በእነ እስከዳር ይርጋ ክስ መዝገብ በ”በሽብር” ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህመም እንደሞተ የተገለጸ ቢሆንም፣ ታላቅ ወንድሙ ግን ሟቹ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለበት ገልጿል። ታላቅ ወንድሙ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ ሟቹ ከሶስት ቀናት በፊት አጎቱ ሲጠይቀው ምንም አይነት የጤና ችግር እንዳልነበረውና አሟሟቱ ደንገተኛ እንደሆነበት ለኢሳት ተናግሯል። አቶ ገበየሁ ፈንታሁን ማዕከላዊ 8 ቁጥር በሚባል ጨለማ ቤት ታስሮ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ በሹፍርና ሙያ ይተዳደር የነበረው አቶ ገበየሁ በ2009 ዓም የግንቦት7 አባል ነህ በሚል ከባህርዳር ተይዞ ከመጣ በሁዋላ የ4 አመታት እስር ተፈርዶበት ነበር። በዚሁ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 1ኛ ተከሳሽ እስከዳር ይርጋ ጥር 9/2010 ዓም የተፈታ ሲሆን፣ አቶ ገበየሁም ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።
No comments:
Post a Comment