ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008)
በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ ተቃውሞውን ለማዳፈን የተንቀሳቀሰው የአጋዚ ሰራዊት በአምባ ጊዮርጊስ 26 ሰዎችን መግደሉ ተነገረ። በአጋዚ ሰራዊት በተኮሰው ጥይት የቆሰሉ በርካታ የአምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች ወደ ጎንደር ለህክምና ሆስፒታል መወሰዳቸው ታውቋል።
በህወሃት ባለስልጣናት ልዩ የግድያ ትዕዛት የተሰጠው ጸጉረ-ልውጥ የሆነ ገዳይ የአጋዚ ቡድን በሰላማዊ ህዝብ ላይ በሰነዘረው ጥቃት ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 26 ሰዎችን መግደሉ የታወቀ ሲሆን፣ ከእናቶችንና ህጻናትን ውጭ አብዛኛው የተከማው ህዝብ በሽሽት ወደ ጫካ መግባቱ እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል።
በአምባ ጊዮርጊስ ከተማ ይኖሩ የነበሩ ወጣቶችችን የአጋዚ ወታደሮች በየቤቱ እየገቡ እየደበደቡ የነበረ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ወጣቶች ግን ድብደባውን በማምለጥ ወደጫካ ገብተዋል፥ በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር መዋሏን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል።
የአምባ ጊዮርጊስ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስለት፣ በሌላ አካባቢ የሚኖረህ ህዝብ በወያኔ አገዛዝ ላይ እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል። “ያለንበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው” ያሉት ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አንድ ሰው፣ ብዛት ያላቸው ኦራል መኪና ወታደር ጭኖ በመምጣት በሰላማዊው ህዝብ ላይ የርሸና እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ቄስ፣ አዛውንት ሳይሉ ሁሉንም እየተኮሱ የሚገሉት የአጋዚ ወታደሮች፣ በገጠር የሚኖረውን ህዝብ ጭምር በማስፈራራት መሳሪያቸውን ለመንጠቅ እየሞከሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የአጋዚ ወታደሮች ከድብደባ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ወጣቶች አነጣጥረው እየተኮሱ እየገደሉ እንደሆነ ለኢሳት መረጃ ያደረሱት ምንጮች፣ ወጣቶች ወደ ጫካ በመግባት የአጋዚን ወታደሮች ለመፋለም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በአምባ ጊዮርጊስ የሚደርሰውን ጭፍጨፋ አለም እንዲያውቅ ኢሳት እንዲያስተላልፍላቸው የጠየቁት የአምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች፣ ከዚህ በኋላ በረሃ ገብተው ወያኔን እንደሚፋለሙ ቃል ገብተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በመተማ ከተማ ትናንት ረቡዕ ህወሃት/ኢህአዴግ ባሰማራቸው ታጣቂዎች ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። ህወሃት በመተማ ከተማ ሰራዊቱን በማሰማራት በህዝቡ ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በመተማ የስልክ መስመርና ማንኛውም መገናኛ መንገድ የተዘጋ ሲሆን፣ የአገዛዙ ሰራዊት ምን አይነት እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም።

No comments:
Post a Comment