Sunday, June 15, 2014

የዞን 9 ጦማሪዎች እና ጋዜጠኛው ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

ያለምንም ክስ ላለፉት 50 ቀናት ፖሊስ የምርመራዬን አልጨርስኩምና ተጨማሪ ቀጠሮ ይሰጠኝ ጥያቄና በፍርድ ቤቱ መፍቀድ የተነሳ እየተጉላሉ የሚገኙት የዞን 9 ጦማሪያን እና ጋዜጠኛው ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ 28 ቀናት ፖሊስ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።

በፌደራል ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ የቀረቡት ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት፣ ኤዶም ካሳዬ፣ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ እና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ሲሆኑ ጉዳያቸውን ለመከታተልም በርካታ ሰዎች ፍርድ ቤት መገኘታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል። እንደዘጋቢዎቹ ከሆነ ባልተነገረ ክስ ላለፉት 50 ቀናት በእስር ቤት እየማቀቁ የሚገኙት ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ መንፈሳቸው ጠንካራ እንደነበር ለማየት ተችሏል። የታሳሪዎቹ ወላጆችና ሴቶች በፍርድ ቤቱ ሲላቀሱ እንደነበር ያስተዋሉት ዘጋቢዎቻችን ተጨማሪ 28 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ ብዙዎችን እንዳበሳጨ ጠቁመዋል።

ዘ-ሐበሻ

No comments:

Post a Comment