Tuesday, June 30, 2015

በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የሚቀርቡት የፖለቲካ ክሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቂኝ እየሆነ ነው።

ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም በ1997 ምርጫ ወቅት በቅንጅት መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና በሲቪክ ተቋማት መሪዎች ላይ የቀረበው ክስ ፣ 24 ሰአታት አስቂኝ ፊልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር። በፍርድ ቤቱ የነበረውን ሁኔታ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት በሚል ርእስ ዘርዝሮ ማቅረቡ ይታወቃል።
በቅርቡ አይ ኤስ ኤስ የተባለው አሸባሪ ድርጅት በ30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ለማውገዝ መንግስት በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ተቃውሞ መርተዋል፣ በተቃውሞው ተሳትፈዋል እየተባሉ በእስር በሚሰቃዩ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ክስም እንዲሁ ፈገግ እያሰኘ ነገር ግን በዚያው ልክ እያሳዘነና አገራችን የገባችበትን የወርደት ደረጃ እያመላከተን ነው።
ቴዎድሮስ አስፋው ፣ ያሬድ ደመቀና አንዋር ከድር በተባሉ ወጣቶች ላይ የቀረበው ክስ እንዲህ ይላል ” ተከሳሽ የሃሰት ወሬዎችን በማውራት ጥላቻና የፖለቲካ ሁከት ለመቀስቀስ በማሰብ በ14/08/07 ዓም ከጧቱ 12 ሰአት ሲሆን በአዲስ አበባ ክ ከተማ በ01/02/03 በአሸባሪዎች ጥቃት ምክንያት ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሰዎችን በመሰብሰብ ” መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው” የሚል ሃሰተኛ ወሬዎችን በማውራት ሁከት መቀስቀስ ወንጀል ተከሷል። ”


Monday, June 29, 2015

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው

እነ ቴዎድሮስ አስፋው ጥፋተኛ ተባሉ

• ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ እንዲሰፍን እየታገልኩ መሆኔ በክስ ማቅለያነት እንዲወሰድልኝ›› ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ‹‹ኢህአዴግ ሌባ ነው፣ ህገ መንግስቱ ወረቀት ነው፣ ታፍነናል፣ ታስረናል፣ መለስ የሞተው ደንግጦ ነው፣ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በቁሙ የሞተ ነው፣ ቴዎድሮስ ለህዝብ ነው የሞተው›› በሚል ብጥብጥና ሁከት ፈጥራችኋል፣ የሀሰት ወሬ አውርታችኋል ተብለው የተከሰሱት እነ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ሰኔ 22/2007 ዓ.ም አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ

(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ 5 የአጋዚ ጦር አባላት የነበሩ የስርዓቱ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በመክዳት አስመራ ገቡ:: እነዚሁ 5 ታጋዮች ኤርትራ የሚገኘውን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቅለዋል:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል ይታገሉ የነበሩም ሆነ የሕወሓት ጦርን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመምረጥ ወደ ኤርትራ በመሄድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን እየተቀላቀሉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ:: ሰሞኑን ይህንኑ ንቅናቄ የተቀላቀሉት 5ቶ የአጋዚ ጦር አባላት
1ኛ. ግራማ ተላይነሕ
2ኛ. ሄኖክ እንዳልካቸው
3ኛ ስለሺ ተስፋሁን
4ኛ. ምርት ይሁን መንገሻ
5ኛ ስማቸው ካሴ ይባላሉ።


Sunday, June 28, 2015

5 የመኢአድ አባሎች አንዳርጋቸው ፅጌን ይመስክርልን አሉ

በነ ዘመነ ካሴ መዝገብ የተከሰሱት 5 የመኢአድ አባሎች ናቸው አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርብላቸው ነው የጠየቁት የተከሰሱት የግንቦት 7 አባል ናችሁ ተብለው ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ስልጠና ተሰጥቷችሁ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ስትንቀሳቀሱ ነበር ተብለው ላለፉት ሁለት አመታት በእስር የሚገኙት
እነዚህ ተከሳሾች አንዳርጋቸው ፅጌ የሚባል ሰው አናውቅም አንዳርጋቸው አሱ አውቃቸዋለሁ አሰልጥኛቸዋለሁ የሚል ከሆነም በናንተ ቁጥጥር ስር ስላለ ችሎቱ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ይዘዝልን እና ይመስክርልን ወይም ይመስክርብን ሲሉ ለፍርድ ቤት አመልክተዋል አቶ አንዳርጋቸው ቀርቦ ምስክርነት ይሰጥ ይሆን ? አቃቤ ህግ በህይወት ይኑር አይኑር የማይታወቅ ሠው ይቅረብልን ማለት አግባብነት የለውም ብሏል ለማንኛው ቀጠሮው ሀምሌ 03/2007 ዓም ስንተኛ ችሎት እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ ፍርድ ቤቱ ግን ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው


በወጣት ተመስገን ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል የኢህአዴግ የግፍ አስተዳደር መገለጫ ነው ሲል መድረክ አስታወቀ

ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣት ተመስገን ታፈሰ ተሰማ ዕድሜው 22 ዓመት ሲሆን በትምህርት ደረጃውም በማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪ ያገኘ ወጣት ነው፡፡ ትውልዱና ዕድገቱ በደቡብ ክልላዊ መንግስት በቡርጂ ወረዳ ውስጥ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የኢማዴ-ደህአፓ/መድረክ አባል ሆኖ ለመታገል የወሰነና በመድረክ አባልነታቸው ምክንያት በሀገራቸው ሠርተው የመኖር የዜግነት መብታቸውን እየተነፈጉ አስተዳደራዊ ግፍ እየተፈጸመባቸው ካሉ ወጣቶች አንዱና ተጫባጭ ምሳሌ ሆኖ የሚገኝ ወጣት ነው ብሎአል መድረክ።
መድረክ የወጣቱን በደል ሲዘረዝር “የቡርጂ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ለትራንስፖርት አቅርቦት አደረጃጀት ስምሪት ባለሙያ፣ የሥራ መደብ ሠራተኛ ለመቅጠር በ05/09/07 የቅጥር ማስታወቂያ አወጣ፡፡ በማስታወቂያው መሠረት የጽሑፍና የቃል ፈተናዎች የተሰጡ ሲሆን የጽሑፍ ፈተናው ከመቶ ዘጠና፣ የቃል ፈተናው ከመቶ አምስት እና የትምህርት ማስረጃው ከመቶ አምስት እንዲይዝ ተደርጎ ውድድሩ ተካሄደ፡፡ ይኼው ጽ/ቤት በ18/09/07 በቁጥር 327-ኢ2-05 ባወጣው የውድድር ውጤት መግለጫ ማስታወቂያ መሠረት አቶ ተመስገን በጽሑፍ ፈተናው 84፣ በቃል ፈተናው 5፣ እና በትምህርት ማስረጃው 5 በድምሩ 94 ከመቶ በመግኘት በከፍተኛ ነጥብ አንደኛ ወጥቶ አለፈ፡፡ ” ይላል።

Friday, June 26, 2015

I need my dad to be here, pleads daughter of ‘Ethiopian Mandela’ as she stars in play dramatising plight of kidnapped father

Published: 26 June, 2015
by KOOS COUVÉE

IMAGINE celebrating your 16th birthday while your loving dad, who has committed no crime, is on death row 4,000 miles away in a jail where you fear he may be tortured.

This scenario is in fact reality for Helawit “Holly” Hailemariam, 15, from Clerkenwell, whose father, Andargachew Tsege, a British man from Holloway and a prominent opposition activist in his native Ethiopia, is languishing in a jail in the East African country.

On Wednesday, a new play by Islington Community Theatre starring Helawit and five of her friends marked the anniversary of Mr Tsege’s kidnapping while he was travelling through Yemen.

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

ሰኔ ፲፰ (አስራ ሰምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ አንዳርጋቸው የህግ ድጋፍ በማያገኙበትና ይግባኝ ሊጠይቁ በማይችሉበት ሁኔታ በአስከፊ ሁኔታ መታሰራቸውን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሀሞንድ አውግዘዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው አያያዝ እና ደህንነት እንደሚያሳስበን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብንገልጽም ከቃል ያለፈ መልስ አለገኘንም፣ የምክር እና ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት መብትም አላገኙም ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ በተደጋጋሚ ለቀረበው ጥያቄ ኢትዮጵያ መልስ መንፈጓ ከፍተኛ ዋጋ በሚሰጠው የእንግሊዝና የኢትዮጵያ ግንኙነት ላይ ጥላ አደጋ ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸው በአስቸኳይ የህግ ድጋፍና ምክር እንዲያገኙ፣ በቤተሰቦቻቸውም እንዲጎበኙ መንግስት እንዲፈቅድ ለቴዎድሮስ አድሃኖም መናገራቸውንም የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባወጠው መግለጫ ጠቅሷል።
አቶ አንዳርጋቸው በየመን ተላልፈው ከታሰሩ ልክ አንደኛ ዓመት መሆናቸውን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባው መንግስት የተወሰደው እርምጃ ተቀባይነት እንደሌለው በግልጽ ያመላከተ ነው ተብሏል።
የውጪ ጉዳይ ቢሮው ጉዳዩን ከዲፕሎማሲያው ልውውጥ በላይ በማድረግ ለአደባባይ ማብቃቱን ዘጋርዳያን ዘግቧል።
ከእንግሊዝ መንግስት ከፍተኛ እገዛ የሚያገኘው ኢህአዴግ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለሰጡት ማስጠንቀቂያ የሰጠው መልስ በመግለጫው አልተጠቀሰም።
ኢህአዴግ በውጭ ሃይሎች ግፊት እንደማይንበረከክ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የኢህአዴግን እጅ ሊጠመዝዙ የሚፈልጉ ሁሉ ገንዘባቸውን ይዘው በሊማሊሞ መሄድ ይችላሉ ብለው ነበር።


UK tells Ethiopia its treatment of opposition official imperils ties

LONDON
UK tells Ethiopia its treatment of opposition official imperils ties
The British government told Ethiopia on Thursday its treatment of an imprisoned opposition figure, who is also a British national, was unacceptable and that the case risked hurting ties between the two countries.
Andargachew Tsige was sentenced to death in 2009 in absentia over his involvement with an opposition political group and another trial handed him life behind bars three years later. He was arrested in Yemen in 2014 and extradited to Ethiopia.
British Foreign Secretary Philip Hammond said on Thursday he had discussed the matter with Tedros Adhanom Ghebreyesus, his Ethiopian counterpart, and delivered a stern message.
"I am deeply concerned that, a year after he was first detained, British national Andargachew Tsige remains in solitary confinement in Ethiopia without a legal process to challenge his detention," Hammond said in a statement after the call.
"I am also concerned for his welfare and disappointed that our repeated requests for regular consular access have not been granted, despite promises made."
Britain summoned Ethiopia's chargé d'affaires in August last year to seek assurances that Tsige would not be put to death.
Secretary-general of the Ginbot 7 political group, he was among 20 opposition figures and journalists charged with conspiring with rebels, plotting attacks and attempting to topple the government.
Hammond said Britain's ties with Ethiopia were at risk.
"Ethiopia's failure to grant our repeated and basic requests is not acceptable," he said. "The lack of progress risks undermining the UK’s much valued bilateral relationship with Ethiopia."
(Reporting by Andrew Osborn; Editing by Stephen Addison )
Source - Reuters


Wednesday, June 24, 2015

በፍርድ ቤት ውሳኔ የተፈቱት ሰላማዊ ዜጎች በድጋሚ በመንግስት ታፈኑ።

ኢሳት ዜና (ሰኔ 17, 2007)

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አራት የፓርቲ አባላት ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች በድጋሚ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አራቱ ተከሳሾች ፍርድ ቤት ከተከሳሾች ፍርድ ቤት ካስተላለፋቸው ከሁለት ወር በላይ በእስር ቤት በመቆየታቸው ምክኒያት ሰኞ ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።

አራቱ ተከሳሾች ማክሰኞ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወጡ ቢደረግም በእስር ቤቱ በር ላይ ፖሊሶች እና የደህንነት ሀይሎች ከእስር የተፈቱትን አባላት በድጋሚ ለእስር እንደዳረጉዋቸው ከሀገር ቤት የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በቂሊንጦ እና ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የነበሩት ተከሳሾች መንግስት በሊቢያ የተገደሉ ኢትዮጲያንን ግድያ ለማውገዝ ጠርቶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ለእስር ተዳርገው መከሰሳቸው ይታወሳል።

ጉዳያቸውን ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤትም ትላንት ሰኞ ባስተላለፈው ውሳኔ ተከሳሾች ከተላለፈባቸው የሁለት ወር የእስር ቅጣት በላይ በእስር ቤት በመቆየታቸው ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል።

ይሁንና የቂሊንጦ እና 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ኤርሚያስ ጸጋዬ፤ ዳንኤል ተስፋዬ ፤ ወይንሽት ሞላንና ቤተልሄም አካለወርቅ ከእስር ቤት ቢፈቷቸውም የጸጥታ ሀይሎች በደቂቃዎች ልዩነት በድጋሚ በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።

አራቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በነጻ እንዲሰናበቱ ከተወሰነ በኋላ በምን ምክኒያት በድጋሚ ለእስር እንደተዳረጉ ከመንግስት አካላት የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ከሀገር ቤት የደረሰን መረጃ አክሎ አመልክቷል ።

ከወረት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ መንግስት በሊቢያ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ግድያ ለማውገዝ ጠርቶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ብጥብጥን ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ከ 1ሺ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

ለእስር ከተዳረጉ መካከልም ከመቶ የሚበልጡ ክስ ተመስርቶባቸው የሚገኝ ሲሆን አራቱ የፓርቲ አባላት ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ ሲተላልፍ የመጀመሪያው እንደሆነ ታውቋል።
የቀሪ ታሳሪዎች የክስ ሂደትም በተላያዩ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ፍርድ ቤቶች በመካሄድ ላይ ይገኛል።


አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ሪፕሪቭ ዘመቻ ጀመረ

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝ አገር የሚገኘው ሪፕሪቭ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስቲር ዴቪድ ካሜሩን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል። አቶ አንዳርጋቸው ለአንድ ሳምንት መታሰራቸው ረጅም መሆኑ ሳያንስ ለአንድ አመት ታስረው መቆየታቸው ለማሰብም የሚከብድ ነው ሲል የህግ ድጋፍ በመስጠት የሚታወቀው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ገልጿል። በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሪፐሪቭ ዌብሳይት በመግባት በፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻው እንዲሳተፉ ጠይቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በግፍ የታሰሩበትን አንደኛ አመት በማስመልከት በቤልቦርን ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
ኢትዮጵያውያኑ የእንግሊዝ መንግስት እስካሁን ጉዳዩን ችላ ማለቱን በመቃወም እና አሁንም አቶ አንዳእጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግ በማሳሳብ የተዘጋጀውን ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ሰጥተዋል።
በጀርመን አገር በዱስልዶርፍ እንዲሁም በሙኒክ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸውን ዘገይቶ የደረሰን ዜና ያመለክታል። በዱስልዶርፍ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞቸውን በእንግሊዝ ቆንስላ ፊት ለፊት አካሂደዋል።


አንድ ኢህአዴግን ከድተዋል የተባሉ ጎልማሳ በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ሰሃራ በረሃ አቅራቢያ ተገደሉ፣ ሌሎች አምስት ወጣቶችም በአደጋው አልቀዋል

ሰኔ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያሬድ ንጉሴ የተባለ ባለፈው ወር አውሮፓ የገባ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ለኢሳት እንደገለጸው በቅርቡ 25 ኢትዮጵያውያንና 2 ኤርትራውያን ሆነው ከሱዳን ወደ ሊቢያ ሲጓዙ፣ ደንጎላ በምትባል ቦታ ላይ በሱዳን የመከላከያ ሰራዊት አጃቢነት የመጣ ኢትዮጵያዊ የደህንነት ሰራተኛ የ48 አመት ጎልማሳ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ከመኪና አስወርዶ በሽጉጥ እንደገደለው ገልጿል። “ወታደሮችን የጫነው መኪና” ከጎን በኩል መጥቶ የተሳፈርንባትን መኪና ሲጋጫት ሁላችንም ወደ ጎን ወደቅን የሚለው ያሬድ፣ ሁለት ወጣት ባለትዳሮችን ጨምሮ 5 ወጣቶች ወደያውኑ ሞታቸውን በፎቶአስደግፎ ተናግሯል።
የልጆቻቸውን መሞት ላልሰሙት ወላጆች ሲባል ኢሳት በአደጋው የሞቱትን ኢትዮጵያውያን ስም ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል። እንዲሁም መሞታቸው የተነገረው የቀድሞው የኢህአዴግ አባል ስምም ለቤተሰቦቻቸው ሲባል ይፋ አያደርግም።
ሟቹ የቀድሞው የኢህአዴግ አባል ” እግዚአብሄር በሰላም ያስገባኝ እያሉ” ሲጸልዩ እንደበር የሚናገረው ያሬድ፣ የደህንነት ሰራተኛው ፎቷቸውን ይዞ ከመጣ በሁዋላ ከመኪና ላይ አውርዶ በሽጉጥ ገድሏቸዋል ብሎአል። የደህንነት ሰራተኛው መገናኛ ሬዲዮ ይዞ እንደነበርም ተናግሯል።
የ5ቱ ኢትዮጵያውያንን አስከሬን ሰሃራ በረሃ ላይ ቀብረው በአካባቢው ነዋሪዎች ድጋፍ ተርፈው በመጨረሻ ሊቢያ መግባታቸውንም ገልጿል።
ኢትዮጵያውያንን ከሱዳን ወደ ሊቢያ እንዲሁም ወደ አውሮፓ በማሻገር በኩል ሱዳን የሚገኘው ኢምባሲ ሰራተኞች እጅ እንዳለበት ያሬድ ተናግሯል። በተዘዋዋሪ መንገድ ገንዘብ የምንሰጠው ለኢምባሲ ሰራተኞች ነው የሚለው ያሬድ፣ የግለሰቦችን ስም እየጠቀሰ የተዘረጋው መረብ ምን እንደሚመስል አጋልጧል። ከያሬድ ንጉሴ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል። በጉዳዩ ዙሪያ ሱዳን የሚገኘውን የኢትዮጵያን ኢምባሲ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም


Amnesty International Asks Ethiopia to Investigate Suspicious Murders and Human Rights Violations

The suspicious murder of opposition leaders and wide-spread human rights violations against opposition party members over the past few weeks raises questions about Ethiopia’s elections, said Amnesty International as the parliamentary poll results were announced yesterday.

The organization has also expressed concerns about the failure of the Africa Union Elections Observer Mission (AUEOM) and the National Elections Board of Ethiopia (NEBE) to properly monitor and report on allegations of widespread abuses before, during and after the election.

Tuesday, June 23, 2015

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከሰነዓ አለም አቀፍ አውሮፓላን ጣቢያ ታፍነው ከተወሰዱ በዛሬው ዕለት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ. ም፣ አንድ ዓመት ይሞላቸዋል። የወያኔ አረመኔዎች ይህን ዓይነት የውንብድና ተግባር ሲፈጽሙ በከፍተኛ ደረጃ ያሰሉት፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን፣ ንቅናቄው ብሎም ሕዝቡ፣ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት፣ የሚያደርገውን ትግል ለማዳከምና ከተቻለም ደግሞ ለማጥፋት እንደሆነ፣ ምንም የማያጠራጥር ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ የወያኔዎች ስሌት በምን ያህል ትክክል ነበር ?

ባለፈው አንድ አመት ውስጥ፣ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸመው የውንብድና አፈና ተግባር፣ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባለው ሕዝብ ልብ ውስጥ

Monday, June 22, 2015

እነ ወይንሸት ሞላ እንዲፈቱ ተወሰነ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡ አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት ሞላ አንድ ላይ ሆነው ፈጽመውታል ያለውን ክስ ማስረዳት እንዳልቻለ የገለጸው ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ መካከል የኤርሚያስ ፀጋዬ መከላከያ ምስክሮች በቦታው እንዳልነበረ እንዳስረዱ ገልጾ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡


የወንይሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሾቹ በቦታው እንዳልነበሩና ወንጀሉን እንዳልፈፀሙ አላስረዱም በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 6 ወር እንደሚያስቀጣ የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር የፈረደባቸው ሲሆን ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ፈቃዱ ‹‹የተከሰስኩት በፖለቲካ አመለካከቴ ነው›› በማለቱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተቃውመሃል በሚል 3 ወር እስራት ፈርዶበታል፡፡ ከሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀ

Sunday, June 21, 2015

መድረክ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ 1 እንዲሁም በትግራይ 1 አባላቶቹ መገደላቸውን ይፋ አደረገ

መድረክ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞንና በትግራይ ክልል ሁለት አባላቱ በ3 ቀናት ልዩነት እንደተገደሉበት አስታወቀ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በትግራይ ክልል የመድረክ አባል የነበረው አቶ ታደሰ አብርሃ እንደተገደለበት በመግለጫው ያስታወቀ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ደግሞ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን አቶ ብርሃኒ ኤረቦ የተባሉ የመድረኩ አባል ተገድለው ትናንት ጠዋት አስከሬናቸው መገኘቱን የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በምዕራብ ትግራይ ዞን የአረና/መድረክ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው በዘንድሮው ምርጫ በዞኑ የምርጫውን ሥራ በማደራጀት፣ በመቀስቀስና ታዛቢዎችን በመመደብ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የቆዩት አቶ ታደሰ አብርሃ አርአያ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብድበው መገደላቸውን መድረክ አስታውቋል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ለጊዜው ማንነታቸው በግልጽ ተለይቶ ያልታወቁ 3 ሰዎች ወደ ቤታቸው በመግባት በተፈጸመባቸው አሰቃቂ ድብደባ ሕይወታቸውን ያጡት አቶ ታደሰ፤ በምርጫው ቅስቀሳ ወቅትም በኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል ያለው መድረክ፤ “ምርጫው ሲያልፍ አንድ በአንድ እንለቅማችኋለን፤ የትም አታመልጡንም” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያም ደርሶባቸው ነበር ብሏል፡፡

Saturday, June 20, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ከሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ

• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዛሬ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አቀወ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Friday, June 19, 2015

በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች  በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት.....

በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች  በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት ያልተፈለጉትን ለማሰናበት ተብሎ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ወታደሮች አገልግሎታችን ግዜ ያበቃ በመሆኑ መሰናበት አለብን  በማለታቸው የተነሳ ስብሰባው እንደተቋረጠ ታወቀ።

ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት- በሰሜን እዝ በክፈለ ጦሩ አዛዦች ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለና ብርጋዴር ጀነራል ማዓሾ በየነ የተመራው ስብሰባ ግንቦት 21 2007 ዓ/ም የተካሄደ ሲሆን። እንደ አጀንዳ ያቀረቡት ደግሞ ከአስርና ከስባት አመት በላይ ካገለገሉት መካከል የተወሰኑትን ለማሰናበት በሚል ቢነጋገሩም ብዛት ያላቸው የሰራዊቱ አባላት ግን ከተባለው የአገልግሎት እድሜ በላይ ያገለገሉ ስለሆኑና። ላቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም“ ግዳጃችን ስለፈፀምን የሚገባንን ሰጥታችሁ ሸኙን” በሚል በአንድ ድምፅ ስለተቃወሙ ስብሰባውን እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው በማከል እንዳስረዳው- በአገልግሎት ስም የተወሰኑት ልንሸኝ ነው የሚለውን ሃሳብ እንደ ሽፋን እንጂ ዋናው አላማው ግን በወታደሩ ውስጥ በተካሄደው የግንቦት 16/ 2007ዓ/ም ምርጫ በረከት ያለ ድምፅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰጥቶ በመገኘቱ የተነሳ ይህ ደግሞ ለሰራዊቱ አዛዦች የራስ ምታት ስለሆነባቸው በምርጫ ጊዜ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መርጠው ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉት ወታደሮች ለመቀነስ የታለመ ሴራ ቢሆንም ነገር ግን ሳያስቡት ግርግር በመከሰቱ አጀንዳውን እንዳስቆሙት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።


Thursday, June 18, 2015

ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው 

ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣
1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡
በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ለሰማዕታቱ አደራ የምንሰጠው ምላሽ ምንድነው?

ኢትዮጵያ አንድ ተጨማሪ ወጣት ልጇን አጣች። ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓም ማታ የደብረ ማርቆሱ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ኢሰብዓዊ በሆነ ድብደባ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ወጣት በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ በጽናት ታግሏል። ለኢትዮጵያ ይበጃል ብሎ ባመነበት መንገድ ተጉዞ ለትግሉ ሕይወቱን ሰጥቷል። ሳሙኤል በሕይወቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በትክክል ያውቅ ነበር፤ ለህልፈት የዳረገው አደጋ በመድረሱ በፊት ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሰውበታል፤ ሆኖም ግን ግንባሩን አላጠፈም። በሕይወቱ ላይ ያንዣንበበውን አደጋ ምን ያህል የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ በመገመቱ “ከታሠሩኩም ህሊናዬ አይታሰርም፤ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ። በተለይ የኔ ትውልድ አደራ!”የሚል ኗሪውን እረፍት የሚነሳ ተማጽኖ በጽሁፍ አስቀምጦ የመጨረሻውን ከፍተኛ ዋጋ ከፍሏል። ለዚህ የሙት አደራ ምላሻችን ምንድነው?

የሟች ሳሙኤል አወቀ ጉዳይ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች እየተዘገበ ነው።

ኢሳት ዜና (ሰኔ 11, 2007)

ሰኞ ምሽት በደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው እጩ የፓርላማ አባልና የህግ ባለሙያ ሳሙኤል አወቀን በተመለከተ አለም አቀፍ ሚዲያዎች የዜና ሽፋን እየሰጡት ይገኛሉ። የ ሀያ ሰባት አመቱ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ማንነታቸው ባልታወቁ ሁለት ሰዎች አሰቃቂ ድብደባ ከተፈጸመበት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ብሉምበርግ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በባህር ዳር ከተማ ለመኖሪያ ቤት ባለ ይዞታዎች ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተመልሶ ተሰበሰበ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ 2007 ቅስቀሳን ተንተርሶ በህዝቡ ዘንድ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢህአዴግ፤ በከተማዋ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች ለረዢም አመታት ለኖሩ የይዞታ ባለመብቶች ከምርጫው በፊት ሰጥቶት የነበረውን በባለ ቀለም የብአዴን አርማና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መልሶ በመውሰድ ውሳኔውን ለመሻር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ኢህአዴግ “በየክፍለ ከተማው ከ380 በላይ አባወራዎችን የይዞታ ማረጋገጫ በመስጠት የመኖሪያ ቤት ባለቤት አድርጌአለሁ፡፡” በማለት በመገናኛ ብዙሃን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሂድ ቆይቷል። ይዞታችሁ ጸድቆላችኋል የተባሉ የህብረተሰቡ ክፍሎች ደስታቸውን ሲገልጹ ቢቆዩም፤ ምርጫው ካለቀ በኋላ ግን “የተሰጠው የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ችግር ስላለበት እንደገና መመርመር አለበት” በሚል ሰነዱን ገቢ እንዲያደርጉ ታዘዋል።

በርካታ ነዋሪዎች ለክልል ሪፖርተራችን እንደገለጹላት ባሳለፍነው ሳምንት በግንቦት ሃያ ክፍለ ከተማ የይዞታ ቦታ ማረጋገጫ ሰነድ የተሰጣቸው ነዋሪዎች፣ ቤት ለቤት በመዘዋወር ሰነዱን ይዘው ወደ ክፍለ ከተማው ጽሕፈት ቤት በመሄድ እንዲያሰተካክሉ በገዢው መንግስት ካድሬዎች ሲዋከቡ ነበር።

በግንቦት ሃያ እና በሌሎች ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ባለ ይዞታዎች ከዓመታት በፊት በከተማዋ መሃል ነዋሪዎች የነበሩ ሲሆን፣ በቤት ክራይ በመማረር እና ተከራይተው ሲኖሩበት የነበረው የቀበሌ ቤት ለባለሃብቶች በመሸጡ ምክንያት ከከተማው ዳርቻ ወጣ በማለት መሬት ከገበሬዎች እየገዙ ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ አዳዲስ ቤቶችን ገንብተው ይኖራሉ።

የገዢው መንግስት ካድሬዎች በየክፍለ ከተማው የሚያደርጉትን የምረጡኝ ቅስቀሳ ሙሉ በሙሉ ባሸናፊነት ለመወጣት በሚል ነዋሪውን ለማታለል የፈጠሩት ዘዴ መሆኑን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፤ ካድሬዎች በግንቦት ሃያ ክፍለ ከተማ የጀመሩትን የይዞታ ቦታ ሰነድ ንጥቂያ በመቀጠል በበላይ ዘለቀ፣በህዳር 11 እና በሽምብጥ ክፍለ ከተማዎች በቀጣዩ ሳምንታት በማስፋፋት ለምርጫ መቀስቀሻ የሰጡትን የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በተከታታይ እንደሚነጥቁ ምንጮች ገልጸዋል።

ከምርጫ በፊት ባደረጉት ቅስቀሳና በየመንደሩ በተደረጉ ልዩ ልዩ የማግባቢያ የቡና ጠጡ ዝግጅቶች የህብረተሰቡን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እናገኛለን ብለው የገመቱት ካድሬዎች፣ ህብረተሰቡ ያልተጠበቀ ምላሽ ማሳየቱ ሳያበሳጫቸው አልቀረም ስትል አስተያየቱዋን አስፍራለች።


Wednesday, June 17, 2015

የሰማዕታት ደም ይጮሃል፤ ይጣራል!!! (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ)

አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡

ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።

ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም

በሶስት ሰዎች ታንቀው ተገደሉ።

ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።

ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።

የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።
ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።

ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።

ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።
በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም...!
መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ...!
ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO..!



Andy Tsege: Fears grow over state of mind of British activist who languishes in Ethiopian jail

Fears are growing for the state of mind of a British father of three who has languished in a secret jail in Ethiopia for almost a year.

Andargachew “Andy” Tsege, who has been sentenced to death, reportedly told the British ambassador during a rare visit: “Seriously, I am happy to go – it would be preferable and more humane.”

Next week marks the first anniversary of Mr Tsege, a leading opponent of the Ethiopian regime, being imprisoned during a trip to Africa.

Amid growing concerns for the 60-year-old Briton’s well-being, he was visited by ambassador Greg Dorey on in April.

A report of the ambassador’s visit was sent to Mr Tsege’s partner, Yemi Hailemariam, the mother of their three children.

The details it contains, combined with a lack of any progress since the visit was made, have left her at “breaking point” she told The Independent yesterday.

Ms Hailemariam was warned by Sarah Winter, head of country casework at the Foreign Office: “Some bits of this report will be distressing. Please make sure you read it when you’ve got good support around you.”

The visit was not held in the jail where Mr Tsege is being kept in solitary confinement, and took place in front of security officials. “Andargachew looks physically in reasonable shape but has health concerns. And he appears in a bad place psychologically. No evidence of mistreatment, other than the solitary nature of his confinement,” states the report.

Mr Dorey recalls Mr Tsege commenting: “Seriously, I am happy to go – it would be preferable and more humane. I said I doubted the government would wish to execute him and that in any event we would lobby strongly against this as a matter of principle.”

Mr Tsege saw no reason to stay alive, according to the report. “He was aware of the wider debate on euthanasia and could ask for this: it would relieve the pain,” it adds.

Mr Tsege, who is in solitary confinement, also told the ambassador that prison guards feared he might harm himself but he had not attempted this.

Mr Tsege’s partner Yemi, who lives in north London, described her shock at seeing the report: “The FCO had told me the content of the readout, I was sad but it does not compare to how I felt when I saw it in black and white. I was very devastated.”

Foreign Secretary Phillip Hammond has written to his Ethiopian counterpart to warn that relations between Britain and Ethiopia would be jeopardised if anything happened to Mr Tsege. He is understood to have called for the Briton to be transferred to a normal prison, be allowed regular visits and be treated by a doctor.

But Ms Hailemariam said: “Now we are two months later and nothing has changed. I am at a breaking point… What is it about this case that does not make the ambassador be absolutely outraged that he is being treated the way he is by the Ethiopian government? What is it about us as a family that makes it so not worth it for the Foreign Secretary to change tack and just ‘keep raising it’ without any substantive result?”

Pressure is building on the Government to demand the release of Mr Tsege. The case is being looked at by Juan Mendez, the UN special rapporteur on torture. And Reprieve is calling for the Briton to be freed and returned to the UK.


አንድ የፌደራል ፖሊስ 3 ባልደረቦቹንና አንድ ቻይናዊ ገደለ

ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል::
የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት እየገቡ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው።
ፖሊሶቹ ለሰበተ-ሚኤሶ ባቡር ስራ ቻይናዎችን እንዲጠብቁ የተመደቡ ናቸው። ቻይናዊው ሰራተኛና ሶስቱ ፖሊሶች ህዝቡን በተለይም የቀን ሰራተኞችን ያለ ክፍያ የሚያሰሩ እንዲሁም ለባቡሩ ካሳ ያልተከፈለበት እርሻን አስገድደዉ መንገድ እንዲሰራ እንደሚያደርጉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ገዳዩ ፖሊስ ድርጊቱን ሲቃወም በመቆየቱ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ መሆኑንና ያለመያዙም ሚስጢር ከህዝብ መጠለያ በማግኘቱ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ድርጊቱ ከተፈጸመ በሁዋላ የባቡር ስራው መቆሙን ምንጮች ገልጸዋል። ኢሳት ቻይናውያን ሰራተኞች ስለሚፈጽሙት በደል ተደጋጋሚ አቤቱታዎች ሲደርሱት ቆይቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። የቻይናዊውን ግድያ በተመለከተም መንግስት እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።


ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ

ሰኔ 8 ቀን 2007 ምሸት ሳውዲ አረቢያ የገቡት የኢትዮጵያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ጉብኘት ያለተጠበቀና እንግዳ መሆኑን የሚናገሩ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ምንጮች በዲፕሎማቱ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፤ ሚንስትሩ ከሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ቢሄዱም የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ጉብኝት ኦፊሴላዊ ይሁን በድብቅ እስካሁን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ጅዳና ሪያድ ያሉት የመንግስት ዲፕሎማቶች ምንም አይነት ነገር እንደማያውቁ ከቆንስላው ጽ/ቤትና ከሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የሚንስትሩን ድንገተኛ ጉብኝት ተከትሎ ማምሻውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ የነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች ፡ የልማት ማህበራት ተወካዮች ለደጋፊዎቻቸው በሚስጠር ጥሪ ማስተላለፋቸውን የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኑ በዚህ መልክ ወደ ጃዳ መግባታቸው ዲፕሎማት ብለው ለሾሞቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ ላይ እምነት እንደሌላቸው አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቀርብ ግዜ ወዲህ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ለስራ ጉብኘትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳወዲ አረቢያ ሲገቡ የኤንባሲው ዲፕሎማቶች መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከአንድ አመት በፊት አቶ በረከት ስመኦን በሚስጠር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው ያስታውሳሉ ፡፤
በሳውዲያዊው ቱጃር ሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው እኩለ ለሊት ሳውዲ የገቡት አቶ በረከት ስመኦን ጅዳ ከተማ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ያወቁት ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ መሆኑን የሚገልጹ እነዚህ ወገኖች በዲፕሎማቱና በመንግስት መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን በማውሳት የመረጃ ክፍተቱን ለማሞላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው ይነገራል። ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ሚንስቲር ገብረክርስቶስ በሙስና ስለ ሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል ። አንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ሰራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስቲር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ጉብኘት በሳውዲም ይሁን በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም የተባለ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሎሏ፡፤ዘግይቶ የድረሰን ዜና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣኑ ወደ ሪያድ ከተማ እንደሚያቀኑ የቆንስላው መረጃዎች ገልጸዋል


Tuesday, June 16, 2015

ሳሙኤል አወቀ ተገደለ



የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡

Monday, June 15, 2015

ፍርድ ቤቱ በዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ ለብይን ቀጠሮ ሰጠ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ
13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ
ሲ.ዲው በችሎት መታየቱን ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው ለዳኞች ብቻ ተመልከተውት በማስረጃነት እንዲያዝ እንዲደረግ ወስኗል። ይህን ተከትሎ ተከሳሾች በብይኑ ላይ አለን ያሉትን አቤቱታ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያሰሙ ሲሆን ፣ ፍርድ ቤቱ
ግን ብይን ባገኘ ጉዳይ ላይ አቤታቱውን ከመመዝገብ ውጭ ለውጥ እንደማይኖረው ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ተከሳሾች ለቀረበባቸው ክስ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጋዜጣው ዘግቧል።


በጭልጋ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ5 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች በወዱት እርምጃ ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ ወጣቶች መገደላቸውን፣ ከ10 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ መቁሳላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

   የቅማንት ተወላጆች የራስ አስተዳደር መብት ይሰጠን በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት “ጥያቄያቸው በክልሉ ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ሊታይላቸው” ይገባል የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ጥያቄ አቅራቢዎቹ የራስ አስተዳደሩ በ120 ቀበሌዎች ተግባራዊ እንዲሆን ሲጠይቁ፣ የክልሉ መስተዳደር በበኩሉ ውሳኔውን የሰጠሁት ለ42 ቀበሌዎች ብቻ ነው ብሎአል። የመስተዳደሩን ውሳኔ በመቃወም ፣ ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴው ሰኔ 7 ጭልጋ ላይ፣ ሰኔ 14 ደግሞ ጎንደር ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ቢጠራም፣ የሰሜን ጎንደር ዞን መስተዳደር ከአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረበለትን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ኮሚቴው መፍረሱን በመግለጽ ምላሽ ደብዳቤ ልኳል።
የኮሚቴው አባላትና ደጋፊዎች የመስተዳደሩን ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው ባለፈው ቅዳሜ ቅስቀሳ ለማድረግ በጭልጋ ከተማ ተንቀሳቅሰዋል። ከአርማጭሆ ወረዳ የመጡ የብሄረሰቡን የባህል ልብስ የለበሱ 7 ወጣቶችን ፖሊስ በመኪና ጭኖ በመውሰዱ ግጭት መጀመሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።በአካባቢው በሚታየው ውጥረት የተነሳ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡንም ነዋሪዎች ይናገራሉ።


በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ
እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ዱላ የቀን ተቀን ህይወት ነው፣ ኢትዮጵያውያኑ በዱላ ብዛት
አካላቸው እየጎደለ ነው ብሎአል። አንድ እርጉዝ ሴት በበኩሏ ተይዛ ገንዘብ ከፍላ መለቀቋን ገልጻለች።
መንግስት ሊቢያ የሚገኙ ዜጎችን ወደ አገር እየመለስኩ ነው ቢልም፣ ኢትዮጵያውያኑ ግን “ግብጽ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስንደውል አግኙት ተብሎ የሚሰጠን ሰው ስልክ ፣ ‘ፓስፖርት ይዛችሁዋል?’ እያለ ይቀልድብናል፣ ገንዘብም
ይጠይቀናል” በማለት እየረዳቸው እንዳልሆነ ገልጸዋል።


Saturday, June 13, 2015

60 የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ለ3 ቀናት ግምገማ አካሄዱ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም
ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን አግኝተዋል።
በህወሃት አባላት የሚመሩ ተቋማት ውጤታማ ሲባሉ ፣ ሌሎቹ ደካሞች ተብለዋል። በአመራር የማይቀጥሉ፣ ከሃላፊነት ዝቅ የሚሉና ለከፍተኛ ስልጣን የሚበቁ አመራሮች ተለይተው ታውቀዋል።
ከግምገማ በኋላ ብዙዎቹ አመራሮች የተስፋ መቁረጥ ስሜት ፊታቸው ላይ በግልጽ ሲነበብ፣ የተሻለ ውጤት የተሰጣቸው ጥቂት አመራሮች ደግሞ ከወዲሁ ደስታቸው የተለየ እንደነበር እየገለጹ ነው፡፡
በግምገማም ወቅት አመራሮች እርስ በርስ ይመወነጃጀሉ ከባድ ቃላትንም የውራወሩ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡። ግምገማው በለያየ ቅርጽና ይዘት በሌሎች አካላት ላይ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት በሃዋሳ እንዲቀጥል እቅድ
ተይዟል።


አልሸባብ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በማእከላዊ ሶማሊያ በተደረገው ጦርነት ታጣቂ ሃይሉ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል።ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል።አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ ወታደሮችን አድፍጠው በመጠበቅ ጥቃት ፈጽመዋል።ለ12 ሰአታት ያክል የቆየ በከባድ መሳሪያዎች የታጀበ ጦርነት መካሄዱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አልሸባብ በጥቃቱ 30 ወታደሮችን መግደሉንና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደሙን ገልጿል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ባለስልጣን የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጨማሪ ሃይል እንደሚጣላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።

ሞቃዲሾን ከደቡቡ ክፍል ጋር በሚያገናኘው መንገድ ላይ ተደጋጋሚ የደፈጣ ጥቃት ይፈጸማል። ሚያዚያ ላይ 6 የአፍሪካ ህብረት ተዋጊዎች በተመሳሳይ መንገድ ተገድለዋል። የኢትዮጵያ ጦር ወታ ገባ በማለት በሶማሊያ ከ7 አመታት በላይ አስቆጥሯል። ካለፈው አመት ጀምሮ በአፍሪካ ህብረት ስር ሆኖ በባይዶዋ አካባቢ ጥበቃ እያደረገ ነው።



በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከምርጫ ጋር በተየያዘ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከምርጫ ጋር በተየያዘ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ ንደሚገኙ ከከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 11 ለም ተብሎ በሚጠራው ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በሃሰት እየተውነጀሉ በስርዓቱ ታጣቂዎች እየታሰሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከትምህርት ቤቱ ከታሰሩት ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ ሲራክ ለማ የተባለ የ9ኛ ክፍል ተማሪ፤ ያሬድ ፋሲል እና አላምረው ይደግ የተባሉት ደግሞ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችና ሌሎችም አምስት ተማሪዎች የሚገኙባቸው እንደሆኑ ሊታወቅ ተችሏል።

እነዚህ ተማሪዎች እናንተ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ስለሆናችሁ ለሌሎች ተማሪዎች ዓመፅ እንዲያስነሱና የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና አንፈተንም በሉ እያላችሁ ታነሳሳላችሁ ተብለው ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ከለም ትምህርት ቤት በፖሊሶች ተይዘው እንደተወሰዱ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገልፀዋል።

እንደዚህ አይነት ህጋዊ ያልሆነ ተግባር በለም ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን እየታየ ያለው በሁሉም የሃገራችን ሃይስኩል ትምህርት ቤቶች እየተፈፀመ ያለ እኩይ የስርዓቱ መገለጫ ባህሪው እንደሆነ ምንጮቻችን ያደረሱን መረጃ አክሎ አስረድቷል።


የፌደራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን ሃብት ይፋ ለማድረግ ወኔው አንሶታል ተባለ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት የመመዝገብ ሥራዎችን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ቢሆንም ባሉበት
ጫናዎች ምክንያት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡
ኮምሽኑ የባለስልጣናትን ሀብት እንዲመዘግብ ስልጣን ሲሰጠው በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመን ይፈጥራል ተብሎ ነው፣ ይሁን እንጅ ኮምሽኑ የባለስልጣናቱን ሃብት ምዝገባ ከማካሄድ በስተቀር ለመገናኛ ብዙሃንና ለሕዝብ ይፋ
ለማድረግ ድፍረቱን አላገኘም፡፡
የሐብት ማሳወቅና ምዝገባ መረጃዎች በቀላሉ ለተጠቂዎች ተደራሽ ለማድረግ የሐብት አስመዝጋቢዎችን የምዝገባ መረጃ በአግባቡ ለይቶና የሰነድ መለያ ኮድ ተሰጥቶት ተደራሽ በሚሆንበት አግባብ መደራጀቱን ኮምሽኑ ለሕዝብ ይፋ ካደረገ ከአንድ ዓመት በላይ የሆነው ቢሆንም፣ አሁንም ይህንን የምዝገባ መረጃ ይፋ ለማድረግ ባለበት ጫና ምክንያት ማድረግ ሳይችል ቀርቷል።

Friday, June 12, 2015

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያ ድንበር በመጣስ ጥቃት ፈጸመ!፡፡ 

ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007)

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያ ድንበር በመጣስ በጎንደር አብደራፊ አካባቢ በባለሃብቶች ይዞታ ላይ ጥቃት መፈጸሙን እማኞች ለኢሳት ገልጹ። ከቀናት በፊት ወታደሮች በባለሃብቶች የእርሻ ተቋማት ላይ በፈጸሙት ጥቃት ተሽከርካሪዎችና ግምቱ ከፍተኛ የሆነ ንብረት በእሳት ቃጠሎ ውድመት እንደደረሰበት ታውቋል።

ከ 20 እስከ 30 ኪሎሜትር የሚሆን የኢትዮጵያ ድንበር ጥሰው የገቡ የሱዳን ወታደሮች የፈጸሙት ድርጊት ምክንያት እንዳልታወቀና እርምጃው በአካባቢው ነዋሪ ዘንድ ስጋት ፈጥሮ መገኘቱን እማኞች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። ለጊዜው በሰዎች ላይ ስለደረስ ጉዳት የታወቀ ነገር አለመኖሩን የገለጹት ነዋሪዎች፥ ለወታደሮች ጥቃት ከኢትዮጵያ ወገን የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን አስታውቀዋል።

የሱዳን ወታደሮች እና ታጣቂዎች ተመሳሳይ ድርጊትን ከዚህ በፊት ሲፈጽሙ እንደቆዩ የገለጹት እማኞች፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ቢገኝም ምንም አይነት አጸፋ አለመውሰዱ በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ማሳደሩም ታውቋል። በሁለቱ ሃገራት መካከል ተፈጽሟል የተባለውን ድንበር የማካለል ስምምነት ተከትሎ የሱዳን የጸጥታ ሀይሎች በአካባቢው ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጽሙ መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ከዚህ በፊት አብደራፊ በተፈጸመ ተመሳሳይ ድርጊት በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የመንግስት የፀጥታ ሃይል የአካባቢው ነዋሪ ምንም አይነት እርምጃ እንዳይወስድ ሲያሳስቡ መቆየታቸውን ከእማኞች ለመረዳት ተችሏል። በሰሞን (ቅዳሜ) ድንበር በመጣስ በሱዳን ወታደሮች ተወስዷል ስለተባለው ወታደራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያ ወገን የተሰጠ ምላሽ የለም።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሁለቱ ሀገራት ተፈጽሟል የተባለውን የድንበር ስምምነት ተከትሎ ምንም አይነት መሬት ለሱዳን እንዳልተሰጠ ሲያስተባብሉ መቆየታቸው ይታወቃል። የተፈጸመውም ስምምነት ከዚህ በፊት የነበሩ መንግስታት የፈጸሙት ውል ነው ሲሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ሁለቱ ሃገሮች የፈጸሙት የድንበር ስምምነት በርካታ ለም መሬትን ለሱዳን የሚሰጥ ነው በማለት የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴን ጨምሮ የተለያዩ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን ሲቃወሙ መቆየታቸውም የሚታወስ ነው።

በአብደራፊ ተፈጽሟል የተባለውን ጥቃት አስመልክቶም የሱዳን መንግስት የሰጠው ምላሽ የለም።

ምንጭ፤-ኢሳት
ኢሳት የኢትዮጵያውያን አይና ጆሮ ነው
ኢሳትን ይርዱ


Thursday, June 11, 2015

አቶ ዳዊት አስራዳ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ ከፍሎ ታሰረ

• እስካሁን 36 ሺህ ብር ከፍሏል

የቀድመው አንድነት አመራር አቶ ዳዊት አስራደ ትናንት ግንቦት 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5000 ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ በትናንትናው ችሎት ፖሊስ ተከሳሾቹ ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ምስክሮችና መረጃዎችን አሰባስቦ እስኪያቀርብ ጊዜ ድረስ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ የነበር ቢሆንም አቶ ዳዊት አስራደ፣ አቶ አለነ ማህፀንቱና ወይዘሪት ሜሮን አለማየሁ የ5000 ብር ደሞዝ ያለው የሰው ዋስ ወይንም ገንዘብ አስይዘው ከእስር እንዲወጡ ፈቅዶ ነበር፡፡

ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው ቁም ነገሮች

በደቡብ  ኢትዮጵያ ሸካ ዞን የሚገኙ የቴፒ ወጣቶች በህወሓት አገዛዝ የሚደርስባቸው በደል አንገሽግሿቸው ራሳቸውን አደራጅተው በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰድ ከጀመሩ በርካታ ወራት ተቆጥረዋል። እነዚህ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአካባቢያቸው የሚገኝን አንድ የፓሊስ ጣቢያ ወረው እስረኞችን ማስፈታታቸው በመላው ኢትዮጵያ እንዲታወቁ ምክንያት ሆኗል፤ የአገዛዙ ሚዲያም ድርጊቱ መፈፀሙ በተዘዋዋሪም ቢሆን አምኗል።

ለፍትህ፣ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት እና ለአገር አንድነት ግድ ያለን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከቴፒ ወጣቶች የምንማራቸው በርካታ ቁም ነገሮች ያሉ ቢሆንም የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለን እናምናለን።

1. “ጥቂቶች ነን፤ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለው ተስፋ ቆርጠው በደልን ለመቀበል አልመረጡም፤
2. ዓላማቸው ትልቅና ሀገራዊ ቢሆንም እርጃዎቻቸው አካባቢ ተኮር አድርገዋል፤
3. የሚወስዷቸው እርምጃዎች በአቅማቸው መጠን እንዲሆኑ በማድረግ በራሳቸው ላይ ያለው መተማመን እንዲጎለብት ማድረግ ችለዋል፤
4. እንደሁኔታው በፍጥነት መሰባሰብና መበታተን የሚችል ቀልጣፋስብስብ ማደራደት ችለዋል፤ እና
5. በከፍተኛ ሥነሥርዓት በመታነጽ ከቴፒ ሕዝብ ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ እያተደረጉ ነው

የ2007 ምርጫን የወያኔ መንግስት በሁሉም ክልሎች በከፍተኛ ድምጽ ምርጫውን እነዳሸነፈ ማወጁ ይታወሳል  ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ውጥረት የነገሰ  ሲሆን  የምርጫውን የውጤት ማጭበርበር በመቃወም  ከሌላው ክልል በበለጠ በኦሮሚያና፣ በአማራ ክልሎች የህዝቡ ቋጣ በከፍተኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን፣በዚህም የተነሳ  በአማራ  ክልል የብአዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ያላቸው እምነት እያሽቆለቆለ በመመጣቱ በክልሉ ላይ የሚገኙት የመንግስት ድርጅቶች በልዩ ሃይል እንዲጠበቁ ማድረጋቸውን ተገለፀ::

የደህንነት ተቋማት ከፍተኛ በጀት ተመደበላቸው

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ2008 ዓም ከመደበው በጀት ውስጥ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ፍትህና ደህንነት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል።
የፌዴራል መንግሥት የመደበኛ ወጪ ዝርዝር እንደሚሳየው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 9. 5 ቢሊየን ብር፣ የፌዴራል ፖሊስ 1. 6 ቢሊየን ብር፣ ፍትሕና ደህንነት 3. 5 ቢሊየን ብር ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡
መከላከያ በ2007 ዓም ከተያዘለት በጀት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው በጀቱ በ 1 ቢሊየን 600 ሚሊዮን ብር ከፍ ብሎአል። ጦርነት የለም በሚባልበት ሁኔታ የመከላከያ በጀት ከአመት አመት መጨመሩ ሪፖርቱን አነጋገሪ ማድረጉን ዘጋቢያችን
ገልጿል። የ2008 በጀት ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጉድለት አሳይቷል። ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የ2007 ምርጫ መቶ በመቶ በሕዝብ ተመርጦ ማሸነፉን በምርጫ ቦርድ በኩል ከታወጀ በሁዋላም
ሁከት ሊቀሰቅሱብኝ የችላሉ ያላቸውን የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ፣ የመኢአድና የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችን እያሳደደ ማሰሩን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ለደህንነት ተቋማት የሚመደበው በጀት መጨመር ከዚሁ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል
ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል።


ኢህአዴግ በምርጫው አገኘሁት ያለውን ውጤት ለማብሰር የያዘውን የድጋፍ ሰልፍ እቅድ በፍርሃት ሰረዘ

ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ለመላ አገሪቱ በወረደ ጊዚያዊ አደረጃጃት፣ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንዲሁም በተለያዩ የግንባሩ ጽ/ቤቶች በተሰጠ መመሪያ መሰረት የተዋቀረው የድጋፍ ሰላማዊ
ሰልፍ ኮሚቴ የድጋፍ ሰልፍ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል። ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ህዝቡ በድጋፍ እንዲመሰክር እና ሚዲያዎቹ በቀጥታ እንዲዘግቡት መመሪያ ከወረዳ በሁዋላ፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ተሰብስቦ ሰላማዊ
ሰልፉ እንዲደረግ አይመከርም ሲል በሙሉ ድምጽ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ለእቅዱ መሰረዝ በምክንያትነት ያቀረበው በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች ኢህአዴግ የህዝቡን ድምጽ አላገኘም የሚል ነው። የድጋፍ ሰልፍ መጥራት በራሳችን ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ እንደመጥራት ይቆጠራል ያለው ምክር

Tuesday, June 9, 2015

ምርጫ ሲባል፣ መሳይና አስመሳይ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም )

June 9, 2015

ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ።Prof. Mesfin Woldemariam

ከአገር የተሰደዱት ጋዜጠኞች ሳይሆኑ አሸባሪዎች ናቸዉ ተባሉ።

ኢሳት ዜና (ግንቦት 27 2007)

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት የፈጸመባቸዉን ወከባ በመሸሽ ከሃገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን እዉነተኛ ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ የተሾሙት ልዑክ ገለጡ።

በወቅታዊ የኬንያና የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ዘ ስታንዳርድ (The Standard) ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ በኬንያ በስደት ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች የእዉነት ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

የፍትህ ሚኒስትር አምስት መጽሄቶችንና ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ በማድረግ ጋዜጠኞቹ ህዝብን ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አሰራጭተዋል ሲል በሌሉበት ክስ መስርቶ ይገኛል።

CPJን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደዉን እርምጃ በማዉገዝ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።

የሽብርተኛ ወንጀል ህጉ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ከአራት አመት ወዲህ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ለእስር መዳረጋቸዉን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ።

ከአገር የተሰደዱት ጋዜጠኞች ሳይሆኑ አሸባሪዎች ናቸዉ ተባሉ።

ኢሳት ዜና (ግንቦት 27 2007)

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት የፈጸመባቸዉን ወከባ በመሸሽ ከሃገር የተሰደዱ ጋዜጠኞችን እዉነተኛ ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ የተሾሙት ልዑክ ገለጡ።

በወቅታዊ የኬንያና የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ ዘ ስታንዳርድ (The Standard) ከተሰኘ ጋዜጣ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ በኬንያ በስደት ላይ የሚገኙትን ጋዜጠኞች የእዉነት ጋዜጠኞች አይደሉም ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

የፍትህ ሚኒስትር አምስት መጽሄቶችንና ጋዜጦችን ከህትመት ውጭ በማድረግ ጋዜጠኞቹ ህዝብን ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አሰራጭተዋል ሲል በሌሉበት ክስ መስርቶ ይገኛል።

CPJን ጨምሮ የተለያዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች በጋዜጠኞች ላይ የተወሰደዉን እርምጃ በማዉገዝ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።

የሽብርተኛ ወንጀል ህጉ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ከአራት አመት ወዲህ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ለእስር መዳረጋቸዉን የተለያዩ አካላት ይገልጻሉ።


Monday, June 8, 2015

አቃቢ ህግ በእስር ላይ በሚገኙ ታዋቂ ፖለቲከኞች ላይ ምስክሮችን ማሰማት ጀመረ

ሰኔ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በተከሰሱት በአብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሽና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አቅርቦ ማሰማት ጀምሯል።


አቃቢ ህግ “ምስክሮቼ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል” በሚል ችሎቱ ምስክሮችን በዝግ እንዲያሰማ እንዲፈቅድለት ጠይቋል። ተከሳሾች በበኩላቸው የአቃቢ ህጉን መከራከሪያ አጥብቀው መቃወማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና ደቡብ ክልል ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ ‹‹አቃቤ ህግ እስከ ሞት በሚያደርስ ወንጀል ከሶናል፤ ይህን ጉዳይ በግልጽ መከታተል አለብን፡፡ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብም መፍረድ አለበት›› በማለት ችሎቱ ምስክሮችን በግልጽ እንዲሰማ ጠይቋል። ሌላው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩሉ ‹‹እኛ ዋስትና ተከልክለን በእስር ቤት ነን፤ የምስክሮች ስም ዝርዝር እንኳ አልተገለጸልንም፡፡ ታዲያ ማን ነው ምስክሮች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ የሚያደርስባቸው?›› ሲል አቃቤ ህግ ያቀረበው ምክንያት ተቀባይነት እንደሌለው አስረድቷል።

Sunday, June 7, 2015

የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው

ከደቡብ ምስራቅ እዝ የከዱ ዘጠኝ የባሌ ክፍለሃገር ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ መኮንኖችን ለመያዝ ማደኑን አንደቀጠለ አና አስካሁን ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተቀላቅለዋል ከሚባል ውጪ ያሉበት ቦታ ምንም ፍንጭ እንደሌለ ለጦር ሃይሎች መምሪያ የደህንነት ክፍል የመጣ መረጃ መጠቆሙን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::

በተለያዩ ጊዜያት ከባለፉት ሳምንት ጀምሮ ድንበር ዘለል ወረራ በኬንያ ላይ ያደረገው የወያኔ ሰራዊት ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ጦርነት ገጥሞ አንደነበር ሲታወስ የከዱ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተደባልቀው የወያኔን ሰራዊት አንደወጉ ቢገለጽም አስካሁን ድረስ የኦነግ ታጣቂ ሃይሎችን ያሉበትን ኣከባቢ ለማግኘት ኣለመቻሉን መረጃዎቹ ሲጠቁሙ ኣሉበት የተባሉ ኣከባቢዎችን በሃገር ውስጥ ደኖች ላይ ኣንደተለመደው አሳት በመልቀቅ አና ጎረቤት ሃገሮችን በመውረር በሃይል ለማዳከም ስራዎች አየተሰሩ አንደሆን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

ወያኔ የጋረደብንን የመበታተን አደጋ ለማክሸፍ ትግላችንን ማቀናጀትና በአንድ የአመራር ጥላ ሥር ማሰባሰብ ወቅቱ የሚጠይቀን እርምጃ ነው

ትግራይን ከተቀረው የአገራችን ክፍል ለመገንጠልና የትግራይን ሪፑፕልክ ለማቋቋም ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ የዛሬ 40 አመት ደደቢት በረሃ ውስጥ የተፈጠረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ፡ በለስ ቀንቶት የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ ወዲህ፡ በስሙ የሚነግድበትን የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በአገራችንና በመላው ህዝባችን ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎችና ያደረሳቸው ሰቆቃዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::

ከነዚህ ወንጀሎች ሁሉ የከፋውና ምናልባትም የሚቀጥለውን ትውልድ ጭምር ዋጋ ያስከፍላል ተብሎ የሚፈራው ምዕራባዊያን ቅኝ ገዥዎች አህጉራችን አፍሪካን በተቀራመቱበት ወቅት የአገዛዝ ዘመናቸውን ለማራዘምና ቅኝ የገዙዋቸውን ህዝቦች ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ እንዲመቻቸው የተጠቀሙበትን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊስ በምድራችን ተግባራዊ በማድረግ ለዘመናት የተገነባውን የህዝብ አንድነትና የአገር ሉአላዊነት ሊያናጋ በሚችል መልኩ በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍለን የጎሪጥ እንድንተያይ የተፈጸመብን ደባ ነው::

Saturday, June 6, 2015

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 16 ሰዎች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው

‹‹አማራ በመሆኔ ዘሬን እንዳልተካ ተደርጌያለሁ›› 1ኛ ተከሳሽ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ከወራት በፊት በሽብር ተጠርጥረው ከአማራ ክልል ተይዘው በእስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ የዞን አመራሮች የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ በ13/07/07 በተጻፈና ዛሬ ግንቦት 28/007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በንባብ በተሰማው የአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው በአንደኛ ተከሳሽ ጌታቸው መኮንን መዝገብ 16 ሰዎች የሽብር ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡
ከተከሳሾቹ መካከል የመኢአድ፣ የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት የተካተቱበት ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በ2001 ዓ.ም የወጣውን የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) በመተላለፍ ክስ እንደተመሰረተባቸው ተመልክቷል፡፡

Wednesday, June 3, 2015

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2006 በጀት ዓመት ያለምንም ማስረጃ ገንዘብ ከሚያወጡ መንግስታዊ ተቋማት መካከል የደህንነት ተቋም ዋንኛው መሆኑን አጋለጠ፡፡

ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር የ2006 ዓ.ም የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ ሪፖርት ትላንት ለፓርላማው ያቀረበ ሲሆን በዚህ ሪፖርቱ ያለምንም ማስረጃ ገንዘብ ያወጡ 19 መንግስታዊ ተቋማት የተገኙ ሲሆን እነዚህ ተቋማት በድምሩ ከ473 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አውጥተው ተገኝተዋል፡፡ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ላቅ ያለውን ድርሻ ማለትም 274 ሚሊየን ብር ያወጣው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ በቀጣይም በምክትል ጠ/ሚኒስትር ወ/ሮ አስቴር ማሞ የሚመራው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር 111 ሚሊየን ብር፣ መቱ ዩኒቨርሲቲ 16 ሚሊየን ብር፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ 12 ሚሊየን ብር፣ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 10 ሚሊየን ብር ወጪ አውጥተው ተገኝተዋል፡፡ዋና ኦዲተር በዚህ ወጪ ላይ በሰጠው አስተያየት ማስረጃ ያልቀረበለት ሂሳብ በቂ ማስረጃ እንዲቀርብበት ያሳሰበ ሲሆን አለበለዚያ ገንዘቡ ወደመንግስት ካዝና እንዲመለስ አዟል፡፡ዋና ኦዲተር አያይዞም ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ መወራረዱ ሲጣራ በ78 መ/ቤቶች ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ በደንቡ መሰረት ሳይወራረድ መገኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በወቅቱ ሂሳብ ከማያወራርዱት ተቋማት መካከል መከላከያ ሚኒስቴር 144. 2 ሚሊየን ብር፣ ፌዴራል ፖሊስ 64. 4 ሚሊየን ብር ድርሻ ወስደዋል፡፡


ተጨማሪ የኢትዮጵያ ጸጥታ ሃይል ወደ ሶማሌ ክልል መሰማራቱ ተገለጸ

ኢሳት ዜና (ግንቦት 25, 2007)

በኢትዮጵያና ጎረቤት ሶማሊያ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደራዊ ሃይል ወደስፍራው ማሰማራቷ ተገለፀ።

በእስካሁኑ የኢትዮጵያ ልዩ ሃይሎችና በሶማሊያ የጎሳ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደዉ ግጭት በትንሹ ከ50 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል ሲሉ ተቃዉሞ ማሰማታቸውን ሶማሊ ከረትን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል።

የጋልጋይዱድ ክልል ሃላፊ የሆኑት ሁሴን አርፎ የኢትዮጵያ ወታደሮች የፈፀሙትን ጥቃት ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቀያቸዉ መፈናቀላቸዉንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ መሆናቸዉን ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

ልዩ ሃይል እየተባሉ የሚጠሩት የፀጥታ ሃይል አባላት የወሰዱት እርምጃ የዘር ማጥፋት ድርጊት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል የክልሉ ሃላፊ አክልዉ ገልጸዋል።
በአካባቢዉ ዉጥረት አለመርገቡን የሚናገሩት ነዋሪዎች በበኩላቸዉ ተጨማሪ የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች በድንበሩ ዙሪያ መሰማራቱን ተናግረዋል።

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በመንግስት ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በምርጫ ማግስት ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ለእስር የተዳረገችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት፡፡
ዛሬ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 490/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት አሸባሪ፣ ታርዷል ወገኔ፣ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ፣ ወያኔ አሳረደን፣ ናና መንግስቱ ናና፣ ወያኔ አሸባሪ...በማለት እጅን አጣምሮ ወደላይ በማድረግ ታስረናል›› በማለት ሰላማዊ ሰልፉ እንዲታወክ አድርጋለች በሚል ተከሳለች፡፡ በተጨማሪም በሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም ቂርቆስ አካባቢ ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባኤን›› በማወክ እንደተከሰሰች የክስ ቻርጁ ያሳያል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ‹‹በምስክሮች ላይ ማስፈራራት እየተፈጸመ ስለሆነና ምርመራየንም ስለጨረስኩ›› በሚል ፖሊስ ዛሬ ቤተሰቦቿ እንኳ ሳይሰሙ ወ/ሮ ንግስትን ፍርድ ቤት አቅርቦ ክስ መስርቶባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው በቀጣይ አርብ ግንቦት 28/2007 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡



Monday, June 1, 2015

አገራችን ከህወሓት አፈና ነፃ ለማውጣት ያለን አማራጭ መንገድ ምንድነው?

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህወሓት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ የሚወርደው ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽን ባቀናጀ ሁሉገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ለሁለቱም የትግል ዘርፎች ተስማሚ የሆኑ አደረጃጀቶችን አዘጋጅቷል።

ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ታጋዩ ከመኖርያ ወይም ከሥራ ቦታው ሳይለቅ በህቡዕ የሚከናወን ትግል ነው። ሕዝባዊ አመጽ ደግሞ ከመኖሪያና ሥራ ቦታ ለቆ መንቀሳቀስን ይጠይቃል። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች የህወሓትን ህጎች በመቃወም የሚደረጉ ናቸው። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች ድርጅት፣ ዲሲሊንና ጽናትን ይጠይቃሉ። ለድላችን ሁለቱም የትግል ዘርፎች እኩል ዋጋ አላቸው። እናም ከዛሬ ጀምሮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባለውና አቅሙ በሚመቸው የትግል ዘርፍ ይሳተፍ። ሕዝባዊ ኃይልን መቀላቀል የቻለ ይቀላቀል፤ ያልቻለው በያለበት ተደራጅቶ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ይታገል።

የመንግስት ወታደሮች በሞያሌና በኦጋዴን ሃይላቸውን እያጠናከሩ ነው

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሁለት ሳምንታት የኢትዮጵያ እና የኬንያ ድንበር የተለያዩ ግጭቶችን አስተናግዷል እንደ አይን ምስክሮች ገለጻ። ዩኒፎርም የለበሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኬንያ በመግባት የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር አባላትን ለማደን ቢሞክሩም እስካሁን አልተሳካላቸውም። የመንግስት ወታደሮች ወደ ኬንያ ሞያሌ ከተማ በመግባት ቦሩ ሁካ የተባለ የ55 ዓመት የትምህርት ቤት ዘበኛ በጥይት በሳስተው ገድለውታል። ነዋሪዎች የኦነግ አባላት የሆኑ ታጣቂዎች የተደበቁበትን ቦታ እንዲያሳዩ ይገደዱ ነበር። ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ኦነግ ወታደሮች ወደ ሞያሌ ከተማ በተከታታይ በመግባት ጥቃ

ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር አብራችሁዋል በሚል የተያዙት ክስ ተመሰረተባቸው

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ነዋሪ መሆናቸው የተነገረው አቶ ዘመነ ምህረቱ እና ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሰረታባቸው ሪፖርተር ዘግቧል።አቶ ዘመነ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው በክሱ የተመለከተ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ መስከረም 18፣ 2007 ዓም በጎንደር በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ አባላትን በመሰብሰብ ” የወያኔ መንግስት መውደቂያው ደርሷል።አንድ የቶር አውሮፕላን፣ 12 የጦር ጄኔራሎች ከድተው ወደ ኤርትራ ገብተዋል። ኢህአዴግ በጦር ካልሆነ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን አይለቅም። የህዝብ እምቢተኝነት በመፍጠር የወያኔን መንግስት መጣል አለብን፣ በ2007 ዓ.ም. የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ አይካሄድም፡፡ ወደ ምርጫው አንገባም፡፡ ሌላ አማራጭ መጠቀም አለብን…›› ” የሚል ክስ እንደተሰመረተባቸው ጋዜጣው ዘግቧል።በዚሁ መዝገብ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌትነት ደርሶ ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ከግንቦት7 ከፍተኛ አመራር ከሆኑት ዶ/ር ክፈተው አሰፋ ጋር በመገናኘት ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል ተብሎአል።በዚሁ መዝገብ ተከሰው የቀረቡት ሌላው የአዲስ አበባ ነዋሪ አቶ መለሰ መንገሻ ሲሆኑ ፣ እርሳቸውም የአርበኞች ግንባር አባል ነበሩ ተብሎአል። ተከሳሹ ሰው በመመልመል ስራ ላይ መሳተፉንና በመንግስት ባለስልጣናትላይ ጠቃት ለመፈጸም ሲያጠና ነበር የሚል ክስ እንደተመሰረተበት ጋዜጣው ዘግቧል።


“ባለፈው ሰረቁ ነው ሚባለው ያሁኑ ግን ዘረፋ ነው” ዶ/ር መረራ

* “በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል”

* “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም”

* ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ

* ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል

ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ጠቅሰው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ442 የምርጫ ክልሎች ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ መግለጹን ተክትሎ  መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና መኢአድ የምርጫውን ውጤት አንቀበለውም ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለመያዝ በኢህአዴግ ውስጥ ሀይለኛ የሆነ የስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት መፈጠሩ ታወቀ

የወያኔ ባለስልጣኖች ብዙ ሰዓት የፈጀ የውስጥ ስብሰባ ማድረጋቸው እና በስብሰባው ሀይለኛ የሆነ የእርስ በእርስ የቃላት ሽኩቻ ማድረጋቸውንና የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታውን ማን ይያዘው በሚለው ጉዳይ በመካከላቸው አለመግባባት መፈጠሩ የደረሰን ዜና ያስረዳል:: በደረሰን ዜና መሰረት በስብሰባው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ላይ ከባለስልጣናቱ ከኢህአዲግ የተለያዩ ወቀሳ እና ትችት የደረሰባቸው ሲሆን በደረሰን ዜና መሰረት ጠቅላይ ሚኒስር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታቸውን ሳይለቁ እንደማይቀርና በአቶ ደሳለኝ ቦታ የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን ህህዋቶች በከፍተኛ ሮጫ ላይ እንደሚገኙ እና ዶክተር ቴድሮስ አዳኖምንና፣ አቶ አርከበ እቁባይን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ሰዎች ታላቅ የስልጣን ሹካቻ ላይ እንደሚጋኙ እና የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ ሳይቆጣጠሩት እንደማይቀር ለማወቅ ተችሏል::