሄደ መሆኑን ለችሎት ያስታወቀው ፖሊስ፣ ኮሎኔል ደመቀን በሽብርተኛ ወንጀል ድርጊት የሚጠረጥራቸው በመሆኑ ያቀረቡት የዋስትና መብት ተቀባይነት እንዳያገኝ ተቃውሞ አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም ከፖሊስና ከኮሎኔሉ የቀረቡ ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 3, 2008 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ለኢሳት የደረሰ መረጃ አመልክቷል።
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከትግራይ ክልል የተላኩ የደህንነት ሃይሎች ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለመውሰድ ሞክረዋል በማለት ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውን ተከትሎ ድርጊቱ ወደ ግጭት መለወጡ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment