ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
ነዋሪነታቸው በተለያዩ ሃገራት የሆነ ኢትዮጵያውያን አትሌት ፈይሳ ሌልሳን ለመደገፍ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ40ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ቢቢሲ ሰኞ ዘገበ።
አትሌቱ በኢትዮጵያ ያለውን ግድያና አፈና በመቃወም ወደ ሃገሪቱ እንደማይመለስ መግለጹን ተከትሎ በርካታ ስራዎች ለአትሌቶቹ ድጋፋቸውን እየገለጹ እንደሚገኝ የዜና አውታሩ በዘገባው አስፍሯል።
አትሌቱ በሌላ ሃገር ለሚያደርገው የፖለቲካ ጥገኝነት ይረዳ ዘንድ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን አትሌቱን ለመደገፍ ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝነት እስከ ሰኞ ድረስ ብቻ ከ40ህሺ ዶላር (800 ሺ ብር) በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ለመረዳት ተችሏል።
የህግ ባለሙያዎችን ያካተተ አንድ ቡድን በአሁኑ ወቅት አትሌቱን በሪዮ ለማግኘት ወደ ብራዚል በማቅናት ላይ ሲሆን አትሌቱ የማራቶን ውድድሩን ሲጨርስ የእጅ ምልክቱን የሚያሳየው ተቃውሞ በሃገር ውስጥ የቴሌቪዥን ስርጭት በድጋሚ ሳይታይ መቅረቱን የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

No comments:
Post a Comment