Thursday, June 11, 2015

በአማራ ክልል የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ እያተደረጉ ነው

የ2007 ምርጫን የወያኔ መንግስት በሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ድምጽ ምርጫውን እነዳሸነፈ ማወጁ ይታወሳል  ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ውጥረት የነገሰ  ሲሆን  የምርጫውን የውጤት ማጭበርበር በመቃወም  ከሌላው ክልል በበለጠ በኦሮሚያና፣ በአማራ ክልሎች የህዝቡ ቋጣ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን፣በዚህም የተነሳ  በአማራ  ክልል የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቆለ በመመጣቱ በክልሉ ላይ የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ ማድረጋቸውን ተገለፀ::


 ከክልሉ ባገኘነው መረጃ መሰረት ግንቦት 16/2007 ዓ/ም የተካሄደውን የይስሙልና ከምርጫውም በኋላ ወያኔ /ኢህአዴግ መቶ በመቶ እንዳሸነፈ በተለያዩ ሚዲያዎች በተገለፀው ግዜያዊ ውጤት ባለመርካቱ የተነሳ    በአማራ ክልል የሚኖሩ የክልሉ ነዋሪዎች  ድምፃችንን ተሰርቀናል በማለት በተለያየ መንገድ ቁጣቸውን  እየገለፁ ሲሆን ከዚህም የተነሳ  በክልሉ ያሉ የወያኔ ካድሬዎች  ህዝቡ ተቃውሞ ሊያነሳ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት እነደፈጠረባቸውና በፍርሃት ውስጥ እነደሚገኙ ታውቋል ::

 በክልሉ ያለውን የህዝቡን ቋጣ ተከትሉ ለተፈጠረባቸው ስጋት የወያኔ ካድሬዋች እየወሰዱ ያሉት እርምጅ በክልሉ የሚገኙት እንደ ሱር ኮንስትራክሽን፤ ባንኮች፤ ቴሌና የመሳሰሉት ድርጅቶችን ቀደም ሲል በህጋዊ መንገድ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የጥበቃ ሰራተኞችን በማባረር ልዩ ጥበቃ ተብለው በሚታወቁ ታጣቂዎች እንዲጠበቅ እያደረጉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣ ወያኔዎች ይህንን ማድረጋቸው የበለጠ የህዝቡን ቁጣ እንደሚቀሰቅሰው የአካባቢው ነዋሪዎች እየተናገሩ ይገኛሉ::

ይህ አይነቱ በታጣቂ ሓይሎች ተደርጎ ህዝቡ ዓመፅ እንዳያካሂድ ተብሎ የሚደረግ የተጠናከረ የጥበቃ አካሄድ በአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላው ያገራችን አካባቢዎች ውስጥ ለውስጥ እየተሰራበት እንደሆነ።ያገኘነው  መረጃ ያስረዳል::

ሪፖርተር ገዛኸኝ አበበ


No comments:

Post a Comment