- የመከላከያ እና ፖሊስ ሰራዊቱ ላይ አለመተማመኑ እየጨመረ መጥቷል።
- የደህንነት አባላቱ መረጃን በግል ጥቅም በመለወጥ እየሰሩ ነው የሚል ግምገማ ቀርቦባቸው ተንጠዋል።
- የሃገሪቱን ጉዳይ በተመለከተ ለበታች “ተከታይ ” ባለስልጣናት መረጃ መስጠት ቆሟል።
- የሕወሓት ታጣቂዎች ከምቾት ኑሮ ተነስተው ለመሸሽ እንጂ ታጥቀው ደም ለመፋሰስ ዝግጁ አይደሉም ።
በኢትዮጵያ ውስጥ መጭው ጊዜ በህዝቡ ዝምታ ተከትሎ በስርአቱ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ይከተላል የሚል መረጃ መሰማት ከጀመረ ጀምሮ በወያኔ ባለስልጣናት እና በቅርብ ሰዎቻቸው ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤ መኖሩን ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል።የአስመራ ተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ ሪሞት ኮንትሮል ወያኔ እጅ ነው ስለዚህ የትጥቅ ትግል ወያኔን አያስፈራውም ያሉት ምንጮች የሃገር ውስጥ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ወያኔ ልሙጥ የሚላቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ አጋር ዲያስፖራዎች በለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ህዝቡን በማንቃት ረገድ እያደረጉት ያለው ርብርብ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው እንዳስደነገጣቸው ሲታወቅ በድንጋጤ የመጣ ለኢሕአዴግ አንዳንድ ወቅታዊ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ያሉ ባለስልጣናት ከሃገር እንዳይወጡ እና ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ፓስፖርታቸውን ከመነጠቅ ጀምሮ በአይነቁራኛ እንደሚጠበቁ ታውቋል። የሕወሓት ታጣቂዎች ከምቾት ኑ
ሮ ተነስተው ለመሸሽ እንጂ ታጥቀው ደም ለመፋሰስ ዝግጁ እንዳልሆኑ ከምንጮቹ ተሰምቷል።በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣተር የሚረዱ ስብሰባዎች በስፋት ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ሰራዊቱም ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተሰረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል።የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል።በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መንግስት አቀፍ እንቅስቃሴ በተመለከተ ከሕወሓት ባለስልጣናት ውጪ ለበታች ተከታይ ባለስልጣናት ምንም አይነት መረጃ መስጠት እንደቆመ ሲታወቅ ማንኛውም ሃገራዊ ጉዳይ አልቆ እና በአፈጻጸም ደረጃ ላይ ሆኖ እንደማንኛውም ሰራተኛ እንደሚሰሙ ባለስልጣኖቹ በመናገር ላይ መሆናቸው ታውቋል ። በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ግምገማ የደህንነት አባላት መረጃዎችን በግል ጥቅም በመለወጥ አሳልፋቹ እየሸጣችሁ ናቸው በሚል መገምገማቸውን የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል።እንደ ምንጮቹ ከሆነ መረጃን ያለምንም ርሕራሔ መረጃው በአምስት ደኢቃ ውስጥ ጠላት እጅ ገብቶ ያገኘነው ነው ሲሉ የአዲስ አበባው ደህንነት ሹም አቶ ጸጋዬ ተናግረዋል።በዚህ ግምገማ የተከፉት የደህንነት አባላት በመንግስት ባለስልጣናቱ እየተናጡ ቢወረፉም ዝምታን መርጠዋል። #ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment