ለፈው ቅዳሜ ከወልቂጤ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው አነስተኛዋ የዳርጌ ከተማ በፖሊሶች እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የተነሳው ግጭት ይህንን ዜና እስከፃፍኩበት ድረስ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ከተማዋን በመልቀቅ ወደወልቂጤ እና ወሊሶ ከተሞች በመሠደድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካባቢው ከሚኖር ግለሠብ ለማጣራት እንደሞከርኩት ግጭቱ የተቀሰቀሰው ቅዳሜ በ24/08/2007 ዓ.ም አንድ በአካባቢው በስራ ላይ የተሠማራ ፖሊስ በግብርና የሚተዳደር ግለሠብን በአጋጣሚ በተነሳ ፀብ ምክንያት በጥይት ተኩሶ በመገድሉ ሲሆን ይህንን የተመለከቱት የአካባቢው ነዋሪዎች በስፍራው ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ጉዳዩን ለማስረዳት እና ፍትህ ለማግኘት ባቀኑበት ሠዓት የወረዳው ፖሊስ ጣቢያ አስተዳዳሪ የአካባቢውን ማህበረሠብ “እናንተ መንግስቱ ሐይለማርያም አምጥቶ የኛ መሬት ላይ ያሠፈራሁ ናችሁ ፀጥ ብላችሁ የማትቀመጡ ካልሆነ ለቃችሁ ወደመጣችሁበት መሄድ ትችላላችሁ” በማለታቸው የተነሳ ነው፡፡ ይህንን የሠሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ከፖሊሶች ጋር በተፈጠረ እሰጣ ገባ ምክንያት ግጭቱ የተከሠተ ሲሆን ግጭቱ ተባብሶ ማክሠኞ እለት ተጨማሪ አንድ የዳርጌ ነዋሪ ህይወቱ ሲያልፍ የአንድ ፖሊስ ህይወትም እንዳለፈ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርኩት የአካባቢው ነዋሪ እንደገለፀልኝ ከሆነ የወረዳው ፖሊስ መምሪያ የተናገረውን የተለያዩ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች እንደሚናገሩት ገልፆ እኛ ስደተኛ አይደለንም እዚህ አካባቢ በ1970ዎቹ የሠፈራ ፕሮግራም መሠረት ስንመጣ አውሬ ብቻ ይኖርበት የነበረን ባዶ ቦታ አልምተን ነው እዚህ የደረስነው በማለት ከገለፀልኝ በኋላም የሌላ ክልል ተወላጅ በመሆናችን ብቻ መድሎ ይደርስብናል ይህንንም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን ሲል ገልፆልኛል፡፡
በ1970ዎቹ የደርግ መንግስት በወቅቱ ከተለያዩ የአማራ ክልሎች የተወጣጡ ህዝቦችን በተለያዩ የሐገራችን ክልሎች ማስፈሩ ይታወሳል፡

No comments:
Post a Comment