
ሁኔታዎች በማባበልና አባል እንዲሆኑ በማስቻል ሕወሃት በሕዝብ ላይ ለሚፈጽማቸው ጥቃቶች መረጃ አቀባይ፣ጉዳይ ፈጻሚና የአገዛዙ የድጋፍ ሃይል በማድረግ ሲጠቀምባቸው ኖሯል። በዚህም ምክንያት የሕወሃት ካድሬዎች የበቀል ርምጃ ሲወሰድባቸው በሌላ በኩል ከአገዛዙ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበራቸው የትግራይ ተወላጆች የጥቃት ሰለባ መሆናቸው አግባብ አይደለም ብሏል መግለጫው። እናም የዚህ አይነቱን በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቃት መከላከል የሚያስፈልገው ኢፍትሃዊ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ሰላማችንና አንድነታችን አደጋ ስላለው ነው ሲል የሁለቱ ድርጅቶች መግለጫ አመልክቷል። ይህም ችግር የተፈጠረው አገዛዙ “ሕወሃትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ናቸው” በማለቱ መሆኑንም በምክንያትነት አስቀምጧል። ሕወሃት ላለፉት 25 አመታት በሕዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የትግራይ ምሁራን ዝምታን መምረጣቸው አግባብ እንዳልሆነም መግለጫው አሳስቧል። የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ በመግለጫው የትግራይ ምሁራን ዝምታቸውን ትተው ከሕዝቡ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የሕወሃት አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጭፍጨፋ በማውገዝ በቅርቡ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment