ከዚህ ቀደም በሲቭል ደህንነት ሲያገለግሉ የነበሩ እና ካለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ ወታደራዊ ካኪ በመልበስ ከወታደሩ ጋር ተመሳስለው በየሰራዊት እዝ ውስጥ የተሰገሰጉ ሰላዮች/ወታደራዊ ደህንነቶች ለስብሰባ አዲስ አበባ መክተማቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::
የሰራዊቱን አባላት እንዲሰልሉ እና በአባላቱ መካከል የጋራ አንድነት እንዳይፈጠር የመከፋፈል መርዝ እንዲረጩ በወታደራዊ ደህንነት ትጥቅ የተሰገሰጉ ሰላዮች የተመደቡበት ስራ አለመሳካቱ እንዲሁም ይሰራዊቱ አባላት በቡድን እየሆኑ ሰራዊቱን ጥለው መኮብለላቸው የሰላዮቹ ተልእኮ አለመስመሩን ተከትሎ የተጠራ ስብሰባ ከፍተኛ ፍጭት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል::ስብሰባውን ይመራሉ ተብለው የሚጠበቁት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊ እና ብ/ጄ ገብረኪዳን ሲሆኑ ጎን ለጎን ከየእዙ የትወጣጡ የሕወሓት ወታደራዊ መኮንኖች ለስብሰባ የተጠሩትን ሰላዮች ይገመግማሉ ተብሎ ይጠበቃል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶስተኛው ዙር የፌዴራል ፖሊሶች ግምገማ እንደሚካሄድ ለተቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል::ባለፉት ግምገማዎች የተለያዩ የፌደራል ፖሊስ አባላቶች ተገምግምው ለእስር የተዳረጉ በደምወዝ የተቀጡ እና በማስጠንቀቂያ የታለፉ እንደነበሩ ሲታወስ በአሁን ግምገማ ባለፍው ወያነ በጠራውና ጸረ አይሲስ ተብሎ ለፖለቲካ ፎጆታ በዋለ እና በርካቶች በታፈሱበት ፌዴራል ፖሊሶች ባነቡበት ሰልፍ ዙሪያ እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚገመገሙ ታውቋል::በአሁኑ ወቅት በታማኝነት እየሰሩ ያሉት የፌዴራል ፖሊስ ካኪ የለበሱ የአግአዚ ወታደሮች እንደሆኑ እና ዋናዎቹ ፌዴራል ፖሊሶች በበላይ ትእዛዞች እየተሰላቹ እንደመጡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች በመናገር ላይ ናቸው::

No comments:
Post a Comment