ሰኔ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ሸፈራው ሽጉጤ በዘረጉት ከፍተኛ የዝርፊያ ሰንሰለት በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ መዝረፋቸውን ከአስተማማኝ ምንጮች የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የምንጮቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል፣ ምረመራውን ያካሄደውን የኦዲት ክፍል ለመግለጽ ባንችልም፣ መርምራውን የካሂዶት ኦዲተሮች ግማሾቹ ማስፈራሪያ ደርሶአቸው ስራቸውን ለቀዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ክልሉ ወንዶ ኢንዶውመንት ኩባንያዎች በየቀኑ ከ50 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ይቀበላሉ። ወንዶ ድርጅት ከደቡብ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚሄደውን ጫት ቀረጥ እንዲሰበስብ ስልጣን የተሰጠው ሲሆን፣ በየኬላዎቹ ጫት ጭነው ከሚመጡ መኪኖች በኪሎ ግራም ለቀረጥ ለኮቴና ለተለያዩ ወጪዎች በሚል 11 ብር ይቀበላል። አንድ መኪና በአማካኝ እስከ 5 ሺ ኪሎ ግራም ጫት የሚጭን በመሆኑ፣ በመኪና እስከ 55 ሺ ብር ከፍያ ይፈጸማል። ወንዶ ድርጅት ለመንግስት የሚያስገባው በቀን 60 ሺ ብር ሲሆን ይህም ከአንድ መኪና ጫት ከሚገኘው ገቢ ጋር ተመጣጣኝ ነው። በእየቀኑ እስከ 20 መኪና ጫት የሚቀረጽ ሲሆን፣ በቀን እስከ 1 ሚሊዮን 100 ሺ ብር ይሰበሰባል። አዲተሮች በ2005 ዓም ባደረጉት ምርመራ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ አለመሆ
ኑን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ኦዲተሮቹ መቀሌ ለስልጠና ትፍለጋላችሁ ተብለው ከተጠሩ በሁዋላ ፣ በስፍራው በተገኙት የደህዴን ባለስልጣናት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። የኦዲተሮች ሪፖርትም ይፋ እንዳይደረግ ተደርጓል። ከ2005 ዓም በሁዋላ ወንዶ ከጫት የሚሰበስበው ገንዘብ በቀን 110 ሺ ብር የደረሰ ሲሆን፣ ለእነ አቶ ሽፈራው የሚተላለፈውም ገንዘብ በዛው ልክ ከፍ ብሎአል። ስራውን የሰሩት ኦዲተሮች ከማስጠንቀቂያው በሁዋላ ስራቸውን በመልቀቃቸው ከ2005 ዓም ወዲህ ያለውን የገንዘብ መጠን ለማወቅ አይቻልም። ኦዲተሮች ከአዋሳ ይልቅ መቀሌ ለምን እንደተጠሩ እስካሁን ባያውቁም፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ ከደቡብ እስከ ትግራይ የተዘረጋ መሆኑን እንዳመላከታቸው ያምናሉ። አቶ ሽፈራው በራሳቸውና በዘመዶቻቸው በኩል የያዙዋቸው የንግድ ድርጅቶች ከፍተኛ ሲሆኑ፣ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር በፈጠሩት ከፍተኛ የጥቅም ቁርኝት አንድም ቀን ጥያቄ ቀርቦባቸው አያውቅም። ሌላው የደቡብ ክልልን ሲመሩ የነበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝና ቤተሰቦቹ በታናሽ እህታቸው የተሰየመ ቤትሄሌም ሶሊዳሪቲ የሚባል የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ተቋም የመሰረቱ ሲሆን፣ ሃዋሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለስልጣን ኦዲት ባደረገበት ወቅት፣ 24 ሚሊዮን ብር ገንዘብ ተገኝቶበታል። የኦዲት ምርመራው ሃዋሳ በሚገኘው የጉምሩክ ሃላፊ ትእዛዝ ይፋ እንዳይሆን የተደረገ ሲሆን፣ ምርመራውን ያካሄዱት 3 ሰራተኞች ከስራ ተባረዋል። በክልሉ የሚፈጸመው ሙስና ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን የሚገልጹት ምንጮች፣ በተለይ በመሬት ሽያጭ ባለስልጣናቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየመዘበሩ ነው። ከላይ እስከታች ያሉ የክልሉ ባለስልጣናት የሙስና ሰንሰለት በመዘርጋታቸው አንዱ ሌላውን ለመጠየቅ አቅም እንደሌለው የመረጃው ምንጮች ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment