Thursday, August 25, 2016
Tuesday, August 23, 2016
77,000 dollars raised in a crowd funding in less than 24 hours for hero marathoner Feyisa Lilesa
77,000 dollars raised in a crowd funding in less than 24 hours for hero marathoner Feyisa Lilesa
Athlete calls for the removal of a ruthless regime in Ethiopia
By Engidu Woldie
ESAT News (August 23, 2016)
ESAT News (August 23, 2016)
A crowd funding has raised over 77,000 dollars in a little over 24 hours after Olympic silver medalist Feyisa Lilesa crossed his wrists at the finish line in Rio on Sunday to bring the repression of his people to the attention of the world community.
Solomon Ungashe who coordinates the crowd funding on the social media said in his Facebook post that the goal was to reach 100,000 by Tuesday.
“Two members of the support team has arrived in Rio de Janeiro to meet with Feyisa Lelisa and provide the support he needs,” said Ungashe.
The athlete meanwhile called on all Ethiopians to come together as one and remove the brutal regime.
The athlete who spoke to ESAT also challenged fellow athletes and other Ethiopians to protest the killings and mass incarceration perpetrated by the regime.
Lilesa instantly got the attention of the international media and was the headline in the major newspapers across the globe. The Los Angeles Times, New York Times, the Washington Post and all the major British and Australian newspapers carried his story of heroic deeds highlighting the brutality of the minority regime in Ethiopia that has killed hundreds and imprisoned tens of thousands of people in the last one year.
Lilesa told ESAT that the fact that he ceased the opportunity to send a message to the world has given him more satisfaction than the silver medal he won.
He said he has seen the brutality of the regime himself when he paid visits to his relatives unlawfully incarcerated by the regime.
“I have no words to describe the horror,” Lilesa said.
Monday, August 22, 2016
በአውስትራሊያ ለኢሳት ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ
ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓል በማስመልከት በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄዱ።
በአውስትራሊያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዝግጅት አካል በሆነው የሲድኒው 6ኛ አመት የኢሳት የምስረታ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍ በተለያዩ መልክ መግለጻቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ የሲድኒ ዝግጅት ኢሳትን ለመደገፍ 35 ሺ ዶላር አካባቢ መሰብሰቡንና ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በክብር እንግድነት በመገኘት ከታዳሚው ጋር ኢሳትን በተመለከተ ውይይት አካሄዷል።

በክልሎች ሲካሄዱ የቆዩ ተቃውሞዎችን ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ሲያገናኝ የቆየው መንግስት ችግሩ ከአገልግሎት አሰጣት ችግር የመነጨ ነው አለ
ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በጸረ-ሰላም ሽብርተኛ ቡድኖች የተዘጋጀ ነው ሲል የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት የአገልግሎት አሰጣት ችግሮች ለተቃውሞ ምክንያት ሆኗል በማለት ሰኞ አስታወቀ።
በሃገሪቱ ስላለው የጸጥታ ጉዳይ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች ማብራሪያን የሰጠው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ለአምባሳደሮቹ መግለጹን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በሃገሪቱ እየተባባሰ የመጣውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ተቃውሞ ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ ሊዛመት ይችላል በማለት ዜጎች በእንቅስቃሴያቸው ላይ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ አርብ ማሳሰቢያን ማውጣቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሃገሪቱ የሚፈጸሙ ግድያዎችን እና እስራትን በመቃወም የተለያዩ የተቃውሞ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እሁድ በሪዮ ኦሎምፒክ የተቃውሞ መልዕክቱን ያስተላለፈው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ጥሪውን አቀረበ።
እሁድ በአለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ስለሆነ የተቃውሞ ድርጊቱ ከኢሳት ጋር ቆይታን ያደረገው አትሌት ሌሊሳ በተለይ አንጋፋ የኢትዮጵያ አትሌቶች የገዢው የኢህአዴግ መንግስትን ግድያ እና አፈና በመቃወም ተመሳሳይ ድርጊትን እንዲወስዱ ጠይቋል።
ካገኘሁት ሜዳሊያ ይልቅ ያስተላለፍኩት መልዕክት ደስታን ሰጥቶኛል ሲል የገለጸው አትሌቱ እጁን በማጣመር ተቃውሞን በአለም አደባባይ ማቅረቡ ሃላፊነትን የመወጣት ድርጊት እንደሆነ አስታውቋል።

ለአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የዕርዳታ ገቢ እየተሰበሰበ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
ነዋሪነታቸው በተለያዩ ሃገራት የሆነ ኢትዮጵያውያን አትሌት ፈይሳ ሌልሳን ለመደገፍ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ40ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ ማሰባሰባቸውን ቢቢሲ ሰኞ ዘገበ።
አትሌቱ በኢትዮጵያ ያለውን ግድያና አፈና በመቃወም ወደ ሃገሪቱ እንደማይመለስ መግለጹን ተከትሎ በርካታ ስራዎች ለአትሌቶቹ ድጋፋቸውን እየገለጹ እንደሚገኝ የዜና አውታሩ በዘገባው አስፍሯል።
አትሌቱ በሌላ ሃገር ለሚያደርገው የፖለቲካ ጥገኝነት ይረዳ ዘንድ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን አትሌቱን ለመደገፍ ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝነት እስከ ሰኞ ድረስ ብቻ ከ40ህሺ ዶላር (800 ሺ ብር) በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ለመረዳት ተችሏል።
የህግ ባለሙያዎችን ያካተተ አንድ ቡድን በአሁኑ ወቅት አትሌቱን በሪዮ ለማግኘት ወደ ብራዚል በማቅናት ላይ ሲሆን አትሌቱ የማራቶን ውድድሩን ሲጨርስ የእጅ ምልክቱን የሚያሳየው ተቃውሞ በሃገር ውስጥ የቴሌቪዥን ስርጭት በድጋሚ ሳይታይ መቅረቱን የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Friday, August 19, 2016
የኢትዮጵያ መንግስት ተመድ በአማራና ኦሮሚያ ለተፈጸሙት ግድያዎች የማጣራት ጥያቄ ይፋዊ የእምቢተኝነት ምላሽ ሰጠ
ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108)
የኢትዮጵያ መንግስት ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የተፈጸሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ለቀረበለት ጥያቄ ተባባሪ እንደማይሆን ይፋዊ የጽሁፉ ምላሽን ሰጠ።
በክልሎቹ እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን “ህገወጥና በሽብርተኛ ቡድኖች” የሚካሄዱ ናቸው ሲል በምላሹ ያሰፈረው መንግስት ከተቃውሞው ጋር በተገኛኘ የሞቱ ሰዎችን ጉዳት የደረሰባቸውን አካላት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር የራሱን ማጣራት እንደሚያካሄድ አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በሁለቱ ክልሎች የሃይል እርምጃዎችን እንደተፈጸሙ በመግለጽ አሳሳቢ ነው ሲል ያስታወቀው ድርጊት በአለም አቀፍ ገለልተኛ ቡድን ማጣራት እንዲካሄድበት ተጠያቂ መሆን ያለባቸው አካላት ለፍትህ እንዲቀርቡ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል።
ይሁንና ስዊዘርላን ጄኔቭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኗሪ መልዕክተኛ በኩል ምላሽ የሰጠው መንግስት የቀረበለትን ጥያቄ ከመቀበል ይልቅ የራሱን ምርመራ እንደሚያካሄድ በጽሁፍ መልስ ገልጿል።

በህወሃት/ኢህአዴግ ባለቤትነት የሚተዳደረው ፋና በግል ድርጅት ስም የንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ ተሰጠው
ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108)
የህወሃት የግል ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና በግል ድርጅት ስም የመጀመሪያን የንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ ተሰጠው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የቴልቪዥን ፍቃድ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ለማንም የግል ድርጅት ፍቃድ ሳይሰጥ ቆይቷል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት ጊዚያቶች ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ የግል ንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር ጥያቄ ያቀረቡት የህወሃት ኢህአዴግ ኩባንያዎች የሆኑት ሬዲዮ ፋና፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና ድምጸ ወያኔ መሆናቸው ታውቋል።

የአዲስ አበባ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ እሁድ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ
ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108)
የአዲስ አበባ ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ በቀጣይ እሁድ በአብዮት አደባባይ ለሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በነቂስ እንዲወጣ ጥሪ አቀረበ።
ኮሚቴው ነሃሴ 13 ቀን 2008 ዓም ባወጣው መግለጫ፣ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከጫፍ እስከ ጫፍ እየተቀጣጠለ ባለ ህዝባዊ እምቢተኝነት ውስጥ እንደምትገኝ፣ በተለይም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከ700 በላይ ወገኖቻችን መገደላቸው፣ በ10ሺዎች ለእስር እንግልትና መሰወር መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

የአሜሪካ መንግስት ዜጎቹ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አሳሰበ
ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108)
በኦሮሚያና አማራ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ ሊዛመቱ ይችላሉ በሚል የአሜሪካ መንግስት ዜጎች በእንቅስቃሴያቸው ላይ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አርብ አሳሰበ።
በሃገሪቱ እየተካሄዱ ባሉ ተቃውሞዎች ዙሪያ መግለጫን ያወጣው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሁለቱ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለው ተቃውሞ ወደ ሌሎች ክልሎችና አዲስ አበባ ሊዛመት እንደሚችል ማሳሰቢያ መውጣቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የሃገሪቱ ኢምባሲ በበኩሉ የኢንተርኔት አገግልሎቶችን ጨምሮ የሌሎች መገናኛ መንገዶች መስተጓጎል ከዜጎች ጋር በሚያደርገው ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮበት እንደሚገኝ አስታውቋል።

Thursday, August 18, 2016
ተመድ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግድያ የማጣራት ጥያቄ የልማት ኣጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008)
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ያቀረበውን ጥሪ የሃገሪቱ የልማት አጋሮች እንዲደግፉት ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ።
የሃገሪቱ የልማት አጋሮች የድርሻቸውን ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርባቸው ሲል የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ድርጊቱ መንግስት ያለተጠያቂነት ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደል እንደማይችል ጠንካራ መልዕክትን የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ አስታውቋል።

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በመጪው ቅዳሜ ነጭ ልብስ በመልበስ በህወሃት/ኢህአዴግ የተገደሉትን ሰዎች እንደሚያስቡ አስታወቁ
ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008)
በተለያዩ የተቃውሞ ስልቶች ውስጥ የቆዩ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከፊታችን ቅዳሜ ነሃሴ 14, 2008 ዓም ጀምሮ “ነጭ በመልበስ” እና በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ አዲስ መርሃግብር መንደፋቸውን ሃሙስ አስታወቁ።
ጥቁር በመልበስና ከቤት ባለመውጣት አድማ ውስጥ የቆዩት ነዋሪዎቹ ሙሉ በሙሉ ነጭ የመልበሱ ስነ-ስርዓት የቀድሞ ጠቃላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን የመታሰቢያ ዝጅግት በሚያካሄዱበት ቀን በተቀራኒ አለባበስ ተቃውሞን ለማንጸባረቅ እንደሆነ አስረድተዋል።
የጀመሩት ተቃውሞ በተለያዩ መልኮች ቀጣይ እንደሚሆን የተናገሩት ነዋሪዎች የከተማ ህዝብ ከቅዳሜ ጀምሮ ሁለት መልዕክቶችን ማስተላለፍ እንደሚጀምር ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል።

በጎንደር የአምባ ጊዮርጊስ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ወቅት የታሰሩ 14 ሰዎችን አስለቀቁ
ኢሳት (ነሃሴ 12 ፥ 2008)
በሰሜን ጎንደር ዞን ስር አምባ ጊዮርጊስ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች ሃሙስ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ በቅርቡ ለእስር የተዳረጉ 14 ነዋሪዎችን በከተማዋ ከሚገኝ እስር ቤት በሃይል ማስለቀቃቸውን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ።
የከተማዋ ነዋሪዎች ሰኞ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኘተው ያላቸው ጥያቄ እንዲሰሙ ያቀረቡትን ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ምክንያት በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ሃሙስ ተቃውሞን ሲገልጹ መዋሉን ለመረዳት ተችሏል።

Wednesday, August 17, 2016
የኮሌራ በሽታ በተለያዩ ከተሞች ተከስቶ እንደሚገኝ ተነገረ
ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008)
በአዲስ አበባ ከተማ በመሰራጨት ላይ ያለው የኮሌራ በሽታ በመቀሌ ከተማም መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ረቡዕ አስታወቀ።
በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ተከስቷል በተባለው በዚሁ በሽታ አምስት ሰዎች ምልክቱ ተገኝቶባቸው በህክምና ላይ መሆናቸውን የጤና ባለሙያዎች ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
በሰኔ ወር በአዲስ አበባ ከተማ ስርጭቱን የጀመረው ይኸው የኮሌራ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ጉዳትን እያደረሰ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ የመለክታል።
የበሽታውን ስርጭት ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በትንሹ ስድስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ከ 3ሺ የሚበልጡ ነዋሪዎች በበሽታው መያዛቸውን ለመረዳት ተችሏል።

ህወሃት/ኢህአዴግ በአምስት ከተሞች ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ አቅዷል ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008)
ህወሃት የሚመራው መንግስት የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በማሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ትላልቅ ከተሞች የሽብር አደጋ በማድረስ በአልሸባብ ላይ ለማላከክ ማቀዱን ተገለጸ።
የሽብር ጥቃት እንዲደርስባቸው በህወሃት አመራር የተመረጡ ከተሞች አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ጎንደር፣ ባህርዳርና፣ ሻሸማኔ መሆናቸው ተነግሯል። በተጨማሪም ህወሃት በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ጥቃት ለመፈጸም ማቀዱን ለኢሳት ከደረሰውና ለህዝብ ይፋ ከሆነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
ህወሃት/ኢህአዴግ ሶማሊኛ ተናጋሪ የሆኑትን የሶማሌ ክልል ተውላጆችን ወደተጠቀሱት ከተሞች በማምጣት በህዝቡ ላይ ጥቃት ለመፈፀም እንዳቀደ የተናገሩት የኢሳት ምንጮች፣ ይህ የሽብር ጥቃት በጸረሽብር ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የወሰደው አቋም አለም አቀፍ ድጋፍ ያስገኝልኛል ብሎ እንደሚያስብ ለማወቅ ተችሏል። በከተሞች ላይ የህወሃት አመራር ሊወስደው ያሰበው ጥቃት በአገር ውስጥ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በጸረሽብር ህግ መሰረት ለማስቆም ይረዳል ብለው እንደሚያስብ ተነግሯል።

በጎንደር ከተማ የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በጸጥታ ሃይሎች ተስተጓጎለ
ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008)
ሰሞኑን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ ረቡዕ ምሽት በጎንደር ከተማ ሊካሄድ የነበረውን ልዩ የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት መስተጓጎሉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።
ላለፉት ሶስት ቀናት ከቤት ባለመውጣት አድማ ውስጥ የቆዩት የከተማዋ ነዋሪዎች ዝግጅቱን ለመታደም ወደ አደባባይ ቢወጡም ከጸጥታ ሃይሎች ጋር አለመግባባት መፈጠሩን እማኞች አስረድተዋል።
በከተማዋ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ልዩ ሃይል ተሰማርቶ እንደሚገኝ የተናገሩት እማኞች ነዋሪዎች ሃዘናቸውን ለመግለጽ በመስቀል አደባባይ ቢገኙም የጸጥታ ሃይሎች ዝግጁትን ለመበተን ሙከራ ማድረጋቸውን አስረድተዋል።

የአማራና ኦሮሞ ፊዴራል ፖሊስ አባላት ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008)
የአማራና የኦሮሞ የፌደራል ፖሊስ አባላት ያልታጠቀ ህዝብ ላይ አንተኩስም ብለው አቋም መያዛቸውን ተከትሎ፣ የህወሃት ባለስልጣናት የአማራና የኦሮሞ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በምስጢር በመጥራት ዛቻና ማፈራሪያ መስጠታቸው ተነገረ።
የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሃላፊዎች ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ራሳችንን ለማዳን ምን ማድረግ አለብን በሚል የኦሮሞና የአማራ የፌዴራል ፖሊስ አባላትን በመለየት ማወያየታቸው ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል።

በደብረማርቆስ የተጀመረው አድማ ረቡዕ እንደቀጠለ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 11 ፥ 2008)
ማክሰኞች ከሰዓት በኋላ በደብረ ማርቆስ ከተማ የተጀመረው የሰራ ማቆም አድማ ረቡዕ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉንና ነዋሪው የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ እንዲያበቃ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ።
የከተማዋ ነዋሪ ያነሱት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ምክንያት ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸው ይታወሳል።
ተቃውሞ ረቡዕ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን የተናገሩት እማኞች በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም የግል ድርጅቶች በአድማው ተሳታፊ መሆናቸውን ከዜና ዝግጅት ክፍላችን ጋር ቃለምልልስን ያደረጉ የደብረማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች አስረድተዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ባለፈው ቅዳሜ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍን በማድረግ በጎንደር እና ባህር ዳር ከተሞች እንዲሁም በኦሮሞያ ክልል የተፈጸሙ ግድያዎችን ማውገዛቸው ይታወሳል።

Friday, August 5, 2016
“በህወሀት ሽብር፣ ትጥቁን አይፈታም ጎንደር” – በሰሜን አሜሪካ ከሚኖሩ የአርማጭሆ ተወላጆች የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በዚህ ወር፣ በታሪካዊ መዲናችን በጎንደር ከተማ፣ ሁለት ታላላቅ ክስተቶች ተፈጽመዋል። ሀምሌ 24፣ 2008 ዓም ጎንደር ላይ የታየው ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ አለምን አስደንቋል። ይህ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ የተሳተፈበት፣ በላቀ ስነምግባርና ቆራጥነት የተመራው ሰልፍ፣ የአማራውን ህዝብ ታላቅነትና ደግነት አስመስክሯል። በዚህ ታሪካዊ ሰልፍ፣ ከመላው የአማራ ክልሎች የተሰባሰው ህዝብ፣ ለወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ብቻ ሳይሆን፣ በመላው ኢትዮጵያ በሚኖረው የአማራው ህዝብ ላይ ህወሀት የሚፈጽመውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ በአንድ ድምጽ በማውገዝ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ እውነተኛ የዜጎችን እኩልነት የሚያስከብር፣ የሀገራችን ሉዓላዊነት የሚረጋግጥ፣ የእምነት ነጻነትን የሚንከባከብ ሥርዓት እንዲመሰረት በአንድ ድምጽ ጥሪ አድርጓል። ይህን አዲስ ትግል መዕራፍ የከፈተልን፣ ጀግናው የጎንደር ህዝብ፣ ህወሀት የከፈተበትን ጥቃት ለመከላከል ሀምሌ 5 ቀን፣ የፈጸመው ተጋድሎና የከፈለው መስዋዕትነት ነው። የጎንደር ህዝብ ጀግኖች ልጆቹን ገብሮ ያቀጣጠለው ትግል እንዲሳካ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በህብረት ልንነሳ ይገባል።
የጎንደር ህዝብ ከእንግዲህ በህወሃት /ኢህአዴግ አንገዛም አለ
ሐምሌ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጎንደር ከተማ ህዝብ ገንፍሎ በመውጣት በህዋሀት ኢህአዴግ ላይ ያለውን ተቃውሞ ሲያሰማ ውሎአል። ከእየቦታው የተሰባሰበው የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በቀጥታ በመተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። በአዘዞ በአርሶአደር ታጣቂዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። የህዝቡን ትግል ለመርዳት ከወልቃይትና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር መግባታቸውን ተከትሎ ወታደሮቹ ጥቃታቸውን ቀንሰዋል። በልዩ ሃይል እና በመከላከያ መካከል ልዩነት መፈጠሩንም የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ሰራተኞች ተቃውሞ እያሰሙ ነው
ሐምሌ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አስተዳደር ያለሰራተኞቹ ፈቃድ ለአባይ ግድብ በሚል የአንድ ወር ደሞዛቸውን ከነሐሴ ጀምሮ እንደሚቆርጥ ማስታወቁን ተከትሎ ሰራተኞቹ ተቃውሞውአቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የሰራተኛው ተቃውሞ ያስፈራው አስተዳደሩ ውሳኔውን ለሚቀጥለው ወር መተላለፉን አስታውቋል።
በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በጎርፍ አደጋ ተጠቁ፡፡
ሐምሌ ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር በ2 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በመገንባት ላይ ያለው ርብ ግድብ ከመፍረሱ ጋር ተያይዞ ከ17 በላይ ሰዎች መሞታቸው እንዲሁም ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ከደረሰባቸው በሁዋላ፣ የግድቡ ውሃ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎችን ማጥለቅለቁ ታውቋል፡፡በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ መንገድ ዳርና ወደተራራ ቦታዎች በመሄድ ለመስፈር ሙከራ እያደረጉ ነው።
ግድቡ በ4 አመታት ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ ከ8 አመታት በሁዋላም ግንባታው ፈቅ አላለም።
ሶስት የኢሲኤ (ECA) ሰራተኞች ታሰሩ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ቦምብ እና መሳሪያ ተገኝቷል በሚል ሶስት የድርጅቱ ሰራተኞች የሆኑ ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ። ዋና ሃላፊው ሚስተር ካርሎስ ሎፔዝ የድርጅቱን ሰራተኞች ባልተጣራ ጉዳይ አሳልፈው መስጠታቸው በሰራተኞች ዘንድ እያነጋገረ መምጣቱንም መረዳት ተችሏል።
አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታተ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጽ/ቤት ግቢ ወስጥ ተገኘ ከተባለው መሳሪያ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች ሚኪያስ ቸርነት፥መላኩ ቡልቶ፣ እና ፋንታሁን ገድሉ መሆናቸውም ታውቋል።
ባህርዳር የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው ተባለ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጊዜው ያለፈበትና ምላሽ ያገኘ መሬቱም የትግራይ ነው በማለት መግለጫ የሰጡት የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት፣ ባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ባለሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት መደብደብ የጀመረው አርብ ምሽት ሲሆን፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በድንጋይ እየተደበደበ ይገኛል። ተቃውሞው በከተማዋ እየሰፋ መገኘቱንም መረዳት ተችሏል።
በእነብርሃኑ ተክለ ያሬድ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው 4 ተከሳሾች እስራት ተበየነባቸው
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
ባለፈው አመት ወደ ኤርትራ በመጓዝ የግንቦት ሰባት ሃይልን ለመቀላቀል ሙከራ ሲያደርጉ በድንበር ላይ ተይዘዋል ተብለው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው አራት ተከሳሾች ከአራት እስከ አምስት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።
ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የግንቦት ሰባት አባል በመሆንንና አባላትን በመመልከል አድርጎታል በተባለው ክስ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአምስት አመት ጽኑ እስራት ተወስኖበታል።
በአዲስ አበባና በክልሎች ስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ተባለ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
ከሃሙስ ጀምሮ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ እንዳልሆነ ታውቋል።
ሃሙስ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለስልጣናት በክልሉ የተቃውሞ ሰላምዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ድረገጾች ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው ሲሉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸው ይታወሳል።
በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎች ወደኦሮሚያ ክልል እንዳይጓዙ ማሳሰቢያ ሰጠ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
የአሜሪካ መንግስት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሃገሪቱ ኤምባሲ የሚሰሩ ሰራተኞች ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዳይጓዙ አሳሰበ።
በክልሉ ቅዳሜና እሁድ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ በማህበራዊ ድረገጾች ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑን የገለጸው የሃገሪቱ መንግስት ከኢምባሲው ሰራተኞች በተጨማሪ አሜሪካውያን በክልሉ ሊያደርጉ ባሰቡት ጉዞ ላይ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።
በኦሮሚያ ክልል የታቀደው ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘለት ቀንና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ተገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በኦሮሚያ ክልል ሊካሄድ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች በማስተባበር ላይ የሚገኙ አካላት ህዝባዊ ተቃውሞ በተያዘለት ቀንና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ለኢሳት ገልጸዋል።
ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት እነዚሁ አካላት የተቃውሞ ሰልፍን ለማድመቅ የሚረዱ የተለያዩ ግብዓቶች መዘጋጀታቸውን እና ህዝቡ ያለውን ጥያቄ ለማሰማት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስረድተዋል።
በጎንደርና ኦሮሚያ የሚካሄዱትን ተቃውሞችን ለመግታት እርምጃ እንደሚወሰድ ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ገለጹ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሃዝባዊ መሰረት የሌለው ነው ሲሉ ከቀናት በፊት የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ መንግስት ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን ለመወጣት ህገወጥ ያለውን ድርጊት ለመግታት እርምጃን እንደሚወስድ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የጎንደር ከተማ ተቃውሞ እየተካሄደ ባለበት ወቅት መግለጫን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡ አሉ የሚላቸውን ችግሮች በዴሞክራሲያው መንገድ ለመፍታት የሚችልበት ሰፊ እድል አለ ሲሉ ተናግረዋል።
በጎንደር መጠነ ሰፊ ግጭት እየተካሄደ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
አርብ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ የጀመሩትን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ በከተማ መጠነ ሰፊ ግጭት በመካሄድ ላይ መሆኑን እማኞች ለኢሳት አስታወቁ።
የከተማዋ ነዋሪዎች አርብ ረፋድ የወልቃይት ጠገዴ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ መባሉን ተከትሎ ለተቃውሞ ፍርድ ቤት ቢሰባሰቡም ድርጊቱ ወደ ግጭት መለወጡ ታውቋል።
የጎንደርን ህዝባዊ እምቢተኝነት በአጎራባች አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በጎንደር ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ያለውን ውጊያ ተከትሎ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ የሚኖሩ ዜጎች ትግሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ። ይህ ዜና እየተጠናከረበት ባለበት ሰዓት በጎንደር ከተማና አካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ሲሆን፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት መንገድ መዝጋቱ ታውቋል።
በጎንደር ውጊያ እየተደረገ ነው
ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)
በአዘዞ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ተነገረ። 24ኛው ክፍለ ጦር ማዘዣ አካባቢ በህዝቡና በመከላከያ እየተደረገ ያለው ውጊያ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ተፋፍሞ መቀጠሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። መከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ እየተጠቀመ መሆኑንም ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Wednesday, August 3, 2016
የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ምላሽ ተሰጥቶበታል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)
የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ከተመለሰ ዓመታት አልፈውታል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ። ዛሬ ጥያቄውን የሚያነሱ የሌሎች ሃይሎች እጅ ስላረፈበት ነው ሲሉም የመንግስት ያሉትን አቋማቸውን ገልጸዋል። የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር እና የብዓዴን አመራር አባል አቶ ካሳ ተክለብርሃንም ወልቃይት በትግራይ ክልል የተከለለው ነዋሪዎቹ ትግሬዎች በመሆናቸው ነው ሲሉ ዕርምጃው ትክክል ነበር ሲሉ ማጠናከሪያ ሰጥተዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላት ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ወልቃይት የትግራይ ነው ማለታቸውን ተቃውሙ
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)
የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የወልቃይትን አማራነት አስመልክቶ ባህርዳር ውስጥ የሰጡት ምላሽ ተገቢ አለመሆኑንና፣ በገሃድ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ የከዳ ምላሽ መሆኑን አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያዊነት በማያምን አካል የተሰጠ ምላሽ ነው ሲሉ የገለጹት የኮሚቴ አባላቱ፣ ህዝቡ ያነሳውን ጥያቄ ምላሽን እስኪያገኝ ድረስ ሰላማዊ ትግላቸው ቀጣይ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል።
በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ያነሱ ነዋሪዎች ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጡ ቢደረግ ጥያቄው ግልጽ መልስን እንደሚሰጥ የኮሚቴ አባላቱ አክለው ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በወልቃይት ጠገዴ አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ እንጂ አካባቢው የትግራይ አካል ነው ሲሉ ምላሽን እየሰጡ ይገኛል።

በአዲስ አበባ የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠር አለመቻሉ ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በመዲናይቱ በመሰራጨት ላይ ያለውን የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ መቆጣጠር አለመቻሉንና ተጨማሪ በርካታ ሰዎች በየዕለቱ በበሽታው በመያዝ ላይ መሆናቸውን ይፋ አደረገ።
የኮሌራ በሽታው ስርጭት ከተጠበቀው በላይ መሆኑን ተከትሎ የከተማዋ ጤና ቢሮ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በዘመቻ ጀምሯል።
የኮሌራ በሽታው ስርጭት ከተጠበቀው በላይ መሆኑን ተከትሎ የከተማዋ ጤና ቢሮ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በዘመቻ ጀምሯል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በግጭት ከምትታመሰው ደቡብ ሱዳን መውጫን አጥተው እንደሚገኙ ገለጹ
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)
ነዋሪነታቸው በጎረቤት ደቡብ ሱዳን የሆነ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ በመዛመት ላይ ካለው ግጭት መውጫን አጥተው እንደሚገኙና ከመንግስት ምላሽ ማጣታቸው ለኢሳት አስታወቁ።
ከመዲናይቱ ጁባ በቅርብ ርቀት ላይ በመካሄድ ያለው ግጭት ወደ ዋና ከተማዋ ይዛመታል በሚል የተለያዩ ሃገራት ዜጎቻቸውን ከደቡብ ሱዳን እያስወጡ መሆናቸው ታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ በሃገሪቱ ዳግም በተቀሰቀሰው ግጭት ከ60 ሺ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው በመፈናቀል ጎረቤት ዩጋንዳ በመሰደድ ላይ መሆናቸውን አመልክቷል።

የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት ለስራው ማስኬጃ የሚሆን ብድር አለመገኘቱ ተገለጸ
ኢሳት (ሃምሌ 27 ፥ 2008)
ከውጭ ብድር በማግኘት ከሁለት ቢሊዮን ዩሮ በላይ ግንባታው እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረው የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጄክት ለስራው ማስኬጃ የሚሆን ብድር አለመገኘቱ ተገለጸ።
ለፕሮጄክቱ ማስኬጃ የሚሆነው 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ብድር እንዲያፈላልግና ግንባታውን እንዲያከናውን ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ መንግስት በሚፈልገው የወለድ ምጣኔ ብድር ማግኘት አለመቻሉን አስታውቋል።
ለፕሮጄክቱ ማስኬጃ የሚሆነው 2.5 ቢሊዮን ዩሮ ብድር እንዲያፈላልግና ግንባታውን እንዲያከናውን ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው የጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ መንግስት በሚፈልገው የወለድ ምጣኔ ብድር ማግኘት አለመቻሉን አስታውቋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)