ISIS፣ ደቡብ አፍሪካ፣ የመን እና አልሻባብ ወገኖቻችን ላይ እያደረሱ ያለውን በደል በመቃወም ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያን እና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንድ ላይ በመሆን ነበር በ 29.04.2015 በቬየና ይህን ሰላማዊ ሰልፍ ያደረግነው። ይህ ሰልፍ ከሾቶንቶር ዩንቨርስቲ አንስቶ መዳረሻውን ስቴፈን ፕላትዝ ነበር። በዚህ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን ከነዚህም መካከል STOP GEWALT GEGEN IMMIGRANTEN, GEGEN MENSCHEN LÖTEN MENSCHEN, ISIS & TPLF ARE TERRORIST THEY KILLED INNOCENT ETHIOPIAN, EU STOP SUPPORTING TPLF, STOP ALSHABAB የሚሉት ይገኙበታል።
ማንኛውም ህዝብ ከሀገሩ ተሰዶ በባዕድ ሀገር ኑሮውን ለመግፍት የሚገደደው፣ በባህር ላይ ህይወቱን እንዲያጣ የሚደረገው እንዲሁም በአሸባሪዎች አንገት ለመቀላት ምክንያት የሚሆነው በሀገሩ ላይ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በሀገሩ ላይ በነፃነት መኖር ባለመቻሉ ነው።
ለምሳሌ የሀገራችንን የኢትዮጵያን ብንመለከት ህዝቡ ለስደት የሚዳረገው አምባገነን የሆነ አንድ ቡድን ሀገራችንን በእጅ አዙር ቀኝ ግዛት ስለገዛት የመናገር፣ የመፃፍ፣ የመደራጀት፣ የፈለገውን ፖርቲ የመደገፍ መብቱ ተረግጦ እኔ ብቻ ያልኩት በማለት ወጣቱን በከፍተኛ ሁኔታ በማኮላሸት እና ተስፍ መቁረጥ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ የስራ ማጣት፣ ተምሮ እንዳልተማረ በማድረግ፣ የወያኔ አባል ካልሆኑ ምንም አይነት ተስፍ እንዳይኖራቸው በማድረግ ሀገራቸውን ለቀው ወደ አልፈለጉት ሀገር ህገወጥ በሆነ እና ህይወታቸውን ለከፍ አደጋ ለሚጥል ስደት እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል። ለዚህም ነው ወገኖቻችን በደቡብ አፍሪካ በጎማ የተቃጠሉት፣ በየመን የተገደሉት፣ በሜድትራኒያ ባህር ውስጥ የሰመጡት እና በሊቢያ የተሰውት። ይህም አጉልቶ የሚያሳየው በሀገራችን ላይ ያለውን የፖለቲካ እና የአስተዳደር ችግር ነው። ምክንያቱም ሰው ቢደላው ከሀገሩ ባልተሰደደ ፣ ባልተዋረደ፣ በቢለዋ ባልታረደ፣ ከፎቅ ባልተወረወረ፣ በእሳት ባልተቃጠል ነበር። ለዚህም ነው ለአውሮፓ ህብረት እና ለኦስትርያ መንግስት ድምፃችንን ያሰማንነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን እግዚአብሄር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን መንግስተሰማያት ያዋርስልን ለቤተሰቦቻቸው እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እመኛለሁ።
No comments:
Post a Comment