Thursday, September 29, 2016

ተጨማሪ መረጃዎች ስለ “ደህንነቱ|” መሥሪያ ቤት [ታደሰ ብሩ]

“ስለ ‘ደህንነቱ’ መሥሪያ ቤት ከማውቀው በጥቂቱ” በሚለው አጭር መጣጥፍ ላይ በርከት ያሉ የውስጥ መልዕክቶች ደርሰውኛል። በበጎም ይሁን በክፉ የፃፋችሁልኝ ሁሉ አመሰግናለሁ፤ በግልም አመሰግኛቸዋለሁ።
ከተላኩልኝ አስተያየቶች በተለይ አንዱ ትኩረቴን ስቦታል። በውስጡ ተረብ ያለበት ሆኖ “የፃፍከው በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ነው፤ ‘ከማውቀው በጥቂቱ’ አልክ እንጂ ከአጠቃላይ ጉዳዮች ያለፈ የምታውቀው ዝርዝር ነገር የለም፤ ቢኖርህ ኖሮ ለነገ የምታቆይበት ምክንያት አይኖርህም ነበር፤ ቢያንስ ደጋፊዎችህን ለማስጠንቀቅ ሁለት ሶስት ስሞችን ትጠራ ነበር” የሚል ነው የመልዕክቱ ይዘት ነበር። አስተያየት ሰጪው እልህ ውስጥ ሊያስገናኝ የፈለገ ይመስላል። እኔ በቀላሉ እልህ ውስጥ የምገባ ሰው አይደለሁም፤ ሆኖም ቆም ብዬ እንዳስብበት አደረገኝ።
ስለ ህወሓት መሥሪያ ቤት ተጨማሪ ነገሮችን መናገር ህወሓትን ለማሸነፍና በምትኩ ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈባት አገር ለመመሥረት ለምናደርገው ትግል ምን ያህል ይጠቅማል? ተጨማሪ ነገር ብጽፍ በዚህ እኩይ መሥሪያ ቤት ያሉ ቅን ሰዎችን ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል? የሚለውን እንዳስብበት አደረኝ። በእኔ ስሌት ከጉዳቱ ጥቅሞ በልጦ ስላገኘሁት እነሆ ተጨማሪ ነገሮች ማለት ፈለግሁ።

ከቁንጮ ልጀምር ፀጋዬ በርሄ – የጠቅላይ ሚ/ሩ የደህንነት አማካሪ ነው። ይህ ሰው ከህወሓት ሹማምንት በደነዝነት ቀዳሚውን ወንበር የያዘ ነው፤ ሆኖ ትልቅ የአዕምሮ ሥራ የሚፈልገውን “የደህንነት አማካሪነት” ሥራ ይዟል። ለኔ ኢንተለጀንስ የአዕምሮ ሥራ ነው፤ የመጀመሪያውና ወሳኙ ጦርነት የስነልቦና ጦርነት ነው፤ ጠላትን በስነልቦና፣ በአዕምሮ ማሸነፍ ይገባል። ፀጋዬ ጭንቅላት የፈጠረበት ስለመሆኑም እንኳን እጠራጠራለሁ።
ጌታቸው አሰፋ: የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ነው። ይህ ሰው ውስብስብ ነው፤ ባሁኑ ሰዓት ህወሓት ጌታቸውን የሚያህል ሰው ያለው አይመስለኝም። አገራችን የገባችበት አጣብቂኝ የመረዳት አቅም አለው ብዬ አምናለሁ። ሆኖም የህወሓት ልምዱ ውስን አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አድርጎታል ብዬ አስባለሁ። ከህወሓት ውጭ ያለውን ዓለም አያውቀውም፤ ያስፈራዋልም። የህወሓት የቁልቅለት ጉዞ ይታየዋል፤ ግን ስለኢትዮጵያ ቅን የሚያስቡ ሰዎች ከኢህአዴግ ውጭ አሉ ብሎ ለማመን ይቸግረዋል። በዚህ ኃላፊነቱ ላይ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል መሆኑ ምን ያህል እንደጎዳው መገንዘቡን እጠራጠራለሁ።
በጀነራል ዳይሬክተሩ ስር አምስት ምክትል ዳይሬክተሮች አሉ። አምስቱም ቦታዎች የጦርነት ቦታዎች ናቸው። በህወሓት ውስጥ ያለው ሽኩቻ ለማጥናት እነዚህን አምስት ወንበሮች መመልከት ይበቃል። አሁን ህወሓት ውስጥ ሁለት ዋና ዋዋ መስመሮች አሉ፤ አንዱ በሳሞራ የኑስ የሚመራው የመለስ ሌጋሲ አራማጆች [እንብላ፣ እንዝረፍ፣ እንጠቅልል ባዮች] ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በጌታቸው አሰፋ የሚመራ “ተው ረጋ ብለን እናስብ” ባይ ነው። እናም በዚህ ፍትጊያ ሳቢያ አምስቱ ምክትል ዳይሬክተሮች በየጊዜው ይፐወዛሉ። ስለዚህ እነሱን ሳልጠራ ልለፋቸው፤ ገና ያልተረጋጋ ቦታ ነው፤ አንዳንዶቹን ግን ከታች በሌሎች አጋጣሚዎች አነሳቸዋለሁ።
በቀጥታ ወደ ዋና ዋናዎች የህወሓት ሰላዮች እና ምድባቸው አመራለሁ። ከዚህ በታች ስማቸውን የምዘረዝራቸው ሰዎች ሁሉም ማለት ይቻላል እድሜዓቸው ከ 60 በላይ ነው፤ አሁንም ሁሉም ማለት ይቻላል የህወሓት አባላት ናቸው፤ “የኢንተለጀንስ ትምህታቸውን ያጠናቀቁት” በባዶ 6 ንፁሀን ዜጎችን በመግረፍ ነው። ከእነዚህ ውስጥ 70% የሚሆኑት ማንኛውንም ዓይነት ለውጥ ይጠላሉ።
1. ጥበቃ ዋና መምሪያ: መኮንን (ወዲ ኮበል) ይህ የVIP ጥበቃን ጨምሮ አየር መንገድንም ይቆጣጠራል
2. ክንፈ ማሰልጠኛ: ታደለ ፀጋዬ ዳይሬክተር፤ ዶ/ር ሀሽም ተውፊቅ ም/ዳይሬክተርና የአስተዳደርና ፋይናንስ ኃላፊ
3. የቴክኒክ መረጃ: ማዕሾ ( ማዕሾ ከአምስቱ የጌታቸው ምክትሎች አንዱ ነው) የሚመራው ቢሆንም ጌታቸው በቀጥታ ይቆጣጠረዋል
4. የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ: ገ/ዮሃንስ ተክሉ ዋና ዳይሬክተር
5. የውጭ መረጃ ዋና መምሪያ: ሀደራ ( ሀደራው ሌላው ከአምስቱ የጌታቸው ምክሎች አንዱ ነው) ይመራው የነበረ ሲሆን አሁን ገና ቋሚ ሰው አልተተካም። ልዑል ታፈረ ምክትል ነው።
6. የውስጥ ደህንነት ጥበቃ ዋና መምሪያ: አማኑኤል ኪሮስ ዋና ዳይሬክተር ሲሆን ደርበው ደመላሽ ምክትሉ ነው
7. ፀረ ሽብር መምሪያ: ተስፋዬ ዑርጌ ኃላፊ ሲሆን (አግ7፣ ኦነግ፣ አልሸባብ ወዘተ.) ሲሆኑ ምንም እንኳን የራሱ ዋና ክፍል ቢኖረውም አርበኞች ግንቦት-7 ን የመምሪያው ኃላፊ በቀጥታ ይከታተላል።
7.1. የአርበኞች ግንቦት-7 ዋና ክፍል ኃላፊ ሸዊት በላይ ነው [ይህንን ጽሁፍ በመመርመር ጽህፍ እንደሚበዛበት፤ ዛሬ ሰክሮ እንደሚያድር እገምታለሁ]
8. የክትትል መምሪያ ኃላፊ: አፅብሃ ግደይ
9. የፀረ ስለላ መምሪያ ኃላፊ: ነብዩ ዳኘ
10. የኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ: ቢኒያም ማሙሸት
11. የአስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ: ፍቅሩ በቀለ
12. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክትትል ኃላፊ: አብይ ኃይሉ [እጅግ ከሚያሳዝንኝ ነገሮች አንዱ የዚህ ክፍል ሥራ ነው። ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን መማሪያዎች ሳይሆን እስር ቤቶች ያደረጓቸው የዚህ ክፍል ሠራተኛች ናቸው። የዚህ ክፍል ሠራተኞች የሚሠሩት ደባ ለተከታተለ 32 ዩኒቨርስቲ ሳይሆን 32 እስር ቤቶች እንደተገነቡ ይገባዋል]
13. የፖለቲካ ፓርቲዎች ክትትል ዋና ክፍል ኃላፊ: አመለወርቅ ገ/ሃዋሪያ (አቶ)፤ ይስሃቅ ይህደጎ ም/ኃላፊ [ይህ ክፍል ፈቃድ ተሰጧቸው የሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በጠላትነት ፈርጆ ሊያጠፋቸው ሌት ተቀን ይሠራል]
14. የኢኮኖሚ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ: መድህኔ ታደሰ ኃላፊ፤ ፍቃዱ መረሳ ም/ኃላፊ
15. ጥናት መምሪያ ኃላፊ: በላይ አሰፋ ሲሆን አሁን ለምን እንደሆነ ባልገባኝ ሁኔታ እየፈረሰ ያለ መምሪያ ነው
16. የክልሎች ማስተባበሪያ መምሪያ ኃላፊ: ግርማ ተገኝ ሲሆን 9 ን ክልሎችና አዲስ አበባንም ይመራል:: ከእነዚህ መካከል፦
16.1. የአማራ ክልል ኃላፊ: እንግዳው አበባው
16.2. የደቡብ ክልል: እዮብ ተወልደ
16.3. ኦሮሚያ ክልል: አዲሱ በዳዳ ያስተባብራሉ
17. የአዲስ አበባ ደህንነት ዋና ክፍል: ጎሃ አፅብሃ ገ/ሂወት ሲሆን 10ሩን ክ/ከተማዎች ያስተባብራል
17.1. አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ: ጋሻው አበበ ኃላፊ
17.2. ቦሌ ክ/ከተማ ኃላፊ: ምስጋናው አየለ:
17.3. ን/ላፍቶ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሲሳይ ገ/ፃዲቅ ኃላፊ
17.4. ልደታ ክ/ከተማ ኃላፊ: አሸናፊ ነጋሽ ኃላፊ
17.5. ኮልፌ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሀይሉ ታደሰ ኃላፊ
17.6. ቂርቆስ ክ/ከተማ ኃላፊ የሺጥላ ካሳ ኃላፊ
17.7. አራዳ ክ/ከተማ ኃላፊ: ሀጎስ ሀለፎም ኃላፊ
17.8. የካ ክ/ከተማ ኃላፊ: ክፍሎም በየነ ኃላፊ
17.9. ጉለሌክ /ከተማ ኃላፊ: ሳሙኤል ታፈሰ ኃላፊ
17.10. አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኃላፊ: አዲስ አለነ ናቸው::
- See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/22153#sthash.p2qefH1w.dpuf

No comments:

Post a Comment