መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና
የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው።
እስካሁን በተደረገው አፈሳ የወረዳው ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ ተቃዋሚዎችን ይረዳል በሚል ሲያዝ፣ ከ20 ያላነሱ የመንግስት ሰራተኞችና መምህራንም ተይዘዋል። ሁለት ፖሊሶች ደግሞ አምልጠው ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለዋል።
በአካባቢው ያለው አለመረጋጋት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ፌደራል ፖሊሶችና መከላከያ በህዝቡ ላይ ሽብር እየፈጠሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመናገር ላይ ናቸው። በአብርሃጅራ የፋርማሲስት ባለቤት የሆኑትና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው አቶ አበራ
ጀግኔ ድንበር አቋርጠው አርበኞች ግንቦት7ትን ተቀላቅለዋል ተብሎ መወራቱ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አፈሳውንና ጥቃቱን እንዲያባብሱ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
No comments:
Post a Comment