ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2009)
በብሪታኒያ ሃሙስ የፓርላማ አባላትን ለመምረጥ በተካሄደ ምርጫ ሃገሪቱ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው አለም አቀፍ ድጋፍ በፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ ቀረበ።
የብሪታኒያ መንግስት ለበርካታ ደሃ ሃገራት ሲሰጥ የነበረው ይኸው ድጋፍ የሰብዓዊ መብትን ቅድሚያ አልሰጠም እንዲሁም ድጋፍ ለታለመለት አላማ አልዋለም የሚል ትችት ሲቀርብበት መቆየቱ ይታወሳል።
ይኸው የሃገሪቱ አለም አቀፍ ዕርዳታ ሃሙስ ሲካሄድ በዋለው ምርጫ በኮንሰርቫቲቭ፣ በሌቨርና በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መነጋገሪያ ሆኖ መዋሉን ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትሯ ቴሬሳ ሜይ ፓርቲ የሆነው የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሃገሪቱ ስትሰጥ የቆየችው አለም አቀፍ ድጋፍ በአተገባበሩና በትርጓሜው ዙሪያ ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት አቋምን ይዟል።
የሌቨርና ሌሎች ፓርቲዎች ድጋፍ መቀጠል እንዳለበት ቢስማሙም የሃገሪቱ መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ ዳግም መጤን እና ድህነት ለቅረፍ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ማተኮር እንዳለበት መከራከርያ ሃሳብን አቅርበዋል።
የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተለያዩ ደሃ ሃገራት ሲሰጥ የቆየው ድጋፍ የሰብዓዊ መብት መከበርን ግምት ውስጥ የከተተ አይደለም በሚል በሃገሪቱ የፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል።
በርካታ የፓርላማ አባላት ብሪታኒያ የምትሰጠው ድጋፍ የሰብዓዊ መብት መከበርን ጨምሮ የገንዘብ ልገሳው ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል።
የብሪታኒያ መንግስት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለተለያዩ ደሃ ሃገራት ሲሰጥ የቆየው ድጋፍ የሰብዓዊ መብት መከበርን ግምት ውስጥ የከተተ አይደለም በሚል በሃገሪቱ የፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል።
በርካታ የፓርላማ አባላት ብሪታኒያ የምትሰጠው ድጋፍ የሰብዓዊ መብት መከበርን ጨምሮ የገንዘብ ልገሳው ለታለመለት አላማ ስለመዋሉ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በማሳሰብ ላይ መሆናቸው ታውቋል። የብሪታኒያ ንግስት ለኢትዮጵያና ለሌሎች ደሃ ሃገራት በአመት ወደ 12 ቢሊዮን ፖውንድ ስተርሊንግ ገንዘብ በድጋፍ መልክ ሲሰጥ መቆየቱን ለመረዳት ተችሏል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያደጉ ሃገራት ከአጠቃላይ አመታዊ ምርታቸው 0.7 በመቶ የሚሆነውን ለአለም አቀፍ ድጋፍ እንዲያውሉት ከአመታት በፊት መመሪያን ያወጣ ሲሆን፣ ብሪታኒያ እቅዱን ተግባራዊ በማድረግ ከአምስት ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን ችላለች።
ይሁንና ሃገሪቱ ለደሃ ሃገራት የምትሰጠው ድጋፍ ለታለመለት አላማ አልዋለም ተብሎ በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ግለሰቦች ዘንድ ጭምር ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል።
የብሪታኒያ አለም አቀፍ የልማት ትብብር ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥኝ በኩል ለሚተላለፈው ፕሮግራም ወደ 150 ሚሊዮን ብር አካባቢ ለመስጠት ቢወሰንም፣ ዕርምጃውን በሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃንና በፓርላማ አባላት ዘንድ ተቃውሞን አስነስቶ ድጋፍ እንዲቀር መደረጉ ይታወሳል።
የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት ሙዚቃዊና ትምህርታዊ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ፕሮግራሙ ያመጣው ለውጥ የለም ሲሉ ተችተዋል። ሃገሪቱ ለኢትዮጵያ የትምህርትና ጤና አገልግሎት ስትሰጠው የነበረው የገንዘብ ድጋፍም በጋምቤላ ክልል ሰፋፊ የእርሻ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ለመስጠት ለተካሄደው ዘመቻ ውሏል ተብሎ ሲቀርብበት የሚታወስ ነው።
የብሪታኒያ መንግስት ሲሰጥ የቆየው በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር በመንግስት ለተከናወነ ስራ መዋሉ ሲገለጽ ቆይቷል። በአለም ባንክ የገለልተኛ ቡዳን የተካሄደ ጥናትም የብሪታኒያ ድጋፍ ከታለመለት አላማ ውጭ ስለመዋሉ ማረጋገጫ ያቀረቡ ሲሆን፣ የጥናቱ ይፋ መደረግን ተከትሎ ብሪታኒያ ባባንኩ በኩል የምትሰጠው ድጋፍ እንዲቋረጥ አድርጋለች።
የአለም ባንክ በኢትዮጵያ በሚሰጠው ድጋፍ ላይ የማስተካከያ ዕርምጃ እንደሚወስድ በወቅቱ ሲገልፅ ቆይቷል።
ሃሙስ በብሪታኒያ ሲካሄድ የዋለው የፓርላማ አባላት ምርጫ አሸናፊ ፓርቲን ለመለየት የሚያስችል ሲሆን፣ የቴሬሳ ሜይ ፓርቲ የሆነው የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አብላጫ ወንበርን ማግኘት ካልቻለ ብሪታኒያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኒስቲር ትመርጣለች ተብሏል።
ይሁንና በምርጫው የሜይ ፓርቲ ድል ይቀናዋል ተብሎ ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment