Tuesday, June 3, 2014
የዞንዘጠኝ ጦማርያን ተጨማሪጊዜተጠየቀባቸው።
ኢሳት ዜና :-እሁድ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የ 28 ቀናት ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማርያን ማህሌትፋንታሁን፣አቤልዋበላናበፍቃዱኃይሉ ናቸው።
ጦማርያኑ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ሲጠይቅባቸው በመሀል ዳኛዋ ውድቅ ተደርጎ የ15 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ አይዘነጋም።
ይሁንና ችሎቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ በአራዳ ምድብ ችሎት ሢሰየም ውሳኔውን ያሳለፉት ዳኛ ከቦታው እንዲነሱ እና በቦታቸው ሌላ ዳኛ እንዲተኩ ከመደረጉም ባሻገር፤ ፖሊስ የዛሬ 2 ሳምንት ያቀረበውና በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰጠበት ጥያቄ ዳግም ተነስቶ እና በአዲስ ተተኪው ዳኛ ተቀባይነት አግኝቶ ጦማርያኑ ተጨማሪ የ 28 ቀናት የቀጠሮ ጊዜ ተጠይቆባቸዋል።
በዝግ በታየው በእሁዱ ችሎት እንዳለፉትጊዜያትየታሳሪዎቹአንዳንድቤተሰቦችወደውስጥእንዲገቡአልተፈቀደላቸውም፡፡
የጦማርያኑ ቤተሰቦች፣ወዳጅ ዘመዶች፣ጓደኞች እና አድናቂዎች በፍርድ ቤቱ ዙሪያ ተሰብስበው የውሳኔውን ዜና በሚጠባበቁበት ወቅት በስፍራው ተመድበው በነበሩ የስርዓቱ አገልጋይ ጠባቂዎች ወከባ እና መንገላታት እንደደረሰባቸው በስፍራው የተገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል።
በተለይም የጦማሪ በፈቃዱ ሀይሉ እናት ጮኸው እስኪያለቅሱ ድረስ በአንዲት ፖሊስ በሀይል እየተገፈተሩ እንዲንገላቱ መደረጋቸው በስፍራው የተገኙትን ሰዎች በሙሉ በእጅጉ ያሳዘነ እና ስሜታቸውን የነካ ሆኗል።
እንዲሁም ችሎቱን እንዳይከታተሉ ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ከስፍራው እንዲርቁ በፖሊስ ሲዋከቡ ፡”ወደፍርድቤቱየመጣነውየፍርዱንውሳኔለመስማትናወዳጆቻችንንለማየትሆኖ ሳለ ለምንእንወጣለን?” የሚል ጥያቄ ያቀረበው ጋዜጠኛ በላይ ማናየ፤ ለሰአታት በፖሊሶች ታግቶ እና መታወቂያውን ተነጥቆ በዛሬው እለት ማእከላዊ ወንጀል ምርመራ እንዲቀርብ ታዟል።
ሆኖም ጋዜጠኛ በላይ ዛሬ ወደ ማእከላዊ ቀርቦ መታወቂያውን እንዲመልሱለት ቢጠይቅም፤ መታወቂያውን ሊያገኝ ቀርቶ በወጉ የሚያናግረው አጥቶ ተመልሷል።
ጋዜጠኛ በላይ በታገተበት ወቅት በስርኣቱ ታማኝ ታጣቂዎች ከደረሰበት ውክቢያ በላይ እጅግ የተሰማው የሰነዘሩበት ስድብ መሆኑን ጠቅሷል።
ምን ብለው ነው የሰደቡህ? በማለት ከኢሳት ጥያቄ የቀረበለት ጋዜጠኛ በላይ ማናየ፦” ስድቡ እኔ ላይ ሳይሆን ህብረተሰቡ ላይ ያነጣጠረ ነው። ብገልጸው በአብሮና ተከባብሮ መኖራችን ላይ መሻከርን ሊፈጥር ስለሚችል እና እንደነሱ መውረድ ስለሚሆንብኝ አልናገረውም”ብሏል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment