Thursday, April 30, 2015

ግብፅ፤ በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውን የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ መቀመጫ ለመደምሰስ ዝግጅቷን አጠናቀቀች

የግብፅ መንግስት በምስራቃዊ ሊቢያ ዴርና ከተማ የከተመውን አይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ኃይል ለመደምሰስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የወታደራዊና የደህንነት መረጃዎችን በማጠናከር የሚዘግበው ዴብካ ፋይል ድረ ገጽ ይፋ አደረገ።

ግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለው የምድር ጦር እና አየር ሃይሏን በማቀናጀት በምስራቅ ሊቢያ የሚገኘውን የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ኃይል ለመደምሰስ እና ምስራቅ ሊቢያን ለመቆጣጠር የግብፅ ወታደራዊ ሃይል በተጠንቅ መሆኑ ታውቋል።

ግብፅ ይህን ወታደራዊ ዘመቻ የምታከናውነው ፕሬዚዳት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በደረሳቸው የሀገር ውስጥ ደህንነት መረጃ ሲሆን የደህንነት መረጃዎቹ እንደሚያሳዩት በምስራቅ ሊቢያ የከተመው የአይ.ኤስ.አይ.ኤስ አሸባሪ ቡድን በግብጽ ብሔራዊ ደህንንት ላይ አደጋ መጋረጡን ነው። ይህም ሲባል፣ የእስልምና መንግስትን ለመመሥረት ያቀዱት እነዚሁ አሸባሪዎች በአንዳንድ የግብፅ ከተሞች ሰርገው መግባታቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በግብጽ ጦር ሰራዊት ውስጥም መስረጋቸው የደህንነት መረጃዎች አሳይተዋል።

መሰቦ ስሚንቶ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ማቅረቡን ማቋረጡ ተሰማ

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት የልማት ድርጅት ፣ ኢፈርት ንብረት የሆነው መሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ላለፉት ሶስት አመተት  ያለተቀናቃኝ በከፍተኛ ዋጋ ለአባይ ግድብ ስሚንቶ ሲያቀርብ ከቆየ በሁዋላ ፣ ስራውን አቋርጧል።

የአባይ ግድብ ግንባታ የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይፋ ከተደረገ በኃላ በባለስልጣናት መካከል ውዝግብ መነሳቱ ታውቋል። ጉባ የሚገኘው  የስሚንቶ ማምረቻ በመሰቦ ስር እንዲሆን መወሰኑ የውዝግቡ መነሻ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህን ተከትሎ ፋብሪካው ላልተወሰነ ጊዜ አቅርቦቱን አቋርጧል፡፡ በህወሃት ባለስልጣናት ተፅኖ ያለምንም ጫረታ ያሸነፈው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ፣ ትራንስ እና ጉና በሚባሉ የህወሃት የትራንስፖርት ድርጅቶች ስሚንቶ ወደ ግድቡ በማመላለስ ባለፉት 3 አመታት

18 የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊሶች ተባረሩ

ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ፣ የማረሚያ ቤቱ ሹሞች ፖሊሶችን ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚፈልጓቸው ከገለጹላቸው በሁዋላ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ፖሊሶች የሞባይል ስልኮች ተቀብለው ፍተሻ አድርገዋል።
በፍተሻው ወቅት 18 ፖሊሶች ከኢንተርኔት የተለያዩ ፎቶዎች፣ ጽሁፎችንና ቀስቃሽ ዘፈኖችን በማውረድ በስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠው የተገኘ ሲሆን፣ ፖሊሶቹም ወዲያዉኑ እንዲባረሩ ተደርጓል። በተለይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ግራፍ በተገኘባቸው ፖሊሶች ላይ
ክስ ለመመስረት እንደታሰበ ለማወቅ ተችሎአል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ፍተሻዎች ከ30 በላይ ፖሊሶች መንግስትን የሚያወግዙና የተቃዋሚ መሪዎችን ፎቶዎች ስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠዋል በሚል ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ እንዲገቡ ሲደረግ፣ ሌሎች
ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ጉዳያቸው እየተጣራ ነው።
በስርአቱ የተማረሩ የፌደራል ፖሊሶች በብዛት በመጥፋት ላይ መሆናቸውንም የደረሰን መረጃ ያሳያል። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በርካታ የፌደራል ፖሊሶች ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም ተብለው እየተገመገሙ ነው። አብዛኞቹ ፖሊሶች
በህዝቡ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ፍላጎት አለማሳየታቸው የመንግስት ባለስልጣናቱን አሳስቧል።
በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት በአዲስ አበባ በ10ሩም ክ/ከተሞች በሚገኙ ወጣት መዝናኛ ማዕከላት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነዋሪዎችን ሰብስቦ ባለፈው ሳምንት ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ንጹሃን ዜጎችን ለማፈንና ለማሰር እንዲመቸው በወቅቱ የተቀረፀውን ቪዲዮ
በዲቪዲ በመክፈት በቴለቪዥን በማሳየት ከዚህ ቴሌቪዥን የምታዩዋቸውን ወጣቶች ጠቁሙ፣የማን ልጅ ነው፣ይህንን ወጣት የሚያውቅ ካለ መረጃ ለመሰብሰብ እየጣረ ነው።
ድርጊቱ በህብረተሰቡ መካከል መከፋፈልና ጠላትነትን ለመፍጠር ተብሎ እርስ በርስ በመጠቋቀም አንድነትን ለማፍረስ ያሰበው ሴራ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
የመንግስት ካድሬዎች ” በሰፈራችሁ ስራ የሌለው ልጅ ማንነው?” በማለት እየጠየቁ ሲሆን፣ አላማውም ምርጫው እስኪያልፍ ድረስ ከአዲስ አበባ ውጪ በማረሚያ ቤት አቆይቶ ለመልቀቅ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
እስካሁን በተጠየቁት ጥቆማዎች ህብረተሰቡ ልጆችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።


ኢትዮጵያ በታሠሩ ጋዜጠኞች ብዛት በአፍሪካ አንደኛ ነች!!!

ኢትዮጵያ እሥር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን፤ ቪየትናም ደግሞ የኢንተርኔት ፀሐፊዋን ወይም ብሎገሯን ታ ፎንግ ታንን እንዲለቅቁ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቃል አቀባይ ጄፍ ራትካ ናቸው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ይህንን የመንግሥታቸውን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት፡፡


Wednesday, April 29, 2015

ልብሴን እንዳወልቅ ከታዘዝኩ በኋላ ራቁቴን በወንድ መርማሪዎች ፊት ስፖርት እንድሰራ እገደድ ነበር›› ትላለች የዞን ዘጠኟ ማህሌት ፋንታሁን፡፡

ጋሻው መርሻ .

ፈቃዱ የተባለ በአሁኑ ሰዓት ቂሊንጦ ታስሮ የሚገኝ የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪ የነበረ ወጣት ማዕከላዊ በተባለ ማጎሪያ ቤት ታስሮ በነበረበት ወቅት ራቁቱን እንዲቆም ይደረግ እንደነበር ተናግሯል፡፡ ‹‹ወንድ መርማሪዎች ፊት ለፊት ራቁቴን ስቆም ሀፍረት እንደሚሰማኝ የተረዱት መርማሪዎች ይድነቅህ ብለው ሴት መርማሪዎች ፊት ከ3 ሰዓት ላላነሰ ጊዜ እርቃኔን እንድቆም እገደድ ነበር›› ይላል ፈቃዱ በወቅቱ ስለነበረው ነገር ሲያስረዳ፡፡ እንደ ፈቃዱ ምስክርነት ከሆነ ሴት መርማርዎቹ ፈቃዱን ፊት ለፊታቸው አስቁመው ጌም ይጫዎታሉ፡፡ ይሳሳቃሉ፡፡ ‹‹እኔን ራቁቴን ከሶስት ሰዓት በላይ እስቁመው ደብድበው ይሸኙኛል›› ይላል የሕሊና እስረኛው ፈቃዱ፡፡

በተመሳሳይ ‹‹ልብሴን እንዳ

የብአዴን አባላት በአማራው ሕዝብ ምላሽ የተነሳ ጭንቅ ውስጥ መውደቃቸው ተዘገበ

በአማራ ክልል የሚገኙ የብ.አ.ዴ.ን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ባለስልጣናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የምረጡን ቅስቀሳ ህዝቡ ስላልተቀበለው በከባድ ስጋት ላይ መውደቃቸው ታወቀ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::

በአማራ ክልል የሚገኙ ባልስልጣኖች በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ህዝቡ እንዲመርጣቸው ያካሄዱት ቅስቀሳ በህዝብ ተቀባይነት በማጣቱና በስርዓቱ ላይ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሊመርጡ ይችላሉ በሚል የጠረጠሯቸውን ንፁሃን ዜጎች ንብን የያዘ ፖስተር ቀድዳችኋል በማለት እያሰሯቸው መሆናቸው ሊታወቅ ተችሏል።

ንብ ያለበትን በራሪ ወረቀት ቀደዳችሁ በሚል ከታሰሩት ወገኖች መካከል የተወሰኑትን ለመግለፅ ያህል ሙስጠፋ አሊ ነዋሪነቱ ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና፥ መኩየ ሃይሉ ከባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03፥ ታደሰ ጌቱ ከላሊበላና ሌሎችም መሆናቸውና ህዝቡ በላዩ ላይ እየወረደ ያለውን ግፍ ተቋቁሞ በኢ.ህ.አ.ዲ.ግ አንገዛም በማለት ተቃውሞው እየቀጠለ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰን መረጃ አስረድቷል።


ኤዶምንና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን የ45 ሚሊዮን ሴቶች ክብርን ነው ያቀለሉት – ግርማ ካሳ

ኤዶም ካሳዬ ጋዜጠኛ ናት። ማህሌት ፈንታሁን ደግሞ «ሰለሚያገባን እንጦምራለን» በሚል የአለም አቀፍም ሆነ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት በሚፈቅድላቸው መሰረት፣ ብሎግ ከሚያደርጉ ዞን ዘጠኞች አንዷ ናት። ኤዴሞም ሆነ ማህሌት የጻፉት፣ የተናገሩት የተደበቀም ሆነ የተሸፈነ ነገር የለም። ለፍትህ ከመቆማቸው በቀር ያጠፉት ጥፋት የለም። ወንጀላቸው አገራቸውን መዉደዳቸው ነው። ሆኖም ሕወሃት «ሽብርተኞች» ብሎ ካሰራቸው ይኸው አንድ አመት ሆናቸው። ቢያንስ ከ27 ጊዜ በላይ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል። አስቡት በአንድ አመት ዉስጥ ቢያንስ 27 ጊዜ !!!!!

የአገሪቷ ሕገ መንግስት በማረሚያ ቤት ያሉ እስረኞች በምን መልኩ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ አስቀምጧል። በአንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ፣ እስረኞችን ጨምሮ፣ ኢሰብአዊ ፣ ጭካኔ የተሞላባቸዉና ክብርን የሚነኩ ቅጣቶች ሊቀበል እንደማይገባ ያስቀምጣል። ሆኖም ረእቡ ሚያዚያ 14 ቀን፣ የአዲስ አበባ ሰልፈኞች እንዳሉት፣ ለሕወሃት ሕገ መንግስቱ ወረቀት ብቻ ነው። እህቶቻችን ሞራላዊ፣ መንፈሳዊና የሴትነት ክብራቸውን በመድፈር ፣ ራቁታቸውን ሆነው በአረመኔ የሕወሃት ወንድ ምናምንቴዎች ፊት ስፖርት እንዲሰሩ መገደዳቸው ምን ያህል እንደ አገር መዝቀጣችንን የሚያሳይ ነው። በርግጥ ኤዶምና ማህሌትን ብቻ ሳይሆን ሕወሃቶች ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን የአገራችንን እናቶችና እህቶች ነው የደፈሩት።

የማዕከላዊ ዕዝ አባላት በከተማ ውስጥ የሠራዊቱ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ ነው

የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በገዢው የኢህአዴግ ስርአት ውስጥ የሚገኙ የማእከላዊ እዝ ሰራዊት አባላት ወደ ከተሞች በመሄድ ህውከት እየፈጠሩ እርስ በራሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸውን ምንጮቻችን ገለፁ።

እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላይ በሚገኝ “ብሄራዊ ሆቴል” ውስጥ ሚያዚያ 4/2007 ዓ/ም የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑት ወታደሮች መጠጥ በመጠጣት እርሰ በራሳቸው ተጣልተው ከፍተኛ ግርግር እንደተነሳ የገለፀው መረጃው ህውከት ፈጣሪ ከሆኑት የሰራዊቱ አባላትም መቶ አለቃ ደሳለኝና ምክትል መቶ አለቃ አየለ ናሳ የተባሉት መሆናቸውና በጠርሙስና ሌሎች የሆቴሉን ንብረት በማንሳት እየተወራወሩ መደባደባቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በተከሰተው ብጥብጥ ሁለቱም መኮንኖች በከባድ መጎዳታቸውና በተለይ ምክትል መ/አለቃ አየለ ናሳ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ከሁለት ቀን በኋላ እንደሞተ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።


በአማራ ክልል ብቻ እሚካሄድ ትጥቅ ማስፈታት

በአማራ ክልል ብቻ እሚካሄድ ሰሞኑኛ ወንጀል

በአማራ ክልል አሁንም ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት እንደቀጠለ ነው። የወያኔ ሎሌዎች በየገጠሩ እየዞሩ አማራውን ጠመንጃችሁን ካላስመዘገባችሁ ማዳበሪያ አታገኙም እያሉ በማስፈራራት አማሮች ሳይወዱ በግድ ጠብመንጃቸውን እያስመዘገቡ ይገኛሉ። ያስቸግራሉ የተባሉትን ደግሞ እየተቀሙ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህም እየተደረገ ያለው ሁለት ነገር ነው፤
1- እንደተለመደው ወያኔ ለአማራው ባለው የማይለውጥ ጥላቻና ንቀት የተነሳና ፤
2- ኮሽ ባለች ጊዜ የተመዘገበውን ጠብመንጃ በየቤቱ ለመልቀም ያመቸው ዘንድ ነው። ወያኔ ሌት ተቀን እንደሚደሰኩረው መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ካሰፈነ፡ አማራውን ለምን ጠመንጃውን ይቀማል? ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ የማያደርገውን በአማራው ህዝብ ላይ የመሳሪያ መቀማትና የትጥቅ ማስፈታት ያለምክንያት አይደለም “ጅብ ቀን ቀን የምትደበቀው ለምንድነው ሲሉት፡ ሌሊት ሌሊት የምሰራውን ስለማውቅ ነው” እንዳለው ሁኖበት እንጂ። እና በአማራው ህዝብ ላይ ወያኔ እየሰራው ያለው ጉድ ወይንም ወንጀል እንዳለ ከዚህ በላይ ምን ይኖራል? በነገራችን ላይ ይሄ መሳሪያ ማስፈታት ገንዘብ የሚያስገባ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ከሁሉም የሚያበሳጨው ግን ለህዝብና ለሀገር ሲል አጥንቱን የከሰከሰን፥ ደሙን ያፈሰሰንና እንደጧፍ የነደደት ህዝብ ማክበር ሲገባ፡ በነፍጠኝነትና በጠላትነት ተፈርጆ ማንም እየተነሳ ሲገድለው፤ ሲሰድበው፤ ሲያንኳስሰውና ሲዘለፈው ቆሞ የሚያይ አማራ ሲገኝ ነው። አማራው ዛሬ ማንም ጎጠኛ እየተነሳ አፉን ሊያፍታታበት የቻለው አማራው ለራሱ ሳይኖር ለሌላው ኖሮ ሳለ አማራውን ወያኔና በወያኔ ብርና ዶላር ገፋፊነት ወረቀት የሚያበላሹ ቅጥረኞቹ ጸሀፊና ጋዜጠኛ በሉኝ ባዮች አማራውን የስህተትና የጥፋት ቋት በማድረግ ለህዝብና ለአገር ያደረገውን አንዳች ነገር እንደሌለ በመካድ ነጋ ጠባ ውንጀላን በመደርደር ዋሾ ቅጥረኛ በመሆናቸው ነው። ከነዚህ ቅጥረኞች በተጨማሪ ተማርን ብለው የአማራን ታሪክ አጣመው በምሁርነት ካባ የሚጽፉ ሆዳሞችም አልጠፉ። እነዚህም ቢሆኑ በጠላትና በፈረንጅ ትምሀርት ቤቶች ገብተው የክህደትና መሀይምነት ዶክተሮች የሆኑ ናቸው። በነገራችን ላይ ወያኔ በአማራ ላይ የሚያደርሰው ሁሉ የጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ አካል ነው። ይህንን ዝም ብሎ የሚያይ የአማራ ልጅ ያልታደለና የተደየነ ብቻ ነው። የወያኔው የእጅ ስራ የሆነው ብዓዴን እንደሆነ የአማራን ህዝብ ከከዱትና ከጠሉት ከራርመዋልና የአማራን ህዝብ ይታደጋሉ ብሎ መጠበቅ ፋይዳ ቢስነት ነው። ብዓዴን ስለአማራ ይሉኝታን ከገደለ ከርሟል። በዚህም የተነሳ ወያኔ ካፈጣጠሩ አንስቶ በብዓዴን ሽፋን የአማራን ህዝብ ከማጥፋት ሌላ ራሱም በቀጥታ ተሰማርቶ ህዝባችንን እየፈጀው ይገኛል። ስለዚህ መላ ያማራ ተወላጅ የሆንህ ሁሉ ቆሻሻውንም ከጫንቃህ ላይ አንሳና ተነሳ። ስለዘርህ ስትል ዛሬውኑ ስርየትንና ንጹህነትን ፈላጊ ሁን። እና በዚህ ያደቆነኝ ሰይጣን ይጨርሰኝ ባዮች በበዙበት አገራችን ውስጥ የህዝባችን መጥፋት የሚቆጭህ ወዲህ በለኝ። የተማርን ነን የምንል የአማራ ተወላጆች ደግሞ የአማራውን ሙሉና ሀቀኛውን ታሪክ እናስተምር! ሁላችንም አማራን ስለመታደግ የምንችለውን ሁሉ እናደርግ ዘንድ ጥሪ አስተላልፍላችኋልችሁ።


ራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር ፍትህ ማጣቱን የሚያትት ደብዳቤ ጽፎ ማለፉ ታወቀ

ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር ፍትህ ማጣቱን የሚያትት ደብዳቤ ጽፎ ማለፉ ታወቀድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ ባሃድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በጊምቢቾ ከተማ የፊዚክስ መምህር የነበረው ጌታቸው አብራሃም ፣ በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል።

የመድረክ አባል የነበረው መምህር ጌታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። የተቃዋሚ አባል በመሆኑ ብቻ የ3 ወር ደሞዙን እንዳያገኝ የተከለከለው መምህር፣ አቤቱታውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ሲያቀርብ ቆይቷል። በመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ደብዳቤ

ጽፎና የመድረክን የምርጫ አርማ ከጎኑ አድርጎ በምክር ቤቱ ግቢ ውስጥ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል። መምህሩ ራሱን ማቌጠሉን ተከትሎወደ ሆሳእና ሆስፒታል ቢወሰድም ሊተርፍ አልቻለም።

ጓደኞቹ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ የ28 አመቱ መምህር ጌታቸው ጤነኛ እና ጥሩ ጸባይ የነበረው ነው። የመምህሩ የቀብር ስነስርአት ባለፈው አርብ በጊምቢቾ ከተማ ተፈጽሟል።

በተመሳሳይ ዜናም በአፋር ክልል ቡሩ ሞዳይቶ ከተማ ላይ ከሰል በማክሰል ይተዳደር የነበረ ነዋሪ፣ የክልሉ ፖሊሶች 50 ሺ ብር የሚያወጣውን ከሰሉን ስላቃጠሉበት ተበሳጭቶ መርዝ በመጠጣት ራሱን አጥፍቷል።

ተመሳሳይ እርምጃ የወሰደው ሌላው ነጋዴ መትረፉ ሲታወቅ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ቤት መቃጠሉም ታውቋል።

ፖሊሶች ዛፍ ምንጠራን ለመከላከል በሚል ምክንያት እርምጃውን መውሰዳቸው ታውቋል። ነዋሪዎች ፣ መንግስት ደን እንዳይመነጠር ቢፈልግ እንኳ፣ ነጋዴዎች እስካሁን የያዙትን እንዲሸጡ በማድረግ ተጨማሪ ቁጥጥር ማድረግ ይችል ነበር ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በርካታ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎችና የቀድሞ የህወሃት ጦር ጡረተኞች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ደን እየመነጠሩና ከሰል እያከሰሉ ወደ ሱዳን እንደሚልኩ ይታወቃል።


የወያኔ መንግስት የአንድ ቀን የሰላም ጉባኤ ጠራ

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ
ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት ምርጫ ቦርድ በተለይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት ያለማንገራገር እንዲቀበሉ ለማግባባት ሙከራ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያዊያን በሊቢያ በረሃ በአይኤስ አሸባሪ ቡድን በግፍ መገደላቸውን ለመቃወም ባለፈው ሳምንት በመንግስት በተጠራው ሰልፍ ላይ ሕዝቡ በግልጽ ለኢህአዴግ መራሹ መንግስት ያለውን ጥላቻ ካንጸባረቀ ወዲህ በኢህአዴግ ካድሬዎችና አባላት ዘንድ ከፍተኛ
ድንጋጤ መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን፣ ከምርጫው ውጤት ጋር ተያይዞ ሁከት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት የኢህአዴግ አባላትን አስጨንቆአል፡፡ ነባር የኢህአዴግ አመራሮች ወደ ክልሎች በመሄድ ፣ ህዝቡን ለማረጋጋት ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ
ያመለክታል። ህዝቡ ግን አሁንም ምሬቱን እየገለጸ ነው
ኢህአዴግ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ተቃውሞውን አስነስተውታል በማለት ውንጀላ ቢያሰማም ህዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም። ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፌደራል ፖሊሶች ተቃውሞውን ለመግለጽ በወጣው ህዝብ ላይ
የወሰዱት እርምጃ ፣ ህዝቡን ይበልጥ አስቆጥቷል፡፡ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል ምርጫውን ተከትሎ ህዝባዊ አመጽ ይነሳል አይነሳም የሚል የህዝብ መጠየቂ ፎርም አሰራጭቶ በትኗል።
የፌደራል ፖሊስ ከ1 ሺ በላይ ወጣቶችን ይዞ ማሰሩን አምኖ፣ ይሁን እንጅ 150 ዎችን ብቻ አስቀርቶ ሌሎችን መፍፋቱን ገልጿል። ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አሁንም ድረስ ወጣቶች እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው።
ኢህአዴግ ያቋቋማቸው የወጣትና የሴት ሊግ አደረጃጀቶች ሰዎችን እየጠቆሙ በማሳሰር ላይ መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል።
በአገር ቤት የሚታየው ቁጣ በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ እየተንጸባረቀ ነው። በስዊድን በተደረገ የሻማ ማብራት ስነስርአት ላኢ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተገኝተዋል። የተለያዩ የሃይማኖት አባቶችና የድርጅት መሪዎች
በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ወገኖች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍ አውግዘዋል። ለኢትዮጵያውያን ስደትና መከራ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ተጠያቂ መሆኑንም ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።
በዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በአይ ሲሲ በግፍ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን አስበዋል።


በባሌ ጎባ ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተበተነ

በባሌ ጎባ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራ ሰልፍ ህዝቡ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መበተኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በባሌ ጎባ በተጠራው ሰልፍ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ ይቆጠብ›› የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አሸባሪ ነው›› በሚል ህዝቡን ቀስቅሰው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሆኖም ሰልፉ በሚደረግበት ጎባ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ በመኪና ቅስቀሳ እያደረገ ስለነበር ሰልፉ ላይ ሰማያዊን እንዲያወግዝ ተጠርቶ የነበረው ህዝብ ‹‹አሸባሪ የምትሏቸው ሰዎች ሰላማዊ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ አሸባሪ ከሆኑ ለምን የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጋሉ? አሸባሪ ያልሆኑትን ሰዎች ለምን አሸባሪዎች ናቸው ትሉናላችሁ?›› በሚል ሰልፉን ጥለው በመሄዳቸው ሰልፉ እንደተበተ ተሰምቷል፡፡ ህዝቡ ሰልፉን ጥሎ በመሄዱ የቀሩት ካድሬዎችም ወደ ቀበሌ የስብሰባ አዳራሽ በመሄዳቸው ሰልፉ ወደ ስብሰባ ተቀይሯል ተብሏል፡፡


Saturday, April 25, 2015

Eritrea and Ethiopia named most censored countries in Africa

Eritrea and Ethiopia have been named as the most censored African countries in a report compiled by the Committee to Protect Journalists (CPJ).

According to the CPJ release, the list is “based on research into the use of tactics ranging from imprisonment and repressive laws in the harassment of journalists and restrictions on Internet access.”

Eritrea ranked number one while Ethiopia came in fourth in the list of 10 most censored countries in the world. The eight other countries on the list are North Korea, Ethiopia, Azerbaijan, Vietnam, Iran, China, Myanmar, and Cuba.

Friday, April 24, 2015

እየተስተዋለ - ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

እነዚህ ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸው፡፡ ሃይማኖታቸውን አንለውጥም ብለው የተሠዉ፡፡ ‹ስደተኛ ኢትዮጵያውያን› የሚለውን አገላለጽ ነፍሴ ትጸየፈዋለች፡፡ ከአኩሪው የሰማዕትነት ተግባራቸው በላይ ስደተኛነታቸው ለማጉላት ስለሚያኮበኩብ፡፡ ሰው በሀገሩ ቢኖር፣ ቢሠራና ቢከብር የመጀመሪያ ምርጫው ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያውያን፡፡ ነገር ግን ‹እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል› ይባላልና የቸገረው ቢሰደድ ምን ይፈረድበታል? በርግጥ ስደቱ በሰላም፣ በሕግና በጤና ቢሆን የማይወድ የለም፡፡ ግን ሁል ጊዜ ይቻላል ወይ? ምቹ ሁኔታስ አለ ወይ? ዛሬ ከአውሮፓ፣ አሜሪካና አውስትራልያ፣ ከአፍሪካና እስያ ገንዘባቸውን እየላኩ አንዳንዴ ከቡና በላይ አንዳንዴም ከቡና ቀጥሎ የውጭ ምንዛሬውን የሚያስገኙልን ወገኖች አብዛኞቹ ዛሬ ‹ሕገ ወጥ› በምንለው መልኩ የሄዱ አይደለም ወይ? እንዲያ እንዲሆኑ ያደረጋቸውን መሠረታዊ ምክንያት መፍታት እንጂ የሆኑበትን መንገድ ማውገዝ ምን ይጠቅማል?

Wednesday, April 22, 2015

Partnership with a Dictatorship guarantees neither security nor stability in Ethiopia

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy is deeply saddened by the completely reckless remarks made by Wendy Sherman, US Undersecretary of State for Political Affairs. The recent remark made by Wendy Sherman in Addis Ababa is uncharacteristic of the US State Department, and it totally contradicts   the Department’s annual human rights report on Ethiopia.  The remark was thoughtless, misguided and as the statement issued by Freedom House aptly put it, it is woefully ignorant and counter-productive.

The most recent US Department of State Human Rights Report on Ethiopia describes the state of human right in Ethiopia in the following two unambiguous statements:

የአርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትናዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤  ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችንአይሲስበተሰኘህሊናቢስ፣ፀረ-ሰውእናፀረ-ስልጣኔቡድንበሊቢያበአሰቃቂሁኔታየመገደላቸውመርዶከትናንት ወዲያሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓምደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው።  ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች  ስብዕናችንን ገፈፉን።

“[ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ ስለተሰውት ሰማዕታት ያወጣው መግለጫ] የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የቅዱስ ሲኖዶሱን መግለጫ አየሁት፡፡ መጀመሪያ ነገር ቋሚ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ መክሮበታል ብዬ ለማመን ይቸግረኛል፡፡ የተጻፈበት ቋንቋ ቤተ ክህነት ቤተ ክህነት አይልም፡፡ ለመሆኑ ለሰማዕታት የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አጥታችሁ ነው? ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ የሰማዕታቱ ዜግነት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምን እንደሚጠቅማት ነው፡፡ መንግሥት የዜግነትን ጉዳይ ቢያነሣ ኃላፊነቱ በዜጎቹ ላይ የተወሰነ ስለሆነ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን ‹መልዕልተ ኩሉ› የተባለቺውን ዘንግታው ነው የዜግነት ጉዳይ ያሳሰባት? ምንም ኢትዮጵያዊነታቸው የማያጠራጥር ቢሆንም፣ ጠላታቸው እንኳን የመሰከረላቸው ቢሆንም፣ ዓለም ያወቃቸው ቢሆንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ግን ሱዳኖችም ሆኑ ሩዋንዳዎች፣ ሶማልያዎችም ሆኑ ጅቡቲዎች የተሠውትኮ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን የሰማዕትነት ክብሩ የሞተለት ክርስቲያናዊ ምክንያት ነው፡፡ የሞቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናችሁ ተብለው ነው፡፡ በቃ፡፡

ደግሞስ ‹የዜግነትና የማንነት መረጃውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ነው› የሚሉን ማነው ጥረት እያደረገ ያለው? መንግሥት ነው ካላችሁ ‹መንግሥት ጥረት እያደረገ ነው› በሉ እናንተም ጥረት እያደረጋችሁ ከሆነ ንገሩን፡፡ ቤተሰቦቻቸውኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው፡፡ ለምን ለየሀገረ ስብከቱ መመሪያ በመስጠት ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ከበዳችሁ? እረኛ በጎቹን በሪሞት ይጠብቃል እንዴ?
እጅግ ያስገረመኝና ያሳዘነኝ ነገር ደግሞ ክርስቲያን በመሆናቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉ ወንድሞች ከቤተ ክርስቲያን የምጠብቀውን ሦስት ነገር ከመግለጫው ማጣቴ ነው፡፡ የመጀመሪያው የመታሰቢያ ጸሎት ሊደረግ ይገባው ነበር፡፡ በምንም ለማናውቃቸውና ለማያውቁን የኢንዶኔዥያ ዜጎች ሱናሚ መታቸው ብለን በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ያደረግን ሰዎች ለሚያውቁንና ለምናውቃቸው ክርስቲያን ወገኖች ጸሎት ለማድረግ ለምን እንደከበደን እንጃ፡፡ ለመሆኑ ከአንድ አባት ከጸሎት በላይ ምን ሊገኝ ይገባ ነበር?

‹ማንነታቸው ተረድተን በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን እናድርጋለን› ይላል መግለጫው፡፡ ለመሆኑ ከክርስትና በላይ ምን ማንነት አለ? የብሔር፣ የብሔረሰብ ማንነት ነው የምታጣሩት? ከዚያ ይልቅ ሁኔታውን የሚከታተል፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኝና ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊም ቀኖናዊም ተግባር ነገሮችን የሚያመቻች ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋማል ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ምነው በአንድ አጥቢያ ገንዘብ ተወሰደ ሲባል ሲኖዶሳዊ ኮሚቴ ይቋቋም የለምን?

ሦስተኛው ያሳዘነኝ ነገር ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ የሚደርሰውን ኀዘን የምትገልጥበት ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሥነ ሥርዓት የሌላት ይመስል ኀዘንን በሴኩላር መንገድ ስትገልጥ ማየቴ ነው፡፡ እኔ የጠበቅኩት ለአንዳንድ ክርስቲያን ላልሆኑ ‹ታላላቅ ሰዎች› ቀብር እንኳን የሚከፈተው የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከፍቶ፣ ለቢዮንሴ እንኳን ያልተነፈጋት ማኅሌት ተቁሞ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ጳጳሳቱ የሚገኙበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተደርጎ፣ መግለጫው በጸሎቱ ፍጻሜ ይሰጣል ብዬ ነበር፡፡ የመግለጫው አሰጣጥ ግን የዕለት ተዕለት ተግባርን በተመለከተ የሚሰጥ ሳምንታዊ መግለጫ ነበር የሚመስለው፡፡ ኦርቶዶክስ ኦርቶዶክስ አይሸትም፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት እንኳን የሦስት ቀን ብሔራዊ ኀዘን ሊያውጅ መሆኑን ሲገልጥ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን የጸሎት ሳምንት አለማወጇ የታሪክ ትዝብት ውስጥ የሚከታት ነው፡፡

እኔ የሲኖዶሱ መግለጫና አገላለጡ ወርዶብኛል፡፡ ሲኖዶሳዊም መስሎ አልታየኝም፡፡ ሊቃውንቱ ያዩት፣ ጳጳሳቱ የተወያዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ያሹት፣ ቀኖናዎቹ የዳሰሱት፣ ትውፊቱ የነካው፣ ባሕሉ ያጠነው አልመስልህ አለኝ፡፡ ‹ወይ እንደ እስክንድ ተዋጋ ወይ የእስክንድርን ስም መልስ› አለ ታላቁ እስክንድር፡፡


Monday, April 20, 2015

የምናዝነው ስንት ሰው ሲሞት ነው? በዲያቆን ዳንሄል ክብረት

በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ስለሚሞቱት ዜጎቻችን የሚሰጡት መንግሥታዊ መግለጫዎች ሁለት ነገር የጎደላቸው ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰብአዊ ስሜት፡፡ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ስለሌላው ሰብአዊ ፍጡር መከራና ስቃይ ሲሰማ መጀመሪያ አንዳች የኀዘን ስሜት ይሰማዋል፡፡ ከዕውቀት ይልቅ ስሜት ለሰዎች ቅርብ ነውና፡፡ ባለሥልጣን ቢሆን፣ ፖሊስ ቢሆን፣ ዳኛ ቢሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ሰው ነውና ስሜት አለው ተብሎ ይታሰባል፡፡ ያዝናል፣ ይከፋዋል፣ ልቡ ይረበሻል፣ ሆዱ ይባባል፣ ኅሊናው ይደማበታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህም የመጀመሪያው ሥራው ማዘን ቀጥሎም ኀዘኑን በወጉ መግለጥ ነው፡፡
ሰሞኑን የማያቸው መግለጫዎቻችን ግን የኀዘን ወግ በሀገራችን የሌለ የሚያስመስሉ ናቸው፡፡ መሪዎቻችን ወደ አደባባይ ወጥተው ለሞቱት ወገኖቻችን እንደ ኢትዮጵያዊነት ኀዘናቸው የሚገልጡት፣ ጥቁር ልብስ ለብሰው የምናያቸው፣ ነጠላ የሚያዘቀዝቁት ስንት ሰው ሲሞትብን ነው? የሚያስብሉ ናቸው፡፡ ኀዘንኮ ፖለቲካ አይደለም፣ ፓርቲ አይደለም፣ ርእዮተ ዓለም አይደለም፣ ሊብራልም አብዮታዊ ዲሞክራሲም አይደለም፡፡ ኀዘን ሰብአዊነት ነው፡፡ የሚመራቸው ዜጎቹ፣ የሚያሠማራቸው በጎቹ ሲታረዱና ሲሞቱ ኀዘኑን በይፋ የማይገልጥ መሪና እረኛ መቼ ነው ኀዘኑን የሚገልጠው?

በግፍ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን በተመለከተ የአርበኖች ግንቦት 7መግለጫ  April 19, 201

ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ  የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

Saturday, April 18, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶርክተር ብርሃኑ ነጋ ዌንዲ ሼርማን ስለተናገረችው መልስ ሰጡ

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶርክተር ብርሃኑ ነጋ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር ዌንዲ ስለተናገረችው የሰጡት አጭር ቆይታ ከዚ ቀደም ዌንዲ ሼርማን ኢራንን በተመለከተ ተናግራ የሆነ ነገር ይቅርታ እንድታደርግ ተደርጋለች። እኔ እንደሚመስለኝ ምን ያህል ጭንቀት ውስጥ ወያኔዎች እንደገቡ እንዳለ ነው የሚያመላክተኝ እንደው ይሄን ነገር ተናገሪልን ብለው ለምነው ያናገሯት ነው የሚመስለው ምክንያቱም እንደሚታወቀው በሁሉም አቅጣጫ ይሄ ስርዓት ሊቆጣጠረው የማይችለው የህዝብ አመፅ እና ግፊት ውስጥ እየገባ ነው ያለው ይሄንን በህዝብ የሚመጣ ግፊት እንደው ትንሽ አሜሪካ የሆነ ነገር ከተናገረች ሰዎ መለስ ይልልኛል ከሚል ቅዥት የተነሳ አንድ ነገር ብትልልኝ ብለው ነው የሚመስለኝ። ለኔ በጣም እታየኝ ያለው ሁኔታ በቀላሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሆነ ህብረተሰቡ በፍጹም እያመፀ እንደሆነ በደንብ የተረዱት ይመስለኛል። እና እቺ የመጨረሻ ለማረጋጋት ይቻል እንደሆነ ለመሞከር የተደረገ ነው የሚመስለው በአሜሪካኖች በኩል ይሄ ግን የሚገርመው ነገር ለዴሞክራሲ እና ለነፃነት ለእኩልነት የሚደረግን ትግል አሜሪካ አንድ ነገር ተናገረች፣ እራሺያ አንድ ነገር ተናገረች፣ ቻይና አንድ ነገር ተናገረች የሚቆም ነገር አይደለም ህብረተሰቡ ነው ኑሮውን የሚያውቀው ያ ህብረተሰብ ያለበትን ኑሮ አይቶ በቃኝ ብሎ ከተነሳ ማንም የሚያቆመው ሀይል የለም። ሙሉውን ቃለ መጠየቅ ታች ያለውን የኢሳት ሬዲዮ ተጭነው ያድምጡ http://ethsat.com/esat-radio-17-april-2015/


Wednesday, April 15, 2015

ሞያሌ ከትናንት ምሽት እስከ ዛሬ እኩለቀን ድረስ በተኩስ ተናጠች

ሚያዝያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ከትናንት ሰኞ ምሽት ጀምሮ እስከ ዛሬ ማክሰኞ እኩለቀን ድረስ ከተማዋ በተኩስ ስትናወጥ ውላለች።
አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት የተኩሱ ልውውጡ የተካሄደው በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና በሶማሊ ክልል ልዩ ሚሊሺያዎች መካከል ነው፡፡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አንድ የክልል 5 ጠባቂ መግደላቸውን ተከትሎ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል ሚሊሺያዎች በየሰዎች ቤት እየገቡ እቃዎችን ከመሰባበርና ከመዝረፍ በተጨማሪ ከተማዋን በተኩስ ሲበጠብጡዋት አድረዋል።
ጧት አካባቢ በአማርኛ ፣ በኦሮምኛና በሶማሊኛ የተጻፉ ወረቀቶች መበተናቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ጽሁፎቹ በከተማው ያሉትን ባንዶች ለመቅጣት መጥተናል የሚል ይዘት እንዳለው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በማግስቱ ለገዢው ፓርቲ ቅርበት አላቸው የሚባሉ ድርጅቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል።
አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት የሶማሊ ክልል ተጣቂዎች ምሽት ላይ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አስቁመው በሚፈትሹበት ጊዜ፣ አንደኛው ለምን ትፈትሹታላችሁ በማለት ፈታሹን የገደለው ሲሆን፣ መረጃው በሶማሊ ክልል ታጣቂዎች ዘንድ በመድረሱ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ መነሳሳታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የክልሉ ታጣቂዎች ሌሊት ላይ በወሰዱት እርምጃ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ማክሰኞ ጠዋት ደግሞ የከተማዋ የሶማሊ ተወላጆች የመከላከያን ድርጊት በመቃወም ወደ አደባባይ የወጡ ሲሆን፣ በመኪኖች እና በተለያዩ ድርጅቶች ላይ ባደረሱት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአል። የፌደራል ፖሊሶች ተከታታይ ጥይቶችንና አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር ቢችልም፣ ውጥረቱ እስከ ምሽት ዘልቋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ውለዋል።
የፌደራል ፖሊስ አባላት ከረብሻው ጋር እጃቸው አለበት ብለው የሚጠረጥሩዋቸውን ሰዎች ይዘው በማሰር ላይ ናቸው።


Saturday, April 11, 2015

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ወክባ እየተፈጸመ ነው ተባለ።

ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው፤ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እስረኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽም የቆየው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰሞኑን ደግሞ በከሰዓቱ
የእስረኞች መጠየቂያ ክፍለ ጊዜ ጠያቂ እንዳይገባላቸው እገዳ ጥሏል።
የማረሚያ ቤቱ አ

Friday, April 10, 2015

የመን ለሚገኙ ወገኖቻችን እንድረስላቸው!

የመን የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን አደጋ ላይ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የመብት አፈና፣ ሥራ አጥነት፣ ችጋርና ተስፋ ማጣት ለመሸሽ የራሳቸውንና የዘመዶቻቸውን ጥሪት አሟጠው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለሚሰደዱ ወገኖቻችን የመን መሸጋገሪያቸው ናት። ዛሬ የህወሓት ወዳጅ የሆኑም ያልሆኑም የየመን አምባገነን ገዢዎች እርስ በርሳቸው እየተላለቁ፤ ከምድር እሳት እየነደባት መሆኑ ሳያንስ ከሰማይም እሳት እየዘነበባት ነው።

እንኳን አሁንና በሰላሙም ጊዜ የመን ለኢትዮጵያዊያን ምቹ አልነበረችም። በበረሀ ጉዞ የዛሉ እግሮች፤ ከአቅማቸው በላይ በጫኑ ታንኳዎች ባህር በመሻገር የታወኩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የመን ጠረፍ ላይ የሚጠብቃቸው ተጨማሪ እንግልት፣ ስቃይና መደፈር ነበር። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር የደረስበት አሳፋሪ ደረጃ መገለጫ ሆኖ ቆይቷል። በየመን፣ ወገኖቻችን ተደብድበዋል፤ አካላቸው በስለት ተዘልዝሏል፤ ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ተደፍረዋል፤ ጓዳችን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታፍኖ ለህወሓት ተላልፎ ተሰጥቶብናል። አሁን የመን እየነደደች ነው።

Thursday, April 9, 2015

" ምስክር ፈላጊው ችሎት " - 27ተኛ የፍርድ ቤት ውሎ

በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል ያሉ አምስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡። የምስክሮቸን ቁጥርም 35 ነው በማለት ቀይሮታል፡፡
ባለፈው የተሰሙት 13 ምስክሮች ሲሆኑ በዛሬው ችሎት ባልተካደ ነገር ላይ ሲመሰክሩ የዋሉት የደረጃ ምስክሮች
14ተኛ ምስክር ተወዳጅ ኃ/ማርያም ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 34 ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹የመጣሁበት ኬዝ ግንቦት 7/2006 ዓ.ም በምኖርበት ልደታ 5ኛ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ጠይቆኝ በታዛቢነት ያየሁትን ለመመስከር ነው፡፡ ማህሌት ጤና ጥበቃ ሚ/ር ትሰራለች መሰለኝ፣ እዚያ መስሪያ ቤት ፖሊስ ማህሌት ኮምፒውተርና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሲበረብር አይቻለሁ፡፡ መንግስት መስሪያ ቤት የምትጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ የተገኙ ሰነዶች ላይ ማህሌት ስትፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ የፈረምነው ግንቦት 7/2007 ዓ.ም ነበር፡፡ የገጹን ብዛት አሁን አላስታውስም፤ ወደ 40 ገጽ ይሆናል፡፡ እንግሊዝኛና አማርኛ ጽሁፎች አሉበት፡፡ የተወሰነ የፖለቲካ ይዘት የነበረው አለ፡፡ የፖለቲካ ፕሮግራም ማኒፌስቶ አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ

Wednesday, April 8, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ

አቡበከር አህመድ እንደዘገበው
መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነውን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳይገነቡ በሚል መመሪያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል።
በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን እያሰፋችበት በሚገኘው በዚህ ወቅት ላይ ይህ አይነቱ ወሳኔ መተላለፉ መንግስት ህብረተሰቡን ከእምነቱ ለማራቅ ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው::
ዉሳኔው ሌላ መመሪያ እስኪመጣ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በቅርቡ በተለያዩ እምነቶች ለእምነት ተቋም መገንቢያ ተብለው የተከለሉ ቦታዎችን መንጠቅ እንደተጀመረም ምንጮች አካተዉ ገልፀዋል።


Monday, April 6, 2015

“ህዝቡ ነጻ አውጪዎችን መጠበቅ ሳይሆን ራሱን ነጻ መውጣት አለበት” አቶ ዮናታን ተስፋዬ (የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ )

በእድሜ ትንሹና ገና ከመምጣቱ የህዝብን ትኩረት ለማግኘት የበቃው ሠማያዊ ፓርቲ በተለይም ከአንድነትና መኢአድ ሁለት ሁለት ቦታ መሰንጠቅ በኋላ ጎልቶ የመታየት ቀለሙ ይበልጥ የደመቀ ይመስላል ። ፓርቲው ከየት ተነስቶ እስከምን ይጓዛል ? የሚለውን ጥያቄ ከወቅታዊ ሁነቶች ጋር በማዛመድ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ከሆነው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ጋር 1:50 ሰዓት የፈጀ ቃለመጠይቅ አካሂደናል ። በፌስ ቡክ የደረሱኝንና ሌሎች ጥያቄዎችን አንስቻለሁ

ኢትዮ -ሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመው መቼ ነው ?

አቶዮናታን – 2004 ዓ.ም ታህሳስ ወር ጠቅላላ ጉባኤውን አድርጎ በይፋ መመስረቱን አውጇል ። ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቶ የመዘገበው ግን ሐምሌ /2004 ዓ.ም ነው ።

ኢትዮ – ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች እያሉ ሰማያዊ ፓርቲ ለምን ተቋቋመ ? ቁጥሩን በአንድ ከመጨመር ባለፈ ሌሎች ያልሰሩትን ምን የመሰራት አላማ ኖሮት ነው?

Saturday, April 4, 2015

Ethiopian Brutality, British Apathy

by GRAHAM PEEBLES

On 23rd June 2014 Andergachew Tsige was illegally detained at Sana’a airport in Yemen whilst travelling from Dubai to Eritrea on his British passport. He was swiftly handed over to the Ethiopian authorities, who had for years posted his name at the top of the regime’s most wanted list. Since then he has been detained incommunicado in a secret location inside Ethiopia. His ‘crime’ is the same as hundreds, perhaps thousands of other’s, publicly criticising the ruling party of Ethiopia, and their brutal form of governance.

Born in Ethiopia in 1955, Andergachew arrived in Britain aged 24, as a political refugee. He is a British citizen, a black working class British citizen with a wife and three children. Despite repeated efforts by his family and the wider Ethiopian community – including demonstrations, petitions and a legal challenge – the British government (which is the third biggest donor to Ethiopia, giving around £376 million a year in aid), have done little or nothing to secure this innocent man’s release, or ensure his safe treatment whilst in detention.

የወያኔ አገልጋዮች ፕ/ መስፍን ላይ ጥቃት አደረሱ!!! 

የት ሂዱ ነው?

ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላላን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞትን ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡

Friday, April 3, 2015

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈፀመበት

በየመን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ጥቃት ተፈፀመበት በየመን ሰንዓ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለትናንት አጥቢያ ጥቃት እንደተፈጸመበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ እንዳስታወቁት በጦር መሳሪያ ጥቃቱ ጉዳት የደረሰበት ኢትዮጵያዊ የለም።

አምባሳደሩም ሆኑ ሌሎች ዲፕሎማቶች በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው ያስታወቁት። ኢምባሲ በየመን ያላቸው አብዛኛዎቹ አገራት ኢምባሲዎቻቸውን ከዘጉ ሳምንታት ተቆጥረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ “ከዜጐቻችን በፊት አንወጣም ብለው ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ላሉ ዲፕሎማቶችእና የአስተዳደር ሰራተኞች ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

በሌላ ዜና ከየመን ተመላሽ የሆኑ የመጀመሪያዎቹ 30 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ደርሰዋል። እስካሁን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከ2 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተመዝግበዋል። የተመዘገቡትን ዜጎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አገራቸው ለመመለስም መንግስት የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆኑን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

በየመን የሆቲ አማፂያን እና የአልቃይዳ ክንፍ ሰፊ ግዛት እየተቆጣጠሩ በመምጣት የአገሪቱ መዲና ሰነዓን ይዘዋል። በአገሪቱ መንግስት ደጋፊዎች እና በአማፂያኑ መካከል የሚደረገው ግጭት የቀጠለ ሲሆን፥ በተለይም በባህር ዳርቻዋ ከተማ ኤደን ጦርነቱ ተባብሷል ነው የተባለው። በህጋዊ መንገድ የተቀመጠውን የአገሪቱን መንግስት ወደ መንበሩ ለመመለስም በሳዑዲ አረቢያ መሪነት የአከባቢው አገራት ተጣምረው የዓየር ጥቃት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።




ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!

ለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።

Thursday, April 2, 2015

ሕወሓት የብአዴን እና ኦሕዴድ ሰዎችን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል

የብአዴን አባላት አሁንም ፈዘው የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ ራሳቸውን እና ሕሊናቸውን ለመጠየቅ ያልቻሉበት ደረጃ ላይ ናቸው:የመሻሻል ምልክቶች ቢታዩም መልሰው ይከስማሉ ያሉት የዚህ መረጃ አድራሾች ብኣዴንን አዳክሞ በአማርኛ ተናጋሪ ሌሎች ብሄሮች በተሻሻለ መልኩ ለመተካት በሕወሓት በኩል እየተሸረበ ያለው ሴራ በውስጡ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ እንዲነቅዝ አድርገዋል ያላቸውን አባላቱን ሁሉ ነቅሰው በማውጣት በብልሃት መዋጥ የሚሉ ስልቶች በብአዴን ካድሬዎች ዘንድ ጥያቄዎችን አጭሯል::ሕወሓት ኢሕኣዴግ ላይ እንከን ይፈጥሩ ይሆናል ለማሸነፍም ይሁን ለማጭበርበር እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን የብኣዴን በማግለል የጀመረውን ጉዞ መቀጠሉ ሲታወቅ ኦሕዴድ በበኩሉ ከተለያዩ ጸረ ልማት የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የበላይ የወረደ ትእዛዝ ሊፈጽሙ አልቻሉም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሰንሰለት ሰርተዋል የተባሉትን አባላቱን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል::

የአገዛዝ እድሜውን ለማስረዘም የማይቧጥጠው ነገር ያሌለው ሕወሓት በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል የተስፋፋው የውስጥ ሰላም ማጣት እና አለመተማመን ስላሰጋው በመጀመሪያ በብኣዴን ውስጥ ያሉትን እና ያሰጋሉ የተባሉ ባለልጣናትን እና ካድሬዎች ማስወገድ ስለሆነ ይህንኑ ስራውን በወያኔ ሚዲያ ላይ ባሰማራቸው ሰዎች ላይ እንደሚጀምር ታውቋል::በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ የብኣዴን ሰዎች በእረፍት ስም እቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ ሲሆን ካድሬዎችም እንዲሁ እረፍት እንዲወስዱ ፎርም እንዲሞሉ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል::ከእረፍት ከመመለሳቸው በፊት ለእያንዳንዱ በግል አርፎ እንዲቀመጥ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ የደህነንት አካል መዘጋጀቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::


Wednesday, April 1, 2015

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ ቤትፈላጊዎችን አስመርሯል


መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመጪውን ምርጫ መቃረብ ተከትሎ በአዲስአበባ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ 32ሺ ያህል ብዛት ያለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ከሳምንት በፊት ቢወጣም

ቅድሚያ ክፍያው የዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም በላይ ሆኗል።

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዋጋ ካለፈው ዘጠነኛ ዙር ጋር ሲነጻጸር እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ ራሱ አስተዳደሩ የጠቀሰ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎም አንድ መኝታ ያለው ቤት በካሬ 3ሺ 438 ብር ሲከፈልበት፣

ለ48 ነጥብ 34 ካሬሜትር ቤት 166ሺ ብር ገደማ ይሸጣል። የ20 በመቶ ቅድመ ክፍያው ደግሞ 32ሺ 238 ብር ይሆናል።

ባለሁለት መኝታ ክፍል ኮንዶሚኒየም የ20 በመቶ ቅድመ ክፍያ ወደ 64ሺ ገደማ ሲሆን፣ ይህን ያህል ብር በአንድ ጊዜ ከፍሎ ከባንክ ጋር ለመዋዋልና ተጨማሪ የቤቱን ማጠናቀቂያ ወጪ ለማውጣት በወር ገቢ ለሚተዳደሩ

በርካታ ሰዎች አስቸጋሪ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ቤት ፈላጊ ተናግረዋል ፡፡

አንድ ቤት ፈላጊ ባለአንድ መኝታ ኮንዶሚኒየም ቤት በዕጣ እንደደረሳቸውና በቅድሚያ የሚከፈለው የቤቱ ጠቅላላ ግምት 20 በመቶ ማለትም ወደ 32ሺ ብር ገንዘብ በአንዴ ለመክፈል መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል መንግስት የመኖሪያ ቤትን ችግር ለመቅረፍ በተመጣጣኝ ዋጋ በመስራት ዝቅተኛውን ሕብረተሰብ ጭምር የቤት ባለቤት አደርጋለሁ ብሎ ቃል ገብቶ እንደነበር ያስታወሱት አስተያየት ሰጪው፣ በአሁኑ ሰኣት

ግን ቤት ባለቤት መሆን የሚችለው 20 በመቶ ክፍያ ያጠናቀቀና ከባንክ ጋር መዋዋል የሚችል ብቻ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች ቤታቸውን ሳይረከቡ የሚቀሩ ሲሆን ፣ ብዙዎች ደግሞ ከአቅም በላይ ለሆነ ብድር በመዳረግ የኑሮ ቀውስ ውስጥ እየገቡ መሆኑን በመጠቆም ይህ ሁኔታ የግንባታውን ዓላማ የሳተ ነው ሲል ተችተውታል።


ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አበበ ገላው አጋለጠ

አዲስ ቮይስ– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትና የሚኒስትሩ ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና የበላይ ሃላፊ የሆኑት “ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ የሃሰት ፕሮፌሰር እደሆኑ አዲስ ቮይስ ባካሄደው እረዘም ያለ ምርመራ ማረጋገጥ ችሏል።። ግለሰቡ ለ15 አመታት በፕሮፌሰርነት አገልግየዋለሁ የሚሉት አንድ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ እንደማያውቃቸው የገለጸ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪ ያገኙበት ተቋምም በአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት “የዲፕሎማ ወፍጮ” (diploma mill) ተብሎ የተፈረጀ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።


“ፕሮፌሰር” መኮንን ሃዲስ ከኦክቶበር 2010 ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ ሆነው በመንግስት የተሾሙ ሲሆን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩ ወቅት ዋና አማካሪያቸው ሆነው ያገለገሉት እኚሁ ግለሰብ በአሁኑ ግዜ የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ዋና አማካሪ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናትና ትንተና ክፍል የበላይ ሃላፈ ሆነው በመስራት ላይ ይገኛሉ።