Thursday, September 22, 2016

እኛ ሰፈር ነው አሉ… አንድ ቀን ሌባ ተያዘ… [አቤ ቶኮቻው]

gonder-2ከዛ የሰፈሩ ሰው ሁሉ ሌባ ሌባ ሌባ እያለ የአካባቢው ሰው አጅቦት ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየሄደ ሳለ በመንገዱ ርዝመት የተዳከሙት የአካባቢው ሰዎች ግማሹ ወደ ኋላ ሲቀር ግማሹ ድምጹ ሲቀንስ ግዜ ሌባው ሆዬ አልሄድም አለ። ፖሊሱም ፈጠጥ ብሎ ምን ሆነህ ነው… ሂድ እንጂ… ቢለው ይሙቅልኝ! ጭብጫቦው ሌባ ሌባ የሚለው ድምጽ ቀዝቅዟል…. አንሷል…. ብሎ ግግም አለ አሉ… የሌባ አይነ ደረቅ አሙቁልኝ ይላል ማለት ይሄኔ ነው… ሃሃ( የዚህ ታሪክ ባለቤት እኔ ነኝ የሚል ካለ መውሰድ ይችላል… )
በጎንደር ከተማ አንዲት ሴት ከተማውን እሳት ልትለኩስ ስትል፤ በቁጥጥር ስር ውላ በፖሊስ እና ህዝብ አጀብ ታጅባ ”እሰይ ሞቅ አለለኝ” በሚል ኩራት ታጅባ ስትሄድ አይተናታል።

ይቺ ሴት ማናት? አላማዋስ ምንድነው? ጎንደርን እሳት ለመለኮስ ስትነሳ ስፖንሰር ያደረጋት ማነው? የትግራይ ተወላጅ ስለመሆኗ መታወቂያዋ ያስረዳል። ሴትዮዋን የላከቻት ኢህአዴግ መሆኗ ምንም ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ኢህአዴግ ይቺን ሴት ለአቃጣይነት ስትመለምላት ምን አስባ ነው? አትያዝም ብላ አስባ…. ? ወይስ ብትያዝም ቢሳካላትም ለኢህ አዴግ ፖለቲካዊ ጥቅም ያስገኝላታል… ?
እንደኔ አተያይ… ቢሳካላት የተለመደው ”አሸባሪዎች አቃጠሉ” ዜማ ይለቀቅብናል.. ባይሳካም ደግሞ በዝች ሴት የተነሳ ከትግራይ ህዝብ ጋር መቃቃር ውስጥ እንድንገባ እና እርስ በርሳችን ስንባላ ባለስልጣኖቹ ባለ ጊዜዎቹ ስራቸውን ሊሰሩ ይጠቅማቸዋል…
ለማንኛውም አሸባሪው መንግስት የላካት እጩ አሸባሪት በህዝብ ትብብር በቁጥጥር ስር ውላለች! እንኳንም ተያዘች… እውነት እውነት እላችኋለሁ ይቺን ሞቅ ባለ የእጩ አሸባሪ አቀባበል የታጀበች አሸባሪት በፍጹም ከትግራይ ህዝብ ጋር እንደማናዛምዳት እናረጋግጣለን!!!

No comments:

Post a Comment