ኢሳት (መስከረም 24 ፥ 2009)
የእሬቻ ዕልቂትን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በመዛመት ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ማክሰኞ በመዲናይቱ አዲስ አበባ መቀስቀሱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ።
በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ረፋድ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ በአየር ጤና ብስራተ-ገብርዔል አካባቢ ተዛምቶ ማምሸቱ ታውቋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በስም ያልገለጧቸው ሃይሎች ሁከት ለመፍጠር ጥረት አድርገዋል ሲል ማክሰኞ ምሽት ድርጊቱን አረጋግጧል።
በመዲናይቱ አዲስ አበባ የተስተዋለውን ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎ የአለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኞች ከስራ መውጫ ሰዓታቸው አስቀድመው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ መደረጉም ታውቋል።
ማክሰኞች ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በርካታ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውንና ነዋሪዎች በጊዜ ወደ ቤት ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ መታየቱንም እማኞች አክለው ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment