
ተጠናቀቀ። ህፃን መሐመድ እስኪነቃ ወደሚያርፍበት ክፍል ተወሰደ፡፡ ህፃን መሐመድ ግን ሊነቃ አልቻለም፡፡ የህክምና ባለሞያዎች ህፃን መሐመድ ከፍተኛ ክትትል የሚያስፈልግበት ሁኔታ ላይ እንደሆነ በመረዳት በድንጋጤ በመረባረብ የቻሉትን ማድረግ ጀመሩ፡፡ ሆኖም ህፃን መሀመድ መንቃት አልቻለም። የህክምና ባለሞያዎች ሁኔታውን በመመልከት ወደ ህይወት ማቆያ ክፍል እንዲገባ አደረጉት፡፡ በደቂቃዎች ይነቃል የተባለው ህፃን ለወራት እራሱን ከሳተበት ሊነቃ አልቻለም፡፡ የህክምና ባለሞያዎች በፈፀሙበት ስህተት ሳይነቃ ቀናት ወራት ተቆጠሩ። ዓመታት አለፉ።12 ዓመት። በ4 ዓመቱ ሆስፒታል የገባው ህፃን መሀመድ መንቃት ሳይችል 16 ዓመት ሞላው። ምንም መፍትሄ የለም። እናት ሃሊማ ላለፉት 12 ዓመታት ሆስፒታልና ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ቢቆዩም ለልጃቸው ፈውስና ፍትህ ሊያገኙ አልቻሉም። ለ9አመታት ባደረጉት ትግል ጉዳዩ የሳኡዲ የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዘንድ ደርሶ ጤና ጥበቃ ሚኒስተርም ጉዳዩን የሚያጣራ ከፍተኛ የህክምና ባለሞያዎችን ያቀፈ ቡድን በማዋቀር ጉዳዩን ለማጣራት ችሎ ነበር፡፡ አጣሪ ቡድኑም ህፃን መሐመድ አብዱልአዚዝ አሁን ላለበት ሁኔታ ዋነኛ ሰበቡ የህክምና ባለሙያዎች የተፈፀመ ስህተት መሆኑን አረጋገጧል፡፡ ሆስፒታሉ ለፈፀመው ጥፋት የ2.4 ሚሊዬን ሪያል ካሳ እንዲከፍል ኮሚቴው ውሳኔ አስተላለፏል። ይሁንና ወ/ር ሃሊማ እንደሚሉት የተባለው ካሳ ትክክለኛ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደሉም። እስካሁንም በእጃቸው የገባ ገንዘብ የለም። ወ/ር ሃሊማ አሁን ከአቅሜ በላይ ሆኗል። ለልጄም ማድረግ ያለብኝን አድርጌአለሁ። ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንም ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንዳልቻለ የገለጹት ወ/ሮ ሃሊማ ወደ ሀገር ቤት እንድመለስ የኢትዮጵያ ህዝብ ይተባበረኝ ስሉ ተማጽነዋል።
No comments:
Post a Comment