ኢሳት ዜና :- ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በአካባቢው የሰፈሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ የሚወስዱት እርምጃ እየተባባሰ መጥቶ ረቡዕ ሌሊት ለሃሙስ አጥቢያ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የፌደራል ፖሊሶች ወደ አንድ ወጣት መኖሪያ ቤት ሰብረው በመግባት እርሱንና እናቱን
ጅማ
በአምስት አምስት ጥይኦች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ወደ ካምፓቸው አምርተዋል። የከተማው ህዝብ ተቃውሞውን ለማሰማት ሃሙስ ጠዋት ወደ አደባባይ ቢወጣም የጠበቀው የፖሊስ ዱላ ነው።
እማኞች ለኢሳት እንደገለጹት ወ/ሮ መንበረ የተባሉ የከተማዋ ነዋሪ በሆቴል አገልግሎት ኑሮአቸውን የሚገፉና በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ የሚከበሩ ልጃቸው ዮናስም እንዲሁ በጸባዩ ምስጉን የሆነ የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚ ነው። የፌደራል ፖሊሶች ወደ ወ/ሮ መንበረ ሆቴል ገብተው ሲጠጡ ከቆዩ በሁዋላ አንከፍልም
በማለት መውጣታቸው ያበሳጨው ልጃቸው ወጣት ዮናስ ” የዚህ መንግስት አገልጋዮች ስለሆናችሁ ነው” በሚል ተናግሮአቸዋል። ወታደሮቹ ምንም ሳይሉ ወደ ካምፓቸው ካመሩ በሁዋላ ፣ ሌሊት ላይ መሳሪያቸውን ይዘው በመምጣት የዮናስ እናትን ቤት በር ሰብረው በመግባት ዮናስን በ5 ጥይት ደብድበውታል።
እናቱ ወ/ሮ መንበረ ” እባካችሁ ልጄን አትገደሉብኝ” ሲሉዋቸው ፖሊሶቹ እርሳቸውንም በ5 ጥይቶች ገድለዋቸው ወደ ካምፓቸው ተመልሰዋል።
ድርጊቱ ያስቆጣቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ከቀበር በፊት የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉም፣ በፖሊሶች ዱላ ተደብድበው ተበታትነዋል። ጅማ ጧት አካባቢ በተኩስ ስትናወጥ መዋሉዋንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ አንድ የጅማ ነዋሪ አነጋግረናል
ከአንድ ሳምንት በፊት አንዋር የተባለ ወጣት በጩቤ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደለ በሁዋላ ህዝብ ድርጊቱን ለመቃወም ወደ አደባባይ ቢወጣም በተመሳሳይ መልኩ በፖሊሶች ተደብድቦ ተባሯል።
ከአንድ ወር በፊት ደግሞ ኬኔዲ መንገሻ የሚባል አዲስ ቅጥር የመንግስት ሰራተኛ በፖሊሶች ተገድሏል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ በህዝቡ ላይ የሚወስደው እርምጃ መጨመሩ ህዝቡ በስጋት እንዲኖር አድርጎታል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እየሆነ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ የጅማ ፖሊስን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment