Tuesday, February 27, 2018

በነቀምት ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ። ዛሬ ጠዋት አንድ ወጣት በአልሞ ተኳሽ ወታደር መገደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂን በመጣስ ተቃውሞ እያደረጉ ባሉ የነቀምት ነዋሪዎች ላይ ተኩስ የከፈቱት የአገዛዙ ወታደሮች ከ20 በላይ ሰዎች ማቁሰላቸውም ታውቋል። ቤት ለቤት አፈሳ የተጀመረ መሆኑኑም ተመልክቷል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ኦፌኮ አመራሮች በወለጋ ደጋፊዎቻቸውን ለማግኘት ቀጠሮ የያዙት ከአስቸኳይ አዋጁ ይፋ መሆን ቀደም ብሎ ነበረ። አመራሮቹ መርሃ ግብራቸውን ጠብቀው በየከተሞቹ እየተገኙ ደጋፊዎቻቸውን ሲያነጋግሩ ቆይተው ወደ ነቀምት ያመራሉ። ነቀምት ለመድረስ 5 ኪሎ ሜትር ሲቀራቸው በኮማንድ ፖስቱ መታገታቸውን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት። የነቀምትን ስታዲየም ሞልቶ የሚጠብቃቸው ህዝብ ዜናውን ሲሰማ ወዲያኑ የተቃውሞ ድምጽ ማሰማት መጀመሩ በወቅቱ ተገልጿል። አስቸኳይ አዋጁ ስለሚከለክል ህዝብ መሰብሰብ አትችሉም የተባሉት የኦፌኮ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ነቀምት በተቃውሞ ተናወጠች። መንገዶች በተቃጠሉ ጎማዎች ተሞሉ። አገዛዙ ከስልጣን እንዲወርድ የሚጠይቁ መልዕክቶች አደባባይ በወጣው ህዝብ መስተጋባት ጀመሩ። ትላንት መሀል ነቀምት የጦርነት ቀጠና ይመስል ነበር። (ድምጽና

የፊታችን ሐሙስ የተጠራው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ ተራዘመ።

የምክር ቤቱ ስብሰባ የኢሕአዴግን ሊቀመንበር ለመምረጥና ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን ግለሰብ ለመወሰን እንደነበርም ለመረዳት ተችሏል። በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች በተለይም በሕወሃትና በኦሕዴድ መካከል ያለው ፍጥጫ ለስብሰባው መራዘም ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረም ታምኖበታል። ከእያንዳንዱ አባል ፓርቲ 45 በአጠቃላይ 180 አባላት ያሉት የኢሕአዴግ ምክር ቤት በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ምትክ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርን ለመምረጥ ስብሰባ የተጠራው ለፊታችን ሀሙስ የካቲት 22/2010 ነበር። በዚህ ስብሰባ ላይ የሚመረጠው የኢሕአዴግ ሊቀመንበር አርብ በተጠራው የፓርላማው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ እንደሚሰየም የተጠበቀ ቢሆንም ምክንያቱ ባልተገለጸ ሁኔታ ስብሰባው ተራዝሟል። ለአንድ ሳምንት የተገፋውና እንደገና ለቀጣዩ ሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር የተያዘለት የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በተለመደው አሰራር በስራ አስፈጻሚው በቀረቡለት ሶስት እጩዎች ላይ ድምጽ መስጠት ይጠበቀበት ነበር፡ አዲስ ፎርቹን ከአዲስ አበባ እንደዘገበው። ሆኖም ይህንን የተለመደ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የማያስችል ሁኔታ በመፈጠሩ በድርጅቱ የ29 አመታት ታሪክ ድምጽ እስኪሰጥ ድረስ የሚመረጠው ሰው የማይታወቅበት ሁኔታ ተከስቷል። እንደከዚህ ቀደሙ በሚቀርቡት እጩዎችም ሆነ በሚመረጠው ግለሰብ ላይ በኢሕአዴግ ደረጃ ስምምነት ባለመኖሩ ለሊቀመንበርነቱ ሶስት ሰዎች ከፊት መስመር ላይ መቆማቸው

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በሁለተኛ ዙር ምርጫ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።

ይህ ዜና በዚህ መልኩ ተስተካክሎ ከመወጣቱ በፊት በድርጅቱ ፌስ ቡክ ገጽ ላይ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውይፋ ሆኖ ነበር። የደኢሕዴን ፌስ ቡክ ደረገጽ የመጀመሪያው መግለጫ የ1 ኛ ዙር ወጤት ሰለነበር ሰህተቱ መፈጸሙን አምኗል። የደኢሕዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ በየጊዜው ሲቀያየር ቆይቶ በመጨረሻ አቶ ሺፈራው ሽጉጤን ሊቀመንበር፥ አቶ ሲራጂ ፈጌሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። ቀደም በሎ ግን አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን ደኢሕዴን በፌስ ቡክ ገጹ መግላጫ አውጥቶ ነበር። እንዲህ አይነቱ መዘበራረቅ አገዛዙ ያልተረጋጋና ግራ የተጋባ መሆኑን እንደሚያመላክት የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ። ከወሰጥ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ በአቶ ሲራጅ ፈጌሳና አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ምርጫ መካካል ደህንነቱና መከላከያው እየተወዛገቡ ነበር። የመከላከያ ኢታማዦር ሹሙ ጄናራል ሳሞራ የኑስ ሲራጅ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመረጡ ጫና ሲያደርጉ ደህንነቱ ደግሞ ኣአቶ ሺፈራው ሽጉጤ እንዲመረጡ ሲያግባባ ነበር። ከምርጫው ጋር በተያየዘ የደሕዴን ፌስ ቡክ ደረ ገጽ ቆየቶ ባወጣው መግለጫ አቶ ሲራጂ ፈጌሳ ሊቀመንበር ሆነዋል በሚል ያወጣው መረጃ የመጀመሪያ ዙር ወጤት ነበር ብሏል። እናም የመጀመሪያው መግለጫ የተሳሳተ ነበር ሲል ማስተባበያ አውጥቷል። የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ነገ እሮብ ይካሄዳል ከተባለ በኋላ ለሚቀጥለው ሳምንት ድንገት መቀየሩ በሃገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ተዘግቧል።ምክር ቤቱ የድርጅቱን ሊቀመንበር ለመምረጥ በነገው እለት ስብሰባ ያካሂዳል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ኢሕአዴግ ሊቀመንበሩን ነገ ካልመረጠ ደግሞ አርብ በሚካሔደው አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር አይሰየምም ማለት ነው። ፓርላማው ሲሰበሰብ በአስቸኳይ አዋጁ ላይ በመነጋገር ብቻ ወሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሶማሌ ክልል ከሚገኘው ጄል ኦጋዴን እስር ቤት በይቅርታ ተፈቱ የተባሉ ከ1500 በላይ እስረኞች ተመልሰው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ መደረጉ ተገለጸ።

 ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ሽፋን የሰጡት የፍቺ ዜና ሳምንት ሳይሞላው እስረኞቹ ወደ ጄል ኦጋዴን ገብተዋል ያለው የሶማሌ ክልል ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ መገናኛ ብዙሃኑ በአስቸኳይ የሰሩትን ዜና እንዲያስተባብሉ ጠይቋል። እስረኞቹ መፈታታቸው ተገልጾ፣ ፎግራፍና ቪዲዮ ከተቀረጹና ዜና ከተሰራጨ በኋላ የዚያኑ ዕለት ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን የአክቲቪስቶቹ መረብ ለኢሳት በላከው መረጃ ላይ ተገልጿል። ጄል ኦጋዴን በሶማሌ ክልል ጂጂጋ አቅራቢያ የሚገኝ ከሀረር ከተማ በ80ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለ እስር ቤት ነው። ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምበት እስር ቤት በመሆኑ በዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ‘’የሰቆቃ ማዕከል’’ በሚል እንደሚጠራ ይነገራል። ከጄል ኦጋዴን ገብቶ በህይወት መትርፍ የማይታሰብ ይላሉ የሶማሌ ክልል ተወላጆች የአክቲቪስቶች መረብ ሰብሳቢ አቶ ጀማል ዲሪዬ። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጄል ኦጋዴን ከ1500 በላይ እስረኞች መለቀቃቸው ሲሰማ ለብዙዎች ያልተጠበቀ ዜና ሆኖ ነበረ። የሶማሌ ክልል መንግስት የተፈቱትን እስረኞች በሰልፍ ደርድሮ፡ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃንን ጋብዞ የእስረኞቹን መፈታት ሲገልጽ ለቤተሰቦቻቸው ትልቅ ደስታ እንደነበረ በወቅቱ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ከሮይተርስ በተጨማሪ ኤኤፍፒ ፡

ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላም ቢሆን ሕዝቡ ተቃውሞውን በመቀጠሉ የአገዛዙ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ መታዘዙን የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት ገለጸ።

 ኮማንድ ፖስቱ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴና ደምቢዶሎ የተካሄደውን የሕዝብ ተቃውሞ በመጥቀስ የአገዛዙ ታጣቂዎች የሕዝብ ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ ከማድረግ ይልቅ ርምጃ እንዲወስዱ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል። የፓርላማ አባላት አስቸኳይ ጊዜውን እንዳያጸድቁ በሕዝብ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑም ሕገ ወጥ ተግባር ነው ብሏል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፉት ሁለትና ሶስት ቀናት በኦሮሚያ አካባቢዎች በተለይም በነቀምቴና ደምቢዶሎ የተፈጠረው ሁኔታ የአፈጻጸም መመሪያውን የጣሰ ነው ብሏል። በነዚሁ አካባቢዎች የእጅ ቦምቦች ሳይቀር ተወርውረዋል ያለው መግለጫ የመንግስት ታጣቂዎች የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ጥንቃቄ በማድረጋቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አስታውሷል።ተቃውሞውን ያስነሱት ጸረ ሰላም ሃይሎች ናቸው ሲልም የሕዝቡን ተቃውሞ መግለጫው አጣጥሎታል እናም የአገዛዙ ታጣቂዎች መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገራቸውን ተረድቻለሁ ነው

Monday, February 26, 2018

በነቀምቴ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ።

Image may contain: one or more people, people standing, people walking and outdoorበነቀምቴ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ለሰዓታት ታግተው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጋቸውን ተከትሎ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ የአገዛዙ ታጣቂዎች ህዝቡ ላይ ሲተኩ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል። ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ አልወጣም። ደጋፊዎቻቸውን ለማግኘት ወደ ወለጋ ያመሩት የኦፌክ አመራሮች አስቸኳይ አዋጁን የሚጥስ ተግባር ነው በሚል በፌደራል ፖሊስ ጉዛቸውን እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። በደምቢዶሎ በሳምንቱ መጨረሻ በአገዛዙ ታጣቂዎች በተወሰደ

በሳዑዲ አረቢያ ለ12 ዓመታት በስቃይ ሆስፒታል የሚገኘው ልጃቸው ፍትህ እንዲሰጠው ኢትዮጵያዊቷ እናት የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ።

Image may contain: 1 person, selfie and closeupወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚል ሁሴን በህክምና ባለሙያዎች በተፈፀመ ስህተት መንቃት ሳይችል የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የቀረው ልጃቸውን ይዘው ወደ ሀገር ቤት ለመግባት የኢትዮጵያውያንን ድጋፍ ጠይቀዋል። ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳላደረገላቸው የገለጹት ወ/ሮ ሃሊማ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው እንዲቆም መጠየቃቸው ታውቋል። ህፃን መሐመድ አብዱለዚዝ ከወላጅ እናቱ ከወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚል ሁሴን እና ከአባቱ አቶ አብዱልአዚዝ ያህያ በሳኡዲ አረቢያ በመካ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡ ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ሃሊማ ሙዘሚል ሁሴን እንደሚሉት ልጃቸው የ4 አመት ህፃን በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ቀላል የአተነፋፈስ ችግር ለህክምና በሚል በጅዳ ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ በሆስፒታሉ የገጠማቸው ግን ያልተጠበቀ ዱብእዳ ሆነባቸው። ህጻን መሀመድ ቀላል የቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው የህክምና ባለሙያዎቹ ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ። ቀዶ ጥገና ህክምና ሊደረግለት የ4 ዓመቱ ህጻን መሀመድ ይወሰዳል። ቀዶ ጥገናው ደቂቃዎች ይወስዳል ቢባልም ረጅም ሰአታትን ፈጅቶ

የዋልድባ መነኮሳት በእስር ቤት የሚደርስባቸውን በደል አስመልክቶ ለፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳወቁ

ታሪካዊው የዋልድባ ገዳም ይዞታችን አይነካ ማለታቸውን ተከትሎ ከዋልድባ ገዳም ተይዘው በማእከላዊና በተለያዩ እስር ቤቶች ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው የቆዩት መነኮሳት የደረሰባቸውን ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት በደብዳቤ አሳውቀዋል። በጻፉት ደብዳቤ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰቶች በዝርዝር አቅርበዋል። መነኩሳቱ በጻፉት ደብዳቤ እንደገለጹት መነኮሳት እንደመሆናችን ሃይማኖታችን የሚያስገድደንን የራሳችን አልባሳት አስኬማ እንጠቀማለን። ይህን አልባሳታችን የምናወልቀው ስንሞት ብቻ ነው። ይህን አልባሳታችንን እንድንለውጥ መገደድ ማለት እምነታችንን እንድንሽር፣ በእግዚያብሔር ስም የተሰጠንን ክብር እንዲዋረድ ማድረግ እንደሆነ ይሰማናል። በመሆኑም የእምነት ልብሳችንን ከምንቀይር የስጋ ሞታችንን እንደምንመርጥ ለእስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች በተደጋጋሚ ገልጸናል። ይሁን እንጅ የእስር ቤቱ አስተዳደር መጀመርያ ላይ ተቃውሟችንን የተቀበለ የመሰለ በመሆኑ በእኛ በኩል ለዚህ ፍርድ ቤት አቅርበን የነበረውን አቤቱታ ሳንገፋበት ቀርተናል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የእስር ቤቱ አስተዳደር አልባሳቱን እንድናወልቅ ከፍተኛ ጫና እያደረገብን ከመሆኑም በላይ ለከፍተኛ እንግልትና መዋረድ ተዳርገናል። 5ኛ ተከሳሽ አባ ገብረስላሴ ወልደሃይማኖት የደረሰባቸውን ሰቆቃ በዝርዝር ሲገልጹ ”ወደዚህ ፍርድ ቤት ለመምጣት የእምነት ልብሴን እንዳወልቅ ስጠየቅ አላወልቅም በማለቴ ማዕረጋቸውንና የአባታቸውን

አቶ ገበየሁ ፈንታሁን በእስር ቤት ውስጥ ህይወታቸው አለፈ

በእነ እስከዳር ይርጋ ክስ መዝገብ በ”በሽብር” ክስ አራት አመት ተፈርዶበት ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ የነበረው 2ኛ ተከሳሽ ገበየሁ ፈንታሁን ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ግለሰቡ በህመም እንደሞተ የተገለጸ ቢሆንም፣ ታላቅ ወንድሙ ግን ሟቹ ምንም አይነት የጤና ችግር እንደሌለበት ገልጿል። ታላቅ ወንድሙ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ ሟቹ ከሶስት ቀናት በፊት አጎቱ ሲጠይቀው ምንም አይነት የጤና ችግር እንዳልነበረውና አሟሟቱ ደንገተኛ እንደሆነበት ለኢሳት ተናግሯል። አቶ ገበየሁ ፈንታሁን ማዕከላዊ 8 ቁጥር በሚባል ጨለማ ቤት ታስሮ ድብደባ ተፈጽሞበታል፡፡ በሹፍርና ሙያ ይተዳደር የነበረው አቶ ገበየሁ በ2009 ዓም የግንቦት7 አባል ነህ በሚል ከባህርዳር ተይዞ ከመጣ በሁዋላ የ4 አመታት እስር ተፈርዶበት ነበር። በዚሁ መዝገብ ከተከሰሱት ውስጥ 1ኛ ተከሳሽ እስከዳር ይርጋ ጥር 9/2010 ዓም የተፈታ ሲሆን፣ አቶ ገበየሁም ይፈታል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።

የባህርዳር ከነማና የደሴ ከነማ ደጋፊዎች ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ባለፈው ቅዳሜ የባህር ዳር ከነማ እና ደሴ ከነማ የእግር ኳስ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተመልካቾች አገዛዙን የሚያወግዙ መፈክሮችን አሰምተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 10 “ በስፖርት ማዘውተሪያዎች ማዕከላት ከስፖርት ተግባር ውጪ የሆኑ ሁከቶችና ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ ነው” ቢልም ተመልካቾች፣ ተቃውሞአቸውን ከመግለጽ ወደ ሁዋላ አላሉም። ተመልካቾች “ ቢመችሽም፣ ባይመችሽም፣ አንች ወያኔ አለቅሽም፣ ወያኔ ሌባ፣ መሰናበቻ መሰናበቻ አሁን የቀረው ወያኔ ብቻ” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች አሰምተዋል። በፒክ አፑ መኪና ተጠግተው ከሚያልፉት ወጣቶች መካከል ወታደሮች ወደ መኪናችን ተጠጋህ በሚል አንዱን ወጣት መደብደባቸውን ተከትሎ “አትምታው” በሚል ተቃውሞ ተነስቷል። በግርግሩ መካከል የተነሳውን ጩኸት የሰሙ ወጣቶች በአካባቢው ያገኙትን ድንጋይ በመያዝ እየወረወሩ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ፣ ወታደሮች በጉዳዩ ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸውን ተመልካቾች እና በፊት ለፊት የሚገኙ የከተማዋን ነዋሪዎች ጨምር በ ዱላ በመደብደብ በህዘቡ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በህዝብ መካከል ገብቶ በመደባደብ ላይ የነበረን የአገዛዙ ወታደር ወጣች ጎትተው ዱላውን በማስጣል በራሱ ዱላ ሲመቱት እንደነበር በአቅራቢያው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ በተለያዬ አቅጣጫ በመበታተን አካባቢውን ቢለቁም፣ ወታደሮች የጪሰ ቦንብ በመያዝ መንደር ለመንደር በማባረር ጉዳት ሲያደርሱ ታይተዋል፡፡አሰሳው ምሽትም በመቀጠል በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል በሚል የጠረጠሯቸውን ወጣቶች ለማሰር ተንቀሳቅሰዋል።

የነቀምት ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በኦሮምያ ክልል በወለጋ ነቀምት ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ በአካባቢያቸው የተሰማሩት ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲሰረዝ በአጠቀላይ አገዛዙን የሚያወግዙ መፍክሮች ተሰምተዋል። የአጋዚ ወታደሮች በህዝቡ ላይ የተኮሱ ሲሆን፣ ጉዳት መድረሱና አለመድረሱ የታወቀ ነገር የለም። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር ቀደ ነቀምት ሲጓዙ መንገድ ላይ በወታደሮች በመታገታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎቹወደ ከተማ ለመግባት የነበራቸውን እቅድ በመሰረዛቸው ግጭት እንዳይፈጠር ለማድረግ ችለው ነበር። በአገዛ ወታደሮች ድረጊት የተበሳጨው ህዝብ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል።

Sunday, February 25, 2018

“እኔ ተፈታሁ እንጂ፤ የታሰርኩበት ዓላማ አልተፈታም” ኢየሩሳሌም ተስፋው

የሐበሻ ወግ፡- ኢየሩሳሌም ተስፋው፤ በቅድሚያ በቅድሚያ ከእስር ስለተፈታሽ እንኳን ደስ አለሽ?

ኢየሩሳሌም፡- ለወጉ ያህል “እንኳን ደስ አለህ” ልበልህ እንጂ፤ እኔ እንኳን ብዙም ደስ አላለኝም፡፡


የሐበሻ ወግ፡- ማለት?

ኢየሩሳሌም፡- ገና ነው፤ ደስታችን ሙሉ አይደለም፡፡

የሐበሻ ወግ፡- መልካም፤ አንቺም የተከሰስሽውና የታሰርሽው በግንቦት ሰባት የተነሳ ነው….

Wednesday, February 21, 2018

በጉራጌ ዞን የተጀመረው አድማ እንዲቆም ማድረጉን ዘርማ አስታወቀ።

 በዞኑ የሚካሄደውን ትግል የሚያስተባብረው የጉራጌ ወጣቶች ስብስብ ዘርማ ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየውን የስራ ማቆም አድማ ዛሬ እንዲቆም ያደረገው ለቀጣዩ ትግል ተጠናክሮ ለመውጣት ነው ብሏል። በሁሉም የጉራጌ ወረዳዎች የሚደረግ አድማና ተቃውሞ ለማዘጋጀት በማቀድ ላይ መሆኑንም ለኢሳት በደረሰው መረጃ ላይ ተመልክቷል። ከዛሬ ጀምሮ ስራ ያቆሙ የንግድ ቦታዎችና ተሽከርካሪዎች ወደ እንቅስቃሴ እንዲገቡ ዘርማ መልዕክት አስተላልፍፏል። አድማውን መቆጣጠር ያልቻለው አገዛዙ፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለስልጣናትንና የደህንነት ሃይሎችን በጋራ የያዘ ግብረሃይል ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ መላኩም ታውቋል። ዘርማ በጉራጊኛ ወጣት ማለት ነው። የጉራጌ ወጣቶች በዘርማ መጠሪያነት የጀመሩት ትግል እየተጠናከረ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የካቲት 6 የጀመረው በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ዛሬ እንዲቆም መወሰኑን የገለጸው የጉራጌ ወጣቶች ስብስብ ዘርማ የጉራጌ ህዝብ ለተጠናከረ ትግል እንዲዘጋጅ ጥሪ አድርጓል። ወልቂጤ ሊገነባ የታቀደው የዘመናዊ ሆስፒታል ግንባታ ፕሮጀክት ወደትግራይ ተዛውሯል የሚል መረጃ ሰበብ ሆኖ የተጠራቀመ ብሶትና ምሬቱ ፈንቅሎ አድማ ያስጠራው የጉራጌው ተቃውሞ ለሳምንት ቆይቶ ዛሬ እንዲቆም ተወስኗል። የዛሬ ሳምንት ረቡዕ በወልቂጤ

ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈጽም መመሪያ መውጣቱን የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን ገለጹ።

 የአውሮፓ ህብረት፣ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ፣የብሪታኒያና የጀርመን መንግስታት የተቃወሙትን ይህንን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የወጣው ዝርዝር መመሪያ የአደባባይ ሰልፍና የአዳራሽ ስብሰባን ጭምር ከልክሏል። ማናቸውም ወገን ባለስልጣናት ጭምር በጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ለመስጠት ኮማንድ ፖስቱን ማስፈቀድ እንዳለባቸውም አሳስቧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈጽመው መመሪያ ላይ የትራንስፖርት አገልግሎትን ማወክ፣ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረስ፣የሕግ አስከባሪዎችን ተግባር ማወክ፣በትምህርት ተቋማትና በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች አድማ ማድረግ፣ሁከትና ብጥብጥ የሚያነሳሱ ተግባራትን መፈጸም የሚሉትና ሌሎችም ተዘርዝረዋል።የአውሮፓ ህብረት፣አሜሪካ፣ብሪታኒያና ጀርመን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተቃውመውታል። ነገር ግን ሀገራቱ ተቃውሟቸውን ቢያሰሙም የሕወሃት ስርአት ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያ በማውጣት የአደባባይ ሰልፍና የአዳራሽ ስብሰባን ጭምር መከልከሉን አስታውቋል። የፖለቲካ አጀንዳ ማስተጋባትን ሲከለክል ስብሰባ ለማድረግ ፍቃድ መጠየቅን ደግሞ እንደ ግዴታ

Ethiopia: Amhara region continues strike, Gurage zone takes respite to strategize

The three day strike called in the Amhara region went as planned with businesses and transportations shutdown on Wednesday, the third day of the strike called as a show of persistent rejection of the TPLF rule and the recently declared state of emergency. The strike was more prevalent in the city of Gondar while most parts of Bahir Dar have seen shops closed and services interrupted.
Residents who own shops and transportation vehicles have continued the strikes despite threats by authorities of the consequences of severe financial penalties.

Ethiopia: “Game over TPLF,” says U.S. Congressman by Engidu Woldie

A United States Congressman said today in a tweet that the game is over as far as the TPLF regime in Ethiopia is concerned.
Congressman Dana Rohrabacher, a senior member of the House Committee on Foreign Affairs, is a strong critic of the Ethiopian regime. Rohrabacher does not mince words when it comes to brutal regimes anywhere, telling it it like it is.

የዓለም የኢኮኖሚክስ ፎርም የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ባለፉት ስድስት ወራት ከቱሪዝም ዘርፍ ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ በማለት ያወጣውን የውሸት ሪፖርት ውድቅ አደርገው።

 ፎርሙ ከዘርፉ የተገኘው 440 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው ብሏል። በሌላ በኩል ወደተለያዩ አካባቢዎች የተጓዙ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ጉዟቸው መስተጓጎሉንና በመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት ወደ ሐዋሳና አርባምንጭ ተወስደው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውንና ሌሎችም ጉዟቸውን እየሰረዙ መሆናቸውም ታወቋል። የኢትዮጵያ ቱሪዝም ከግዜ ወደግዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን የዘርፉ ባለሙያዎችና የምጣኔ ሀብት ምሁራን ይናግራሉ። እነዚህ አካላት እንደሚሉት የቱሪዝም እንቀስቃሴው ለመዳከሙ በዋናነት የሚጠቀሰው በሀገሪቷ ውስጥ ያለው አለመርጋጋት መሆኑንም ያነሳሉ ። በተለይም ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት በሀገሪቷ ተከስቶ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞና እንቢተኝነት የውጭ ሃገር ጎብኚዎች ወደ ሀገሪቱ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ መሰረዝ አሊያም የግዜ ቆይታቸውን በማሳጣር ወደ መጡበት ሲመለሱ ተስተውለዋል ። ይህ በሆነበት ታዲያ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የቱሪዝም ዘረፉ ውጤታማ መሆኑንና አለም አቀፍ ጎብኝዎችም ወደ ሀገሪቱ ያለስጋት

Tuesday, February 20, 2018

እንግሊዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ እንደሳዘናት ገለጸች

የአገሪቱ የውጭ ግንኙነት መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ፣ “ ወዳጃችን እና አጋራችን ኢትዮጵያ አሳሳቢ በሆነ ጊዜ ላይ ትገኛለች” ብሎአል። ስርዓት ባለው መልኩ የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት አወንታዊ ቢሆንም፣ ይህንን ጥረት የሚያበላሽ ፣ አሳሳቢና አሳዛኝ የሆነ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ሲል በአዋጁ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጽ አድርጓል። አዋጁ ለአለማቀፉ ማህበረሰብ እና ለውጭ አገር ባለሀብቶች ተስፋ የሚያስቆርጥ መልእክት የሚሰድ መሆኑን የገለጸው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ፣ አዋጁ ጊዜ አጭር እንዲሆን እንዲሁም እስካሁን የተደረጉ ለውጦችንም መልሶ የሚንድ እንዳይሆን ተስፋ እናደርጋለን ሲል አክሏል። የሰብአዊ መብቶቸና ህገ መንግስቱ እንዲከበር ፣ ሰዎችን በስፋት የማሰር እንቅስቃሴ እንዲገታና የተጣለው የኢንተርኔት እገዳም እንዲነሳ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጠይቋል። መንግስት ፈጣን፣ ግልጽ፣ ሰላማዊ እና ህገመንግስቱን በጠበቀ ሁኔታ አዲስ አመራር እንዲሰይምና ይህም አመራር የተጀመረው የለውጥ ሂደት እንዲቀጥል እድል እንዲሰጠው መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። የአሜሪካ መንግስት እና የአውሮፓ ህብረተም እንዲሁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አጥብቀው ተቃውመዋል። አዋጁ በአገሪቱ እያሽቆለቆለ ያለውን ኢኮኖሚ ይበልጥ የሚጎዳው መሆኑን በመግለጫው ጠቅሰዋል። ምዕራባውያን አገራት አዋጁን እየተቃወሙት ቢሆንም፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት አዋጁ አገር ለማረጋጋትና የንብረት መውደምን ለመከላከል አስፈላጊ በመሆኑ እንገፋበታለን የሚል መግለጫ እየሰጡ ነው።

ወጣት ንግስት ይርጋን ጨምሮ የተወሰኑ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ተፈቱ

Image may contain: 1 person, smiling, standingሰሜን ጎንደር ተጀምሮ በአማራ ክልል የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ተቃውሞ ፊት ሆነው ከመሩትና ካስተባበሩት መካከል በግንባር ቀደምነት የምትጠራዋ ወ/ት ንግስት ይርጋ ከሷ ተቋርጦ ከእስር ቤት ወጥታለች። በሽብር ወንጀል የተከሰሰችው ወ/ት ንግስት ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት በተዘዋወረችበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባታል።ወ/ት ንግስት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ እስር ቤት በቀዝቃዛና በጨለማ ክፍል ውስጥ ለረጅም ቀናት ታስራለች፣ ያለማንም ጠያቂ፣ ያለችበት ሁኔታ ሳይታወቅ ታፍና ለሳምንታት እንድትቆይ ተደርጋለች፣ ማታ ለምርመራ በሚል ከታሰረችበት ክፍል እየወጣች ሰብዓዊ ክብሯን የሚያዋርዱ ስቃዮች ደርሶባታል፣ በማንነቷ ላይ የተመሰረቱ ስድቦችን ተሰድባለች ፣ ሴትነቷን ተመስርተው ጥቃት እንደፈጸሙባት መናገሯ ይታወሳል። “ ሴት ሁኜ መፈጠሬን እንድትጠላ የሚያደርጉ ተግባራትን እንደተፈጸሙባት፣ እርቃኗን አቁመው እንደተሳለቁባት ፣ የእግር ጥፍሮቿን መርማሪዎቿ እንደነቀሉባት፣ ጥፍሮቿን ከነቀሉ በኋላም ጥፍሮቹ የነበሩበትን ቦታ ቁስል እየነካኩ እንዳሰቃዩዋት እንዲሁም ጸጉሯን በመንቀልም የኢ-ሰብዓዊ ተግባር ሰለባ

በአማራ ክልል የተጠራው የስራ ማቆምና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ።

በመጀመሪያው ቀን አድማ ያልተሳተፉ ከተሞች ዛሬ ተቀላቅለዋል። ጎንደር በተጠናከረ መልኩ የአድማውን እንቅስቃሴ እያደረገች ነው። በባህርዳር በአብዛኛው ሱቆችና መደብሮች ተዘግተዋል። ባህርዳር ከትላንት ይልቅ ዛሬ አድማ ላይ ጠንክራ ብቅ ብላለች። በአገዛዙ ታጣቂዎች ወከባ ከፍተው የነበሩ አንዳንድ የንግድ ቦታዎች ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ አድማውን መቀላቀላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በተለይ በቀበሌ 4 ቡቲክ ተራ፣ ቀበሌ 12 ሜላት መስመር የሚገኙ የንግድ ቦታዎች ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ከታጣቂዎች ጋር ሆነው ለማስከፈት እየተንቀሳቀሱ ቢሆንም የአንዳቸውም የንግድ መደብር እንዳልተከፈተ ለማወቅ ተችሏል። ትላንት በባህርዳር ፓፒረስ በሚባል ሆቴል አቅራቢያ በሚገኝ የደህንነትና ፖሊስ መሰባሰቢያ ቦታ አካባቢ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙም ታውቋል። በዚሁ ጥቃት የደህንነት ክፍሉ ተሽከርካሪ መውደሙ ተገልጿል። አደጋውን ያደረሰው አካል አልታወቀም። በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። የአድማውን ጥሪ ባለመቀበል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 6 ተሽከርካሪዎችም ጥቃት እንደተፈጸመባቸው መረጃዎች አመልክተዋል። ጎንደር ዛሬ ሙሉ በሙሉ

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የተጠራው አድማ ለሰባተኛ ቀን መቀጠሉ ተገለጸ።

 የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑ ሁለት ሰዎች አድማውን አስተባብራችኋል ተብለው ታስረዋል። በእንድብርና በአገና የፌደራል ፖሊስ የሃይል ርምጃ እየተጠቀመ ነው። የጉራጌ ወጣቶች ጥሪ አድረግዋል። በወልቂጤ የተጀመረው አድማ ሳምንቱን ደፍኗል። ዛሬም ወደ እንቅስቃሴ አልገባችም። ባለፉት ሁለት ቀናት አንዳንድ የንግድ ቦታዎች ተከፍተው የነበረ ቢሆንም ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም በኋላ በአድማው የቀጠለችው የወልቂጤ ከተማ ሆቴሎች፣ ንግድ ቤቶች፣ የተዘጉ ሲሆን በከተማዋ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንደተቋረጠ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው የአድማው አስተባባሪዎች እንደሚሉት የጉራጌ ህዝብ የተጠራቀመውን ብሶትና በደል ከዚህ በኋላ የሚሸከምበት ትከሻ የለውም። የህዝቡን ፍላጎት እየተከተልን ተቃውሞንና አድማውን እንቀጥላለን ብለዋል። ትላንት ሁለት የአገዛዙ አባላት አድማውን ታስተባብራላችሁ ተብለው መታሰራቸውም ታውቋል። ለኢሳት የደረሰው መረጃ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ አምባገነን አገዛዝ መሸጋገር አለመሆኑን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት የምንታገልለት ለውጥ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል። በለውጡ ሂደት ስልጣን ሃላፊነት በሌላቸው እጅ እንዳይገባ በከፍተኛ የሃላፊነትና የአጣዳፊነት ሁኔታ መታገል አለብን ሲሉም ገልጸዋል። ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ የወቅቱን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የሕወሃት/ኢሕአዴግ አገዛዝ ለብሔራዊ እርቅ ደንታ እንደሌለው በአሁኑ ጊዜ የደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አመላካች ነው ብለዋል። ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቀባይነት የሌለውና እንደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሚቆጠር ነው ባይ ናቸው።–የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ። እንደ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጻ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎት ከአንድ አምባገነን ወደ

ክሳቸው ተቋርጦ እንዲሁም በፕሬዝዳንቱ ይቅርታ ይፈታሉ ከተባሉ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው ዮናታን ተስፋዬ አሁንም አለመፈታታቸው ታወቀ።

 ክሳቸው ተቋርጦ እንዲሁም በፕሬዝዳንቱ ይቅርታ ይፈታሉ ከተባሉ የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ እነ ጄኔራል ተፈራ ማሞ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረው ዮናታን ተስፋዬ አሁንም አለመፈታታቸው ታወቀ። በክስ መቋረጥም ሆነ በይቅርታ ስማቸው ያልተጠቀሰው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌንና የኢትዮጵያ አየር ሃይል አብራሪ መቶ አለቃ በሃይሉ ገብሬን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችም እንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ መድረክ ዘመቻ ጀምረዋል። ከጎንደሩ ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ ከታሰሩት ውስጥ ክሳቸው ተቋርጦ ይፈታሉ ከተባሉት የፖለቲካ እስረኞች ውስጥ በአማራ ክልል የታሰሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ የተወሰኑት ሲለቀቁ በፌደራል ወህኒ ቤት የሚገኙት ሌሎቹ እስረኞች አለመፈታታቸው ታውቋል። የዋልድባ ገዳም እንዳይፈርስ በተለይም ይዞታው እንዳይነካ ሲንቀሳቀሱ የታሰሩት መነኮሳትም ክሳቸው እንደተቋረጠ ቢገለጽም እስካሁን ግን አለመፈታታቸው ታውቋል። ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞና ብርጋዴር ጄኔራል

Wednesday, February 14, 2018

በኦሮምያ ተቃውሞው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ። በደቡብ በወልቂጤ ለ2 ቀናት የሚቆየው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀምሯል

በኦሮምያ ተቃውሞው ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ
በደቡብ በወልቂጤ ለ2 ቀናት የሚቆየው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ተጀምሯል
(ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) በኦሮምያ ክልል በተለያዩ ከተሞች የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ለ3ኛ ቀን ቀጥሎ ውሎአል። በአዳማ ከእስር የተለቀቁትን የኦፌኮ ምክትል ሊ/መንበር አቶ በቀለ ገርባም ለመቀበል በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ ድጋፉን ገልጿል። አገዛዙን የሚያወግዙ መፈክሮችም ተሰምተዋል። ወጣቶቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ደም ደማቸው መሆኑን፣ ቄሮ ኢትዮጵያን ለማቋቋም ነው እንጅ ለመገንጠል አይደለም” የሚሉ አንድነትን የሚሰብኩ መፈክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል።
በአዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች በተለይም በወለቴ፣ ሰበታና ለገጣፎ ወጣቶች “ እንዲህ ነን” እያሉ ሲጨፍሩ አገዛዙን ሲያወግዙ ውለዋል።
በወሊሶ ህዝቡ ወደ ስታዲየም በመትመም “መንግስት ስልጣኑን ይልቀቅ፣ ፍትሀዊ ምርጫ ይደረግ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከእስር ተለቀቁ

የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) ታዋቂውን ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋን እንዲሁም የቀድሞውን አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዱላአለም አራጌን ጨምሮ፣ በአገዛዙ ከፍተኛ በደልና ሰቆቃ የተፈጸመባት እማዋይሽ ዓለሙ፣የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር የሆኑት እነ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ፣
አርበኞች ግንቦት7 ትን ሊቀላቀል ሲል መንገድ ላይ እንደተያዘ የተነገረለት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ እና የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ አንዱዓለም አያሌው ፣በኦነግ ስም የተከሠሰችው የዩኒቨርስቲ ተማሪዋ ጫልቱ ታከለ ፣የመኢአዱ መሪ አቶ ማሙሸት አማረና የመላው ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያ ፓርቲ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ ክንፈሚካዔል ደበበ ፣አቶ ውብሸት ታዬ ፣አቶ ኦልባና ሊሌሳ እና ሌሎችም የህሊና እስረኞች ተፈተዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ እና አቶ አንዱለአም አራጌ መስከረም 3 ቀን 2004 ዓም በደህንነቶች ታፈነው ከተወሰዱ በሁዋላ ያለፉትን 7 አመታት በከፍተኛ ስቃይ አሳልፈዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር 18 ዓመት አንዱአለም አራጌ ደግሞ የእድሜ ልክ እስር ተፈርዶባቸው ነበር።

Tuesday, February 13, 2018

አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ

 አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ ባለፉት 2 ቀናት በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የኦፌኮ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባ ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ ከእስር ተፈተዋል። ሰሞኑን ችሎት በመድፈር የአንድ አመት እስር የተፈረደባቸው እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ መፈታታቸው ውሳኔውን ላስተላለፉት ዳኞች ትልቅ ውርደት፣ ለመብታቸው በመታገል ላይ ላሉት ቄሮ እየተባሉ ለሚጠሩት ወጣቶች ደግሞ ታላቅ ድል ተደርጎ ተቆጥሯል። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ይፈታሉ የተባሉት እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዱለአም አራጌና ሌሎችም እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ ተጠይቀው አሻፈረን በማለታቸው አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ ከመፈታታቸው በፊት የሚሰጠውን ተሃድሶ በመውሰድ ላይ እያሉ፣ አብረዋቸው የተከሰሱት እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ካልተፈቱ አልፈታም በማለታቸው ተሃድሶውን አቋርጠው በመውጣት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት መመለሳቸው ታውቋል። ወ/ሮ እማዋይሽ በእስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል። አሁን የወሰዱት እርምጃ ብዙዎች አድናቆታቸውን በፌስቡክ እየገለጹ ነው፡

በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል በአንዳንድ አካባቢዎች ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል በአንዳንድ አካባቢዎች ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚጓዙ መንገደኞች በትራንስፖርት እጥረት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። የንግድ እቃዎችን የጫኑ መኪኖች በየቦታው ቆመዋል። በአዲስ አበባ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመው ማንኛውንም እንቅስቃሴ ሲከታተሉ ውለዋል። ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በዙሪያ ከተሞች ከፍተኛ ጭስ መታየቱን ተከትሎ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ከተማውን አስጨንቀውት ውለዋል። የከተማ ህዝቡ ህንፃዎች ላይ ሆኖ የሚከናወነውን በተለያዬ ስሜት ውስጥ ሆኖ ሲከታተለው መቆየቱን ወኪላችን ገልጸዋል። በለገጣፎ ፣ ሰንዳፋ፣ ወለቴና ሌሎችም የከተማዋ አቅራቢያ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች የተደረጉ ሲሆን፣ ወጣቶች መንገዶችን ጎማ በማቃጠል ጭምር ዘግተዋል። ከአንፎ አካባቢ 42 ወጣቶች ተይዘው ካራ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡ በሁዋላ ወደ ኮልፌ እስር ቤት ተዘውረዋል። ከካራ ቆሬ( ሃጂ አንባ) የተነሱ ወጣቶች ወደ መሃል አዲስ አበባ ጉዞ ሲያደርጉ በፖሊሶች ተበትነዋል። በቢሾፍቱ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ ሲያካሂድ ቢውልም፣ የጸጥታ ችገር አልተፈጠረም። በአዳማ ፣ በአርሲ ፣ ሻሸመኔ፣ ኩየራ፣ ቀርሳ ኢላላ፣ ዶሌ፣ አዳባ፣ ዶዶላ፣ ኮምቦልቻ፣ ሀረር፣ መቱ፣ ሞያሌ፣ እና ሌሎችም በርካታ ቦታዎች የተቃውሞ ሰልፎችና የስራ ማቆም አድማዎች ተካሂደዋል። ትናንት ተቃውሞውን ያልተቀላቀሉት ቡሌ

Friday, February 9, 2018

Prominent Ethiopian Prisoners Won't Sign Pardon Letters

Ethiopian journalist Eskinder Nega and two prominent opposition figures have refused to sign letters of pardon from the government, holding up their planned release from prison.
Eskinder and opposition leaders Andualem Arage and Abebe Kesto — all critics of the government — are among 746 prisoners set for release following an announcement Thursday by Ethiopia's attorney general.
But Eskinder's wife, Serkalem Facil, has told VOA's Horn of Africa Service that her husband declined to sign the letter of pardon because it states he was a member of Ginbot 7, a political organization banned in Ethiopia.

Tuesday, February 6, 2018

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኚት ከተማ በሚገኘው እስር ቤት ላይ ባደረሰው ጥቃት 17 እስረኞችን ማስለቀቁን ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታወቀ።


አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ መገለጫ እንደሚያመልከተው ዘመቻ ነጻ ትውልድ በሚል መጠሪያ ማክሰኝት እስር ቤት ላይ በተፈጸመጥቃት ነው 17 እስረኞች ነጻ የወጡት። ትላንት ለሌት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 9 ሰአት ላይ ፈጸምኩት ባለው በዚሁ ጥቃት የእስር ቤቱ ተረኛ መኮንንና ጠባቂ ፖሊስ ተገድለዋል ብሏል። ሌሎች ሶስት ፖሊሶች መቁሰላቸውንም አስታውቋል። ማክሰኚት በሚገኘው እስር ቤት በፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩትን ጨምሮ ከ160 በላይ ወጣቶች ስቃይና ድብደባ

የአጼ ቴድሮስ ሐውልት በደብረታቦር ከተማ በርካታ ሕዝብ በተገኘበት ተመረቀ።

በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በ2 ሚሊየን ብር ወጪ የተሰራው የአጼ ቴድሮስ ሃውልት 7 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት ያለው ነው። በኢትዮጵያ የንግስና ታሪክ ከ1847 እስከ 1860 ኢትዮጵያን የመሩት አጼ ቴድሮስ የሀገር አንድነት ተምሳሌት ናቸው። በከፋፍለህ ግዛው ስልት በተነጣጠለ ሁኔታ በኢትዮጵያ የነበረውን የዘመነ መሳፍንት አገዛዝ ለማስወገድ ደፋ ቀና ያሉት አጼ ቴድሮስ በእንግሊዞች አልማረክም ብለው ራሳቸውን በገዛ እጃቸው ያጠፉ መሪም ናቸው። እጅ መስጠት የሀገርን ክብር ማዋረድ ነው ብለው ራሳቸውን የሰውትን አጼ ቴድሮስን የሚያስታውስ ሀውልት በደብረታቦር አደባባይ ቆሞላቸዋል። ሀውልቱ የተሰራው በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ በተመደበ በጀት መሆኑ ነው የተገለጸው። ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበትና በደብረታቦር ከተማ የተገነባው የአጼ ቴድሮስ ሃውልት የሴቫስቶፎል መድፍ ያለበትና ጦር ይዘው በቁማቸው የሚታዩበት ነው። ሀውልቱ ሲመረቅ በርካታ የደብረታቦር ህዝብ በአደባባዩ ዙሪያ ታድሞ አጼ ቴድሮስን ሲያስታውስና ሲያከብር ውሏል። የአጼ ቴድሮስ ሃውልት በደብረታቦር መመረቅ ትውልዱ ለአንድነቱ ያለውን ጽናት አሁንም እያሳየ መሆኑን እንደሚያመላክት ታዛቢዎች ይናገራሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚኖሩ ነዋሪዎች 200ሺ የሚሆኑት ራሳቸውን መመገብ ባለመቻላቸው የአለም ባንክ ቋሚ ድጋፍ ሊያደርግላቸው መሆኑ ተገለጸ።

አቅመ ደካሞች ለሆኑት በየወሩ ቋሚ ክፍያ በመስጠት እንዲሁም ሌሎቹን ደግሞ በአካባቢ ጽዳትና መሰል ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ገንዘቡ እንደሚከፈላቸው ተመልክቷል። በፍጹም ድህነት ውስጥ ከሚገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች 32ሺ የሚሆኑት አቅመ ደካሞች በመሆናቸው በነፍስ ወከፍ በወር 170 ብር በቤተሰብ ቁጥር ተባዝቶ እንደሚሰጣቸው ተገልጿል። ቀሪዎቹ 168ሺ የሚሆኑት ደግሞ የአካባቢ ልማት ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የአለም ባንክ ክፍያውን እንደሚፈጽም መረዳት ተችሏል። የአለም ባንክ በፍጹም ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከመደበው 450 ሚሊየን ዶላር 70 በመቶው ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መመደቡን የከተማ አስተዳደሩን ሃላፊ ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው አስፍሯል። በአዲስ አበባ ከተማ በ55 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 200ሺ ያህል ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ይህ የእርዳታ ፕሮግራም ለአስር አመታት እንደሚቀጥልም ተመልክቷል። የአለም ባንክ በፍጹም ድህነት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት በ2009 የጀመረው ይህ ፕሮጀክት እስከ 2018 እንደሚቆይም ከዘገባው መረዳት ተችሏል። ኢትዮጵያ በአለም ላይ ከሚገኙ ሀገራት በድህነት ከአለም ከመጨረሻ ሁለተኛ መሆኗን አለምአቀፍ መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢትዮጵያ በታች የመጨረሻ ድሃ ተብላ የምትጠቀሰው ወይንም ኢትዮጵያ የምትበልጣት ብቸኛ ሀገር ኒጀር መሆኗም ይታወቃል።

በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ ወደ ወጭ የተወሰዱ ሰባት ሺ ህጻናት የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ ወደ ውጭ በጉዲፈቻ የሚሰጡ ህጻናት በተገቢው ህጋዊ አሰራር እየተፈፀመ አለመሆኑን ለፓርላማ ገልፀዋል፡፡ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ደሚቱ ሃምቢሳ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ያሉ ደላሎች ወላጆችን በማታለልና ከሌሎች አካላት ጋር በመመሳጠር በህገወጥ መንገድ ህፃናትን ወደ ተለያዩ ሀገራት ልከዋል፡፡ በደላሎች ተታለው ልጆቻቸውን ልከው ያሉበትን ያላወቁ ወላጆችም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ልጆቻቸውን እንዲያገናኛቸው እየተማፀኑ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡ ህጻናቱ ለአሳዳጊዎቹ ሲሰጡ በቂ መረጃ እና አድራሻ ያልተያዘ በመሆኑ ፍለጋው አዳጋች እንደሆነም ሚንስትሯ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው መፍትሄ እያፈላለገ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ህጻናቱ ሊገኙ ይችላሉ ተብሎ በሚታሰብባቸው ስፔን፣ ጣሊያን እና አሜሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት መካሄዱንና ጥረቱ መቀጠሉንም ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ እንዲጎለብት እየሰራ መሆኑንና ወላጆችም በሀገር ውስጥ ልጆቻቸው የሚያድጉበት ሁኔታ መመቻቸት አለበት ነው ያሉት፡፡ የኢትዮጵያ ፓርላማ በቅርቡ በጉዲፈቻ ሕጻናትን ወደ ወጭ መውሰድን የሚከለክል ሕግ ማጽደቁ ይታወቃል። ሕጉ የጸደቀው በጉዲፈቻ ስም በውጭ ዜጎች ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ለበርካታ ጊዜያት በአሳዳጊዎቻቸው ከፍተኛ በደል እንደሚደርስባቸው በመታወቁ ነው ተብሏል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በጉዲፈቻ መልክ ከኢትዮጵያ የሚወሰዱ ሕጻናት ብዙዎቹ ደብዛቸው ሲጠፋ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከመገደል ደርሰዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1999 ወዲህ ብቻ 15 ሺ ሕጻናት በጉዲፈቻ መልክ ወደ አሜሪካ ተወስደዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 ሁለት አሜሪካውያን ባልና ሚስቶች አንዲት ኢትዮጵያዊ ለማሳደግ ከወሰዱ በኋላ ገድለዋት በመገኘታቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳዩ ሲያነጋግር እንደነበር አይዘነጋም።

ጣና ሃይቅ ላይ አዞላና ኢፓማ የተባሉ አረሞች በተጨማሪ ጉዳት እያደረሱ ነው ተባለ።

 እምቦጭ አረም ሃይቁ ላይ እያደረሰ ያለው አደጋም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የውሃ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ የጣና ሃይቅ ባለፉት አመታት የተለያዩ የህልውና ፈተናዎች ገጥመውታል ሲሉ ለቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ተናግረዋል። ፈተናዎቹን የአፈር መከላት፣የደለል ክምችት፣ተገቢ ያልሆነ የስነ-ሕይወት አጠቃቀም፣ልቅ ግጦሽና የባህር ሸሽ እርሻ ናቸው ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰሩ ይገልጿቸዋል። በጣና ዙሪያ የተወለዱትና በሃይቁ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን እንዳደረጉ የሚገልጹት ተባባሪ ፕሮፌሰር አያሌው ወንዴ በተለይም ከጥቂት አመታት ወዲህ በሰሜናዊ ምስራቅ የሃይቁ ክፍል የተከሰተው የእምቦጭ አረም ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረ ይገኛል። ይሄ ስጋት ሳይቀረፍ ከእምቦጭ አረም በተጨማሪ አዞላና ኢፓማ የተሰኙ አረሞች በሃይቁ ላይ መከሰታቸውን ተመራማሪው ገልጸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በሰው ጉልበት የሚደረገው ስራ በማሽን ካልታገዘ በጣና ሃይቅ ላይ የተጋረጠው አስጊ ሁኔታ እንደማይወገድ ተመራማሪው አሳስበዋል። አረሙን ለማስወገድ በተደረገ ጥረት የሰው ህይወት መጥፋቱንና በእባብ ተነድፈው ጉዳት የደረሰባቸው እንዳሉም ነው የተናገሩት። ፕሮፌሰር አያሌው አረሙን ለማስወገድ በቅንጅት እየተሰራ አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።

Monday, February 5, 2018

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ውስጥ ኦህዴድን ከሚወክሉ 45 አባላት አስሩን ማባረሩ ታወቀ።

ሙክታር ከድር እና ወይዘሮ አስቴር ማሞ ማዕከላዊ ኮሚቴው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በመንግስት የተነፈጋቸውን ጥቅማ ጥቅም ኦህዴድ እንደሚያሟላም ቃል ገብቷል። በውጭ ሀገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከተቃዋሚዎች ጋር ጭምር ተባብሮ ለመስራትም ውሳኔ ማሳለፉ ተመልክቷል። በአዳማ በመካሄድ ላይ ያለው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ቀጥሏል። በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል በመሆናቸው ሲያገኙት የነበረው ጥቅማ ጥቅም ሙሉ በሙሉ የተቋረጠባቸው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የሚጓጓዙበት ተሽከርካሪ ጭምር ስላልነበራቸው በከተማ ታክሲና አውቶቡስ ሲጠቀሙ መቆየታቸው ተመልክቷል። በፓርላማ በአዋጅ የጸደቀላቸውን የጡረታ መብታቸውን ጭምር ተነፍገው ባለፉት 12 አመታት ያለ ቋሚ ገቢ ሕይወታቸውን ሲመሩ ለቆዩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተሽከርካሪና ሕክምናን ጨምሮ ጥቅማ ጥቅም እንዲጠበቅላቸው በአዳማ በማካሄድ ላይ ያለው የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ መወሰኑ ታውቋል። ለ10 ቀናት ይቀጥላል የተባለውና በአዳማ እየመከረ ያለው የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ድርጅቱን ወክለው

ለ61 ወታደራዊ መኮንኖች የተሰጠው ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ብሶትና ምሬት ለማዳፈን ያለመ ነው ተባለ።

ፋይል ኢሳት ያነጋገራቸው ሁለት ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደገለጹት ያለዕውቀትና የውጊያ ልምድ በብሄር ኮታ የታደለው ወታደራዊ ማዕረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አቅምን ከግምት ያላስገባ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው። ባለፈው ዓርብ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህወሃት የሚመራው መንግስት 4 የሙሉ ጄነራል፣ የ3ሌተናል ጄነራል፣ የ14 ሜጀር ጄነራልና የ40 ብርጋዴየር ጄነራል ማዕረግ መስጠቱ ይታወሳል። በቀደሙት የኢትዮጵያ መንግስታት ዘመን ለ60 ዓመታት ኢትዮጵያ ሙሉ ጄኔራል አልነበራትም። ባለፈው ዓርብ በፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የተሰጠው የማዕረግ እድገት ኢትዮጵያን የ5ሙሉ ጄኔራሎች ባለቤት የሚያደርጋት ሆኖ ተመዝግቧል። አሁን በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ አንድ ጄኔራል በትምህርትና በልምድ የሚጠበቅበትን ደረጃ ሳያሟላ ማዕረግ መሰጠቱ ለወታደራዊ ባለሙያዎች አስገራሚ ጉዳይ ሆኖባቸዋል። ወታደራዊ አካዳሚ በመግባት አስፈላጊ የሆነውን ዕውቀት ሳያገኙ፣ በውጊያም ሆነ በአጠቃላይ ወታደራዊ ክህሎት በቂ ልምድና አቅም ላይ ሳይደርሱ የሙሉ ጄነራልነት የተሰጣቸው መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዎች ዓለምዓቀፍ

የኢትዮጵያው አገዛዝ በሚቆጣጠረው ኢትዮ ሳት ሳተላይት የግልም ሆነ የመንግስት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግዳጅ እንዲሰራጩ በብሮድካስት ባለስልጣን የቀረበው ሃሳብ ተቀባይነት ማጣቱ ተገለጸ።

በተለይ የኦሮሚያና የአማራ መገናኛ ብዙሃን በዚህ ሳተላይት በኩል እንዲሰራጩ የተደረገው ሙከራ ክልሎቹ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሊሳካ አልቻለም። “ኢትዮ ሳት” በኢንሳ በኩል ቁጥጥር የሚደረግበትና ከፈረንሳይ ኩባንያ አገዛዙ በውድ ዋጋ የተከራየው ሳተላይት ነው። በሳተላይቱ ከ35 በላይ ቻናሎች ሊሰራጩበት እንደሚችልም ነው የተነገረው። በኢትዮ ሳት በኩል የግልም ሆነ የአገዛዙ የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲያስተላልፉ የተፈለገውም በስርጭቱ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ እንደሆነ ታዉቋል። የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ/ኢሳት/ ከአየር ላይ እንዲወርድ አገዛዙ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር በመደራደር “ኢትዮ ሳት” በሚል የሳተላይት ኪራይ ግዥ መፈጸሙም የሚዘነጋ አይደለም።

በአማራ ክልል በዚህ ዓመት የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎትን ከ10 በላይ ለሚሆኑ ከተሞችና ቀበሌዎች ለማዳረስ በሚል የተመደበው 445 ሚሊየን ብር በሕወሃት በመዘረፉ አገልግሎቱን ማግኘት እንደማይችሉ ተገለፀ ፡፡



በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ከሕዝብ በተለያዩ መንገዶች ማለትም ከአገልግሎት ፥ ከአዲስ መስመር ዝርጋታ ጥያቄዎች ፥ ከቅጣትና ከልዩ ልዩ ገቢዎች የሰበሰበው 445 ሚሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መሰጠቱ ታውቋል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሰሜን ምዕራብ ሪጅን የስድስት ወር የስራ ክንውን ሲገመገም በዚህ ዓመት በአማራ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት እንዲያገኙ እቅድ ተይዞላቸው የነበሩ 10 ከተሞች ምንም እንቅስቃሴ አልተደረገላቸውም። ጉዳዩን አስመልክቶ የሕዝብ ማመልከቻ በተደጋጋሚ ሲቀርብ ምላሽ በመጥፋቱ አንዳንድ ሰዎች የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊውን አጥበቀው ሲጠይቁት ” በደብረፅዮን ትዕዛዝ 445 ሚሊየን ብር ወጭ ሆኖ ወደ መቀሌ አካውንት እደገባ እና በዚያ ለልማት ስራ ይውላል ” የሚል ምላሽ ከአሁኗ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር አዜብ ምላሽ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል ፡፡ የኢሳት የመረጃ ምንጭ እንዳመለከተው ኢንጂነር አዜብ ለሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊው በሕወሃት የተወሰደው ገንዘብ ሊመለስ እንደማይችል አረጋግጠውላቸዋል። እናም ስራው እንዲሰራ ከተፈለገ ገንዘቡን ከሕዝብ እንደገና እንዲሰበስብ ማዘዛቸው ነው የተነገረው። በዚህ መሰረት በሪጅኑ አዲስ መስመር እንዲገባላቸው ከጠየቁና ከተመዘገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ገንዘቡ

አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ አራቱ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ /ኦፌኮ/ አመራሮች ለ2ተኛ ጊዜ ተፈረደባቸው።

ተከሳሾቹ በድጋሚ የ6 ወራት እስራት የተፈረደባቸው በችሎት ውስጥ በዳኛው ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ታዘው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል። ጠበቆቻቸው ግን እኛ ከተነሳን ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም ነበር ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ ያሉትን ተከሳሾች አቶ በቀለ ገርባ፣ደጀኔ ጣፋ፣አዲሱ ቡላላና ጉርሜሳ አያኖ ስማቸው በሚጠራበት ወቅት ባለመነሳታቸው ችሎት ደፍረዋል ተብለዋል። በዚሁም መሰረት በአራቱም ተከሳሶች ላይ የ6 ወራት የእስር ቅጣት በድጋሚ ተላልፎባቸዋል። ከዚህ ቀደምም በችሎት ውስጥ ዘመሩ ተብሎ ችሎት በመድፈር ወንጀል ለ6 ወራት እንዲታሰሩ ተፈርዶባቸው እንደነበር አይዘነጋም። ተከሳሾቹ በአሁኑ ችሎት “ባለፈው በመናገራችን ተቀጥተናል”በሚል ከመቀመጫቸው እንዳልተነሱ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ተናግረዋል። ይህን ሲያደርጉ ግን በችሎት ውስጥ በሚጠሩበት ወቅት እጃቸውን ቢያወጡም ፍርድ ቤቱ ካልተነሱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስላላከበሩ ርምጃ እወስዳለሁ በማለት የ6 ወራት እስራት ቀጥቷቸዋል። ተከሳሾቹ ለፍርድ ተቀጥረው ችሎት በመድፈር ቅጣት የተጣለባቸው ያለ አግባብ መሆኑን ጠበቆቻቸው ተናግረዋል። በችሎቱ ፊት እኛ ከተነሳን ተከሳሾች እንዲነሱ አይገደዱም በሚል ጠበቆቻቸው ውሳኔውን መቃወማቸው ተሰምቷል። በችሎት መድፈር አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የተፈረደባቸው አራቱ የኦፌኮ አመራሮች በሁሉም ላይ የመጨረሻውን የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 28/2010 መቀጠሩንም ለማወቅ ተችሏል።

Friday, February 2, 2018

የህውሓት የአዲስ አበባ ልዩ ዞን!" እና የ HD አዲሱ ዲስኩር! ኤርሚያስ ለገሰ

መንደርደሪያ አንድ:- 1998 ዓ•ም•
የመለስ ትሩፋት ባለቤት አልባ ከተማ መፅሐፍ " የአዲስአባ ፓለቲካ ምህዳር" በሚል ርእስ ስር በገፅ 252 ላይ የሚከተለውን ትለናለች፣
" የ1998 ዓ•ም• የአዲሳአባ የፓለቲካ ስራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከአቶ መለስ ጋር በነበረን ስብሰባ " ከእንግዲህ በአዲስአባ ምድር የብሔር አደረጃጀት መከተል ራስን ለተደጋጋሚ ሽንፈት ማዘጋጀት ነው። የመዲናይቱ ነዋሪ በተለይም ወጣቱ በብሔር አደረጃጀት መታቀፍ አይፈልግም" በማለት አቶ መለስ ተናግሮ ነበር። ይህን የአቶ መለስ ውሳኔ ተከትሎ ከህውሓት ውጭ ያሉት የብሔር ድርጅቶች እጃቸውን ከአዲስአባ ላይ አነሱ። ህውሓቶች አስቀድመው ራሳቸውን ከኢህአዴግ ቢሮ ስላገለሉ ውሳኔውን አልቀበልም በማለት በመዲናይቱ የትግራይ አደረጃጀት እስከማቋቋም የሚደርስ የትእቢት እርምጃ ወሰዱ። ለድርድር ቢጠሩም ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ።ሌሎቹንም የእነሱን እርምጃ እንዲከተሉ ከጀርባ አደራጁ። እሰጣ ገባው ሳይጠናቀቅ የኢህአዴግ ጉባኤ በአዋሳ ተጠራ።"
#መንደርደሪያ ሁለት:- 2010 ዓ•ም•
"የኢህአዴግ ሊቀመንበሩ!" አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በትላንትናው እለት ( ከ12 አመት በኃላ) የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ሊግ ኮንፍረንስ ላይ ተገኘ። "ተወዳጁ ኢቲቪ" ( EBC) በዜና ዝግጅቱ ከሐይለማርያም ንግግር ውስጥ የሚከተለውን ቀንጭቦ አሰማን፣
" የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ሊግ አደረጃጀት ኢህአዴግ ከግንባር ወደ አንድ ፓርቲ ለሚያደርገው ሽግግር ምሳሌ ይሆናል። ሕብረ-ብሔራዊ ሆናችሁ መደራጀታችሁ ለተለያየ ጥገኛ አስተሳሰቦች ( ትምክህት፣ ጠባብነት) ያለው ቦታ ምን እንደሚመስል ኢህአዴግ ከእናንተ ትምህርት ይወስዳል።"

የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በአጋዚ ወታደር ተደበደበች

በአዳማ ዩኒቨርስቲ አንዲት የ4ኛ አመት የስነ ሕይወት ሳይንስ ተማሪ የመኝታ ክፍሏ ተሰብሮ በአንድ የአጋዚ ወታደር መደብደቧንና ጾታዊ ትንኮሳ እንደደረሰባት ዘገባዎች አረጋገጡ።
በዩኒቨርስቲው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች በመከላከያ ወታደሮች በሃይል ተገደው እንደሚሳሙም በተቋሙ ጉዳዩን ያጣሩት አካላት አረጋግጠዋል።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር ሃና ተፈራ ጉዳዩን አጣርተው ለቦርድ በማቅረባቸው በአንድ የመከላከያ ጄኔራል ትዕዛዝ ከስራ ተባረዋል።
በአዳማ ዩኒቨርስቲ በአጋዚ ወታደር በመደብደብ ጾታዊ ትንኮሳ የደረሰባት የ4ኛ አመት ተማሪ አሳዛኝ ታሪክን ይፋ ያደረጉት ሃና ተፈራ የተባሉ በተቋሙ የጾታ ጉዳዮች ዳይሬክተር መሆናቸውን የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ያመለክታል።

ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከስልጣን መባረራቸውን ያወቁት በጥበቃ ሰራተኛ ሲታገዱ ነው ተባለ

በቅርቡ ከሕወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የተባረሩትና ከኤፈርት ሃላፊነታቸው የተነሱት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ከስልጣን መባረራቸውን ያወቁት ወደ ቢሮአቸው እንዳይገቡ በጥበቃ ሰራተኛ ሲታገዱ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።
በአቶ ስብሃት የሚደገፈው የሕወሃት አመራር ለወይዘሮ አዜብ ደብዳቤ ሳይደርሳቸው ትዕዛዙን ለጥበቃ ሰራተኛው አስቀድሞ ያስተላለፈው ሞራላቸውን ለመንካት እንደሆነም ምንጮቹ ይናገራሉ።
ወይዘሮ አዜብ ተሽከርካሪያቸውንም ጭምር ድንገት ተነጥቀው በሰው መኪና ወደ ቤታቸው መመለሳቸውም ታውቋል።
መቀሌ ሲካሄድ የነበረውን የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውን ተከትሎ ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚነት የተባረሩት ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሕወሃት የንግድ ተቋም የሆነውን ኤፈርትን እስካለፉት ጥቂት ሳንታት ድረስ ሲመሩ ቆይተው ነበር።

በኤርትራውያንና በአፍጋኒስታውያን መካከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ቆሰሉ

በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌይ በኤርትራውያንና በአፍጋኒስታውያን መካከል በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ።
የጦር መሳሪያ ድንጋይና የብረት ዱላ በጨመረውና ትላንት በተከሰተው በዚህ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች መጎዳታቸው የተገለጸ ሲሆን ቢያንስ አራቱ በጥይት መቁሰላቸውም ተመልክቷል።
ግጭቱ ከአካባቢው የፖሊስ ሃይል በላይ በመሆኑ ተጨማሪ የፈረንሳይ የፖሊስ ሃይል ወደ አካባቢው መሰማራቱም ታውቋል።
በፈረንሳይ የወደብ ከተማ ካሌይ ትላንት የተከሰተው ግጭት መነሻ በትክክል ያልታወቀ ቢሆንም ለስደተኞቹ የሚሰጠውን የምግብ እደላ ተከትሎ ግጭቱ መቀስቀሱ ይፋ ይሆኗል።

Thursday, February 1, 2018

እኔ ስታገል እንጅ ስነግድ አልኖርኩም" ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

Image may contain: 1 person, smiling, closeupጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከመታሰሩ በፊት ወደ አሜሪካ ሀገር እንዲሄድ ብዙ ግፊት ደርሶበት ነበር። ለበርካታ ጊዜ ተለምኗል። ያኔ በተደጋጋሚ ወደ አሜሪካ እንዲሄድ "መንገድ ሲሰጠው" ልጅም ትዳርም አልነበረውም። ቪዛ ሊሰጠው የነበረውም የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።
ተመስገን ከእስር ከተፈታ በኋላ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት የመጣውን የጀርባ ህመም ለመታከም፣ እንዲሁም በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጁለት ፕሮግራም ላይ ለመታደም የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር።
ተመስገን ደሳለኝ ወደ ውጭ ለመሄድ ስለማይፈልግ ፓስፖርቱን እንኳ ያወጣው የሚያከብራቸው ኢትዮጵያውያን አማላጅ ተልከውበት ጭምር ነው። ሆኖም የአሜሪካ ኤምባሲ "ልጅና ትዳር የለህም" በሚል ሰበብ ቪዛ ከልክሎታል።

በአዳማ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉ ተገለጸ።

 ህገወጥ ቤት ለማፍረስ የተጀመረውን እንቅስቃሴ በመቃወም በተደረገው ተቃውሞ ከፖሊስ ጋር ግጭት ተፈጥሮ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል። መንገዶች በድንጋይና በእንጨት ተዘግተው እንደነበር የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች ወደ አመጽ የተቀየረውን የህዝቡን ተቃውሞ ለማስቆም የፖሊስ ሃይል ቁጥሩን ጨምሮ መሰማራቱን ገልጸዋል። በርካታ ሰዎች መታሰራቸውም ታውቋል። በአዳማ/ ናዝሬት ዛሬ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ህገወጥ ቤት ለማፍረስ በከተማዋ አስተዳደር እየተወሰደ ያለውን ርምጃ ለማስቆም ያለመ ነበር። ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ በተካሄደው ተቃውሞ የሰው ህይወት መጥፋቱ የሚታወስ ነው። ቤት አጥተው ከፍተኛ ችግር ውስጥ የገቡ ዜጎች መሬት በመግዛት የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሲያከናውኑና ውሃና መብራትን ጨምሮ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ሲከናወኑ አቁሙ ያላቸው አካል የለም። እስከ መጨረሻው በዝምታ የቆየው የከተማው አስተዳደርም ከዓመታት በኋላ ያለተለዋጭ ቦታና ቤት በላያችን ላይ ቤት እንዲፈርስ መወሰኑ

የአማራ ክልላዊ መንግስት ንብረት ላይ ጉዳት ባደረሱ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ረዳት ኮሚሽነር በሰጡት መግለጫም ንብረት ላይ ጥፋት የፈጸሙ ሰዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል። በወልዲያ፣መርሳና ቆቦ የተገደሉትን ሰላማዊ ዜጎችን በተመለከተ ግን ለህግ የሚቀርብ አካል ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም። ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል በማለት የተሰጠው መግለጫ ብዙዎችን ማስቆጣቱ ተሰምቷል። የአማራ ክልል መንግስት ያወጣውን ይህን መግለጫ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚንቀሳቀሱ የትግራይ መገናኛ ብዙሃን በምስጋና ተቀብለውታል። ክልሉን የሚያስተዳድረው የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ያወጣው መግለጫ ለአንድ ወገን ያደላ፣ በግፍ የተገደሉ ሰዎችን በመተው ለንብረት ውድመት ትኩረት የሰጠ እንደሆነ መረዳት ተችሏል። የህዝቡን ተቃውሞና በቁጣ የወሰደውን ርምጃ ሁከትና ስርዓት አልበኝነት በሚል የገለጸው የክልሉ መንግስት መግለጫ አንዳንዶቹ ማንነትን እየለዩ ጥቃት የሚሰነዘርባቸው መሆናቸውና ዜጐች ለዘመናት ያፈሩት ሀብትና ንብረት በአጭር ጊዜ መውደሙ በምንም መንገድ የክልሉንም ሆነ ችግሩ የተከሰተባቸውን አካባቢ ህዝቦች የማይወክል ተግባር ነው ሲል ኮንኖታል። መግለጫው ማንነትን ሲል በግልጽ ማንን እንደሆነ ያላሰፈረ ከመሆኑም በላይ በንብረቶቻቸው ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ከማንነት ይልቅ

በአፋር ክልል በሚካሄዱ የግንባታና የማምረት ስራዎች እስረኞች በጉልበት ሰራተኝነት መሰማራታቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ።

ይህንን በአለም አቀፍ ሕግ የተከለከለው ድርጊት የሚፈጸመው ከአማራ ክልል በሚወሰዱ እስረኞች ላይ እንደሆነም ተመልክቷል። በተለይ በዳሎል አካባቢ በፖታሺየምና በጨው ማምረት ስራ ላይ የሚገኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች በእስረኞቹ ጉልበት በመጠቀም ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአፋር ክልል ዳሎል አካባቢ በጨውና ፖታሺየም ማምረት የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች አሰማርተዋል። በአብዛኛው በቀን ሰራተኝነትና በኮንትራት ስራ የተሰማሩትን ሰራተኞች ከአፋር ክልልም ሆነ ከሌላ ክልል በቀላሉ ማግኘት ባለመቻሉ የአማራ ክልል እስረኞችን በአነስተኛ ገንዘብ እየተጠቀሙባቸው እንደሆነም ምንጮች ገልጸዋል። ለእስረኞቹ የሚከፈለው ገንዘብ በትክክል ለእስረኞቹ ገቢ ስለመደረጉም የታወቀ ነገር የለም። በስፍራው የሚንቀሳቀሱትና ያራ ኢንተርናሽናልን የመሳሰሉት ኩባንያዎች ሰራተኞቹ እስረኞች ስለመሆናቸው መረጃ ይቅረብላቸው አይቅረብላቸው የታወቀ ነገር ባይኖርም። ከአማራ ክልል የሔዱት እስረኞች በቅርብ ክትትልና ጥበቃ ስር ሆነው በአለም አቀፍ ኩባንያዎቹ ፕሮጀክቶች ውስጥም በቀን ሰራተኝነት

የሕወሃት አገዛዝ ከውጭ ባንኮች በከፍተኛ ወለድ በተለያዩ ድርጅቶች ስም የተበደረውን ገንዘብ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መክፈል እንደተሳነው ተዘገበ።

ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የደረሰ መረጃ እንዳመለከተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ከተበደረው ገንዘብ ባለፈው ጥርና የካቲት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በውጭ ምንዛሪ መመለስ ቢኖርበትም ክፍያውን ብሔራዊ ባንክ ሊፈጽም አልቻለም። በጉዳዩ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጥበት ቢጠይቅም ብሄራዊ ባንክን ጠይቁ ብሎ ጉዳዩን ችላ ማለቱንም ለማወቅ ተችሏል። በኢትዮጵያ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ስራ ማስኬጂያና ለመሰረተ ልማቶች በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ከተለያዩ ባንኮች በብድር መልክ በአገዛዙ ይወሰዳል። ይህም ብድር በከፍተኛ ወለድ በጊዜ ገደብ የሚከፈል ነው። ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በኦ ኤም ኤን በኩል የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው ግን ለአባይ ግድብ፣ ለግቤ 3ና ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የተሰጠ ብድርን በውጭ ምንዛሪ ችግር ምክንያት መክፈል አልተቻለም። የኮርፖሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ለገንዘብ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ባለፈው ጥርና

መንግስት በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ለስራ ወደ ውጭ ሃገራት መጓዝ የሚከለክለውን እግድ ማንሳቱ ተገለጸ።

እግዱ የተነሳው የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በመቅረታቸው መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከጥቅምት 2006 ጀምሮ ታግዶ የቆየው የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት ከጥር 22 ጀምሮ እንዲነሳ የሚኒስትሮች ምክር ቤት መወሰኑ ነው የታወቀው። ምክር ቤቱ ውሳኔውን ሲያሳልፍ ደግሞ የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟሉም የሚል ምክንያትን በማስቀመጥ ነው ሲሉ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮቹ እንደሚሉት ከሆነ በ2008 ተሻሽሎ የወጣው የግል ስራና ሰራተኛ አዋጅ በአስገዳጅነት ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ነበሩ። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች የተጣሱት መንግስት ያጋጠመውን የውጭ ምንዛሪ ድርቅ መቋቋም ስላቃተው ያገኘውን

የትግራይ ምሁራን የሕወሃትን አገዛዝ በማውገዝ ከሕዝብ ጋር እንዲቆሙ የአርበኞች ግንቦት ሰባትና የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ትህዴን/ ጥሪ አቀረቡ።

Image may contain: textሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጡት መግለጫ እንዳሉት የትግራይ ምሁራን ሀገርን እየከፋፈለና የግጭት መንስኤ የሆነውን ህወሃት ባለመውገዝ ዝምታን መምረጣቸው አግባብ አይደልም። ሕወሃትን የትግራይ ሕዝብ አንድ ባለመሆናቸውም በዘር ላይ የተመሰረተ ጥቃት እንዳይኖር ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ሁለቱ ድርጅቶች አሳስበዋል። የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ እና የአርበኞች ግንቦት ሰባት የጋራ መግለጫ እንደሚለው ሕወሃት ሕዝብን በቋንቋና በብሔር እየከፋፈለ ሀገሪቱን ለእርስ በርስ ግጭት እየዳረገ ነው። ይህንን የሚያደርገው የጋራ እሴቶችን በመሸርሸርና የሕዝቡን የአንድነት ታሪክ ጥላሸት በመቀባት ነው ብለዋል። ሕወሃት በትግራይ ሕዝብ ስም እራሱን ወክሎ በርካታ በደል እየፈጸመ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል። “ሕወሃትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነው” በሚል ስብከት የሚሰራቸውን ወንጀሎች በሕብረተሰቡ ስም በመፈጸሙ ሕዝቡ በጥርጣሬ እንዲተያይ አድርጎታል ነው ያለው። እንደ መግለጫው የትግራይ ተወላጆች በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ለረጅም ዘመናት በአብሮነትና በአንድነት የኖሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይሁንና በተለያዩ