ኢሳት (መስከረም 19 ፥ 2008)
ከ30 የሚበልጡ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሃሙስ የሌተናል፣ የሜጀርና፣ የብርጋዴር ጀነራልነት ማዕረግ እንደተሰጣቸው መንግስት አስታወቀ።
በሃገሪቱ ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሾመ የማዕረግ እድገት ተሰጥቷቸዋል ከተባሉት ወታደራዊ መኮንኖች መካከል የሜጀር ጄነራልነት ማዕረግ የነበራቸው ገብራት አየለ ቢጫ በብቸኝነት የሌተናል ጀኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።
በብርጋዴር ጀነራልነት ሲያገለግሉ ነበር የተባሉ 12 ወታደራዊ መኮንኖች ደግሞ የሜጀር ጀኔራልነት ሹመትን ያገኙ ሲሆን፣ 25 ኮሎኔሎች እንዲሁ የብርጋዴር ጄኔራልነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል።
የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ መንግስት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ሹመትን ሲሰጥ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የዛሬውን ጨምሮ ከ120 የሚበልጡ ወታደራዊ መኮንኖች መሾማቸውን ለመረዳት ተችሏል።
ሃሙስ በሜጀር ጄኔራልነት ከተሾሙት መካከል ብርጋዴር ጄኔራል መሃመድ ኢሻ ዘይኑ ትኩዕ፣ ብርጋዴር፣ ጄኔራል ሃለፎም እጅጉ ሞገስ፣ ብርጋዴር ጄነራል ማሾ በየነ ደስታ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ይገኙበታል።
በብርጋዴርል ጀአራልነት ከተሾሙት መካከል ደግሞ ኮሎኔል አዲሱ ገብረየሱስ ገብረዮሃንስ፣ ኮሎኔል ኪዱ አለሙ አሰጉ፣ ኮሎኔል ብርሃኑ ጥላሁን በርሄ፣ ኮሎኔል ግርማ ክበበው ቱፋ፣ እና ኮሎኔል ተክላይ ኪዳኔ ተድላ በቅድመ ተከትል ከተቀመቱት መካከል መሆናቸው ተመልክቷል።
No comments:
Post a Comment