ይህ ዜና በዚህ መልኩ ተስተካክሎ ከመወጣቱ በፊት በድርጅቱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውይፋ ሆኖ ነበር። የደኢሕዴን ፌስ ቡክ ደረገጽ የመጀመሪያው መግለጫ የ1 ኛ ዙር ወጤት ሰለነበር ሰህተቱ መፈጸሙን አምኗል። የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በየጊዜው ሲቀያየር ቆይቶ በመጨረሻ አቶ ሺፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር፥ አቶ ሲራጂ ፈጌሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ቀደም በሎ ግን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ደኢሕዴን በፌስ ቡክ ገጹ መግላጫ አውጥቶ ነበር። እንዲህ አይነቱ መዘበራረቅ አገዛዙ ያልተረጋጋና ግራ የተጋባ መሆኑን እንደሚያመላክት የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ከወሰጥ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ በአቶ ሲራጅ ፈጌሳና አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ምርጫ መካካል ደህንነቱና መከላከያው እየተወዛገቡ ነበር። የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙ ጄናራል ሳሞራ የኑስ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመረጡ ጫና ሲያደርጉ ደህንነቱ ደግሞ ኣአቶ ሺፈራው ሽጉጤ እንዲመረጡ ሲያግባባ ነበር። ከምርጫው ጋር በተያየዘ የደሕዴን ፌስ ቡክ ደረ ገጽ ቆየቶ ባወጣው መግለጫ አቶ ሲራጂ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነዋል በሚል ያወጣው መረጃ የመጀመሪያ ዙር ወጤት ነበር ብሏል። እናም የመጀመሪያው መግለጫ የተሳሳተ ነበር ሲል ማስተባበያ አውጥቷል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ነገ እሮብ ይካሄዳል ከተባለ በኋላ ለሚቀጥለው ሳምንት ድንገት መቀየሩ በሃገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ተዘግቧል።ምክር ቤቱ የድርጅቱን ሊቀመንበር ለመምረጥ በነገው እለት ስብሰባ ያካሂዳል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ኢሕአዴግ ሊቀመንበሩን ነገ ካልመረጠ ደግሞ አርብ በሚካሔደው አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር አይሰየምም ማለት ነው። ፓርላማው ሲሰበሰብ በአስቸኳይ አዋጁ ላይ በመነጋገር ብቻ ወሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment