Tuesday, June 17, 2014

በ10 እስር ቤቶች የተከሰተው ኩፍኝ 9 ሰዎችን ገደለ

 ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው ከ4000 በላይ በሚገመት ታራሚዎች ላይ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች 9 እስረኞች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
“መንግሰት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ በቂ የማረሚያቤት ሰራተኛ የለኝም ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ፤ የህክምና አገልግሎት አይሰጥም” በሚሉ ሰበቦች  አደጋው እንዲባባስ እና ለእስረኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ መረጃው ያመለክታል።
የኢትዩጵያ የቀይ መስቀል ቡድን በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ 16 እስር ቤቶች መንቀሳቀሱም ታውቋል፡፡
በአንድ ክፍል እስከ 50 እስረኞች ታጭቀው በህመም እንደሚሰቃዩ ፤ ለህመማቸውም ተገቢ ህክምና እንዲያገኙ የሚያግዛቸው አካል እንደለሌ መረጃው አመልክቷል።
ከሟቾቹ ውስጥ 3ቱ የሱማሌ ዜጎች ናቸው።
በያዝነው አመት በፌደራል ደረጃ 252 ሺ 104 ኢትዩጵያውያን በእስር ላይ እንደሚገኙ የፌደራል ማረሚያ ቤት የ9 ወር ሪፖርት ያመለክታል።  በክልሎች የታሰሩት እስረኞች ቁጥር ግምት ውስጥ ሲገባ በመላ አገሪቱ ከ600 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ታስረው ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment