Wednesday, March 18, 2015

በሚስጢር የተያዘው የአባይ ግድብ ስምምነት ሊፈረም ነው

መጋቢት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚስጢር ሲያደርጉት የቆዩት ድርድር ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የሶስቱ አገር መሪዎች በተገኙበት በካርቱም እንደሚፈረም መረጃዎች አመልክተዋል።
የፊርማ ስነስርአቱ የፊታችን ሰኞ በካርቱም የሚካሄድ ሲሆን፣ ዝርዝር ይዘቱ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተደርጓል። የአባይ ግድብ ከህዝብ በውዴታና በግዴታ በሚዋጣ ገንዘብ እየተገነባ መሆኑ እየታወቀ፣ ስምምነቱን ገንዘቡን ለሚያዋጣው ህዝብ ይፋ ለማድረግ ለምን እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም።
ሱዳንና ግብጽ ስምምነቱ የግብጽን ፍላጎት ያረካ ነው በማለት አስተያየት በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ግን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ” አዲስ ምእራፍ” የከፈተ ከማለት ውጭ ለኢትዮጵያ ስለሚያስገኘው ጥቅም ምንም ያለው ነገር የለም።


No comments:

Post a Comment